Tuesday, April 5, 2016

1

የወያኔ የኢኮኖሚ ዕድገትእና ሦስት እንቆቅልሾቹ

/ር ዘላለም ተክሉ



[4/2/16]

መቼም ኢትዮጵያ ስታድግና፣ ስትለማ ህዝቦቿውም በደስታ፣ በጥጋብና በሰላም ሲኖሩ
ማየትን የማይመኝ ሰው ካለ እሱ ህመምተኛ መሆን አለበት:: ነገር ግን በምድር ያለው


እውነታ የተገላቢጦሽ በሆነበት ሁኔታ ወያኔዎችና ደጋፊዎቹ አለማቀፍ የፋይናንስ

ተቋማት ይህችን ምስኪን ሃገር በልማት ጎዳና አስመንጥቀናታል፣ በዓለም ፈጣን ዕድገት

ካስመዘገቡት አገራቶች በአንደኛ ደረጃ እንድትሰለፍ አድርገናታል፣ የህዝቦቿን ገቢ

በማሳደግ በጥጋብና በሃሴት እንዲኖሩ እያደረግን ነው እያሉ ሲፏልሉ ዝም ብሎ

መመልከት ህሊናችንን ከዛም በላይ የዜግነት ግዴታችን በከፍተኛ ሁኔታ መዘንጋት
ይመስለኛል::

በዚች አጭር ጽሁፍ እስኪሰለቸን ድረስ እየተነገረን ያለው “አስደናቂ ዕድገት”

Impressive economic growth) ምን ያህል የተዛባና የተጋነነ Cooked data) መሆኑን

ለማሳየት ይሞከራል::ይህንን ለማስረዳት የዓለም ባንክ ስለኢትጵያ ዕድገት

ያከማቸውንና ያጠናቀረውን የብዙ ዓመታት የአሃዝ መረጃTime Seriers database)

ከሎሎች ጎረቤትና ሩቅ ሃገራት ተመሳሳይ መረጃዎች፣ ከ USAID የዕርዳታ መረጃዎችና

ተያያዥ የኢኮኖሚ ቲዎሪዎች ጋር የማገናዛብ ትንተናዎች ተደርገዋል::

እንቆቅልሾቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል-

1የኢትዮጵያ “ዕድገት” ሳይንሳዊ የሂሳብ ስሌት ህግን እንኳን ሽሯል

Ethiopian Growth Narratives disproved the “Rule of 70)


አንድ ሃገር ኢኮኖሚውን በሁለት እጥፍ ለማሳደግ ስንት ዓመታት ይፈጅበታል የሚለውን
ጥያቄ ለመመለስ ኢኮኖሚስቶች “ The Rule of 70” የሚባል የሂሳብ ህግን ይከተላሉ

በዚህ ህግ መሰረት አንድ ሃገር ለተከታታይ ዓመታት በተመሳሳይ የእድገት ቀመር

growth rate) እያደገ ከሆነ፣ ኢኮኖሚውን በሁለት እጥፍ ለማሳደግ የሚፈጅበትን ዓማታት

ለማስላት የሚከተለውን ፎርሙላ መጠቀም ይቻላል



# of years to double the economy = 70/r where

r = growth rate

በዚህ ሳይሳዊ ህግ መሰረት ለአመታት እየተነገረን ያለውን የ 11 በመቶ ዕድገት

ብንጠቀም፣ 70/11፣ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን በሁለት እጥፍ ለማሳደግ ቢያንስ ስድስት

ዓመታት ያስፈልጋታል ማለት ነው::

ነገር ግን ራሱን የዓለም ባንክ አሃዛዊ መረጃንTime Seriers database) በመጠቀም

ከዚህ በታች የተሳለው ግራፍ ( Trend Graph) የሚያሳየን እውነታ ግን ወያኔ ምን ያህል



2

የተጋነነ የዕድገት መረጃን በማምረት Cooked growth data) ዓለምን ሁሉ የማወናበድ

ሥራ እየተሰራ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል::

ከላይ በሚታየው ግራፍ መሰረት በ 2006 የሃገሪቷ አጠቃላይ ምርት GDP) 15.3 ቢሊዮን

ዶላር የነበረ ሲሆን በ 2009 ወደ 32.2 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንዳለ ተመልክቷል:: ይህም

ማለት በየዓመቱ የ 11 በመቶ ዕድገት በተነገረን መሰረት፣ ኢኮኖሚው በሁለት እጥፍ

ያደገው በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው ማለት ነው:: እንዲሁም ከ 32.2 ቢሊዮን

ዶላር ወደ 55.6 ቢሊዮን ዶላር በእጥፍ ለመመንጠቅ ሶስት አመታት ብቻ አንዳስፈለገ

ያመለክታል:: ከላይ በተመለከተው የኢኮኖሚና ሂሳባዊ ስሌት መሰረት የሃገሪቱ ምርት


በሁለት እጥፍ ለማሳደግ ስድስት ዓመታት እያስፈለገ፣ ኢትዮጵያ በሶስት ዓመታት ብቻ

ሁለት እጥፍ እንዲሁም በስድስት ዓመታት ብቻ በአራት እጥፍ ኢኮኖሚዋን አሳዳገች
እየተባለ መለፈፉ ከሳይንሳዊ እውነታ ሁሉ የራቀ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል::

ለዚህም ነው ”የወያኔ ዕድገት“ ሳይንሳዊ የሂሳብ ስሌት ህግን ሽሯል የምንለው:: ወይ

11 በመቶ ዕድገቱ የተጋናነ ነው ወይም ደግሞ ያ ለዘመናት ሲሰራበት የኖረው

ሳይሳዊና ሂሳባዊ ህግ ተሳስቷል ማለት ነው::

የተቀቀለ መረጃ Ccooked dataቁጥር አንድ በሉልልኝ::

2) የእህል ምርት በሶስት እጥፍ እያደገ መራብ ጉድ የሚያስብል እንቆቅልሽ ነውThe


Paradox of Starvation Amidst Ample Production)
በቅርቡ በ The economist የወጣ ጽሁፍ ኢትዮጵያ ከ 2000 እስከ 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ

የእህል ምርቷን በሶስት እጥፍ እንዳሳደገች ዘግቧል::ከዚህ በታች የተቀመጠው ግራፍ 2

ግራፍ 1 - ምንጭየዓለም ባንክ መረጃ 2016በመጠቀም በግል የተሳለ ግራፍ



32.2 Billion

3

እንደሚያመለክተውም፣ ኢትዮጵያ ከ 2006 እስከ 2014 የእህል ምርቷን ከ 160 በመቶ

በላይ እንዳሳደገች ያስረዳል::


ለዘመናት በእህል እጥረትና በረሃብ ለምትጠቀሰው ሃገራችን ይሄ መረጃ እውነት ቢሆን
ኖሮ ሁላችንንም ምንኛ ባስፈነደቀን ነበር:: ነገር ግን በመሬት ላይ ያለው እውነታ

የተገላቢጦሽ ነው::

በቅርቡ በዓለም ዙሪያ ተከሰተ በተባለው የ el nino የዓየር መዛባት ምክንያት በ

ኢትዮጵያ ከ 10 እስከ 15 ሚሊዮን ህዝባችን ለረሃብ አደጋ እንደተጋለጠ እየተነገረ ነው

የወያኔ መንግስትም በመጀመሪያ አካባቢ ዘገባው የሽብርተኞች ወሬ ነው ሲል ቆይቶ፣


በኋላም በቁጥጥር ስር አውለነዋል እያላ ሊያድበሰብስ ቢሞክርም እውናታው ከቁጥጥሩ

ውጭ ወጥቶ አሁን ደግሞ የአለም መንግስታትን ለነብስ አድኑ ዘመቻ አልደረሳችሁልንም
እያለ በመውቀስ ላይ ይገኛል:: ሰሞኑን ደግሞ የ አሜሪካ ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅት

USAID) በጀመረው Disaster Assistance Response Team (DART) 1.5 ቢሊዮን

በሚፈጅ በጀት ወደ 17 ሚሊዮብ ለሚደርሱ ተረጂዎች የአስቸኳይ የምግብና ተያያዥ

እርዳት ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ይፋ አድርጓል

ዋናው እንቆቅልሹ Paradoxአገሪቱ በ 14 ዓመታት ውስጥ በሶስት እጥፍ ያደገ ምርት

ከሰበሰበች እንዴት በ el nino ምክንያት ምርታቸውን ላጡ 10 እና 15 ሚሊዮን ገበሬዎች

መመገብ ተሳናት የሚለው ጥያቄ ነው::


ተገኘ የተባለውን የእህል ምርት እድገት ከሌሎች ጎረቤት ሃገሮችና አስቸኳይ የምግብ

እርዳታ እያደረገች ካለችው አሜሪካ ተመሳሳይ የእህል ምርት ዕድገት ጋርም ለመነጻጸር
ተሞክሮ የተገኘው ውጤት ደግሞ ጉድ የሚያስብል ነው::



4

ከላይ የሚታየው ግራፍ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ የእህል ምርት ዕድገት ከኬንያ፣
ከሱዳንና ከየመን ሁላ እንደሚያስንቅ ነው የምንረዳው:: ታዲያ ይህ እውነት ከሆነ በ el

nino ምክንያት የተከሰተው የዓየር መዛባት ለምን ኢትዮጵያን ብቻ ለረሃብና ለእርዛት

ይዳርጋታልለምን ኬንያዎች፣ ሱዳኖች፣ኢርትራውያን፣ በእርስ በርስ ጦርነት

የሚታመሱት የመንና ሶማሊያን በተመሳሳይ ረሃብ አልተጠቁም


በጣም የሚገርመው ደግሞ የኢትዮጵያ የእህል እድገት ከአሜሪካንም በልጦ መታየቱ
ነው:: አሜሪካን ከኢትዮጵያ ያነሰ የምግብ ምርት እድገት ካላት እንዴ ለኢትዮጵያ

የአስቸኳይ ነብስ አድን የምግብ እርዳታ ትርፍ ምርት ልታገኝ ቻለች

የተቀቀለ መረጃ Ccooked dataቁጥር ሁለት በሉልልኝ::

3ሌላ ዓይ ያወጣ ጉድ - የኢትዮጵያውያን የሥራ አጦች ቁጥር

ከአሜሪካውያን ያንሳል Ethiopians are less unemployed than the



Americans

ከዓለም ባንክ የተገኘውን መረጃ በመጠቀም በኢትዮጵያ ያለውን የሥራ አጥነት ቀመር
ለመመልከት ተሞክሯል:: የተገኘው መረጃ ግን በጣም የሚያስገርምና ጉድ የሚያስብል

ነው:: በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ለስራ ዝግጁ ከሆነው ህዝብ potential labor force)

ውስጥ በስራ አጥነት የተመዘገበው ህዝብ ከ 5 በመቶ ብቻ ነው:: ይግረማችሁና ከዚህ

ግራፍ 2 - ምንጭየዓለም ባንክ መረጃ 2016በመጠቀም በግል የተሳለ



5

በታች ለማነጻጸሪያነት የተሳለውን ግራፍ ስንመለከት፣ የኢትዮጵያ ስራ አጥነት ቁጥር

ከኬኒያ፣ ከሱዳን፣ ከየመን፣ከሳውዲ ዓረቢያና እንዲሁም ከ አሜሪካ ሁሉ እንደሚያንስ ነው
::
5 በመቶ ስራ አጥነት ማለት እኮ ከ 5 እስከ 10 በያዘ ቤተሰብ ውስጥ ሁሉም ስራ ያለው

ወይም ምንም ስራ አጥ የሌለበት ቤተሰብ ማለት እኮ ነው:: በእውነት

No comments:

Post a Comment