Thursday, January 30, 2014

የረፈደበት የወያኔው ዲፕሎማት
(ዘመዴ ወርቁ፣ አውስትራሊያ)

በቅርቡ በአማርኛ ቋንቋ እየተዘጋጀ በሚተላለፈው የአዉስትራሊያው ኤስቢኤስ ሬድዮ፤ በጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ እና በአዉስትራልያ
የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ አረጋ ሃይሉ መሃከል የተካሄደዉን ቃለ-ምልልስ አስደምጦአል።

አምባሳደር አረጋ የስራ መጀመሪያ አብይ ትኩረት ያደረጉት ለዲፕሎማሲዊው ስርዐት ያለው ጨዋታ ሳይሆን ይልቁንም
ሳይረፍድባቸው በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለሻሚዎቻቸው ታማኝነታቸዉን ማረጋገጥ ስለሆነ የሚወዱትን ሁሉ ያደርጋሉ። ሲዋሹ
ታዛቢዎቻቸዉን አይፈሩም። ነገንም አያንሰላስሉትም።

አምባሳደሩ ዲፕሎማት እንደመሆናቸው፤ በዲፕሎማሲ ጥበብ ልቅናው ለሃገሩ የተሻለ ዉጤት ያስገኘ ዲፕሎማት ያዉቁ እንደሁ
በሚል፤ ማንን ያስታውሳሉ በመባል ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ተሻምተው ‘አቶ መለስ ዜናዊን የሚአክል ታላቅ ዲፕሎማት ኢትዮጵያ
አልነበራትም’ ብለው ለመለስ ራዕይ የሙት መንፈስ ጠባቂዎች ታማኝነታችውን ለመግለጽ መልካም አጋጣሚ እንድሆነ የጓጉትን አረጋ
ሃይሉ፤ ጋዜጠኛው በሚታዉቅበት እርጋታው አስታሞ አምባሳደር የተጠየቁት እኮ የሃገራቸዉን ጥቅም ያስከበሩ ዲፕሎማቶችን ነብር
እንጅ መሪዎችን አልንበረም፤ ከሆነም የጠቀሱአቸው ሰው ከእነአክሊሉ ሃብተ ወልድም በላይ የላቀ ጥቅም አስገኝተዋል ብለው
ያምናሉ? ተብለው ሲጠየቁ አሁንም “አዎ! ቢሆንም ከመለስ የበለጠ አልነበረም” የተመለሰለት ዕዉነቱ ብዙም ያልተዋጠለት
ጋዜጠኛ፤ ምን አልባትም ከእዉነት ይልቅ ወገንታኛ የሆኑ ሁነው አይሰማዎትም ብሎ ደግሞ ሲጠይቃቸው ከመንግስታቸው
በተማሩት የማንገራገር ፉከራ ቢጤ ማድረጋቸዉን ሰምቸ አዘንኩ። ዉሻ በበላበት ይጮሃል እንደሚባለው፤ እዉነትም ሆድ
ህልናቸዉን ባዶ ካላደረገባቸው እንዴት መለስ ዜናዊ የሃገራቸው ጥቅም አስክባሪ ዲፕሎማት ናቸው ብለው ሊመስክሩ ይወዱ ነበር
አልኩ።

እኔ እንደሚገባኝ መለስ ዜናዊ ታይቶ በማይታወቅ አኳኋን ሃገር በቀል የኢትዮጵያ ተበቃይ ጠላት እንጅ ተቆርቋሪ አልነበሩምና
የምስክርነቱ ሃሰተኛነት ትንሽ እንኳ የሚመስል ነገር ያልተጨመረበት ካንድ የ58 አመት ዕድሜ ባልቤት ነኝ ከሚል ትልቅ ሰው
የመይጠበቅ ነዉና፤ ውሎ አድሮም የልጅ አንገት የሚአስደፋ ቅሌት ስለሆነ በልጆቻቸዉም የነገ ሕይወት ላይ ጠቁሮ የሚታይ
ስለሚሆን አሳዘኑኝ።

ሌላው ቢቀር መልስ ዜናዊ እኮ፡

 ገና በጥዋቱ በኤርትራ የተነሳው ችግር በሰላም ተቋጭቶ ህዝቡ ለልማቱና ለብልጽግናው እንዳይቆም የሚችሉትን ያህል
ያቀጣጥሉ እንደነበር “የኤርትራ ጥያቄ ከየት ወዴት?” የተሰኝ የጥፋት መጽሓፋቸው ያሰፈሩት ምስክር ነው።

 በለስ ቀንቷቸው ቀን የጎደለባት ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመጀመሪያ ስራቸው ኤርታራን ከ እናት ሃገሯ ገንጥሉልኝ
በማለት ለተባብሩት መንግስታት ማመልከቻ ያቀረቡ በአለም የመጀምሪያዉና ምናልባትም የመጨረሻው የህገር መሪ የነበሩ
ናቸው።
 ባእዳን እንኳ ቢለምኗቸው አይሆንም አሰብ የ ኤርትራ እንጅ የኢትዮጵያ ሊሆን አይገባም በማለት እትዮጵያን በርጅሙ
ታሪኳ የማታዉቅዉን ባህር አልባ እስረኛ የባህር ገባሪ ያደርጉ ሰዉ መሆናቸውን በቅርቡ ሀርማን ኮሆን ለምነው
እንዳልተሳካላቸው መስክረዉባቸዋል።

 በሕወሓት ዉስጥ የነበሩ የ ኢትዮጵያዊነት ተቆርቋሪ ቢአንስም የትግራይን ጥቅም ከኤርትራ የሚስቅድሙትን ለማጥፋት
በተጠነሰሰው ሴራ፤ የቅድሚያ ተሰላፊዉን ሃየሎም አራያን በማጥፋት ያልረኩት ሴረኞች ለብዙህ ሽህ ግራ-ቀኝ ወግኖች
እልቂት ምክንያት የሆነዉን ጦርነት ለኩሰው ካነደዱ በሁላ፤ በሚወዱት የጓዳ በር ሾልከው ካልጀርስ እስክ ኒዮርክ የህግ
ባለሙያዎች ካምፓኒ በደረሰ ሴራ በሃገር እና በንጹሃን ደም ሙተው ለዚህ ገናና ስልጣን ያበቁአቸዉን ሁሉ የበሉ ክፉ ቡዳ
መሆናቸው የተረሳ መስሎአቸው።

 ባአንድነቱ ጥንካሬ ወደር እንድምይገኝለት ወራሪ በአዳን የሚውቁትን ህዝብ ለሃገሩ ክብር ዳግም ጸንቶ እንዳይቆንም
ለሰላሙና ለብልጽግናው ተማምኖ እንዳይቆም፤

 ቋንቋ ብቻ የመለያያ መንገድ በማደርግ ስለልዩነቱ ያልንበረ ታሪክ እይደረሱ በመለያየት እርስ በርስ ለማናከስ የስልጥን
እድሜአቸውን ሁሉ በህገራቸው ያሴሩ ያልአልነበሩ ይመስል ዶጋሊ፤ ጉራ እና መተማ ላይ ተዋድቅው ሃግራቸዉን
ያስክበሩትን ጀጋንወች እና በደማቸው ያስክብሩትን ባንዲራ በማረክስና መታሰቢያቸዉን በማፍረስ የተጠመዱ ካሃዲ ባንዳ
አልነበሩ ሁሉ፤

 የጀግናው አጼ ዮሃንስ ደም ሳይታፈስ የብዙ ጀግና ኢቲዮጵያውያን አጥንት ስይለቀም እነ አፄ ቴዎድሮስ ተወልደው
ያደጉበት ቋራና መተማ ለም መሬታችን አሳልፎ ለሱዳን የሰጠውን የሀገር እና የሕዝብ ጠላት ያቶ አረጋ ሃይሉ ህሊና የበቃ ዲፕሎማት ነው ብሎ ሊመሰክር መቻሉ ማን ያምንልኛል ብለው ሊሆን ይችላሉ።፡ምን አልባት በኢትዮጵያና በሌላው
አለም ዉስጥ የሚኖሩ እትዮጵያዊአን አንድ አስድናቂ የመለስ ዜናዊ የዲፕሎማሲያዊ አተያይ ምን ይመስል እንደነበር እንድ
ምሳሌ ማንሳቱ የሚሻል መሰለኝ።

ኢትዮጵያ ያእሁኑን እምባሲ ከመክፈቷ በፊት የነብራት ቆንሲላ የሚመራው በአንድ አዉስትራሊያዊ ነጭ ነው። ይህ አዉስትራሊያዊ
ነጭ የቆንሲላ ጀኔራል ማእረግ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ነበረ; አሁንም ነው። ይህ ሰው ስለሚወክለው ሃገር ታሪክ ያኗኗር ባህል ሳያውቅ
ምኑም ላልሆነች ሀገር እንዲወክላት ሲደረግ፤ሕወሃት ጫካ በነበረበት ጊዜ የ እርድታ ሰርታኛ ሁኖ ለወያኔ በሰጠዉ እርዳታ ዉልታ
ለመክፈል ሲባል ነው፡፡ ይህን በተመለከተ ካአንድ ያአውስትራልያ ፓርላማ አባል ጋር ስንወያያይ ኣጥብቅው የተገረሙበት ስለነበረ
ተገርሞነታቸውን ሁሌ አስታዉስዋለሁ። እንግዲህ የአረጋ ሃይሉ የላቀ ዲፕሎማሲያዊ ምስክረነት ይህን እና ብዙ ያልተቀስኩቸው
ሀኔታዎች ሁሉ እያወቀ የመሰክረው ነው እና፤ በእኔ በኩል ሰዉ ራሱን ሽጦ መብላት መጀምሩን የተረዳሁበት ክፉ ጊዜ ላይ መገኝታችን
ነዉና የሚምረን አምላክ ቢሰማን እግዚኦ እንበል።






ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
January 24, 2014 

No comments:

Post a Comment