ሰውን ከሃገሩ ምድር ማፈናቀል አረሜናያዊ ወንጀል ነው
ዲሞክራሲያዊ ምትሕብባር ትግራይ/የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር
Tigriaan Alliance for National Democracy
የህወሓት/ኢህአዴግ ከፋፍለህ-ግዛ ፖሊሲ መሰረት ያደረገው ዜጎችን የማፈናቀል አረሜናዊ ተግባር የሰነበተና የተደጋገመ ቢሆንም፤
ስሞኑን ደግሞ ከምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል-ጉምዝ በሺ የሚቆጠሩ የአማራ ብሄረሰብ ኢትዮጵያውያን ለዓመታት ስፍረው ከመሰረቱት
ቀየ በግፍ ተፈናቅለው፤ መድረሻ አጥተው በመንከራተት ላይ እንዲገኙ አድርገዋል። ሰውን ከሃገሩ ምድር ከነቤተሰቡ ማፈናቀል፤
የሚሄድበት ቦታ ማሳጣት ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ሕይወቱ ላይ የቁም ስቃዩን ጭምር ማሳይት ስለሆነ ሰብኣዊ ህሊና ያለው ሁሉ እንደዚሁም
ዓለም-ኣቀፍ ተቁዋማት አረሜናያዊ ወንጀል ነው ብለው መፈረጃቸውና ፈጻሚዎቹ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ መደንገጋቸው አግባብነት አለው።
ከዚህ በፊት በጋምቤላ፤ በጉራፈርዳ፤ በአፋር፤ ሰሞኑን ደግሞ በመኾኒ-ራያ ወዘተ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ላይ ተመሳሳይ አስቃቂ
ግፍ ፈጽመዋል፤ በተለያዩ ከተሞችም እንዲሁ (አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ መቀሌን ጨምሮ) ስላማዊ ተቃውሞ ለሚያሰሙት ወገኖች ሁሉ
በጥይት እየፈጁ የማፈናቀሉ ክፉ ድርጊት አካሂደዋል። ባጠቃላይ በህዝቦቻችን ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂ በደል በመጠኑም በዓይነቱም
መረን የለቀቀ በመሆኑ እንዳው ዘግናኝ ነው ብለን ለመፍትሄው ብንረባረብ ይመረጣል::
የሚገርመው ይህ በቤንሻንጉል-ጉምዝ የተከሰተው የማፈናቀል ድርጊት “መሬቱ ለልማት ይውላል” በሚል ሲሆን ሆኖም የተፈናቃዮቹ
ወገኖቻችን መሬት እየተሸነሸነ ለባእዳን በርካሽ ዋጋ መሸጡ ነው። ባእዳን ባለመሬት-ባለመሬቱ ደግሞ ባእድ አድርገውታል። በርካሽ ዋጋ
የሚሸጥበት ምክንያትም የባለስልጣናቱ የውጭ ኪስ በአዙሪት መሙላት ስለሚያስችል መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ይህ ዜጎችን
የማፈናቀሉ የኢህአዴጎቹ እኩይ ስራ ከስልጣንና ከግል-ጥቅም ጋር የተያያዘ በመሆኑ ወደፊትም የሚያቆሙት አይደለም፤ የሚያቆማቸው
ሓይል እስካልተፈጠረ ድረስ።
ከወዲሁ ግን ጉዳዩን የሚመለከታቸው ዓለም-ኣቀፋዊ ተቁዋማት ዜጎቻችንን በተደጋጋሚ ከሃገራቸው መሬት በማፈናቀል ለስቃይ
የሚዳርጉትን የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ሕግ ፊት እንዲያቀርቡልን አጥብቀን እየጠየቅን፤ መሰረታዊና ዘላቂ መፍትሄ የሚገኘው ግን
በህዝቦቻችን የተባበረ ትግል በመሆኑ በመለስተኛ ልዩነቶች ሳናመኻኝ ለዚህ ትግል እንድንበቃ አበክረን እናሳስባለን።
ይህ ከቤንሻንጉል-ጉምዝ በተፈናቀሉ ወገኖቻችን ላይ የደረሰው አሰቃቂ ኢ-ሰብኣዊ ድርጊት በጋራው ድርጅታችን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ
ትግል ሸንጎ ስም ቀደም ብሎ ያወገዝነው ቢሆንም፤ አሁንም በትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ታንድ) ስም ደግመን ልናወግዘው
እንወዳለን።
በተባበረ ትግል ማንኛውም መፈናቀል ይቆማል !!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
05 ኤፕሪል 2013
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
April 9, 2013
No comments:
Post a Comment