Gaafa: 18/02/15
Date:
ADDA BILISUMMAA OROMOO
OROMO LIBERATION FRONT
በኦሮሞ ህዝብ ሊይ ያነጣጠረውን ኣዯጋ መመከት የኦሮሞ ተወሊጅ የዜግነት ግዳታ ነው!
(የፊንፊኔ “ማስተር ፕሊን” ኣቅዴን በተመሇከተ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የተሰጠ መግሇጫ)
ከኣንዴ ምዕተ-ዓመት በሊይ በኦሮሚያ ሊይ የተዘረጋው የባርነት ኣገዛዝ በሺዎች የሚቆጠር የኦሮሞ ህዝብ ከቀዬውና ከመሬት ይዞታው
ኣፈናቅል መሬት-ኣሌባ ኣዴርጎታሌ። የኢምፓዬሪቱን ከተማ በኦሮሚያ እምብርት ሇማቋቋም ሲወሰዴ በነበረው ከዘር-ማጥፋት
(ጄኖሳይዴ) ወንጀሌ ባሌተናነሰ ዯረጃ ሲወሰዴ በነበረው እርምጃ ኣቢቹና ገሊን የተባለ የኦሮሞ ጎሳዎች ከኣካባቢው እንዱጠፉ
ተዯርገዋሌ። ``ሃገር ማቅናት`` በሚሌ መርህ ሲወዯስ የነበረው ጠሊታዊ እርምጃ በወያኔ የኣገዛዝ ዘመንም ``ሌማትና እዴገት`` በሚሌ
ሽፋን በመቀጠለ በኣሁኑ ወቅት ከቀዬውና ከኑሮው እየተፈናቀሇ ያሇው የኦሮሞ ዜጋ ቁጥር ከበፊቱ ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ ኣሌታየም።
የወያኔ መንግስት ከቀዯሙት ጨቋኝ ገዢዎች የወረሰውን እቅዴና ፖሉሲ ሇማስቀጠሌ ሊሇፉት 23ዓመታት የኦሮሞ ኣርሶኣዯሮችን
እንዯቦላ-ቡሌቡሊ፡ ሇገ-ጣፎ፡ ኣቃቂ፡ ሰበታ፡ ሱለሌታ፡ ቡራዩና ከመሳሰለት ኣካባቢዎች በማፈናቀሌ መሬቱን ሲሸጥና ሲከፋፈሇው ዛሬ
መዴረሱ የተሰወረ ኣይዯሇም።
የኦሮሞ ህዝብን በማይፈይዯውና ከቀዬውና ከመሬቱ ኣፈናቅል ሇዴህነትና ጉስቁሌና የሚዲርገውን የጨቋኝ ገዢዎች እቅዴ
በመቃወምም በርካታ የኦሮሞ ዜጎች የህይወት መስዋዕትነት ከፍሇዋሌ። የታሰሩትና ከባዴ ዴብዯባና ሰቆቃ የተፈጸመባቸው በብዙ
ሺዎች ይቆጠራለ። ሇኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር ሲለ በጠሊት የተገዯለትና ሇእንግሌት የተዲረጉት የኦሮሞ ዜጎች መስዋዕትነት
የከፈለበት ዓሊማ በከንቱ እንዲይቀርና በኦሮሞ ሊይ ያነጣጠረው ይህ የጠሊት እቅዴ እንዲይሳካ ማዴረግ ዛሬም የያንዲንደ የኦሮሞ ዜጋ
ግዳታ መሆኑን መገንዘብ ያስፈሌጋሌ።
የኢትዮጵያ ገዢዎች እቅዴና ፖሉሲ የኦሮሚያን ካርታ መቀየርና የኦሮሞን ህዝብ የለዓሊዊነትና የነጻነት ጥያቄ ሇማፈን መሆኑ ከማንም
የተሰወረ ኣይዯሇም። ሇዚህም የኦሮሞ ህዝብ ከመጀመሪያ ኣንስቶ እስከዛሬ ዴረስ ይህንን የጠሊቶች ሴራ በጀግንነት በመጋፈጥ ሇፍትህና
ሇመብቱ መስዋዕትነት ሲከፍሌ እንዯነበር የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግሌ ሂዯት ይመሰክራሌ። በኢትዮጵያ ገዢዎች በኦሮሞ ሊይ ሲፈጸም
ከዛሬ የዯረሰውን ይህንን ተንኮሌና ክፋትም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሲታገሇውና ሲያታግሌበት እንዯነበርና ኣሁንም እየታገሇው መሆኑ
ግሌጽ ነው።
የፊንፊኔ ማስተር ፕሊን በማሇት የታቀዯውን ይህንን ሴራ ኣስመሌክቶ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሉቀመንበር ኣቶ ዲውዴ ኢብሳ ኣዱሱን
ዓመት 2015ን ምክንያት በማዴረግ ባስተሊሇፉት መሌዕክት ``የፊንፊኔ ማስተር ፕሊን የሚባሇው የቀዯሙት የኢትዮጵያ መንግስታት
ሲያዯርጉት ከነበረው በተሇየና ዘመናዊ መሌክ በተሊበሰ መሌኩ የኦሮሞን ህዝብ ከመሬቱ በማፈናቀሌ ማንነቱን ማጥፋት ሊይ ያነጣጠረ
ነው`` በማሇት ከበስተጀርባው ያሇውን ሴራ ኣጋሌጠዋሌ።
የኦሮሚያን መሬትና ከተሞች ከኦሮሚያ ኣስተዲዯር ስር በማውጣት በፌዳራሌ ኣስተዲዯር ስር ኣስገብተው እንዲሻቸው ሇመሸጥና
ሇመቀራመት ያሇመውን ይህንን ጠሊታዊ እቅዴ በተመሇከተ የወያኔ መንግስት ከፍተኛ ባሇስሌጣን የሆነው ኣባይ ጸሃዬ ሰሞኑን
ባዯረገው ንግግር ``ሇፊንፊኔ የወጣው እቅዴ ስራ ሊይ ይውሊሌ! ይህንን የሚዯናቅፉትን ሁለ ሌክ እናስገባቸዋሇን! ማንነታችንን
እናሳያቸዋሇሌ!`` በማሊት በኦፒዱኦ ኣስተዲዲሪዎችና ሹማምንት ሊይ ሊይ ዝቷሌ። ኣምባገነኖች ሲፎክሩና ሲዝቱ እንዯሚባረሩ የታወቀ
ቢሆንም የዚህ የወያኔ ሹም ፉከራ ወያኔዎች ምን ያህሌ ህዝቡን እንዯሚንቁና ምን ያህሌ እንዯዘቀጡ ያሳያሌ። የኦሮሞን ህዝብ ከምዴረ-
ገጽ በማጥፋትና ሇዴሕነት በመዲረግ የተንዯሊቀቀ ኑሮ መኖር የሇመደት የኢትዮጵያ ገዢዎች የሚያሰሙት ፉከራና ዛቻ የኦሮሞን ህዝብ
ሇመብቱና ሇማንነቱ ከመታገሌ ፈጽሞ ኣያግዯውም። የኦሮሞ ህዝብም ይህ ስራ ሊይ ይውሊሌ በሚሌ የወያኔ ሹም የሚዝትበት እቅዴ
በማንነቱና በመብቱ ሊይ ያነጣጠረ መሆኑን በይበሌጥ ስሇሚገነዘብ ነጻነቱንና ለዓሊዊነቱን ሇመጎናጸፍ እያካሄዯ ያሇውን ትግሌ
በማፋፋም ከግቡ የሚያዯርስ መሆኑ ጥርጥር የሇውም።
ስሇሆነም የኦሮሞ ህዝብ ጠሊት የሆነውን ስርዓት ሇማገሌገሌ ከወሰኑት የኦፒዱኦ ኣባሊት ውጪ የምትገኙ የኦሮሞ ተወሊጆች ኣባይ ጸሃዬ
ያሰማው የንቀትና የተስፋ መቁረጥ ንግግር ጠሊት መቸውንም ጠሊት መሆኑን የሚያረጋግጥ ስሇሆነ፡ የኦሮሞን ህዝብ መብት ሇማስከበር
ከህዝባቸው ጎን በመሰሇፍ እንዱታገለ፡ በሚወስደት ታሪካዊ እርምጃም ከታሪክ ተጠያቂነት እራሳቸውን እንዱያዴኑ የኦሮሞ ነጻነት
ግንባር በዴጋሚ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርብሊቸዋሌ።
تاريخ رقم Lakk.: 006/stm - abo/2015
No.:
جبهۃ تحـرير اورومـى
P.O. Box 6973 Asmara, Eritrea Tel 2911 110236 Email: Caalchis@gmail.com, www.oromoliberationfront.org
ከዚህም በተጨማሪ ሇእኩሌነት፡ ሇዱሞክራሲና ሇፍትሕ እንታገጋሇን የሚለ ሁለ የኦሮሞን ህዝብ የመኖር መብት እየነፈገ
ያሇው ኣርመኔያዊ የጠሊትነት እርምጃ በይፋ እየተፈጸመ ባሇበት በኣሁኑ ወቅት፡ ከማጋሇጥና ከመቃወም ከዲር ቆሞ
መመሌከት ወይንም እንዲሌሰሙ በዝምታ ማሇፍ በታሪክ የሚያስጠይቅ መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኣጥብቆ ያሳስባሌ።
ይህንን የኦሮሞን ህዝብ ማንነት ማጥፋት ሊይ ያነጣጠረውን የጠሊት እቅዴ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በጥብቅ እንዯሚያወግዝና
እንዯሚያከሽፈው በዴጋሚ ሇመሊው የኦሮሞ ህዝብ እየገሇጸ፡ የህዝብን መብት የማያከብርና የሃገር ባሇቤት የሆነውን ህዝብ
የሚያጠፋ እቅዴና ፖሉሲ በህዝብ ትግሌ የሚከሽፍ መሆኑ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እምነት ነው።
ዴሌ ሇኦሮሞ ህዝብ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
የካቲት 18 ቀን 2015ዓም
No comments:
Post a Comment