አንድነታችንን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ብናተኩር ሁላችንንም ይጠቅመናል
Posted by: admin Tags: Posted date: January 27, 2014 | No comment
ምንሊክ ሳልሳዊ
January 27, 2014
የብሔር ፖለቲካ አሳፋሪ ነው፡፡ አንድነታችንን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ብናተኩር ሁላችንንም ይጠቅመናል፡፡ ኢትዮጵያ ምሳሌ ልትሆንበት የምትችልበት ነገር ሃይማኖት ብቻ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ ብሔር ብሔረሰቦችን በውስጧ አቅፋ የያዘች አገር ናት፡፡ አይደለም ሰማንያ ቀርቶ ሁለት ብሔረሰቦች ያሉባቸው አገሮች ግጭት ውስጥ ሲገቡ እናያለን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃቅን ግጭቶች የሉም ማለት ባንችልም፣ በአጠቃላይ ግን ለመኖር የሚያዳግት ግጭት ግን አስተናግዳ አታውቅም፡፡ ይህ ታሪካችን የሚያኮራን ቢሆንም፣ አሁን አሁን ግን የሚስተዋሉት ነገሮች ሃይ ሊባሉ የሚገባቸው ናቸው፡፡ ስለአብሮ መኖር ታሪካችን የማንጠነቀቅለት ከሆነ ይህ አኩሪ ታሪክ ሊበላሽና ሊጠፋ ይችላል፡፡ በተለያዩ ወቅቶች በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚነሱ የብሔር ግጭቶች የጉዳዩን አሳሳቢነት ሊያሳዩን ይችላሉ፡፡ በተለይም አገሪቱ ተስፋ የምታደርግባቸው እነዚህ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጠባብ በሆነ የብሔር ፖለቲካ ውስጥ ገብተው ሲጋጩና ሲበጣበጡ ማየት አሳፋሪ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የአማራ ብቻ አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ብቻም አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የደቡብ ብቻም አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የትግራይ ብቻም አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ናት፡፡ ስለዚህ አንዱ ብሔር ከአንዱ ብሔር አይበልጥም፡፡ አንዱ ብሔር ከአንዱ ብሔርም አያንስም፡፡ ሁሉም እኩል ነው፡፡ አንዱ ከአንዱ ይሻላል በሚል ጽንፈኛ የብሔር ፖለቲካ አንድነታችንን ማፍረስ አይገባንም፡፡ የሁሉም ብሔሮች መገኛ የሆነችውን ኢትዮጵያን መመልከት ይገባል፡፡ በዚህም ረገድ ራሳችንን መሳል ተገቢ ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን በየጊዜው እየዶለዶምን ሄደን አንድነታችንን ልናጣው እንችላለን፡፡
ሃይማኖቶች በመርህ ደረጃ አይጋጩም፡፡ ሁሉም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁሉም የመረጠውን ሃይማኖት የመከተል መብት አለው፡፡ ነገር ግን የአንድ ሃይማኖት ጠበቃ ነኝ በሚል የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ ማድረግ ተቀባይነት የሌለው ድርጊት ነው፡፡ ሰዎች በሚከተሉት ሃይማኖትና በማንነታቸው ፈጽሞ ሊፈረጁ አይገባም፡፡ ምክንያቱም ከሁሉም በላይ ሰውነታቸው ይበልጣልና፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሐሳባቸውን በማንፀባረቃቸው ምክንያት በጠላትነት ሊፈረጁ አይገባም፡፡ ምክንያቱም ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሕገ መንግሥታዊ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሯዊም ነውና፡፡ ጽንፈኛ የሆነ አመለካከት በመያዝ የእኔ መንገድ ብቻ ነው ትክክል ማለት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኋላቀር የሆነ ብቻ ሳይሆን የማያስኬድ ነው፡፡ ስለዚህ ራስን በአንድ ሳጥን ውስጥ ጨምሮ እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን ማለት አንድነታችንን ሸርሽሮ በኋላ ባዶ ሊያስቀረን ይችላል፡፡ በመሆኑም በሃይማኖቱም ሆነ በፖለቲካው እንዲሁም በሌላውም ጉዳይ የእኔ ሐሳብ ብቻ ይንገሥ ማለት ማንንም የትም አያደርስም፡፡ ስለዚህ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ጽንፈኝነትን በማስወገድ አንድነታችንን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ብናተኩር ሁላችንንም ይጠቅመናል ፡፡
Recent News Posts
"Yegna Temnet" New Ethiopian Music 2014
// // January 25, 20143 Little-known Secrets for a Healthy Digestive Tract
// // Editor's Note: The digestive tract is a very important aspect of our body....መታየት ያለበት: “ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” (Video)
// // January 24, 2014 መምህር ደረጄ ዘወይንዬ “ግብረ...
Recent News Posts
"Yegna Temnet" New Ethiopian Music 2014
// // January 25, 20143 Little-known Secrets for a Healthy Digestive Tract
// // Editor's Note: The digestive tract is a very important aspect of our body....መታየት ያለበት: “ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የ666 አሰራር” (Video)
// // January 24, 2014 መምህር ደረጄ ዘወይንዬ “ግብረ...
Popular News Posts
Robert Mugabe Blasted Nelson Mandela as a 'coward' during Victory Speech
// // August 6, 2013 Zimbabwe’s President Robert Mugabe blasted Nelson Mandela...Saudis Beating, Raping, and Killing Ethiopians in Saudi Arabia (Shocking Video)
// // November 12, 2013 Editors Note: We have had enough watching all these...Sign the Petition:"STOP the Violence against Ethiopians in Saudi Arabia"- 22715 Signatures so far;50000 Needed!
// // Zekarias Bekele November 26, 2013 AGAIN...BREAKING NEWS: Ginbot7 Popular Force (GPF) Formed
Ginbot7 Popular Force (GPF) Formation For Immediate Release London, United Kingdom, December...Press Release: Ginbot 7 Popular Force Fundraising Task Force in Norway
// // August 14, 2013 Ethiopia and its citizens have never been endangered...
Contact Us
Copyright © 2012 EthioFreedom
No comments:
Post a Comment