የሞረሽ፣ ጉንጭ አልፊ ወግ
Posted: Amajjii/January 25, 2014 · Finfinne Tribune | Gadaa.com | Comments (3)
ከባህሩ፡ ባይሳ*
ክፉ የወለደው፣ ክፋት ያሳወረው፣
ዛሬም አልተወኝም፣ ዘሬን የጨረሰው።
አፉ ለከት የለዉ፣ ምላሱ መርዝ ነው፣
ቢያከብሩት የሚንቅ፣ ቢተዉት የማይተው፣
በሰው ታሪክ ገብቶ የሚዘላብደው፣
አስቲ ሊጠይቀዉ፣ ማን ስለሆነ ነዉ?
በምን ችሎታው ነው፣ ራሱን የሚክበው?
ሁሉን አዉቃለሁ፣ ሁሉን አቀናለዉ – ባይ፣
አፍራሽ፣ አዉዳሚ፣ ገዳይ – ያለከልካይ!
ዛሬም አልተወኝም፣ ዘሬን የጨረሰው።
አፉ ለከት የለዉ፣ ምላሱ መርዝ ነው፣
ቢያከብሩት የሚንቅ፣ ቢተዉት የማይተው፣
በሰው ታሪክ ገብቶ የሚዘላብደው፣
አስቲ ሊጠይቀዉ፣ ማን ስለሆነ ነዉ?
በምን ችሎታው ነው፣ ራሱን የሚክበው?
ሁሉን አዉቃለሁ፣ ሁሉን አቀናለዉ – ባይ፣
አፍራሽ፣ አዉዳሚ፣ ገዳይ – ያለከልካይ!
አገር ማቅናት – ማሳደግ ኖሮ ቢሆን፣
ስንት ዕድል ነበረ በአዮቶቹ ዘመን።
በፈረንጅ እርዳታ ክፋት አደራጅቶ፣
ጠብማንጃ፣ ማትርየስ፣ መርዝ ጭስ ሸምቶ፣
ጦር እና ጋሻ ብቻ በያዘ ህዝብ ላይ ዘምቶ፣
ስብናዉን ሰልቦ፣ እንዳይኖር ከቶ።
ነበር ያያቱ ታሪክ፣ ለልጁ ያወረሰው፣
በመገንባት ፈንታ፣ ሀገር ያፈረሰው።
መች ይሄ ብቻ ሆነ፣ የክፋቱ መጠን፣
ያ የአንጎላል ጅብ፣ የአንኮበሩ ሰይጣን!
በድብቅ ተረግዞ በአያቱ ማድቤት፣
እንዳይጥሉት ልጅ፣ እንዳያሳድጉት ሕፍረት፣
ያ ጭላማ ንጉሥ፣ የዛር ሐረግ ቆጣሪ፣
የድሪቶ መለኪያ፣ የሰቆቃ ወግ ነጋሪ።
ስንት ዕድል ነበረ በአዮቶቹ ዘመን።
በፈረንጅ እርዳታ ክፋት አደራጅቶ፣
ጠብማንጃ፣ ማትርየስ፣ መርዝ ጭስ ሸምቶ፣
ጦር እና ጋሻ ብቻ በያዘ ህዝብ ላይ ዘምቶ፣
ስብናዉን ሰልቦ፣ እንዳይኖር ከቶ።
ነበር ያያቱ ታሪክ፣ ለልጁ ያወረሰው፣
በመገንባት ፈንታ፣ ሀገር ያፈረሰው።
መች ይሄ ብቻ ሆነ፣ የክፋቱ መጠን፣
ያ የአንጎላል ጅብ፣ የአንኮበሩ ሰይጣን!
በድብቅ ተረግዞ በአያቱ ማድቤት፣
እንዳይጥሉት ልጅ፣ እንዳያሳድጉት ሕፍረት፣
ያ ጭላማ ንጉሥ፣ የዛር ሐረግ ቆጣሪ፣
የድሪቶ መለኪያ፣ የሰቆቃ ወግ ነጋሪ።
ደግሞ ልጁ ዛሬ፣ "ሞረሽ ወገኔ!" ብሎ፣
ያያቱን ኃጢያት እብደቱን አስተባብሎ፣
እራሱ እየገረፈን፣ እራሱ ይጮሃል፣
የኛን ታሪክ ፍቆ፣ የራሱን ይፅፋል።
የ አኖሌን ጡት ቆረጣ፣ ልቦወለድ ይለናል፣
የጨለንቆን እልቂት፣ ጨፍኖ ይክዳል።
'እንዲያዉም ያለቀዉ፣ አማራ እራሱ ነው፣
በኦሮሚያ፣ በአሶሳ ሃዉልት የሚገባዉ።'
ይለናል፣ አፍ ሞልቶ የዚያ ገዳይ ጥላ፣
ተበዳዩን ንቆ፣ ሙት እያጥላላ።
ያያቱን ኃጢያት እብደቱን አስተባብሎ፣
እራሱ እየገረፈን፣ እራሱ ይጮሃል፣
የኛን ታሪክ ፍቆ፣ የራሱን ይፅፋል።
የ አኖሌን ጡት ቆረጣ፣ ልቦወለድ ይለናል፣
የጨለንቆን እልቂት፣ ጨፍኖ ይክዳል።
'እንዲያዉም ያለቀዉ፣ አማራ እራሱ ነው፣
በኦሮሚያ፣ በአሶሳ ሃዉልት የሚገባዉ።'
ይለናል፣ አፍ ሞልቶ የዚያ ገዳይ ጥላ፣
ተበዳዩን ንቆ፣ ሙት እያጥላላ።
ዱሮም ንብ እንጂ፣ ዝንብ ማር አትሰራም፣
ከቆሻሻ ዉላ፣ ለምንም አትረባም!
ዉሎዋን ዘንግታ፣
ታሪኩዋን ረስታ፣
እንደ ንብ ማር ልስራ፣ ብላ ብትነሳ፣
ማን ነው የሚያምናት የጥንቱዋን አለባብሳ?
ደግሞ ሳትሰራ፣ ሳትለፋ ዉላ አድራ፣
ሌላው በደከመበት፣ ባለቤት ሆና ኖራ፣
በጭራ ብትባረር፣ ወይንም ብትሞት፣
እንዴት ትቀናለች፣ በአኖሌ ሃዉልት!
በቀዬው ባለቀ፣ በምስኪን ህዝብ ልክ፣
እጅ፣ እግሩን፣ ጡቱን – ባጣ ወገን ታሪክ፣
እኩል ተበዳይ ነኝ፣ ብላ ብትሞላቀቅ፣
ማንም አይሰማትም፣ ይቺን ከንቱ ደቃቅ።
ከቆሻሻ ዉላ፣ ለምንም አትረባም!
ዉሎዋን ዘንግታ፣
ታሪኩዋን ረስታ፣
እንደ ንብ ማር ልስራ፣ ብላ ብትነሳ፣
ማን ነው የሚያምናት የጥንቱዋን አለባብሳ?
ደግሞ ሳትሰራ፣ ሳትለፋ ዉላ አድራ፣
ሌላው በደከመበት፣ ባለቤት ሆና ኖራ፣
በጭራ ብትባረር፣ ወይንም ብትሞት፣
እንዴት ትቀናለች፣ በአኖሌ ሃዉልት!
በቀዬው ባለቀ፣ በምስኪን ህዝብ ልክ፣
እጅ፣ እግሩን፣ ጡቱን – ባጣ ወገን ታሪክ፣
እኩል ተበዳይ ነኝ፣ ብላ ብትሞላቀቅ፣
ማንም አይሰማትም፣ ይቺን ከንቱ ደቃቅ።
ግንዛቤ ቢኖር፣ ከስር ከመሰረቱ፣
ሁሉም ህዝብ ቢከበር እንደማንነቱ፣
አንዱ ምርጥ ዜጋ፣ ሌላው ሁለተኛ፣
ሆኖ ባይከፋፈል፣ ንፁህ ዘር፣ ዘረኛ፣
መች ይመጣ ነበር፣ የዛሬው ጥላቻ፣
መችስ ይመኝ ነበር፣ ሁሉም ሊሆን ለብቻ!
እንኩዋን ለሀገር ቀርቶ፣ የብዙ ህዝብ ቤት፣
ለመንደር አይበጅም፣ በባዶ መኩራራት።
ሁሉም ህዝብ ቢከበር እንደማንነቱ፣
አንዱ ምርጥ ዜጋ፣ ሌላው ሁለተኛ፣
ሆኖ ባይከፋፈል፣ ንፁህ ዘር፣ ዘረኛ፣
መች ይመጣ ነበር፣ የዛሬው ጥላቻ፣
መችስ ይመኝ ነበር፣ ሁሉም ሊሆን ለብቻ!
እንኩዋን ለሀገር ቀርቶ፣ የብዙ ህዝብ ቤት፣
ለመንደር አይበጅም፣ በባዶ መኩራራት።
ያኔ ነበር እንጂ፣ ያንድነት ቤት ግንብ፣
ጥላቻ ሳይዘሩ፣ ሳይንቁ ሕዝብ።
ዛሬ ምን ዋጋ አለዉ፣ ጉንጭ አልፋ ንግግር፣
ቤቱ ከፈረሰ፣ በወደመ ሀገር!
ባረከሳችሁት ቀዬ፣ ባከሰራችሁት ህዝብ፣
መች ሀገር ይኖራል፣ መች ወገን ከልብ።
መች መኖር ይቻላል፣ ጠፍቶ አላማና ግብ።
ሰዉም እንደ ቁስ፣ ስሙ ተወግዞበት፣
የእናንተ ስም፣ በግፍ ተጭኖበት።
በአሽሙራችዉ ብዛት ቅስሙ ታሰብሮ፣
ማንነቱን ያጣ፣ ህዝብ ዛሬ አምርሮ፣
ይበቃኛል! ሲላችሁ፣
ቁርጡን ሲነግራችሁ፣
አሁን ምን ይባላል፣ የናንተ "ሞረሽ ወገኔ" ማለት?
በዳይ ሆናችው፣ ተበዳይ መጫወት?
እንደ ዝንብ ማሰብ፣ በቆሸሸ ስሌት፣
ለእናንተም አይበጅም፣ የንብ ቀፎ መንካት!
ጥላቻ ሳይዘሩ፣ ሳይንቁ ሕዝብ።
ዛሬ ምን ዋጋ አለዉ፣ ጉንጭ አልፋ ንግግር፣
ቤቱ ከፈረሰ፣ በወደመ ሀገር!
ባረከሳችሁት ቀዬ፣ ባከሰራችሁት ህዝብ፣
መች ሀገር ይኖራል፣ መች ወገን ከልብ።
መች መኖር ይቻላል፣ ጠፍቶ አላማና ግብ።
ሰዉም እንደ ቁስ፣ ስሙ ተወግዞበት፣
የእናንተ ስም፣ በግፍ ተጭኖበት።
በአሽሙራችዉ ብዛት ቅስሙ ታሰብሮ፣
ማንነቱን ያጣ፣ ህዝብ ዛሬ አምርሮ፣
ይበቃኛል! ሲላችሁ፣
ቁርጡን ሲነግራችሁ፣
አሁን ምን ይባላል፣ የናንተ "ሞረሽ ወገኔ" ማለት?
በዳይ ሆናችው፣ ተበዳይ መጫወት?
እንደ ዝንብ ማሰብ፣ በቆሸሸ ስሌት፣
ለእናንተም አይበጅም፣ የንብ ቀፎ መንካት!
* ባህሩ፡ ባይሳ – bbayisa@yahoo.com
Galatoomi Obboo Baahiruu.