Friday, March 20, 2015


የሚሊዮች ንቅናቄ ለሰማያዊ – አንድ ለአምሳ

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ ሕዝባዊ ትንቅንቅ ከገዢው ፓርቲ ጋር ይዟል። ሰማያዊዎች የሚያደርጉት ትግል የነጻነት ትግል ነው። የሚተማመኑት በማንም አይደለም በሕዝቡ ነው። በሕዝቡ ብቻ ! በእኛና በእናንተ ።
ገዢው ፓርቲ ሕወሃት የሰማያዊ ተወዳዳሪዎችን እያሰረ፣ ከምዝገባው እየሰረዘ፣ የቅስቀሳ መልእክቶቻቸውን ሳንሱር በማድረግ አልስተላልፍም እያለ፤ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ሲጠሩ እየከለከለ፣ ህዝቡ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ እንዳይሰማ ትልቅ ጫና እያሳደረ ነው። ይሳካለታል ወይ ? ያንን የምንወስነው እኛ ነን።
የሰማያዊ ፓርቲ ደግመን እንናገራለን የሕዝብ ፓርቲ ነው። ትላንት የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በሚል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በአገሪቷ ክፍል ሁሉ ያሉ አንድነቶች፣ አሁን በብዛት ሰማያዊ ሆነዋል። አሁን ሰማያዊ የምንለው ፣ ከአንድ አመት በፊት ሰማያዊ እንለው የነበረው ብቻ አይደለም። አሁን ሰማያዊ የምንለው ፣ ያኔ ሰማያዊ እንለው የነበረ፣ ያኔም አንድነት እንለው ከነበረው ጋር አብሮ የሆነ ነው። ያኔ አንድነት ሲያደረግ የነበረው የሚሊዮኖች ንቅናቄ አሁን የሰማያዊ ንቅናቄ ሆኗል።
በመሆኑም በሚሊዮን የምንጠር ኢትዮጵያዉያን ሁሉ መነቃነቅ አለብን። ሰማያዊ በየወረዳው የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎችን ይፋ እንዳደረገ፣ በየወረዳው ፣ እንደ ንብ በመበተን የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች ማስመረጥ አለብን።
በራዲዮና በቴሌቭዥን እገዳ ቢደረግም፣ እያንዳንዳችን በግላችን፣ ጎሮቤቶቻችን ጋር ሄደን፣ ሻይ ቡና እየጠጣን ፣ 10 ደቂቃ፣ 15 ደቂቃ አይደለም፣ ከአንድ ሰዓት በላይ በመቆየር መቀስቀስ እንችላለን። እነርሱ ከላይ ሁሉን ቢያፍኑትም እኛ ዉስጥ ዉስጡን ወደ ጎን መዘርጋት ይኖርብናል።
አንርሳ ። የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ ከገዢው ፓርቲ ጋር ሰላማዊ ፍልሚያ እያደረጉ ያሉት እነርሱ ከኛ የተለየ በደል ደርሶባቸው አይደለም። አብዛኞቹ እንደዉም የተማሩና ሥራ ያላቸው ናቸው። ሆኖም «እኔ ከተመቸኝ ስለሌላው ምን አገባኝ» ሳይሉ፣ የእያንዳንዲ ዜጋ መብት እንዲከበር ዋጋ ለመከፈል የተዘጋጁ ናቸው።
እነዚህ ወገኖች ለራሳቸው መብት በመቆማቸው ለኛ እየቆሙ እንደሆነ እያወቀን፣ እንዴት በአካባቢያችን ፣ የድርሻችንን መወጣት እንዴት ያቅተናል ?
ገዢው ፓርቲ፣ አንድ ለአምስት ይል የለም እንዴ። እነርሱ ለጥፋትና ለስለላ ፣ ለአፈና ነው። እኛ ግን ለጥሩ ነገር ተመሳሳይ ሥራ መስራት እንዴት ያቅተናል ?
ለምን አንድ ለአምሳ ብለን እንነሳም ?
እያንዳንዳችን ቢያንስ 50 ኢትዮጵያዉያንን፣ በቀበሌያችን፣ በትምህርት ቤታችን ፣ በስራችም እንዲመርጡ፣ ለሰማያዊ ድጋፍ እንዲሰጡ ለምን አናደርግም ?
የምርጫው ዉጤት የፈለገዉን ይሁን። ግድ የለም። እኛ ግን እስከመጨረሻው ማድረግ ያለብንን ሁሉ እናደርግ። ሰማያዊን እንደገፍ። ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !!!!!!!10858349_771934959558107_7876066551884502810_n
  1. Tekle Aregawi
    | #1
    I strongly gree. Please where is the new office location of the blue party? Tell them to announce.
እንግሊዘኛ አማርኛ





No comments:

Post a Comment