የተጀመረው መብትን የማስከበር ህዝባዊ ትግልና የታየው የመተባበር መንፈስ ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት
ገዢው የወያኔ ቡድን ገና በኣሜሪካ መንግስት ደጋፊነት የሀገሪቷን ስልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በኢትዮዽያውያን ዘንድ ተቀባይነት ያላገኘ ቡድን መሆኑ ግልጽ ነው። ሆኖም ይሄዉ ለሃያ ኣምስት ኣመታት በስልጣን ላይ ሊቆይ ችሏል። ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ተቃዋሚዎቹን እየገደለ፣ እያሰረ ከሀገር እያሳደደ ዛሬ ላይ ደርሷል። በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን የሚያቀርቡትንና የሚጽፉትን ያለ ምህረት በማፈን በገዛ ሃገራቸው የህሊና እስረኞች ሆነው እንዲኖሩ ኣድርጓል። ''ህገመንግስታዊ ስራትና ህገመንግስቱን ለመጠበቅ '' በሚል መፈክር ዜጎችን መኖሪያ ኣሳጥቷል። ቁጥራቸው ያልታወቁትን ጸረ ሰላም፣ ጸረ ልማትና ኣሸባሪ በማለት ገድሏል። በተለይም በኦሮሞ ወጣቶች፣ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች ላይ በማነጣጠር ኣድኖ ጨርሷቸዋል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩትን በታወቁና ባልታወቁ የማሰቃያ ቦታዎች በማጎር ሰቆቃ ፈጽሞባቸዋል። ዛሬም ከምንጊዜውም በላይ የኦሮሞ ተወላጆች በተለይም የነገ ሀገር ተረካቢዎች በዚሁ መንግስታዊ ህገወጥ ቡድን እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ይህ ቡድን በ1997 ምርጫየህዝቡን ድምጽ በኣደባባይ በመስረቁ ህገመንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ድምጻቸውን ለማስከበር ሰላማዊ ሰልፍ የውጡትን ከሁለት መቶ ያላነሱ የኣዲስ ኣበባ ወጣቶችን ያለ ምህረት በጥይት ደብድቦ ገድሏቸዋል። በወቅቱ በኦሮሚያ የተቋቋመው ኣጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ወደ ኣርባ የሚጠጉ ስዎች በኦሮሚያ ተገድለዋል።
ያ ኣልበቃ ብሎት የጸረ ሽብር ኣዋጅ በማውጣት ጭቆናን፣ የመልካም ኣስተዳደር እጦትን፣ የህግ የበላይነት መጣስን በኣጠቃላይ የመንግስታዊ ህገ ወጥነትን የተቹትን ሁሉ ኣሸባሪዎች በማለት በእስር ቤቶች ኣጉሮ ይገኛል። ሙስሊም ኢትዮዽያውያን ህይማኖታቸውን በ ነጻነት ለማካሄድ እንዲችሉ ጣልቃገብነትእንዲቆም በሰላማዊ መንገድ በመጠየቃቸው በርካቶች ተገድለዋል። ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከመንግስት ጋር ተነጋግረው ያለውን ችግር እንዲፈቱላቸው መርጦ የላካቸውን ሰዎች ኣሸባሪዎች ናቸው ብሎ ድራማ በመስራት በሃሰት በመወንጀል ወህኒ ውስጥ ኣጉሯቸው በማሰቃየት ላይ ይገኛል።
ለዚህ ሁሉ ህገወጥነት የጠቀመው የኢትዮዽያን ህዝቦች ለመከፋፈል በመቻሉ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። በመከፋፈላችን ነጣጥሎ ኣጠቃን። ለጥቃት ያጋለጠንን ምክንያት በሚገባ እያወቅን መፍትሔ ለመፈለግ ዝግጁ ሳንሆን በመቅረታችን እነሆ የመንግስታዊው ቡድን ንቀት፣ጭካኔና በደል እያንዳንዱን ቤት በማንኳኳት በሃገራችን ኑሮ ከሲኦል የከፋ ሆኖ ይገኛል። የዚህ መንግስት ንቀት ከመጠን እያለፈ ሂዶ ህዝብን ለዘመናት ከኖረበት በማፈናቀል መሬቱን በመቀማት ለውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች እየቸበቸበ ሚሊዮኖችን በማደህየት በልመና እንዲኖሩ ኣድርጓል።
ኣሁን ደግሞ ''በኣዲስ ኣበባና በዙሪያው የሚገኙ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን'' በሚል የቀሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኣርሶ ኣደሮችን የሚያፈናቅል እቅድ ኣዘጋጅቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ህዝቡን ያላቀፈ፣ ከኑሮው የሚያፈናቅልና ለከፋ ድህነት የሚዳርግ ልማት ህገመንግስታዊ መብቱን የሚጻረር በመሆኑ መተግበር የለበትም በማለት ተቃውሞ ያነሱትን ሁሉ በመናቅ ''ወደዳቹም ጠላችሁ ይተገበራል'' የሚል መልስ በመስጠት እብሪተኛነቱን በዲጋሚ ኣረጋግጧል።
ባለፈው ኣመት በተለያዩ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ ተቃውሞ ያደረጉትን ያለርህራሄ ከ80የማያንሱትን ተማሪዎችና ነዋሪዎችን በጥይት ቆላቸው።
በዚህም ኣመት ማስተር ፕላኑን ኣስመ ልክቶ ለተነሳው ጥያቄ ደንታ በማጣትና በንቀት የኦሮሚያ ምክር ቤት ( ጨፌ ኦሮሚያ) በሚባለው ስብስብ ኣማካይነት ኣዋጅ በማውጣት የማስተር ፕላኑን እቅድ ተግባራዊ የማድረግ እንቅስቃሴውን ቀጠለበት። ከዚህም ሌላ በምእራብ ሸዋ ኣምቦ ኣካባቢ የሚገኘውንና ለዘመናት ሳይነካ ህዝቡ ጠብቆ ያኖረውን የጭልሞን የተፈጥሮ ደን ለባለ ሃብት ሰጥቶ ለማውደም በመንቀሳቀሱ የኣካባቢው የኦሮሞ ተማሪዎች በኋላም ህዝቡን ጨምሮ ኣካሄዱን በሰላማዊ መንገድ በመቃወም ጥያቄ ለማቅረብ ኣደባባይ ወጡ። ለዚህም ኣምባገነኑና ህገወጡ መንግስታዊ ቡድን የሰጠው መልስ በጅምላ መግደልን ነው።በዚህም መሰረት በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ምንም የማያውቁ የትምህርት ቤት ህጻናት ወሬ ለማየት የሚሯሯጡ ሳይቀሩ በጥይት ተቆልተዋል። እናትና ልጅ እቤታቸው ደጅ ላይ በጠላት ጥይት ተደብድበው ወድቀዋል። እርጉዝ እናት በሆዷ ከያዘችው ሽል ጋር በፋሽስቶች ጥይት ተግድላለች።
እስካሁን በተጠናቀረው መረጃ መሰረት ከ100 በላይ ተማሪዎችና ሌሎች የኦሮሞ ተወላጆችን በጥይት ግድሏል።
ተደጋግሞ እንደተነገረው ይህ መንግስት እንደልቡ እንዲፈነጭና ለህዝብ ያለው ንቀት ገደብ ያጣው እኛ ተገዢዎች በመከፋፈላችን ነው። ለሃያ ኣምስት ኣመታት በተናጠል ሲንገረፍ፣ ሲንገደልና እንደ በግ መንጋ ወደ እስር ቤት ሲንጋዝ የኖርነው በኣንድነት ቆመን በቃህ ለማለት ኣለመቻላችን ነው።
ከእንግዲህ እስካሁን የነበረው ሁኔታ መቀየር ኣለበት። ኣሁን ሁላችንም ኣንድ ላይ ሆነን ለነጻነት፣ለእኩልነት ለሰላምና ለዲሞክራሲ በኦሮሚያና ኣማራ ክልል የተጀመረውን ትግል ኣጠናክረን መቀጠል ኣለብን። ሌላ ምርጫ የለም። ኣሁን የማያዳግም ትግል ተጀምሯል። የቀረው ነገር ቢኖር መላው የኢትዮዽያ ህዝቦችን ከዳር እስከዳር ማንቀሳቀስና በትግሉ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው። የነብር ጭራ ኣይይዙም ፣ ከያዙ ኣይለቁም ይላል የኣበው ምሳሌያው ኣነጋገር። የነብር ጭራ ይዘው ከለቀቁ የሚደርሰውን ኣደጋ ስለሚያውቁ ነው እንዲ ያሉት። እነዚህ ኣሁን ከፋፍለው የሚገዙን ነብር ናቸው ለማለት ኣይደለም። እነሱ ህጻናትና ሴት የሚገድሉ ፈሪዎች ናቸው። ተረቱን ያመጣሁት ኣንዴ ቆርጠው የገቡበትን የመብትና የነጻነት ትግል ከጀመሩ ዳር ሳያደርሱ መቆም ለጠላት ጊዜ መሰጠት ስለሆነ የድል ጊዜውን ስለሚያራዝም እንጠንቀቅ ለማለት ነው።
ትግሉ በሁሉም ኣካባቢዎች መቀጣጠል ያስፈልጋል። ይህን ጸረ ህዝብ የወያኔ ቡድን በሁሉም ማእዘናት ፋታ መንሳትና ማጣደፍ ይገባል። ግፍና መከራን ተሸክሞ በውስጥ ማጉረምረምና መቃጠል ዋጋ የለውም።
ይህ በኦሮሚያ የተጀመረው ትግል የሁሉም ኢትዮዽያዊ የመብት ትግል መሆኑን ያለ ማመንታት ማመን ያስፈልጋል። በኢትዮዽያ የሚገኙ የሁሉም ዜጎች መብት እየተረገጠ ፣ ዜጎች በገዛ ሃገራቸው በፍርሃትና በመሸማቀቅ የሚኖሩበት ጊዜ እንዲያበቃ ሁሉም ለመብቱ መታገል ኣለበት። በኢትዮዽያ ከህግና ከህዝብ በላይ ለሆነ ኣገዛዝ ኣንገዛም ማለት ኣለብን።
ትግሉ ዳር እንዲደርስ ከተፈለገ ለእውነተኛ የህዝቦች ነጻነት እንታገላለን ከሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠበቅ ትልቅ ሃላፊነት ኣለ። ትግሉ የተቀናጀ ካልሆነ ኪሳራውና መዘዙ ክፍተኛ ይሆናል። ኣሁን እንደታየው በኦሮሚያ የተጀመረው ሰላማዊ የመብት ጥያቄ በጀብደኛውና የህዝብ ጠ ላት የወያኔ ቡድን ወደ ደም ማፍሰስ ተሸጋግሮኣል። ይህ እንዲቆም የጋራ ትግል ኣስፈላጊ ብቻም ሳይሆን ታሪካዊ ሃላፊነት ነው።
ባለፈው ወር በመላው ኦሮሚያ የተቀጣጠለው የመብት ማስከበር ትግልን ለማዳፈን ገዢው መንግስት የወሰደው የግፍ እርምጃ መላውን የኢትዮዽያ ህዝብ ማስቆጣቱ ግልጽ ነው። በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ ያሉትና ኣምባገነኑን መንግስት ለማንበርከክ የሚታገሉት የፖለቲካ ድርጅቶችንም የትግላቸውን ኣካሄድ እንዲመረምሩ እንዳደረጋቸው ጥርጥር የለም። ለዚህም
ያደረጉትን የትግል ትብብር ጥሪ ማየቱ በቂ ነው። ለምሳሌ የኦርሞ ዲሞክራቲክ ግንባር (ኦዲግ) ቀጥሎ የተመለከተውን የትብብር ጥሪ ኣስተላልፎኣል።
''እንግዲህ የዚያች አገር ጉዳይ ያገባኛል የሚል ማንኛዉም ግለሰብ፣ ድርጅትና ተቋም፤ በአጠቃላይ የሚያስብ አዕምሮ ያለዉ እያንዳንዱ ዜጋ «እስከመቼ ድረስ እየታሠርን፣ እየተደበደብን፣ ከገዛ አገራችን እየተሰደድን፣ ከምንም በላይ ደግሞ በግፍ እየተገደልን በዚህ የጥቂቶች አገዛዝ ሥር እንቀጥላለን?» ብሎ ራሱን መጠየቅ አለበት። ያለምንም ማጋነን የአገራችንና የሕዝቦቻችን መከራና ስቃይ ከልክ ያለፈ ሆኗል። ስለዚህ አንዱ ሕዝብ ሲጠቃ ሌላዉ ከሩቅ ሆኖ የማየት በሽታ ዘላቂ መፍትሔ ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን። ዘላቂ ሊሆን የሚችለዉ መፍትሔ ደግሞ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ተደጋግፈን ለጋራ ድል በጋራ ሆነን መታገል ብቻ ነዉ'' ይላል።
የኦርሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ''The OLF calls upon all Ethiopian to join the Oromo people struggle for freedom, democracy, justice & human rights, and once for all to dismantle the genocidal regime of TPLF. To that effect, the OLF calls for all inclusive struggle that include all political parties and civil organizations that will enable the Ethiopian people to decide their destiny by establishing government of people, for people and by people in Ethiopia. ይህም በኣጭሩ ተባብረን ይህን የኣናሳና ገዳይ ቡድን ኣገዛዝ ኣሰወግደን በህዝብ፣ለህዝብና የህዝብ መንግስት በኢትዮዽያ እንዲመሰረት የጋራ ትግል እናድርግ ነው።
የግንቦት ሰባት ኣርበኞች ግንባር መሪ ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋም ሁሉም ከያለበት ጥያቄውን እያነሳ ትግሉን መቀላቀል እንዳለበትና ከኦሮሞ ተማሪዎች ጎን እንዲቆሙና ለነጻነታቸው እንዲታገሉ ትብብር ኣስፈላጊ መሆኑን ኣጽኖት ሰጥተው ጥሪ ኣቅርበዋል፣ በሃገር ውስጥም የሰማያዊ ፓርቲ ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ( ኦፌኮ) ጋር በጋራ ለመ ስራት መስማማታቸው ታቋል። በጋራ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማ ድረግ ኣቅደው በእምቢተኛው ገዢ ቡድን ተከ ልክለዋል። የሰማያዊ ፓርቲ ኣባላትም የኦሮሞን ህዝብ ትግል ደገፋችሁ ተብለው መታሰራቸውን ሰምተናል።
ይህ ኣሁን የታየው የትብብር መንፈስ ወደ ላቀ ደረጃ ማደግ ኣለበት። ይህ የኣሁኑ የትብብር ጥሪ እንዲሁ በድንገት በተፈጠረው ወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት የተከሰተ ኣይመስለኝም። ሁሉም ኣንዳችን ለኣንዳችን ኣስፈላጊዎች መሆ ናችንን በመገንዘብ የተደረገ ከልብ የመነጨ ነው ብዬ እገምታለሁ። ስለዚህ በኔ ግምት እስካሁን ድረስ እነዚህ ጥሪ ያደረጉ ድርጅቶች በጉዳዩ ላይ መነጋገር ጀምረዋል የሚል እምነት ኣለኝ። ካላደረጉ ያሳዝናል። ምክንያቱም ከዚህ በላይ የሚናባክን ጊዜ የለምና። ተባብረን በኣንድነት ካልቆምን በኢትዮዽያ ሃብት እስከ ኣፍንጫው የታጠቀውን ኣምባገነን ለማስወገድ የማይቻል ባይሆንም ብዙ መስዋእትነትን ያስከፍላል።ለዚህም ነው የጋራ ትግል ኣስፈላጊ የሚሆነው። በተግባር የማሳያው ጊዜ ኣሁን ነው። የዚህ መንግስት ገበናው ኣሁን ለሁሉም ለውጭም ሆነ ለውስጥ ይፋ ሆኗል። ይህ መንግስት የኢትዮዽያን ህዝቦች መብትና ነጻነት ረግጦ መቀጠል እንደማይችል ለሃያ ኣምስት ኣመታት ደግፈው ያቆዩት ጭምር ተገንዝበዋል። ኣሁን እያሰቡ ያሉት ማን ይተከዋል የሚለውን ነው። ጥያቄያቸው ተገቢና ማንም መጠየቅ ያለበት ነው። ስለዚህ የኢህአድግ መንግስት ከመውደቁ በፊት በሚገባ የተደራጀና መንግስታዊ ሃላፊነት የሚሸከም ድርጅት መኖሩ መረጋገጥ ኣለበት። ለህዝብ ፣ በህዝብና የህዝብ መንግሥት ለመመሥረት የሚችል ሃይል መፈጠር ኣለበት።
እስካሁን ድረስ ጭራሽ መነጋገር የማንችል መስለን ኖረናል። ያተረፍነው ነገር ቢኖር ከፋፍሎን ለሚገዛን መመቸት ብቻ ነው። ኣሁንም ይህ ሃይል እንዳንቀራረብ ሌት ተቀን እንደሚሰራ ማወቅ ኣለብን። ይህ ኣሁን የተፈጠረውን መልካም ኣጋጣሚ ተጠቅመን ህዝባችንን ከሰቆቃ፣ ግዲያ፣ እስራትና ስደት ካላዳን ተጠያቂው እኛ እንጂ ገዢዉ መንግስት ኣለመሆኑን ማወቅ ኣለብን።ይህ
ኣሁን የተደረገው የትብብር ጥሪ ወደ ተግባር ካልተቀየርና ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የተደረገ ሆኖ ከቀረ በታሪክ ፊት ተጠያቂ ከመሆንም ኣልፎ ኣሁን ህጻናት ልጆቻችንን በገፍ እየገደለ ካለው ገዳይ መንግስታዊ ቡድን ጋር ከመተባበር ተለይቶ ሊታይ ኣይችልም።
ለትብብር ጥሪው ተግባራዊነት የሚዲያዎች እገዛ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ይችላል የሚል እምነት ኣለኝ። በኦሮሚያ ተማሪዎችና ህዝቡ እያደረገ ያለውን የመብት ትግል ተከታትለው ለሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ላሉት ኢትዮዽያውያንና ሌሎች በማሰራጨት በኩል ያደረጉት ስራ በጣሙን የሚያስመካ ሆኖ ታይቷል። የኢትዮዽያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት)፣ ኦሮሞ ሚዲያ ነትዎርክ(OMN)፣ ገዳና( GADA.COM) ኢትዮሚዲያ ድረገጾች እንዲሁም የተለያዩ ረዲዮ ጣቢያዎች የኣሜሪካ ድምጽ ኣማርኛና ኦሮሚኛ ፕሮግራሞችን ጨምሮ የሙያና የሀገር ግዴታቸውን ተወጥተዋል ለማለት ይቻላል።
ኣሁን የተጀመረውን የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የመተባበር ጥሪም ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስ ጥረት ማድረግ ኣለባቸው የሚል እምነት ኣለኝ።ሶሻል ሚድያም የተጫወተው ሚና በጣሙን የሚደነቅ ነው።
ሚዲያ ሃገር ለመገንባትም ሆነ ለማፍረስ የሚችል ትልቅ ሃይል ነው። ባለፉት ኣመታት ህዝብን ከማቀራረብ ይልቅ የማራራቁ ስራ ጎልቶ ስታይ እንደነበር የሚካድ ኣይደለም። ኣሁን ግን ሰሞኑን እንደታየዉ ህዝቦችንም ሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ ኣመለካከት ያላቸውን በማቀራረብ መርዳታቸዉን ኣጠናክረው መቀጠል ኣለባቸው። ሰዎች የመሰላቸውን ሃሳብ የመስጠት፣ የመጻፍና የመናገር መብት እንዳላቸው ቢታወቅም ኣሁን ኢትዮዽያ ባለችበት ሁኔታ ህዝብን ከህዝብ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያጋጩትን ሃሳቦች፣ ጽሁፎችና ኣስተያየቶች ከማስተናገድ መቆጠብ ኣለባቸው። እኛን ለያይቶን የኣገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም የሃገር ሃብትና ጉልበት የሚያባክነውን ጸረ ህዝብ የሆነውን ኣምባገነን መንግስት በማጋለጥ ላይ በማተኮር ህዝቦቻችን የዚህ መሰሪ ቡድን ድርጊት ሰለባ እንዳይሆኑ ማስተማር፣ መምከርና የማቀራረብ ስራ በሰፊው እንዲሰሩ በበኩሌ ኣደራ እላለሁ።
በኣጠቃላይ ለነጻነት፣ለእኩልነት፣ ለሰላምና ዲሞክራሲይዊ መብታችን መከበር የተጀመረው ትግል ከግቡ እንዲደርስና በጭካኔው ወደር የማይገኝለትን ጸረ ሰላምና ኣሸባሪውን መንግስታዊ ቡድን ለማስወገድ የሃገሪቷ ህዝቦች ተባብረው ትግሉን ማፋፋም ኣለባቸው። በተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች በኩል የቀረቡት የትብብር ጥያቄዎችና የመቀራረብ መንፈስም ለዘመናት ሰቆቃ ላልተለያቸው የኢትዮዽያ ህዝቦች ሲባል ተጠናክሮ ለኣንድ ኣስተማማኝ ውጤት እንዲበቃ ሁሉም መደገፍና ግፊት ማድረግ ኣለበት።
የተባበረ ህዝባዊ ሃይል ምንጊዜም ኣሸናፊ ነው።
በቀለ ጅራታ
የቀድሞ የኦፌዴን ዋና ጸሃፊ
Ethiomedia.com – December 30, 2015
ለውጥ ግድ ይላል!
ብሩህ ቦጋለ፣ ኖርወይ
ሁሌም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብዙ ህጎች በሚቀርቡበት ወቅት ውዝግብ የሚነሳባቸው ነበሩ፡፡ ገዢው ፓርቲ "ሕጎቹ ዲሞክራሲና ልማት የሚያሣልጡ ናቸው" እያለ ሲዘምር በምክር ቤት የሚገኙ አባላት ደግሞ "ሕጎቹ የገዢውን ስልጣን ለማራዘም ዜጎችን ለማጥቃት የተዘጋጁ መሣሪያዎች ናቸው" በማለት በተገደበች ደቂቃቸው ይሟገቱ ነበር፡፡ ከእዚህ ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኛነት ሕግ አንዱ ነው፡፡
ይህ አዋጅ ከነሀሴ 22/2007 ፀድቆ ሥራውን ከምርጫ 2002 ማግዕስት ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀመረ፡፡ ይህን ተከትሎ አዋጁ በተለያዩ ዓለም አቀፍ የመብት ተቋማት እና ምዕራባዊ መንግስታት ዘንድ እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ ይደርስበት ጀመር፡፡ በወቅቱ "አዋጁ ከሕገ መንግስቱ ጋር ይጋጫል" በማለት ምሁራኑም ተቹ፣ ይሁን እንጂ "ሽብርተኛነት፣ ጋዜጠኛነት፣ ተቃዋሚነት፣ ፋኖነት፣ ጦማሪነት… የተባሉ ጉዳዮችን አንድ በማድረግ ሁሉንም በመደዳ ማጥቃቱን ግን አልተወም ነበር፡፡ ይባስ ብሎም በመንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃን አዋጁን "ለመከላከል" ከየትኛውም ሕግ በላይ በዛ ያሉ ዶክመንተሪዎች ተሰሩለት/አዲስ ግንባር ጅሃዳዊ ሀራካት፣ አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ) የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
አዋጁ ለፀጥታ ተቋማት (ለደህንነትና ፖሊስ) ሰፊ መብት የሚሰጥ በመሆኑ አዋጁን መሰረት በማድረግ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ስቃይና ድብደባ እደረሰባቸው ለእስር ተዳረጉ፡፡ ወትሮም የፀደቀበት ዓላማ ይህ በመሆኑ አዋጁ ያልነካው/ የማይነካው የስራ ዘርፍም ሆነ ግለሰብ የለም፡፡ በአጠቃላይ የኢፌድሪ መንግስት ከተቋቋመበት 1987 ጀምሮ ባሉት ዓመታት ውስጥ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካፀደቃቸው ዘጠኝ መቶ የሚጠጉ አዋጆች ውስጥ እንደ አዋጅ ቁጥር 652/2001 አስፈሪ አዋጅ አለ ለማለት ይከብዳል፡፡
ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ክብርን የማያውቀው ኢህአዴግ ለእስክሪብቶ ታንክ ማዘዝ የጀመረው፡፡ ሀሳብን በሀሳብ የመመከት አቅም ማጣት፣ ሀሳብን በማፈን ሌሎችን መቀጣጫ በማድረግ፣ የአሸባሪነት ወይም ሌላ ታርጋ እየለጠፈ ዜጎችን በማሳቀቅ ህጋዊ እውቀትን በተሰጠበት ሀገር ሀሳበን በነፃነት ማራመድና መነጋገነር የተገደበና ከባድ ያደረገው፡፡ እንደኔ እንደኔ ተናግሮ መተማመን የማይችል ወይም ዱላ የሚቀናው አንድም ሀሳብ የለውም አሊያም ደግሞ አለኝ የሚለው ሀሳብ እንደማያሳምን ራሱም ቢሆን ጠንቅቆ ስለሚረዳው ይመስለኛል፡፡
መንግስታችን እሱን ሲያሻው ካልሆነ በስተቀር የማያከብረውን ሕገ-መንግስት "መብት አላችሁ" ብሎ ማሳመን ከባድ ስራ ይመስለኛል፡፡ ከህገ መንግሰቱ ባሸገር ሀገራችን የተፈራረመችው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ስምምነቶች መብቶቻችንን ያስታውሱናል፡፡ እኛም ወግ ደረሰን ብለን ስንጠቀምባቸው ድንገት ከበስተኋላችን የማናውቀው ታርጋ ተለጥፎብን እንገኛለን፡፡ በዚህ ጊዜ አይደለሁም! ብንልም ጌቶች ነህ ብለዋልና "መግባት ወይም መውጣት" አሊያም" ጥምር አገልጋይ" የሚባል ቁርጥ ምርጫ ይሰጠናል፡፡
በሌላ መልኩ "ቀዩ መስመር" በጨቋኝ እና በተጨቋኝ በኩል ሲታይ ፍፁም ለየቅል ነው፡፡ ለጨቋኝ፣ ስልጣኑ፣ ገመናው፣ ባዶነቱ፣ ሙስናው የሚሳበቅበት፣ ይህም ስራውን ተዓማኒነት አሳጥቶ ስልጣን የሚነሳው መስሎ ከታየውና ያገባኛል ባዮች ተደማጭነትን ካገኙ ያ "ቀይ መስመርን" ማለፍ ነው፡፡
ለተጨቋኝ (ለህዝብ) ደግሞ፣ መብቱ ህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጠለት፣ ገዳቢ፣ አገሩ እንጂ ባለስልጣን ወይም ፓርቲ አይደለም የሀገሩን ጥቅም አሳልፎ አይሰጥም፡፡ በዚህም የሀገራችን ህጎች ሆነ ተብለው ለብዙ ትርጉም ተጋላጭ እንዲሆኑ ተደርጓል፤ በስህተት ያልተተረጎሙ ካሉም በስህተት እንዲተረጎሙ ይደረጋል እንጂ ጋዜጠኞችንም ይሁን ተቃዋሚዎችን ከማስከሰስ አይመለሱም፡፡ ይህ ደግሞ ሆን ተብሎ ለሰልጣን ጥብቅና ሲባል የተደረገ እንጂ የቃላት ድህነት ኖሮብን የተፈጠረ የሚመስለን ካለን እውነትም ያልነቃን አለን፡፡
እ.ኤ.አ በ1984 ድሬዝ እና ሴን የተባሉ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪዎች ባደረጉት ጥናት ነፃ መገናኛ ብዙሀን ባሉበት ሀገር ከፍተኛ ድህነት እና ረሀብ ተከስቶ እንደማያውቅ ይጠቁማሉ፡፡ ይህንንም ሲደግፉ ነፃ የሆነ የመረጃ ፍሰት ባለባቸው ሀገራት መንግሰታትን (ዲሞክራሲያዊ ባይሆኑም እንኳን) ከህዝቡ የሚመጣ ግፊት ጫና ውስጥ ስለሚከታቸው እና ይህንንም ለማስወገድ ሲሉ ቀድመው የህዝብን ጥያቄ የሚመልስ እርምጃ ስለሚወስዱ እንደሆነ ይተነትናሉ፡፡ ግለሰባዊ ነፃነቶች (ሀሳብን በነፃነት መግለፅን ጨምሮ) ማክበር በመንግሰት ቁጥጥር ሥር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ምጣኔ ሀብታዊ እድገት እስከ 20% ድረስ ይጨምራሉ፡፡
እንደ በመንግስት የሚተዳደሩ ፕሮጀክቶች ባይሆንም በግል ባለሀብቶች እና ተቋማት የሚካሄዱ ንግዶች ሀሳብን በነፃነት መግለፅ በሚቻልበት ሀገር ለገበያ የሚያቀርቧቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች የህብረተሰቡን ደህንነት ወይም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል ዕቃ ወይም አገልግሎት ቢያቀርቡ ነፃ መገናኛ ብዙህን ሁኔታውን በማጋለጥ ህብረተሰቡን ከጉዳት ይጠብቃሉ፡፡
እንደ ህውሀት/ኤህአዴግ ያሉ የሀሳብ ብዝሀነትን በመቆጣጠር ህዝብ እነሱ የሚሉትን ብቻ እየሰማ እንዲነዳ የሚፈልጉ መንግስታት ግን ሀሳብን ለማፈን ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ የአይን መረብን ማጥለል፣ ጦማሮችን እንደ ከብት ማገድ፣ ዜጎችን መሰለል፣ ጋዜጠኞችን ማዋከብ፣ ማስፈራራትና ማሰር፣ በሳተላይት የሚተላለፉ የሬድዮና የቲቪ ስርጭት ሞገዶችን ማገድ የሚጠቀሱ የአፈና መሣሪያዎቻቸው ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ መንግስት በዜጎች ላይ እያደረገ ያለው ስለላ መጠን ረቀቅ ያለ እና ዘመናዊ ሆኗል፡፡ ፊንፊሸር የተባለ ኢንተርኔትን በመጠቀም ዜጎች ላይ ስለላ ለማድረግ የሚያስችል የረቀቀ ቴክኖሎጂን ከሚጠቀሙ 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ሆናለች፡፡ ይህን ቴክኖሎጂ ለመግዛት ከ350 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ይጠይቃል፡፡ ታዲያ ቁጥር አንድ ጠላቷ ድህነት ለሆነ ሀገር ህገ-መንግስቱን ጥሶ ዜጎችን ለመሰለል ሲባል ብቻ ይህን ያህል ወጪ ማውጣት እውነትም አሀዳዊ ተረክ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደሚኬድ ማሣያ ነው፡፡ ምናልባትም በሳተላይት የሚተላለፉ ሬድዮ እና የቴሌቭዥን ስርጭትን ለማደናቀፍ ምን ያህል የተወሳሰበ ቴክኖሎጂ እንደሚያስፈልግና ለዚህም ሲባል ከፍ ያለ ወጪ እንደሚያስወጣ መገመት ቀላል ነው፡፡
በእርግጥ ማንኛውም መንግሰት (ፓርቲ) የሀሳብ የበላይነት እንዲኖረው ይጥራል፡፡ ኢህአዴግም የሀሳብ የበላይነትን ለማረጋገጥና ለመጎናፀፍ መከጀሉ የሚስተቸው አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጥያቄ የሚስነሳበትና ለትችት የሚጋበዝበት ሁነኛ ችግሩ ማግኘት አለብኝ ብሎ የሚያስበውን የሀሳብ የበላይነት ለመቀናጀት የተሰማራበት የእኔ አውቅልሀለሁ መንገድ ነው፡፡ ይህም የመገናኛ ብዙሃንን፣ በሙሉ በመቆጣጠር ለራሱ ፍፁማዊ ጥቅም ለማግኘት ፕሮፓጋንዳ ይጠቀምበታል፡፡ በሌላ አነጋገር ማንኛውንም ዓይነት የፖለቲካና የርዕዮተ ዓለም ፉክክር እንዲኖር አይፈቅድም፡፡
ኢትዮጵያዊ ማንነት እየጠፋ ኢህአዴጋዊ ቀለም እየተውለበለበ የሚታሰረው ታስሮ፣ የሚሰደደውም በሰው ሀገር ተሸሽጎ ደግሞ ሌላው የቀረው ዜጋ በፍርሀት ዝምታ አጎንብሶ አሊያም አወድሶ የሚኖረው ይኖራል፣ የሚያኗኑረውም "አንድ ቀን …….? እያለ ሰርክ አዲስ ቀን ይናፍቃል፡፡
በመጨረሻ ምናልባት በእኔ እምነት ኢህአዴግ ህገ-መንግሰትን አርቅቆ ህገመንግስታዊነትን ሳይሆን በሁሉም ውስጥ ፍፁማዊ የበላይነትን የተጎነፀፈ ሰርዓት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህ ይህች አገር ለውጥ የግድ ያስፈልጋታል፡፡ ሁሉንም የማይጠቅም ቢሆን እንኳን ለብዙሀኑ ሲባል ለውጥ/ አዲስ ነገር የግድ መምጣት አለበት፡፡ የለውጥ ፍርሀትን እና ተቃውሞን እንደ ችግር ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት አይቻልም፡፡ ነገር ግን በቂ ዝግጀት በማድረግ በተገቢው መንገድ መቀነስ ይቻላል፡፡ የለውጥ ፍርሀትን እና ተቃውሞን ሳይቀንሱ ግን ለውጥን መጠበቅ ዘበት ነው፡፡
የፈረንሳይ የፍርሀት ዘመን አንድ ዓመት ሳይዘልቅ በሞቀ አብዮት ተገፍፏል፡፡ አብዮት አብዮትን እየወለደ ከአራት አብዮት በኋላ የዛሬዋ ፈረንሳይ የበለፀገችና ዲሞክራዊያዊ ሆነ ተወለደች፡፡ ለእኛም ይህ የፍርሀት ዘመን ተገፍፎ ብልፅግና ዲሞክራሲ እንዲመጣ ፍርሃታችንን ለመጋፈጥ መቁረት አለብን፡፡ "መፍራት ካለብን ፍርሀትን ራሱ ነው" እንዲሉ ፈራንክሊን ሩዝቬልት ምናልበት እሰው ሀገር በስደት መኖሬን ከቅንጦት ቆጥረው ይህን ሀሳብ
ፃፍክ በማለት "አመፅን ናፋቂ፣ ግንቦት ሰባት፣ አሸባሪው! አሊያም በኢአህዴጋዊ ቋንቋ አንዳንድ የውጪ ኃይሎች…….." የሚሉ ታፔላዎቸን በመለጠፍ ሀሳቤን የሚያጨናግፉ! አሊያም ከኢአህዴግ ጋር የሚተጋገዙብኝ አይጠፉም ይሆናል፡፡ ግድየለም ያሉትን ይበሉ፣
ግን እናንተዬ፣ "የፕሬስ ነፃነት አለ" ያለን እኮ ራሱ ኢአህዴግ ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው? እሱን አምኖ የፃፈ፣ በነፃነት አቋሙን ያንፀባረቀ ሁሉ ልክ እንደ እኔ ከመንግስት ጋር ይኳረፋል፡፡ ለምን ባልኩ ዛቻ፣ ስድብና እንግልት የሰርክ ቀለቤ ሆነ ሀገሬ የኔ አልመሰልህ አለችኝ፣ እናም ተሰደድኩ፡፡ አሁንም ግን ኢትዮጵያዊነቴን ማንም አይነጥቀኝም፡፡
ለዚህ ሀሳብ መነሻ ሆኖ አሳዝኖ ያስቆጨኝ ኢህአዴጋዊው መንግሰት ከትናንት በባሰ መልኩ ዛሬም የሀሳብ ነፃነት ያፍናል፣ ጋዜጠኞችን እያደነ እስር ቤት ማጎሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ለዚህም ነው ለውጥ የግድ የሚለው ለማለት የተገደድኩት፡፡
ብሩህ ቦጋለ - biruhbogale5@gmail.com
ስዊዘርላንድ
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
January 10, 2016
የተጀመረው መብትን የማስከበር ህዝባዊ ትግልና የታየው የመተባበር መንፈስ ተጠናክሮ መቀጠል ኣለበት
ገዢው የወያኔ ቡድን ገና በኣሜሪካ መንግስት ደጋፊነት የሀገሪቷን ስልጣን ከተቆጣጠረበት 1983 ጀምሮ በኢትዮዽያውያን ዘንድ ተቀባይነት ያላገኘ ቡድን መሆኑ ግልጽ ነው። ሆኖም ይሄዉ ለሃያ ኣምስት ኣመታት በስልጣን ላይ ሊቆይ ችሏል። ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ተቃዋሚዎቹን እየገደለ፣ እያሰረ ከሀገር እያሳደደ ዛሬ ላይ ደርሷል። በሰላማዊ መንገድ ሃሳባቸውን የሚያቀርቡትንና የሚጽፉትን ያለ ምህረት በማፈን በገዛ ሃገራቸው የህሊና እስረኞች ሆነው እንዲኖሩ ኣድርጓል። ''ህገመንግስታዊ ስራትና ህገመንግስቱን ለመጠበቅ '' በሚል መፈክር ዜጎችን መኖሪያ ኣሳጥቷል። ቁጥራቸው ያልታወቁትን ጸረ ሰላም፣ ጸረ ልማትና ኣሸባሪ በማለት ገድሏል። በተለይም በኦሮሞ ወጣቶች፣ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች ላይ በማነጣጠር ኣድኖ ጨርሷቸዋል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩትን በታወቁና ባልታወቁ የማሰቃያ ቦታዎች በማጎር ሰቆቃ ፈጽሞባቸዋል። ዛሬም ከምንጊዜውም በላይ የኦሮሞ ተወላጆች በተለይም የነገ ሀገር ተረካቢዎች በዚሁ መንግስታዊ ህገወጥ ቡድን እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ይህ ቡድን በ1997 ምርጫየህዝቡን ድምጽ በኣደባባይ በመስረቁ ህገመንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ድምጻቸውን ለማስከበር ሰላማዊ ሰልፍ የውጡትን ከሁለት መቶ ያላነሱ የኣዲስ ኣበባ ወጣቶችን ያለ ምህረት በጥይት ደብድቦ ገድሏቸዋል። በወቅቱ በኦሮሚያ የተቋቋመው ኣጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ወደ ኣርባ የሚጠጉ ስዎች በኦሮሚያ ተገድለዋል።
ያ ኣልበቃ ብሎት የጸረ ሽብር ኣዋጅ በማውጣት ጭቆናን፣ የመልካም ኣስተዳደር እጦትን፣ የህግ የበላይነት መጣስን በኣጠቃላይ የመንግስታዊ ህገ ወጥነትን የተቹትን ሁሉ ኣሸባሪዎች በማለት በእስር ቤቶች ኣጉሮ ይገኛል። ሙስሊም ኢትዮዽያውያን ህይማኖታቸውን በ ነጻነት ለማካሄድ እንዲችሉ ጣልቃገብነትእንዲቆም በሰላማዊ መንገድ በመጠየቃቸው በርካቶች ተገድለዋል። ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከመንግስት ጋር ተነጋግረው ያለውን ችግር እንዲፈቱላቸው መርጦ የላካቸውን ሰዎች ኣሸባሪዎች ናቸው ብሎ ድራማ በመስራት በሃሰት በመወንጀል ወህኒ ውስጥ ኣጉሯቸው በማሰቃየት ላይ ይገኛል።
ለዚህ ሁሉ ህገወጥነት የጠቀመው የኢትዮዽያን ህዝቦች ለመከፋፈል በመቻሉ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። በመከፋፈላችን ነጣጥሎ ኣጠቃን። ለጥቃት ያጋለጠንን ምክንያት በሚገባ እያወቅን መፍትሔ ለመፈለግ ዝግጁ ሳንሆን በመቅረታችን እነሆ የመንግስታዊው ቡድን ንቀት፣ጭካኔና በደል እያንዳንዱን ቤት በማንኳኳት በሃገራችን ኑሮ ከሲኦል የከፋ ሆኖ ይገኛል። የዚህ መንግስት ንቀት ከመጠን እያለፈ ሂዶ ህዝብን ለዘመናት ከኖረበት በማፈናቀል መሬቱን በመቀማት ለውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች እየቸበቸበ ሚሊዮኖችን በማደህየት በልመና እንዲኖሩ ኣድርጓል።
ኣሁን ደግሞ ''በኣዲስ ኣበባና በዙሪያው የሚገኙ ከተሞች የተቀናጀ ማስተር ፕላን'' በሚል የቀሩትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኣርሶ ኣደሮችን የሚያፈናቅል እቅድ ኣዘጋጅቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ህዝቡን ያላቀፈ፣ ከኑሮው የሚያፈናቅልና ለከፋ ድህነት የሚዳርግ ልማት ህገመንግስታዊ መብቱን የሚጻረር በመሆኑ መተግበር የለበትም በማለት ተቃውሞ ያነሱትን ሁሉ በመናቅ ''ወደዳቹም ጠላችሁ ይተገበራል'' የሚል መልስ በመስጠት እብሪተኛነቱን በዲጋሚ ኣረጋግጧል።
ባለፈው ኣመት በተለያዩ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ ተቃውሞ ያደረጉትን ያለርህራሄ ከ80የማያንሱትን ተማሪዎችና ነዋሪዎችን በጥይት ቆላቸው።
በዚህም ኣመት ማስተር ፕላኑን ኣስመ ልክቶ ለተነሳው ጥያቄ ደንታ በማጣትና በንቀት የኦሮሚያ ምክር ቤት ( ጨፌ ኦሮሚያ) በሚባለው ስብስብ ኣማካይነት ኣዋጅ በማውጣት የማስተር ፕላኑን እቅድ ተግባራዊ የማድረግ እንቅስቃሴውን ቀጠለበት። ከዚህም ሌላ በምእራብ ሸዋ ኣምቦ ኣካባቢ የሚገኘውንና ለዘመናት ሳይነካ ህዝቡ ጠብቆ ያኖረውን የጭልሞን የተፈጥሮ ደን ለባለ ሃብት ሰጥቶ ለማውደም በመንቀሳቀሱ የኣካባቢው የኦሮሞ ተማሪዎች በኋላም ህዝቡን ጨምሮ ኣካሄዱን በሰላማዊ መንገድ በመቃወም ጥያቄ ለማቅረብ ኣደባባይ ወጡ። ለዚህም ኣምባገነኑና ህገወጡ መንግስታዊ ቡድን የሰጠው መልስ በጅምላ መግደልን ነው።በዚህም መሰረት በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ምንም የማያውቁ የትምህርት ቤት ህጻናት ወሬ ለማየት የሚሯሯጡ ሳይቀሩ በጥይት ተቆልተዋል። እናትና ልጅ እቤታቸው ደጅ ላይ በጠላት ጥይት ተደብድበው ወድቀዋል። እርጉዝ እናት በሆዷ ከያዘችው ሽል ጋር በፋሽስቶች ጥይት ተግድላለች።
እስካሁን በተጠናቀረው መረጃ መሰረት ከ100 በላይ ተማሪዎችና ሌሎች የኦሮሞ ተወላጆችን በጥይት ግድሏል።
ተደጋግሞ እንደተነገረው ይህ መንግስት እንደልቡ እንዲፈነጭና ለህዝብ ያለው ንቀት ገደብ ያጣው እኛ ተገዢዎች በመከፋፈላችን ነው። ለሃያ ኣምስት ኣመታት በተናጠል ሲንገረፍ፣ ሲንገደልና እንደ በግ መንጋ ወደ እስር ቤት ሲንጋዝ የኖርነው በኣንድነት ቆመን በቃህ ለማለት ኣለመቻላችን ነው።
ከእንግዲህ እስካሁን የነበረው ሁኔታ መቀየር ኣለበት። ኣሁን ሁላችንም ኣንድ ላይ ሆነን ለነጻነት፣ለእኩልነት ለሰላምና ለዲሞክራሲ በኦሮሚያና ኣማራ ክልል የተጀመረውን ትግል ኣጠናክረን መቀጠል ኣለብን። ሌላ ምርጫ የለም። ኣሁን የማያዳግም ትግል ተጀምሯል። የቀረው ነገር ቢኖር መላው የኢትዮዽያ ህዝቦችን ከዳር እስከዳር ማንቀሳቀስና በትግሉ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው። የነብር ጭራ ኣይይዙም ፣ ከያዙ ኣይለቁም ይላል የኣበው ምሳሌያው ኣነጋገር። የነብር ጭራ ይዘው ከለቀቁ የሚደርሰውን ኣደጋ ስለሚያውቁ ነው እንዲ ያሉት። እነዚህ ኣሁን ከፋፍለው የሚገዙን ነብር ናቸው ለማለት ኣይደለም። እነሱ ህጻናትና ሴት የሚገድሉ ፈሪዎች ናቸው። ተረቱን ያመጣሁት ኣንዴ ቆርጠው የገቡበትን የመብትና የነጻነት ትግል ከጀመሩ ዳር ሳያደርሱ መቆም ለጠላት ጊዜ መሰጠት ስለሆነ የድል ጊዜውን ስለሚያራዝም እንጠንቀቅ ለማለት ነው።
ትግሉ በሁሉም ኣካባቢዎች መቀጣጠል ያስፈልጋል። ይህን ጸረ ህዝብ የወያኔ ቡድን በሁሉም ማእዘናት ፋታ መንሳትና ማጣደፍ ይገባል። ግፍና መከራን ተሸክሞ በውስጥ ማጉረምረምና መቃጠል ዋጋ የለውም።
ይህ በኦሮሚያ የተጀመረው ትግል የሁሉም ኢትዮዽያዊ የመብት ትግል መሆኑን ያለ ማመንታት ማመን ያስፈልጋል። በኢትዮዽያ የሚገኙ የሁሉም ዜጎች መብት እየተረገጠ ፣ ዜጎች በገዛ ሃገራቸው በፍርሃትና በመሸማቀቅ የሚኖሩበት ጊዜ እንዲያበቃ ሁሉም ለመብቱ መታገል ኣለበት። በኢትዮዽያ ከህግና ከህዝብ በላይ ለሆነ ኣገዛዝ ኣንገዛም ማለት ኣለብን።
ትግሉ ዳር እንዲደርስ ከተፈለገ ለእውነተኛ የህዝቦች ነጻነት እንታገላለን ከሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠበቅ ትልቅ ሃላፊነት ኣለ። ትግሉ የተቀናጀ ካልሆነ ኪሳራውና መዘዙ ክፍተኛ ይሆናል። ኣሁን እንደታየው በኦሮሚያ የተጀመረው ሰላማዊ የመብት ጥያቄ በጀብደኛውና የህዝብ ጠ ላት የወያኔ ቡድን ወደ ደም ማፍሰስ ተሸጋግሮኣል። ይህ እንዲቆም የጋራ ትግል ኣስፈላጊ ብቻም ሳይሆን ታሪካዊ ሃላፊነት ነው።
ባለፈው ወር በመላው ኦሮሚያ የተቀጣጠለው የመብት ማስከበር ትግልን ለማዳፈን ገዢው መንግስት የወሰደው የግፍ እርምጃ መላውን የኢትዮዽያ ህዝብ ማስቆጣቱ ግልጽ ነው። በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ ያሉትና ኣምባገነኑን መንግስት ለማንበርከክ የሚታገሉት የፖለቲካ ድርጅቶችንም የትግላቸውን ኣካሄድ እንዲመረምሩ እንዳደረጋቸው ጥርጥር የለም። ለዚህም
ያደረጉትን የትግል ትብብር ጥሪ ማየቱ በቂ ነው። ለምሳሌ የኦርሞ ዲሞክራቲክ ግንባር (ኦዲግ) ቀጥሎ የተመለከተውን የትብብር ጥሪ ኣስተላልፎኣል።
''እንግዲህ የዚያች አገር ጉዳይ ያገባኛል የሚል ማንኛዉም ግለሰብ፣ ድርጅትና ተቋም፤ በአጠቃላይ የሚያስብ አዕምሮ ያለዉ እያንዳንዱ ዜጋ «እስከመቼ ድረስ እየታሠርን፣ እየተደበደብን፣ ከገዛ አገራችን እየተሰደድን፣ ከምንም በላይ ደግሞ በግፍ እየተገደልን በዚህ የጥቂቶች አገዛዝ ሥር እንቀጥላለን?» ብሎ ራሱን መጠየቅ አለበት። ያለምንም ማጋነን የአገራችንና የሕዝቦቻችን መከራና ስቃይ ከልክ ያለፈ ሆኗል። ስለዚህ አንዱ ሕዝብ ሲጠቃ ሌላዉ ከሩቅ ሆኖ የማየት በሽታ ዘላቂ መፍትሔ ያስፈልገዋል ብለን እናምናለን። ዘላቂ ሊሆን የሚችለዉ መፍትሔ ደግሞ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ተደጋግፈን ለጋራ ድል በጋራ ሆነን መታገል ብቻ ነዉ'' ይላል።
የኦርሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በበኩሉ ''The OLF calls upon all Ethiopian to join the Oromo people struggle for freedom, democracy, justice & human rights, and once for all to dismantle the genocidal regime of TPLF. To that effect, the OLF calls for all inclusive struggle that include all political parties and civil organizations that will enable the Ethiopian people to decide their destiny by establishing government of people, for people and by people in Ethiopia. ይህም በኣጭሩ ተባብረን ይህን የኣናሳና ገዳይ ቡድን ኣገዛዝ ኣሰወግደን በህዝብ፣ለህዝብና የህዝብ መንግስት በኢትዮዽያ እንዲመሰረት የጋራ ትግል እናድርግ ነው።
የግንቦት ሰባት ኣርበኞች ግንባር መሪ ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋም ሁሉም ከያለበት ጥያቄውን እያነሳ ትግሉን መቀላቀል እንዳለበትና ከኦሮሞ ተማሪዎች ጎን እንዲቆሙና ለነጻነታቸው እንዲታገሉ ትብብር ኣስፈላጊ መሆኑን ኣጽኖት ሰጥተው ጥሪ ኣቅርበዋል፣ በሃገር ውስጥም የሰማያዊ ፓርቲ ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ( ኦፌኮ) ጋር በጋራ ለመ ስራት መስማማታቸው ታቋል። በጋራ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማ ድረግ ኣቅደው በእምቢተኛው ገዢ ቡድን ተከ ልክለዋል። የሰማያዊ ፓርቲ ኣባላትም የኦሮሞን ህዝብ ትግል ደገፋችሁ ተብለው መታሰራቸውን ሰምተናል።
ይህ ኣሁን የታየው የትብብር መንፈስ ወደ ላቀ ደረጃ ማደግ ኣለበት። ይህ የኣሁኑ የትብብር ጥሪ እንዲሁ በድንገት በተፈጠረው ወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት የተከሰተ ኣይመስለኝም። ሁሉም ኣንዳችን ለኣንዳችን ኣስፈላጊዎች መሆ ናችንን በመገንዘብ የተደረገ ከልብ የመነጨ ነው ብዬ እገምታለሁ። ስለዚህ በኔ ግምት እስካሁን ድረስ እነዚህ ጥሪ ያደረጉ ድርጅቶች በጉዳዩ ላይ መነጋገር ጀምረዋል የሚል እምነት ኣለኝ። ካላደረጉ ያሳዝናል። ምክንያቱም ከዚህ በላይ የሚናባክን ጊዜ የለምና። ተባብረን በኣንድነት ካልቆምን በኢትዮዽያ ሃብት እስከ ኣፍንጫው የታጠቀውን ኣምባገነን ለማስወገድ የማይቻል ባይሆንም ብዙ መስዋእትነትን ያስከፍላል።ለዚህም ነው የጋራ ትግል ኣስፈላጊ የሚሆነው። በተግባር የማሳያው ጊዜ ኣሁን ነው። የዚህ መንግስት ገበናው ኣሁን ለሁሉም ለውጭም ሆነ ለውስጥ ይፋ ሆኗል። ይህ መንግስት የኢትዮዽያን ህዝቦች መብትና ነጻነት ረግጦ መቀጠል እንደማይችል ለሃያ ኣምስት ኣመታት ደግፈው ያቆዩት ጭምር ተገንዝበዋል። ኣሁን እያሰቡ ያሉት ማን ይተከዋል የሚለውን ነው። ጥያቄያቸው ተገቢና ማንም መጠየቅ ያለበት ነው። ስለዚህ የኢህአድግ መንግስት ከመውደቁ በፊት በሚገባ የተደራጀና መንግስታዊ ሃላፊነት የሚሸከም ድርጅት መኖሩ መረጋገጥ ኣለበት። ለህዝብ ፣ በህዝብና የህዝብ መንግሥት ለመመሥረት የሚችል ሃይል መፈጠር ኣለበት።
እስካሁን ድረስ ጭራሽ መነጋገር የማንችል መስለን ኖረናል። ያተረፍነው ነገር ቢኖር ከፋፍሎን ለሚገዛን መመቸት ብቻ ነው። ኣሁንም ይህ ሃይል እንዳንቀራረብ ሌት ተቀን እንደሚሰራ ማወቅ ኣለብን። ይህ ኣሁን የተፈጠረውን መልካም ኣጋጣሚ ተጠቅመን ህዝባችንን ከሰቆቃ፣ ግዲያ፣ እስራትና ስደት ካላዳን ተጠያቂው እኛ እንጂ ገዢዉ መንግስት ኣለመሆኑን ማወቅ ኣለብን።ይህ
ኣሁን የተደረገው የትብብር ጥሪ ወደ ተግባር ካልተቀየርና ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የተደረገ ሆኖ ከቀረ በታሪክ ፊት ተጠያቂ ከመሆንም ኣልፎ ኣሁን ህጻናት ልጆቻችንን በገፍ እየገደለ ካለው ገዳይ መንግስታዊ ቡድን ጋር ከመተባበር ተለይቶ ሊታይ ኣይችልም።
ለትብብር ጥሪው ተግባራዊነት የሚዲያዎች እገዛ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ይችላል የሚል እምነት ኣለኝ። በኦሮሚያ ተማሪዎችና ህዝቡ እያደረገ ያለውን የመብት ትግል ተከታትለው ለሃገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ላሉት ኢትዮዽያውያንና ሌሎች በማሰራጨት በኩል ያደረጉት ስራ በጣሙን የሚያስመካ ሆኖ ታይቷል። የኢትዮዽያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት)፣ ኦሮሞ ሚዲያ ነትዎርክ(OMN)፣ ገዳና( GADA.COM) ኢትዮሚዲያ ድረገጾች እንዲሁም የተለያዩ ረዲዮ ጣቢያዎች የኣሜሪካ ድምጽ ኣማርኛና ኦሮሚኛ ፕሮግራሞችን ጨምሮ የሙያና የሀገር ግዴታቸውን ተወጥተዋል ለማለት ይቻላል።
ኣሁን የተጀመረውን የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የመተባበር ጥሪም ወደ ላቀ ደረጃ እንዲደርስ ጥረት ማድረግ ኣለባቸው የሚል እምነት ኣለኝ።ሶሻል ሚድያም የተጫወተው ሚና በጣሙን የሚደነቅ ነው።
ሚዲያ ሃገር ለመገንባትም ሆነ ለማፍረስ የሚችል ትልቅ ሃይል ነው። ባለፉት ኣመታት ህዝብን ከማቀራረብ ይልቅ የማራራቁ ስራ ጎልቶ ስታይ እንደነበር የሚካድ ኣይደለም። ኣሁን ግን ሰሞኑን እንደታየዉ ህዝቦችንም ሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ ኣመለካከት ያላቸውን በማቀራረብ መርዳታቸዉን ኣጠናክረው መቀጠል ኣለባቸው። ሰዎች የመሰላቸውን ሃሳብ የመስጠት፣ የመጻፍና የመናገር መብት እንዳላቸው ቢታወቅም ኣሁን ኢትዮዽያ ባለችበት ሁኔታ ህዝብን ከህዝብ፣ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ከፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያጋጩትን ሃሳቦች፣ ጽሁፎችና ኣስተያየቶች ከማስተናገድ መቆጠብ ኣለባቸው። እኛን ለያይቶን የኣገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም የሃገር ሃብትና ጉልበት የሚያባክነውን ጸረ ህዝብ የሆነውን ኣምባገነን መንግስት በማጋለጥ ላይ በማተኮር ህዝቦቻችን የዚህ መሰሪ ቡድን ድርጊት ሰለባ እንዳይሆኑ ማስተማር፣ መምከርና የማቀራረብ ስራ በሰፊው እንዲሰሩ በበኩሌ ኣደራ እላለሁ።
በኣጠቃላይ ለነጻነት፣ለእኩልነት፣ ለሰላምና ዲሞክራሲይዊ መብታችን መከበር የተጀመረው ትግል ከግቡ እንዲደርስና በጭካኔው ወደር የማይገኝለትን ጸረ ሰላምና ኣሸባሪውን መንግስታዊ ቡድን ለማስወገድ የሃገሪቷ ህዝቦች ተባብረው ትግሉን ማፋፋም ኣለባቸው። በተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች በኩል የቀረቡት የትብብር ጥያቄዎችና የመቀራረብ መንፈስም ለዘመናት ሰቆቃ ላልተለያቸው የኢትዮዽያ ህዝቦች ሲባል ተጠናክሮ ለኣንድ ኣስተማማኝ ውጤት እንዲበቃ ሁሉም መደገፍና ግፊት ማድረግ ኣለበት።
የተባበረ ህዝባዊ ሃይል ምንጊዜም ኣሸናፊ ነው።
በቀለ ጅራታ
የቀድሞ የኦፌዴን ዋና ጸሃፊ
Ethiomedia.com – December 30, 2015
መድረክ በኦሮምያ ጉዳይ ባለ አምስት ጥያቄ መግለጫ አወጣ
(ምንጭ - የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ - ቪኦኤ)
ከመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ጉዳይ መምሪያ የወጣው ይህ መግለጫ "ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በማሠርና በማንገላታት የኦሮሞን ሕዝብ ሰላማዊና ሕጋዊ ትግል መግታት አይቻልም" የሚል ነው፡፡
መድረክ ታሥረዋል ወይም በቁም እሥር ይገኛሉ ብሎ የአሥር የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ መሪዎችን የስም ዝርዝር ካወጣበት መግለጫው ውስጥ ጥያቄዎቹና ጥሪው እንደሚከተለው ይነበባል፤
" … 1ኛ፡- የሕዝቡ ሰላማዊ ጥያቄዎች በሚነሱባቸው አከባቢዎች ጥያቄዎቹን በኃይል ለማፈን ተሰማርቶ የሚገኘው የጸጥታ ኃይል እየፈጸማቸው የሚገኙት የግዲያ፣ የእስራትና የማንገላታት እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ፣ 2ኛ፡- በዚሁ ሰላማዊ የሕዝብ ትግል ምክንያት ሕዝቡን ቀስቅሳችኋል በምል ሰበብ ለእስራት የተዳረጉት ከዚህ በላይ የተጠቀሱትና ሌሎችም የኦፌኮ/መድረክ አባላትና በሰላማዊ ትግሉ በመሳተፉቸው ምክንያት ለእስራት የተዳረጉት ዜጎቻችን በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ 3ኛ፡- በሰላማዊ የመብት ጥያቄ በመሳተፋቸው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ተገቢው ካሳ በመንግሥት እንዲከፈላቸው፣ 4ኛ፡- በሰላማዊ ዜጎች ላይ የግዲያና የማንገላታት ተግባራትን የፈጸሙ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡ፤ 5ኛ፡- ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መንግሥት ከኦፌኮ/ መድረክና ከሌሎችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ካለአንዳች ቅድመሁኔታ በመወያየትና በመደራደር ለሕዝቡ ፍትሀዊና ሕጋዊ ጥያቄ በአስቸኳይ ሕገመንግሥታዊ ምላሽ መስጠት ጊዜ ሳይሰጠው ተግባራዊ መሆን የሚገባቸውና አማራጭ የሌላቸው የችግሩ መፍትሔዎች ስለሆኑ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረጉ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ ተመሳሳይ ጭቆናና አፈና እየተፈጸመበት የሚገኘው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ወንድሙ የሆነ ው የኦሮሞ ሕዝብ ባነሳቸው ሕጋዊ ጥያቄዎች ምክንያት እየተፈጸመበት ያለውን ግፍና በደል ሊያወግዘውና የትግል አጋርነቱን ሊያረጋግጥለት ይገባል እንላላን፡፡"
መድረክ የኦፌኮ መሪዎች በእሥር ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ ስማቸውን በዘረዘረበት የመግለጫው ክፍል እንዲህ ብሏል፡፡
"… የኢህአዴግ አገዛዝ ሰሞኑን ያሰራቸው የኦፌኮና የመድረክ የአመራር አባላት ማለትም፡- 1ኛ፡- አቶ በቀለ ገርባ የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር፣ 2ኛ፡- አቶ በቀለ ነጋ የኦፌኮ ዋና ጸሐፊና የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፤(በቁም አሥር ላይ የሚገኙ) 3ኛ፡- አቶ ደጀነ ጣፋ የኦፌኮ ም/ዋና ጸሐፊ፣ 4ኛ፡- አቶ ደስታ ድንቃ የመድረክና የኦፌኮ የወጣቶች ሊግ ሊቀመንበርና የኦፌኮ የኦዲት ኮሚቴ አባል፣ 5ኛ፡- አቶ ጉርሜሳ አያኖ የኦፌኮ የወጣቶች ሊግ ም/ሊቀመንበርና የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል፣ 6ኛ፡- አቶ አዲሱ ቡላላ የኦፌኮ ወጣቶች ሊግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ 7ኛ፡- አቶ ደረጀ መርጋ የኦፌኮ የወጣቶች ሊግ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ 8ኛ፡- አቶ ዓለሙ አብዲሳ የኦፌኮ ወጣቶች ሊግ ዋና ጸሐፊ፣ 9ኛ፡- አቶ ጣሕር -------- የኦፌኮ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ 10ኛ፡- አቶ እስማኤል ----- በኢሉባቦር ዞን የዳርሞ ወረዳ የኦፌኮ ተጠሪ እና ሌሎችም በርካታ የኦፌኮ/መድረክ አባላትና በሰላማዊ ትግሉ በመሳተፋቸው ከመቶ በላይ የተገደሉትና በሺዎች የታሰሩት ወገኖቻችን ጥያቄዎቻቸውና ትግላቸው ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌን መሠረት ያደረገና በሰላማዊ አግባብ የተጀመረ መሆኑን እኛ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳንሆን መላው ዓለምም የሚያውቀው እውነት ነው፡፡…"
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ሰሞኑን ይሰጧቸው በነበሩ መግለጫዎች የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሕዝብ ካልተቀበለው ተግባራዊ እንደማይደረግ መናገናቸውና ኦሮምያ ውስጥ እየታየ ያለው ሁኔታ "የጥፋት ኃይሎች" ሲሉ በጠሯቸው የተቀነባበረ እንደሆነ በመግለፅ መንግሥቱ "የማያዳግም እርምጃ" እንደሚወስድ ሲያውቁ ቆይተዋል፡፡
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
January 9, 2016