Thursday, September 1, 2016

 ኢትዮጵያ፡ ከጭፍን የፖለቲካ ጥላቻ ባሻገር፣ Posted in Amharic Translations By almariam [almariam.com] On August 23, 2016 ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የእምነቴ መርሆዎች፡ በአሁኑ ጊዜ ጥላቻ በኢትዮጵያ ሕዝብ እና በነጻነት፣ በዴሞክራሲ እና በሰብአዊ መብት ጥበቃ የተፈረከሰከሰ ግድግዳ መካከል የቆመ ነገር ሆኖ ይገኛል፡፡ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ጥላቻን የፖለቲካ መጠቀሚያ መሳሪያ አድርጎት ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በዘ-ህወሀት እየተቀነቀነ ያለው የጭቃ ግድግዳ ጥላቻ በሕዝባዊ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አመጽ ዶግ አመድ እየሆነ በየቦታው ባስደማሚ ሁኔታ በራሱ በዘ-ህወሀት ላይ በመፈረካከስ ላይ ይገኛል፡፡ ክልሎች (የዘ- ህወሀት የአፓርታይድ ባንቱስታንስ አቻ) እንደበረዶ ሲሟሙ እንደ ቅቤ ሲቀልጡ በዓይናችን በብረቱ በመመልከት ላይ እንገኛለን፡፡ ዘ-ህወሀት ላለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል ስልጣንን ጠቅልሎ በስልጣን ማማ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ እንዲቆይ ያደረገው ዋና ምክንያት ጭፍን የጎሳ እና የኃይማኖት ጽንፈኝነት የፖለቲካ ጥላቻን ሲያራግብ በመቆየቱ ነው፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በየቦታው ከዘ-ህወሀት የክልል እስር ቤት በሮችን በሰላማዊ አመጽ እየሰበሩ በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ ጀግኖቹ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በጥላቻ ጌቶች ላይ በአስደማሚ ሁኔታ በማመጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች በጽኑ የሰላማዊ የእምቢተኝነት የትግል መንፈስ እጆቻቸውን በማጣመር ምንም ዓይነት የዘ-ህወሀት ኃይል መንፈሳቸውን እንደማይሰብረው በማወጅ “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች” በሚል መሪ ቃል እየተመሩ ጉዟቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዘ-ህወሀት የጥላቻ ሰለባ ሆነው ለበርካታ ጊዜ ከመቆየታቸው አንጻር በስቃዮቻቸው እና መከራዎቻቸው ስፋት እና ጥልቀት እንደ አንድ ሆነው ተባብረዋል፡፡ የኦሮሞ ልጆች በሰላማዊ መንገድ መብቶቻቸውን በመጠየቃቸው ብቻ በግፈኛው አገዛዝ እልቂት በተፈጸመባቸው ጊዜ አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ እና ሌሎች ወላጆች በሙሉ አልቅሰውላቸዋል ምክንያቱም እነዚህ ልጆች የእናት ኢትዮጵያ ልጆች ናቸውና፡፡ የአማራ፣ የትግሬ፣ የጉራጌ እና የሌሎች ወላጆች ልጆች ላይ ዘ- ህወሀት እልቂትን በፈጸመ ጊዜ የኦሮሞ ወላጆች ለእነዚህ ልጆች አንብተዋል ምክንያቱም ሁሉም ልጆች የእናት ኢትዮጵያ ልጆች ናቸውና፡፡ እነዚህ ጥላቻን ሲዘሩ የቆዩት በአሁኑ ጊዜ በህዝቦች ህብረት እና አንድ መሆን የዘሩትን ማጨድ ጀምረዋል፡፡ ዘ-ህወሀት ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የእርሱ ዕድል እና ዕጣ ፈንታ ከትግራይ ሕዝብ ዕድል እና ዕጣ ፈንታ ጋር የተሳሰረ እና የተቆራኘ እንደሆነ አድርጎ በቅጥፈት ሲሰብክ ቆይቷል፡፡ እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን ዘ-ህወሀት ማንንም የኢትዮጵያ እውነተኛ ልጆች አይወክልም፣ ሊወከል የሚችለው ግን ከሁሉም የጎሳ ቡድኖች እና የእምነት ተቋማት ያሉ ሆድ አምላኩ እበላባይ አግበስባሾች እና ከእርሱ የበከተ የሙስና ማዕዱ ተቋዳሽ የሆኑትን አባሎቹን፣ ደጋፊዎቹን እና ግብረ አበር ታማኝ ሎሌዎቹን ብቻ ነው፡፡ ፈይሳ ሌሊሳ በሪዮ ኦሊምፒክ ብር መዳልያ ተሸላሚ የኢትዮጵያ ወጣቶች እምቢተኝነት ምልክት ሲያሳይ የሪዮ ማራቶን የነሐስ ማዳሊያ ያገኘው ፈይሳ ሌሊሳ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ያለውን ታላቅ ክብር ድሉን ከተቀዳጀ በኋላ እጆቹን በማጣመር በዓለም አደባባይ አሳይቷል፡፡ የብልህነት የካርቱን ገጸ ባህሪ ባለው እና በስም ፖጎ እየተባለ በሚጠራው እና በእኔ እድሜ በጣም አስቂኝ ቀልዶችን ያቀርብ በነበረው ቀልደኛ ትችቴን ልጀምር፡፡ በዚያ አስቂኝ በሆነው የእንስሳት የካርቱን ቀልድ ረግራጋማ በሆነ አካባቢ በሚኖር ማህበረሰብ ውስጥ የአሜሪካንን ብዙሀን ህዝብ በመወከል ከተመሳሳይ ጉዳዮች ጋር እየተፋጠጠ ይኖር ነበር፡፡ ያ ማህበረሰብ መፈረካከስ ጀመረ ምክንያቱም የአካባቢው ኗሪዎች በጣም ጠቃሚ እና አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አብረው በመግባባት መኖር አልቻሉም፡፡ በማይረቡ ጉዳዮች ላይ በመጨቃጨቅ እና መጥፎ ባህሪን በሚያንጸባርቅ መልኩ በመወዛገብ ጊዚያቸውን በከንቱ ያሳልፉ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ፖጎ ይኖርበት የነበረው ረግራጋማ ቦታ በፍርስራሽ እና ቁርጥራጭ ቆሻሻ ነገሮች ተሞልቶ አየው፡፡ በዚህ ጊዜ ፖጎ በከፍተኛ ደረጃ በመተንፈስ እና ተስፋ በቆረጠ የስሜታዊነት መንፈስ እንዲህ አለ፣“ከጠላታችን ጋር ተገናኘን፡፡ እርሱም እኛው ነን!“ ነበር ያለው፡፡ ባለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ በፈጠረው እና ኮትኩቶም ባሳደገው የፖለቲካ ጥላቻ ስሜታዊነትን በተላበሰ እና ተስፋ በቆረጠ መልኩ የፖጎን አባባል በመዋስ እንዲህ በማለት አውጃለሁ፡ “በጥላቻ ከተሞሉት ጋር ተገናኘን፡፡ እነርሱም እራሳችን ነን!“ ባለፈው ሳምንት “አእምሯቸው የደነዘ አማሮች፣ የኦሮሞ ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች በ2016 በኢትዮጵያ ምድር እየተነሱ ነውን?” በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው በነበረው ትችት በርካታ የሆኑ መደበኛ እና ሌሎችን አንባቢዎቼን ቀልብ የሳበ ለመሆኑ ትምህርት ወስጀበታሁ፡፡ የዚህ ውሱን የሆነ ትችት በድረገጽ እና በማህበራዊ የግንኙነት መስመሮች በአንባቢዎች ላይ የነበረው ተደራሽነት ልዩ በሆነ መልኩ ከተለመደው በላይ በእጅጉ ልቆ ታይቷል፡፡ ግን ለምን? ተደራሽ ከሆኑት አንባቢዎች ለእኔ ትችት የተሰጡት ግብረ መልሶች የተለያዩ ሲሆኑ ጥቅል መንፈሳቸው እንደሚከተለው ተጨምቀው ቀርበዋል፡ 1ኛ) የጥላቻ ንግግርን እና የጥላቻ አራጋቢዎችን ውስብስብ ጉዳይ በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ በሌላ መልኩ መቅረብ ሲኖርበት እንደዚህ ባለ “አስደንጋጭ” እና “ፊት ለፊት በሆነ መልኩ” በብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች ማቅረብ እንዳልነበረብኝ ሀሳብ ቀርቦልኛል፡፡ 2ኛ) ለበርካታ ጊዜ ውጉዝ ከማሪዮ በመሆን አይነኬ ሆኖ የቆየውን “የጎሳ ንቀት” እና “የጎሳ ጥላቻ” አንገብጋቢ ርዕሰ ጉዳይ ለሕዝብ መወያያ አድርጌ ማቅረብ እንደሌለብኝ ተነግሮኛል፡፡ ለዚህም ይላሉ ምክንያታቸውን ሲያቀርቡ እንደዚህ ያለውን ነገር ለሕዝብ ውይይት በይፋ ማቅረብ ልማዳችን አይደለም (“ነውር ነው”) የሚል ነው፡፡ 3ኛ) ይህ ትችት መቅረብ አልነበረበትም ምክንያቱም የጎሳ ግንኙነቶችን ያሻክራል እናም በዚህ መልኩ በጎሳ ጥላቻው ላይ የበለጠ “ነዳጅ ያፈርከፈክፋል” የሚል ነው፡፡ 4ኛ) በእኔ ትችት ላይ የቀረበውን እና ያንን ድምጹን ከፍ አድርጎ ኢምክንያታዊ በሆነ መልኩ በምስል እና በድምጽ በተደገፈ ሁኔታ የዘረኝነት ቅስቀሳ ሲያካሂድ የነበረውን ሰው ስም እና ማንነት በመጥቀስ ማሳፈር እንደነበረብኝ ይጠቅሳል፡፡ አቅራቢው ምክንያቱም ይላሉ ያ ሰው በኢትዮጵያ ዲያስፖራ የዘ-ህወሀት ዋና ጠርናፊ/አገልጋይ ሎሌ መሆኑ(ኗ) ይታወቃልና ነው የሚሉት፡፡ 5ኛ) እንደዚያ ያለውን “የወረደ ዝቅተኛ” በኢንተርኔት በዓለም አቀፍ ደረጃ እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ ድምጹን ከፍ አድርጎ የጥላቻን መርዝ ለሚተፋ እና ኢምክንያታዊ ለሆነ ሰው ትኩረት ማድረግ እንደሌለብኝ የሚያሳስብ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ “የወረደ ዝቅተኛ” እና በደም ፍላት በንዴት በሚናገር ሰው ላይ ትችት በማቅረቤ ለእነርሱ እውቅና እና ሕጋዊነትን እንደመስጠት እንደሚቆጠር ያላቸውን አስተያየት ገልጸዋል፡፡ 6ኛ) ሁሉም የጥላቻ አራጋቢዎች ጥላቻቸውን በተጠናከረ መልኩ እንዲተፉ የበለጠ የሚያደፋፍር እንዲሆን እንዳደርግሁ ጠቁመዋል፡፡ ምክንያቱም በወደፊቱ በእኔ ትችቶች የሕዝብን ቀልብ እንደሚያገኙ ይጠብቃሉና ብለዋል፡፡ 7ኛ) በዚህ አሁን በሀገሪቱ ውስጥ በጣም አንገብጋቢ በሆነው ጊዜ ላይ ስለጥላቻ እና በጥላቻ ስለተሞሉ ሰዎች ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ መቅረብ አልነበረበትም፣ ምክንያቱም ጥቂት ሰዎችን እንዲበሳጩ እና በንዴት ደመነፍስ በሆነ መልኩ እርምጃ እንዲወስዱ ያደፋፍራልና በማለት አስተያየታቸውን ያቀርባሉ፡፡ 8ኛ) ይህንን ትችት በማቅረብ በእርግጠኝነት በተወሰኑ ቡድኖች ላይ ጥላቻን የማራመድ ተልዕኮ እንደፈጸምኩ ትችት ቀርቧል፣ ምክንያቱም ይላሉ ትችት አቅራቢው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የጥላቻ አራጋቢዎችን ተልዕኮ እንዳራገብኩ ይተቻሉ፡፡ 9ኛ) በአሁኑ ጊዜ ዘ-ህወሀት ለደጋፊዎቹ እና ለተከታዮቹ በእኛ ላይ እየተነሱብን ነው እናም ከእኛ ጎን በመሰለፍ እያንዳንዳችሁ እኛኑ እንድትቀላቀሉ የሚል ስብከት እንዲያካሂድ እንዳስቻልኩት አድርገው ጽፈዋል፡፡ 10ኛ) እኔ እራሴ የጥላቻ አራጋቢ እንደሆንኩ እና የጥላቻ አራጋቢዎችን መልዕክት እራሴ በመድገም ላይ እንደምገኝ እና ከዚህም በተጨማሪ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በዘ-ህወሀት ላይ የማይናወጥ እና ጠንካራ ትችት አቅራቢ እና መንግስት ምንጊዜም ቢሆን መልካም ነገር ቢሰራም በምንም ዓይነት መንገድ ፈጽሞ ዕውቅና እንደማልሰጥ በማድረግ ትችታቸውን አቅርበዋል፡፡ 11ኛ) እኔ ባቀረብኩት ትችት ላይ ሁሉንም የጥላቻ አራጋቢዎች ማቅረብ እንደነበረብኝ እና አንድን የጥላቻ አራጋቢ ቡድን ብቻ ነጥየ በማቅረብ ማስተናገድ መሞከሬ ፍትሀዊ እንዳልሆነ አድርገው ጽፈዋል፡፡ 12ኛ) የጥላቻን ርዕሰ ጉዳይ በሕዝብ ፊት ለውይይት በአደባባይ ማውጣቴ ታላቅ ድፍረት መሆኑን ምክንያቱም ይህ ርዕሰ ጉዳይ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በእርግጠኝነት በግል እንኳ ለመናገር የሚሸሹት እንደሆነ ትችታቸውን አቅርበዋል፡፡ 13ኛ) ይህንን የዘረኝነት ቅስቀሳ ጉዳይ ለሕዝብ በአደባባይ ማቅረቤ ትክክለኛ ሰው መሆኔን ጠቅሰዋል ምክንያቱም ይላሉ አቅራቢው ከብዙ ጊዜ ጀምሮ እኔ የሞራል ስብዕና መሪ እንደሆንኩ በመግለጽ በዚህ እንድቀጥልበት ጠቁመዋል፡፡ 14ኛ) ሌሎቹ ደግሞ እኔ ባቀረብኩት ትችት በጣም እንደተበረታቱ እና ሌሎችንም እንደዚህ ያሉ አይነኬ ጉዳዮችን/taboos እየፈለፈልኩ በማውጣት ለሕዝብ ለአደባባይ እንዳቀርብ ያላቸውን ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ 15ኛ) እንደዚሁም ሁሉ ብዙውን ጊዜ በተረሱ ጎጂ እና ባረጁ ልማዶች፣ ወዘተ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደዚህ ያለ ትችት ማቅረብ እንዳለብኝ ሀሳባቸውን ያቀረቡም አሉ፡፡ የእኔን ትችቶች የሚያነቡ ሰዎች ከእራሳቸው አጀንዳዎች፣ አመለካከቶች፣ ምርጫዎች እና ሀሳቦች ጋር በማዛመድ እንደሚተረጉሟቸው ጥርጥር የለኝም፡፡ ያ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፣ እናም በሕዝብ የአደባባይ የክርክር ጭብጦች እና ውይይቶች ላይ ሊቀርቡ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከላይ ለቀረቡት በርካታ ነጥቦች በሙሉ የእኔ አጭር መልስ የእኔ ትችት ስለጥላቻ እንጅ ጥላቻን ስለሚያራግቡ የጥላቻ አራማጆች ጉዳይ አይደለም የሚል ነው፡፡ የእኔ እምነት ሞሀንዳስ ጋንዲ እንዳሉት “ሀጢያትን እራሱን ጥላ እንጂ ሀጢያተኛውን እራሱን አይደለም“ በማለት ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡ ሰዎች በአጠቃላይ ስለጥላቻ የአስፈሪነት ኃይል ዕውቅና ለመስጠት መፍራቱን ማስወገድ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥላቻ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉልበት ያለው አውዳሚ ኃይል እንደሆነ በሰው ልጆች ላይ ግንዛቤ የተወሰደበት ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ግን ጥላቻ በሁላችንም ልቦች ውስጥ ይኖራል፡፡ ይህንን ልንክድ እንችላለን፣ ጥላቻ አንደሌለ ለመስመሰል አንሞክራለን፡፡ ሆኖም ግን በአልጋችን ላይ ስንጋደም በጨለማ የበቀል ቋንቋ ለበርካታ ጊዚያት በጆሯችን ላይ ያንሾካሹካል፡፡ ጥላቻን በሚመለከት ማንም ከጥርጣሬ በላይ አይደለም፡፡ ማንም ሰው ወይም ደግሞ ሕዝብ በጥላቻ ላይ የጠቅላይነት ይዞታ የለውም፡፡ የአማራ፣ ኦሮሞ፣ የጉራጌ…የአሜሪካ፣ የሩሲያ፣ የቻይና…የጥላቻ አራማጆች ይኖራሉ፡፡ ጥላቻ የሚጀምረው “በእራሳችን እና በእነርሱ አእምሮ” ውስጥ ነው፡፡ ጥላቻን እራሱን እጠላለሁ እንጅ የግዴታ የጥላቻ አራማጆችን እጠላለሁ ማለት አይደለም፡፡ ለጥላቻ አራጋቢዎች እውነታውን እስከ አፍንጫቸው ድረስ እናገራለሁ እንጅ በምንም ዓይነት መልኩ እነርሱን አልጠላም፡፡ የተሰበከው የዘር ጥላቻ በድምጽ እና በምስል ተደግፎ እውነተኛ የሆነ እና መቶ በመቶ ተጨባጭነት ያለውን የዘር ቅስቀሳ በዓለም ላይ ያሉ ወገኖቼ ሁሉ እንዲሰሙት እና የእራሳቸውን ትዝብት በመውሰድ ላለመሞት እና ከእልቂት እንዲተርፉ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳሰብሁ እንጅ ቃሪያ አምባቃሪያ፣ ጨው ጭረጨው ወይም ደግሞ አቁማዳ ቀልቀሎ አላልኩም፡፡ ታዲያ እውነቱ መነገሩ፣ አካፋው አካፋ እንጅ አዷማ መባል የለበትም መባሉ ነውርነቱ ከምን ላይ ነው? ደግሞስ እኛ በይሉኝታ እና በኋላቀር አድርባይ ጎታች ባህል ተጠፍንገን እውነትን ላለመናገር ተሸብበን የምንኖረው ለምን ያህል ጊዜ ነው? የተባለውን እንዳለ ማቅረብም የዘረኝነት ቅስቀሳ ሳይሆን የዘረኝነት ቅስቀሳ እያደረገ ያለውን ሰው ማንነት እና የአስተሳሰብ ዝቅጠት በሕዝብ አደባባይ ማጋለጥ እና እንደ ነፋስ እንዲቀል ማድረግ እንጅ ሌላ ሊሆን ከቶ አይችልም፡፡ ስለዚህ የዘር ቀስቃሹ “…ጎጃሜው (የአማራ ሕዝብ) they are called retards, retards (ደነዞች) ነው የሚባሉት፡፡ጎንደሬው (ሌላው የአማራ ሕዝብ) ጠላት ነው ሊሸለሙ አይገባቸውም፣(ደነዞች) retards ናቸው በአስተሳሰብ፣ በጭንቅላት በጣም ዝቅ ያሉ ዝቅተኞች retards ናቸው…” እያለ በአደባባይ የዘር ቅስቀሳ ያደረገው ሳያፍር የተናገረውን እንደወረደ ሀቁን ማቅረብ የዘረኛውን ሰው ሀሳብ እንዳለ የመደገፍ አባዜ ካልተጠናወተ በስተቀር ነውርነቱ ከምን ላይ ነው? ለዚህ ያዋሉትን ጊዜ እና ጉልበት ዘረኝነትን ለሚሰብከው ሰው በመገሰጽ ለነብሱ ንስሀ እንዲገባ ለተዘለፈው ለብዙሀኑ ሕዝብ ክብር ሲባል ደግሞ በአደባባ ይቅርታ እንዲጠይቅ ቢመክሩት ምንኛ የምሉዕ አስተሳሰብ ባለቤት በሆኑ! ነው ወይስ ደግሞ የዘር ቅስቀሳውን ማድረግ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ቀኖናዊ መርህ ይፈቅዳልና ተዋቸው እዳሻቸው ሕዝብን እየዘለፉ፣ ሀብቱን እየዘረፉ ይኑሩ ነው የሚሉት? አካፋ አሁንም አካፋ መባል እንጅ ማጭድ ወይም ሌላ መባል የለበትም፡፡ ይህ የእኔ መርህ ነው! የምንግባባ ይመስለኛል፡፡ “ሰው ለሰው ተኩላ ነው (Homo homini lupus est” የሚለውን የሰውን ልጅ ታሪክ አውቃለሁ፡፡ እኔ ግን ጥላቻ ነው የሰውን ልጅ ተኩላ የሚያደርገው እላለሁ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በዕጩ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ቅስቀሳው በየመድረኩ ላይ በመሰየም በአሜሪካ ሀገር የጥላቻን ወንጌል በመስበክ ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን እውነተኛው ወንጌል የሚያስተምረን እንዲህ የሚል ነው፣ “የሰው ልጅ ልቦች በበለጠ መልኩ በሰይጣናዊነቶች የተሞሉ ናቸው፣ እናም እየኖሩ ባሉ ሰዎች ልቦች ውስጥ እብደት አለ፡፡“ በእኔ የኃይማኖት ልማድ ከሁሉም ሰይጣናዊነቶች በላይ የሆነ እና ማቋረጫ በሌለው መንገድ መልካም የሆነ አንድ ሰው ብቻ አለ፡፡ ሆኖም ግን “በሰው ልጆች ልቦች ውስጥ ተደብቆ የሚኖረውን ሰይጣናዊነት የሚያውቀው ማን ነው?” እኔ እንደማስበው ከሆነ በእኔ ላይ የቀረቡት በርካታዎቹ የትችት ግብረ መልሶች እና ስሜቶች አስበውበትም ይሁን ሳያስቡት ሁሉም አንድ ነገር ይጋራሉ፡ የጽሁፍ ምርመራ/ሳንሱር (censorship)፡፡ ለእኔ እንደሚመስለኝ የግብረ መልሶቹ ዋና ዳህራ ስለጥላቻ እና የጥላቻ አራጋቢዎች ርዕሰ ጉዳይ መጻፍ እንዳልነበረብኝ ነው አጽንኦ በመስጠት የቀረቡት፡፡ በሌላኛው አማራጭ የህብረተሰቡን ይፋዊ ያልሆነ የዝምታ የድባብ አባዜ (የኢትዮጵያ የማፊያ ወንጀለኞች ዝምታ) የመከተል እና የጥላቻ ንግግር የለም ቢኖርም እንኳ ሊኖር የሚችለው በጋነም ውስጥ ብቻ በዝቅተኞቹ ውስጥ እንጅ በነባራዊ ዓለም ውስጥ በፍጹም የለም እያልኩ የማስመሰል እርባና ቢስ ንግግር እንዳቀርብ ነው የተፈለገው፡፡ በሌላ አባባል እራሴን በእራሴ ላይ የጽሁፍ ምርመራ ገደብ/ሳንሱር (censorship) እንዳስቀምጥ እና ትችት በዚህ መልክ መጻፍ እንደሌለብኝ፣ ወይም ደግሞ ዓለም አቀፍ ጦማሪዎች የሚገናኙበት ድረገጽ እና ማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች በገፍ የሚያሰራጩትን የእኔን ትችቶች ማረም/ ሳንሱር (censor) ማድረግ እንዳለባቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ የጥላቻ ንግግር ሊወገድ ወይም ደግሞ ሊጠፋ አይችልም፣ በዝምታ፣ ወይም ደግሞ በንቀት እና በምንግዴለሽነት፡፡ የጥላቻ ንግግር እንደ እንጉዳይ በጨለማ ውስጥ ይፈላል፡፡ ሆኖም ግን በብርሀን ወሳኝ ትንታኔ እና እውቀት ህልውና እርባና ቢስነቱ ይታያል፡፡ የጽሁፍ ምርመራ/ሳንሱር ለእኔ ጥልቅ ተቃውሞ የማሳይበት እውነታ ነው፡፡ ጥንታዊ የግሪክ ምክር ቤት አባላትን በሚመለከት ጆን ሚልተን በጣም ህይወትን በሚያነሳሳ መልኩ አቅርቦት በነበረው የመናገር ነጻነት እና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት የፍልስፍና መርሆዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የጽሁፍ ምርመራ/ሳንሱር ንግግር ለኔ አስተሳሰብ መሰረታዊ ነው፡፡ የጥላቻ አራጋቢዎች ጥላቻቸውን መግለጽ እንዲችሉ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ እና በሕዝባዊ ውይይቶች ሁሉ የመከላከል የእራሴ ድርሻየን ባለፉት አመታት ተዋጥቼአለሁ፡፡ የዩኤስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትህ አካላት በወጣት አፍሪካ አሜሪካውያን ላይ ለሚያሰራጯቸው የጥላቻ መልዕክቶች፣ ዕጩ ፕሬዚዳንቶች በምርጫ ዘመቻቸው በግትራዊነት አቋም አንድ የተለየ እምነት ያለው ህብረተሰብ ወደ እነርሱ ሀገር እንዳይገባ እገዳ ለሚጥሉት ወይም ደግሞ ተኩሰው ለሚገድሉ እና በኋላ ጥያቄ ለሚያቀርቡ (ምክንያቱም የጥቁሮች ህይወት ጉዳያቸው ስላልሆነ) ታማኝ ላልሆኑ የፖሊስ ኃላፊዎችም ቢሆን እውነታውን እስከ አፍንጫቸው ድረስ እናገራለሁ፡፡ የእምነት ተቋማት ምክር ቤት እየተበላ በሚጠራው እና በኢትዮጵያ ውስጥ የኃይማኖት ጽንፈኝነት ጥላቻን ለመዋጋት ለተመሰረተው ድርጀት በተለያዩ አጋጣሚዎች የእራሴን ሀሳብ ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ2010 በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት የመናገር መብት እንዳለው ሽንጤን ገትሬ እና ፍቅርን በተላበሰ መልኩ ስከራከርለት እንደነበር በርካታዎቹ አንባቢዎቼ እንግዶች አይደሉም፡፡ (“ሚስተር ዜናዊ ኮሌጅ ሄደ!” የሚለውን ትችቴን መመልከት ይችላሉ፡፡ አምባገነኑ መለስ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የስልታዊ ጥላቻ አራጋቢ ዋና መሀንዲስ በመባል ይታወቃል፡፡ የእራሱን ስልጣን ለማጠናከር በሚል እኩይ ዓላማ የጎሳ ክፍፍል እና ጥላቻን በመፍጠሩ ምክንያት ከግብረ አበሮቹ፣ ከመሰሎቹ እና ከታማኝ ሎሌዎቹ ችሮታ ተሰጥቶታል፡፡ በኮሎምቢያ የዓለም መሪዎች መድረክ/World Leaders Forum ላይ አምባገነኑ መለስ አቅርቦት በነበረው ንግግር ላይ ዲያስፖራ ኢትዮ-አሜሪካውያን ምንም ዓይነት ልዩነት የሌለው በሚመስል መልኩ ሁሉም ተቃውሞ አቅርበውበት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ታዋቂ የሆኑ ጋዜጠኞችም ግፊት ነበረበት፡፡ የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ለሆኑት ለሊ ቦሊንገር መለስ ለጉባኤው መጋበዝ እንደሌለበት የሚጠይቅ ጠንካራ እና አነቃቂ የሆነ ደብዳቤ ጽፈው ለነበሩት የእኔ ጀግና እስክንድር ነጋ እና ሰርካለም ፋሲል ለእኔ ልብን የሚነካ የሀሳብ መለያየት የነበረበት ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ አንድ ሰው ከሚወዳቸው እና ከሚያደንቃቸው አጠቃላይ ከሆኑ ጀግኖች እና ጅግኒቶች ይልቅ መርህን ከሰዎች በላይ አድርጎ ማስቀመጥ መቻል በጣም ቆጥቋጭ እና ከመግለጽ በላይ አስቸጋሪና መንፈስ የምበጠብጥ ነገር ነው፡፡ እዚህ ላይ እንዲህ የሚሉትን የፕሮፌሰር ቾምስኪን ምክሮች መጥቀስ አስፈላጊ ነው፣ “የምንንቃቸው ሕዝቦች ሀሳቦቻቸውን በነጻነት በመግለጽ መብቶቻቸው ላይ የማናምን ከሆነ በነጻነት በእራሱ ላይ እምነት የለንም፡፡“ ስልታዊ የጥላቻ አራጋቢ መሀንዲሱ አምባገነኑ መለስ እንኳ ሀሳቡን የመግለጽ መብት አለው ነበር ያልኩት፡፡ እንደ ተማሪ እና እንደ የአሜሪካ የሕገ መንግስት ባለሙያ በጽሁፍ ምርመራ ላይ ያሉኝ ሀሳቦች እንዲህ በሚሉት በዩኤስ ተባባሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ በፖተር ስቴዋርት በሚገባ ተቀምረው ተቀምጠዋል፡ የጽህፍ ምርመራ/ ሳንሱር ህብረተሰቡ በእራሱ ላይ ምንም ዓይነት እምነት የሌለው መሆኑን ያንጸባርቃል፡፡ የጸሁፍ ምርመራ የኃይል አገዛዝን የሚጠቀም አገዛዝ መለያ ዋና ባህሪ ነው፡፡ ከብዙ ገዜ በፊት የእኛን የመጀመሪያውን ማሻሻያ/First Amendment የጻፉት ሰዎች የተለየ ነገር ግልጽ አድርገዋል፡፡ አንድ ማህበረሰብ ጠንካራ ለመሆን የሚችለው እውነተኛ ነጻነት ሲኖረው ብቻ ነው በማለት አምነዋል፡፡ በዚህ ዓይነት የገለጻ አድማሳቸው ብሩህ ሆኖ በሚታያቸው የማህበረሰብ ምርጫ ላይ ከፖሊስ መጥፎ ጣልቃገብነት ወይም ደግሞ ከዳኛ ጠንካራ እጅ ነጻ መሆን ላይ እምነታቸውን ለተሻለ ወይም ደግሞ ለመጥፎ ነገር አስቀምጠዋል፡፡ ስለሆነምየሚጎረብጠውን፣ ለስላሳ እና ብልግና ያለበትን መግለጫ በማረቅ ከምንም በላይ በታማኝነት የሚከላከለው ሕገ መንግስት ነው፡፡ ለእኔ ምንም ዓይነት ዋጋ የሌለው ነው በማለት የገመትኩት መጽሀፍ ለጎረቤቴ ዋጋ ያለው አንድ ነገር ማስተላለፍ ይችላል፡፡ እራሳቸችንን የሰዋንለት ሕገ መንግስት ነጻ ማህበረሰብ እያንዳንዱ ለእራሱ [ለእራሷ] ለመምረጥ የሚያስችል ሰነድ ነው… (በጊዘንበርግ ቪ. ዩናይትድ ስቴትስ፣ 383 U.S 463 (1966)፣ አጽንኦ ተጨምሯል፡፡ ባለፉት አስር ዓመታት መደበኛ አንባቢዎቼ “በስልጣን ላይ ላሉት” እንዲሁም ለስልጣን ረሀብተኞች፣ ለስልጣን ጥመኞች፣ ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ ስልጣን ለሚጠቀሙ፣ ስልጣናቸውን በተሳሳተ መንገድ ለሚጠቀሙ እና ምንም ዓይነት ስልጣን ለሌላቸው ስልጣን የለሾች እውነት መናገር የሚለውን ዓላማዬን ለእራሴ የመረጥኩ መሆኔን ያውቃሉ፡፡ በስልጣን ላይ ላሉት እውነቱን እናገራለሁ ምክንያቱም እንዲህ በሚለው የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል አምናለሁና፣ “እውነት ነጻ ያወጣሀል፡፡“ እውነት በመናገር ተልዕኮዬ ተነሳሽነቱን የወሰድኩት ከፕሮፌሰር ኤድዋርድ ሰይድ እና ከፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ከሁለቱም አቻ ከሌላቸው አንጋፋ ልሂቃን ነው፡፡ ፕሮፌሰር ሰይድ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሕዝቦችን ነጻነት እና እውቀትን በማራመድ ምሁራን እንዲህ የሚለውን ተልዕኳቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፣ “በስልጣን ላይ ላሉት እውነቱን በመናገር፣ በአምባገነኖች እብሪተኝነት በሚደርሰው ስቃይ እና መከራ ለሕዝቡ ምስክር ሆነው በመቅረብ እና ከባለስልጣኖች ጋር በሚኖር ግጭት የሰላማዊ አማጺያንን ድምጽ ሆነው መቅረብ ይኖርባቸዋል“ ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ካለፈው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ጀምረው እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት አምባገነኖች ሁሉ እውነቱን በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡ (እ.ኤ.አ ሕዳር 2015 በፕሮፌሰር መስፍን “አዳፍኔ”: “ኢትዮጵያውያንን ከኢትዮጵያውያን መጠበቅ” በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ትችት ይመልከቱ፡፡) እ.ኤ.አ በ2007 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ተከትሎ ተፈጥሮ በነበረው ውዝግብ የተካሄደውን የወገኖቻችንን እልቂት በመመልከት ወደ ሰብአዊ መብት ጥበቃ ዘው ብዬ በመግባት በግፈኛው እና በአምባገነኑ መለስ የግል ትዕዛዝ በቅጥር ነብሰ ገዳዮች ያለቁትን ባለብሩህ ተስፋ ወገኖቻችንን እልቂት፣ አካለጎደሎነትን እና እስራትን ይፋ በማድረግ እና በማውገዝ ምስክርነት በመስጠት የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተልዕኮዬን ማራመድ ጀመርኩ፡፡ በዚያን ወቅት ገና በመጀመሪያው ጊዜ አሁን በህይወት የሌለው አረመኔው እና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የእርሱን የደህንነት እና ወታደራዊ ኃይሎች በማሰማራት ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቁትን እና የምርጫውን መዘርፍ እና መጭበርበር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ለማሳወቅ ሰልፍ በመውጣታቸው ብቻ በአምባገነኑ የግል ትእዛዝ በጅምላ እንዲጨፈጨፉ በማድረግ እራሱን የማይነካ ጠንካራ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ እርሱም ሆነ ተንቀሳቃሽ ዕቃ ገዳይ ሎሌዎቹ በሕግ ሳይጠየቁ የመቀመጣቸው ሁኔታ የእግር እሳት ሆኖ ያበሳጨኝ እና ያንገበግበኝ ነበር፡፡ ንዴቴ ትንሽ በረድ ካለልኝ በኋላ እንዲህ የሚል ጥያቄ ማንሳት ጀመርኩ፡ ምን ዓይነት ሰብአዊ ፍጡር ነው ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ እንዲህ ዓይነት ዕልቂት እንዲፈጸም ያዘዘው? የተለመዱት እና ማህበረሰቡ የሚቀበላቸው መልሶች ለእኔ አርኪ ሆነው አልተገኙም፡፡ በእርግጥ አምባገነኖች በስልጣን እርካብ ላይ እንደ መዥገር ተቆናጥጠው ለዘላለም ለመኖር በቁጥጥራቸው ስር ያለውን ማንኛውንም ነገር ይጠቀማሉ፡፡ አምባገነኖች በስልጣናቸው ላይ ተጣብቀው ለመቆየት ሲሉ ሰላማዊ ዜጎችን ይገድላሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ያጭበረብራሉ፣ ይደበድባሉ፡፡ በመለስ እና በዘ-ህወሀት የቀረበው የተለመደው የአምባገነኖች ምላሽ እውነት ሆኖ ሰውን ሊያሳምን የሚችል አልነበረም፡፡ ወደ ህወሀት ነገረ ታሪክ ጠለቅ ብዬ ስገባ የፕሮግራም ሰነዳቸውን/ማኒፌስቷቸውን በማጥናት እና የህወሀት የቀድሞ አባላት የህወሀትን ሚስጥር ሲያጋልጡ የኦዲዮ ቪዲዮ ምስል በመመልከት እና በማዳመጥ እንዲሁም በህወሀት የቀድሞ መሪዎች የሚቀርበውን ምሁራዊ ትንታኔ ሳነብ መለስ እና የእርሱ ድርጅት ለፖለቲካ ስልጣን ሲሉ በጥላቻ የሚመሩ የሰይጣን ፈረሶች መሆናቸው ፍንትው ብሎ ታየኝ፡፡ ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ አምባገነኑ መለስ እና ዘ-ህወሀት እነርሱ ከሚለው ይልቅ እኛ በሚል ቡድናዊ የከባቢ አየር ምህዳር ውስጥ ተዘፍቀው መታየታቸው ግልጽ እየሆነ መጣ፡፡ ጥላቻ በአምባገነኑ መለስ እና በግብረ አበር ጓደኞቹ የደም ስር ውስጥ ተዋህዶ ይገኛል፡፡ መለስ እና ዘ-ህወሀት የጥላቻን ኃይል ተገንዝበውታል፣ እናም የበለጠ የፖለቲካ ስልጣንን ለመቆጣጠር በዘዴነት ተጠቅመውበታል፡፡ ቀላል በሆነ የተመሳስሎ አገላለጽ ጥላቻ ከበሰበሰ ስጋ የትል መንጋ እንደሚገነፍል ሁሉ በተመሳሳዬ መልኩ ጥላቻም ከመለስ አፍ ይገነፍላል፡፡ በአንድ ወቅት አምባገነኑ መለስ ታላቅ ከበሬታ የነበራቸውን እና ታዋቂ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ስሜት ያራምዱ የነበሩትን እና አሁን በህይወት የሌሉትን ለእኔ ምርጥ ጓደኛ ለፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡ “ትግራውያን አክሱም አላቸው፣ ያ ግን ለጉራጌዎች ምናቸው ነው? አገዎች ላሊበላ አላቸው፣ ያ ግን ለኦሮሞዎች ምናቸው ነው? ለጎንደሬዎች ቤተመንግስት አላቸው፣ ያ ግን ለወላይታዎች ምናቸው ነው?“ ለመሆኑ እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎች ትርጉም እና አባባል ምን ማለት ነው? አምባገነኑ መለስ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ “ቁራጭ ጨርቅ” ከመሆን የዘለለ ነገር የለውም እንዲሁም “ኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ታሪክ ብቻ ያላት ሀገር ናት፣ ከዚህ ውጭ ሌላ ሀሳብ የሚያራምዱ ካሉ እራሳቸውን በታሪክ ሳይሆን በትረካ ላይ የዶሉ ናቸው” ብሎ ነበር፡፡ አምባገነኑ መለስ ቀደም ሲል ያምን እንደነበረው እና በአሁኑ ጊዜም የእርሱ ተከታይ ግብረአበሮቹ እንደሚያምነት ኢትዮጵያ የሚባል ነገር የለም፡፡ ያለው በአንድ ሀሳባዊ በሆነ ምድር ላይ የተመሰረቱ የብሄሮች ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ስብስብ ብቻ ነው በማለት ምንም ዓይነት አመክንዮ ከሌለው እና ከአስፈሪው ከስታሊን ጽሁፍ ቀምተው ያቀርባሉ፡፡ (እ.ኤ.አ ግንቦት 2016 “ኢትዮጵያ አዲስ ሕገ መንግስት ትፈልጋለችን?” በሚል ርዕስ አቅርቤው የነበረውን ትችት ይመልከቱ፡፡) መለስ እና ዘ-ህወሀት በውል መገንዘብ ያልቻሉት ነገር ቢኖር ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ የምትባል እውነተኛ ሀገር መኖሯን ወደ ኋላ መለስ ብለው ታሪክን ያለማወቃቸው ጉዳይ ነው፡፡ (እ.ኤ.አ ሕዳር 2014 “ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት” በሚል ርዕስ አቅርቤው የነበረውን ትችት ይመልከቱ፡፡) ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአክሱም፣ በላሊበላ፣ በሉሲ (ድነቅነሽ)፣ በሐረር ጀጎል፣ (በዩኔስኮ 4ኛው የእስልምና ቅዱስ ከተማ ተብሎ የተሰየመው)፣ በገዳ እና በጉሚ አስተዳደር ስርዓት እና በሌሎቸ በርካታ ነገሮች ላይ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሞራል እና ሕጋዊ መብቶች እንዳሏቸው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ዘ-ህወሀት ከሚያራምደው ጥላቻ እና የወንጀል ድርጊቶች እራሱን ነጻ ለማድረግ በሌሎች ሕዝቦች ጥላቻ የተፈጠሩ ድርጊቶች አስመስሎ በሀሰት በተቀነባበረ በእራሱ የሸፍጥ ስራ ነገር ይለኩስ እና እራሱ ያለበትን ወቅታዊ ትኩሳት ሁልጊዜ ወደ ሌላ አቅጣጫ የማስቀየስ የማጭበርበር ርኩስ ስነምግበር አለው፡፡ በሰው ልጆች ላይ የሚፈጽሟቸውን ወንጀሎች ለመደበቅ ሲሉ ታሪክን አዛብተው እና አወናብደው ለመጻፍ ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የሴቶች ጡቶች የሚቆርጡ ጨካኝ ንጉስ እንደነበሩ ለማስመሰል እና በኦሮሞዎች እና በአማራዎች መካከል ዘላለማዊ የሆነ ጥላቻ እንዲኖር ሚሊዮኖችን ብር የፈጀ ሀውልት አቁመዋል፡፡ የጭካኔ ጉዳይ በሚነሳበት ጊዜ ከአረመኔው መለስ ዜናዊ እና ከእርሱ ዘ-ህወሀት የበለጠ ጨካኝ እና አረመኔ በምድር ላይ ይኖራልን? እ.ኤ.አ በ2005 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ውዝግብ ተክትሎ ወያኔ ፈጽሞት በነበረው እልቂት መነሻነት በመለስ በእራሱ በተቋቋመው የምርመራ ኮሚሽን የማጣራት የዘገባ ውጤት መሰረት ሆን ተብሎ ታስቦበት እና ተመክሮበት ቢያንስ 193 ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቁ ንጹሀን አማጺዎች እንደተገደሉ፣ ሌሎች 763 ዜጎች ደግሞ የከባድ ቁስለኛ ጉዳት ሰለባ እንደሆኑ በመግለጽ ሙሉ ጥፋቱን በዘ-ህወሀት ላይ ደፍድፏል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 ባወጣው ዘገባው በኦሮሚያ ምንም ዓይነት መሳሪያ ባልታጠቁ 400 ንጹሀን ዜጎች ላይ ለተፈጸመው እልቂት ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ በአገዛዙ ላይ ደፍድፏል፡፡ እንደዚህ ባለው ጭካኔ በተሞላበት የኃይል ጥቃት አረመኔው መለስ እ.ኤ.አ በ2004 በኢትዮጵያ በጋምቤላ በ400 ምንም ዓይነት መሳሪያ ባልታጠቁ ሰላማዊ የሲቪል ዜጎች ላይ የጅምላ እልቂት እንዲፈጸም አድርጓል፡፡ ጨካኙ መለስ በግል ባቀናበረው ትዕዛዙ የኦጋዴን መንደሮች በቦምብ እንዲጋዩ አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግስታት የሂዩማን ራይትስ ዎች አድቮኬሲ ዳይሬክተር የሆኑት ስቴቭ ክራውሻው በአረመኔው መለስ እና በዘ-ህወሀት አማካይነት በኦጋዴን የተፈጸሙት ሰብአዊ የእልቂት ወንጀሎች እንደ “ትንሹ ዳርፉር” ሆኖ ሊቆጠር ይችላል በማለት ገልጸውት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ በእርግጥ የዘ-ህወሀት የጎሳ ጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሙሉ በሙሉ በሸፍጥ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አንድ እና አንድ ዓይነት ብቻ የጎሳ ዝርያ ብቻ ነው ያለው በማለት ሀሳብ የሚያቀርቡ ኢትዮጵያውያን/ት ካሉ ከእነርሱ ጋር ፊት ለፊት ለመሞገት ዝግጁ ነኝ፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዲኤንኤ የዘረ መል ምርመራ እንዲያደርግ የናሙና ጥናት ቢደረግ በኢትዮጵያ ውስጥ ከእያንዳንዱ የጎሳ ቡድን የዘረ መል አመላካቾችን ብቻ አይደለም የሚያገኙት ሆኖም ግን በሚያስደንቅ ሁኔታ በዓለም ላይ በየትም ቦታ ቢሆን የዘር አመላካች ሊገኝ ይችላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አንድ ሰው እውነታውን ለመረዳት ዝግጁ ከሆነ በትንሽ እና በ99 ዶላር ክፍያ ብቻ የአንድን ሰው የዘር ታሪክ አመጣጥ ለማወቅ ይችላል፡፡ “ንጹህ” ከየትም ያልተቀላቀለ የሆነ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትገሬ፣ ወዘተ የሚባል ነገር በፍጹም ሊኖር አይችልም፡፡ የለም! ከብዙ ጊዜ ጀምሬ የእኛ እናት ሀገር የሆነች ኢትዮጵያ እየተባለች የምትጠራ ጥንታዊ ሀገር እንዳለች ስሰብክ ኖሪያለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ክልል/ማጎሪያ በረት እየተባለች እንደ ገና ዳቦ ልትቆራረስ፣ በጎሳ ፌዴራሊዝም ከአለት ላይ እንደወደቀ ብርጭቆ ልትበታተን አትችልም፣ ወይም ደግሞ ለአየር ባየር ጭልፊት ኢንቨስተሮች ልትሸጥ ወይም ደግሞ በድብቅ በሚደረግ የወሰን “ስምምነት” ለሌላ ለባዕድ ሀገር ዜጎች ተላልፋ የምትሰጥ ሀገር አይደለችም፡፡ ዘ-ህወሀት ከእነርሱ ይልቅ ለእኛ የማለት አባዜ ድብቅ የሆነው ስልታቸው ነው፡፡ እኛ የሚለው ማለትም የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ መሪዎች፣ አባላት እና ግብረ አበሮች እንዲሁም በወታደራዊ ብቃት አለን በሚል የአጠራር ቃል እራሳቸውን በእራሳቸው የሚያሞካሹት ሰዎች እራሳቸውን “እኛ” ብለው ይጠራሉ፡፡ በሙስና ባህር ውስጥ በመዋኘት ላይ የሚገኙ፣ በሰው ልጆች ላይ ሰብአዊ ወንጀልን የፈጸሙ እና ስልጣናቸውን ከሕግ አግባብ ውጭ የሚጠቀሙ የዘ-ህወሀት ግፈኞች “እኛ” አሉ፡፡ የትግራይ ተራ የሆኑ ዜጎች እና ሌሎችን ተራ ኢትዮጵያውያንን የሚመስሉት ደግሞ ደም በተጠሙት የህወሀት አማጺ ቡድን ወሮበላ ዘራፊዎች በትግል ላይ በነበሩበት ጊዜ ከጊዜ ወደ ጊዜ ስቃያቸውን እና መከራቸውን ያዩ ነበር፡፡ ዘ-ህወሀት የትግራይን ሕዝብ እንደ መጠለያ ምሽግ አድርጎ ይጠቀምበት ነበር፡፡ ሆኖም ግን ተራው የትግራይ ሕዝብ ዘ-ህወሀት ለእራሱ የወንጀል ድርጊቶች በስማቸው ይጠቀም ነበር የሚል ሀሳብ ሊኖራቸው ይችላልን? የትግራይ ተራ ሕዝቦች በነጻ፣ በፈቃደኝነት እና ያለምንም ጫና በእራሳቸው ፍላጎት ዘ-ህወሀትን ይደግፋሉን? እነዚህን ጥየቄዎች ለመመለስ ማስረጃ መመርመር አለብን፡፡ ያ ማስረጃ ከሌላ ከየትም ሳይሆን የዘ-ህወሀት ነባር መስራች እና የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ከነበረው ከስዬ አብረሃ ይመጣል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 ተደርጎ በነበረው የፓርላማ የማሟያ ምርጫ ተብዬ ወቅት (ስዬ በትግራይ በተወዳደረበት ጊዜ) ስዬ የዘ-ህወሀት የፖሊስ መንስት እያንዳንዱን የትግራይን ተራ ሕዝብ የህይወት እንቅስቃሴ ሳይቀር ሁሉንም ነገር ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ አጋልጦ ነበር፡፡ የትግራይ ሕዝብ ዘ-ህወሀትን እንዲደግፍ ያደርግበት የነበረውን ስቃይ እና መከራ በማስረጃ አስደግፎ አቅርቦ ነበር፡፡ ስዬ ዘ-ህወሀት እንዴት አድርጎ የመንግስትን ሀብት፣ ተቋማትን፣ ጓዳዊ አሰራርን፣ የአድልኦ አሰራርን፣ ጉቦ መስጠትን እና በሙስና መዘፈቅን በመጠቀም ተራውን የትግራይ ሕዝብ በኃይል በማስገደድ ደጋፊ እንዲሆን በማድረግ እና ዘ-ህወሀት የእርሱን የፓርቲ መስመር የማይከተሉትን ወይም ደግሞ በግልጽ የሚቃወሙትን እንዴት አድርጎ እንደሚቀጣ በግልጽ አሳይቶ ነበር፡፡ ስዬ እንዲህ የሚል የክርክር ጭብጥ አቅርቦ ነበር፣ “ለዘ-ህወሀት [በትግራይ ውስጥ] በፓርቲ የፖለቲካ ሥራ እና በመንግስት ሰራተኛ አገልግሎት መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡ የፓርቲው ስራ በመንግስት ቢሮ ፋሲሊቲዎች፣ ትራንስፖርት፣ የውሎ አበል፣ ወዘተ አማካይነት ከመንግስት ስራ ጋር ጎን ለጎን አብሮ ይሰራል“ በማለት ሞግቶ ነበር፡፡ ስዬ እንዲህ በማለት ገለጻውን ይፋ አድርጎ ነበር፡ በትግራይ ክልል ዘ-ህወሀት በገጠር አካባቢዎች በጸጥታ ኃይሉ እና በፖለቲካው መዋቅር ላይ ጥብቅ በሆነ መልኩ የተሳሰረ መረብ እንዲኖር በመንደር ደረጃ ሊያገለግሉ የሚችሉ ዋና መሰረቶችን በመጣል ሁለት መዋቅሮችን ፈጥሯል፡ ዋሂኦ እና የልማት ጉጂሌ/Wahio and Development Gujille (DG):: በህወሀት መዋቅራዊ ሰንሰለት ዝቅተኛው ክፍል/unit ዋሂኦ በመባል ይጠራል፡፡ እናም ይህ ክፍል/unit እስከ 20 የሚደርሱ የህወሀትን አባላት ይይዛል፡፡ በአንድ መንድር ውስጥ እንደ መጠኑ ብዛት እስከ 20 ዋሂኦዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በአንድ መንድር ውስጥ ያሉ ዋሂኦዎች ሊቀመንበሮች በተራቸው ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ ቡድን በመሆን ይደራጁ እና የመጀመሪያ ዊዳቤ/Primary Widdabe (PW) በመባል ይጠራሉ፡፡ የእራሳቸውን ሊቀመንበሮች እራሳቸው ይመርጡ እና በመንደር ደረጃ የሚካሄዱትን ሁሉንም የመንግስት እና የፓርቲ እንቅስቃሴዎች ይቆጣጠራሉ፡፡ ህወሀት በእያንዳንዱ መንደር በእያንዳንዱ ሰው ላይ እኔን ከመሳሰሉት ሰዎች አካሄድ ጋር ግንኙነት አላቸው ብሎ በሚጠራጠራቸው ሰዎች ላይ ጥናት ያደርጋል፡፡ ከደርግ አገዛዝ ጋር በትጥቅ ትግሉ ተሳትፎ የነበራቸው በርካታ ነባር የህወሀት ታጋይ አባላት አሉ፡፡ ሆኖም ግን ፓርቲው በተሰነጠቀበት ወቅት ከእኔ እና ከሌሎች ከእኔ መሰል ሰዎች ጋር ወገንተኝነት ይኖራቸዋል በሚል ምክንያት ከጥርጣሬ ውስጥ የሚገቡትን ሰዎች ከፓርቲው አባልነት ያስወግዷቸዋል፡፡ ከዚህም በላይ በትጥቅ ትግሉ እና አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ወይም ሶስት ልጆች የተሰውባቸው ቤተሰቦች ምንም ዓይነት እረዳት የሌላቸው በርካታ ቤተሰቦች አሉ፡፡ የዘ-ህወሀት ካድሬዎች የድምጽ መስጫ የሚስጥር ካርድ የምርጫ ሂደቱን እንዴት አድርገው እንደሚያጭበረብሩበት መረጃዎችን ተቀብያለሁ፡፡ መራጮች/ድምጽ ሰጭዎች ለህወሀት ማን ድምጽ እንደሰጠ እና ማን እንዳልሰጠ የሚያሳዩ ካሜራዎችን ሚስጥራዊ በሆኑ ቦታዎች ላይ አስቀምጧል በማለት በህወሀት ይነገራቸዋል፡፡“ ስዬ እንዲህ በማለት ዘገባውን ደምድሟል፡ እ.ኤ.አ በ2010 ተካሂዶ የነበረው የማሟያ ምርጫ በህወሀት ለህወሀት ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የተደራጀ እና የተያዘ የውሸት ዴሞክራሲያዊ የማታለያ ምርጫ ነበር፡፡ የምርጫ ቦርዱ ገለልተኛ ሆኖ እንዲታይ ለማስመሰል በማሰብ በህወሀት የቀበሌ እና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር እና ግምገማ ሲደረግ ይታይ ነበር፡፡ በገጠሩ አካባቢ በሚገኙት ቀበሌዎች እና መንደሮች የሚኖሩት በርካታዎቹ አርሶ አደሮች የህወሀት አባላት እንዲሆኑ ይገደዳሉ፡፡ ማንም ሰው የትም ቢሄድ የሚያገኘው የህወሀትን አባላት ነው፡፡ በተጫባጭ ሁኔታ ሲታይ የህወሀት ጥቅሞች የተባሉ ነገሮች ሁሉ የህወሀት አባል ላልሆነ ለማንም ሰው ሁሉ ዝግ ናቸው፡፡ አባል ያልሆኑ ሰዎች እንደጠላት ይፈረጃሉ፣ እናም ህይወታቸው ወደገሀነምነት ይለወጣል፡፡ ህዝቦችን የሚያስተሳስሯቸው ሰንሰለቶች ሴፍቲ ኔት እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፕሮግራሞች/Safety Net and Emeregency Programs የሚባሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ፕሮግራሞች ሕዝቡ ሙሉ በሙሉ ለገዥው ፓርቲ አጎብዳጅ እንዲሆን በመስራት እና በማጦዝ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ“ በማለት ነበር ሀሳቡን የደመደመው፡፡ በእርግጥ ዘ-ህወሀት የትግራይን ሕዝብ ይወክላልን? የትግራይ ሕዝብ ነጻ በሆነ መልኩ እና በእራሳቸው ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት ብቻ ዘ-ህወሀትን ይደግፋሉን? የትግራይ ሕዝብ የዘ- ህወሀት መደበቂያ ምሽግ ነውን? ወይም ደግሞ የትግራይ ሕዝብ ምንም ዓይነት እረዳት እንደሌቸው የዘ-ህወሀት ሰለባ ሆነው እንደሚሰቃዩት እንደ የኦሮሚያ፣ ወይም ደግሞ እንደ አማራ ክልል እና እንደሌሎች ክልሎች ሁሉ ምንም ዓይነት እረዳት የሌለው ነውን? በዘ-ህወሀት መንግስት የቀድሞ ፕሬዚዳንት በነበሩት በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀረቡትን ማስረጃዎች ደግሞ እስቲ እንመርምራቸው፡፡ ዶ/ር ነጋሶ እ.ኤ.አ መስከረም 2009 በኦሮሚያ ክልል በቀለም ወለጋ ዞን በዶምቢዶሎ ሲካሄድ የነበረውን ልዩ ሁኔታ በመለየት ይገልጻሉ፡፡ ዘ-ህወሀት የመለስን መሪ ዕቅድ የጨዋታ መጽሀፍ በኦሮሚያ እና በትግራይ ውስጥ በአንድ ዓይነት ሁኔታ የተገበረው ለመሆኑ ከዚህ በታች የቀረበው የዶ/ር ነጋሶ ገለጻ ይፋ አድርጓል፡ ፖሊስ፣ የጸጥታ ኃይሉ ቢሮዎች ሰራተኞች በተለያዩ መንገዶች ስለአንድ አባወራ የተለያዩ መረጃዎችን ይሰበስባሉ፡፡ ከእነዚህ መንገዶች አንዱ “ሻኔ” በአሮሞኛ “አምስት” እየተባሉ የሚጠሩትን ድርጅቶች እና መዋቅሮች ያካትታል፡፡ አምስት አባዎራች በአንድ ላይ ሆነው በአምስቱ አባወራዎች ላይ መረጃዎችን በሚሰበስብ በአንድ መሪ ተጠርንፈው/ተጠፍንገው (በአንድ ላይ ተደርገው) ይዋቀራሉ… የደህንነቱ ኃላፊ የሰበሰበውን መረጃ በቀበሌ በከፍተኛ አስተዳደራዊ ደረጃ ላይ ላለው ለእርሱ የበላይ አለቃ ያስተላልፋል፡፡ የቀበሌው አለቃ ደግሞ በተራው ለወረዳው ፖሊስ እና የደህንነት ቢሮ ያሳውቃል፡፡ እያንዳንዱ አባወራ ወደ እራሱ የመጡ እንግዶች እና ጎብኝዎች ካሉ ወዲያውኑ የመጡበትን ምክንያት፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ፣ ምን እንዳሉ እና በምን እንቅስቃሴዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ዘገባ እንዲያቀርብ ይጠበቃል… ኦህዴድ/ኢህአዴግ የሚመራቸው ማህበራት (የሴቶች፣ የወጣቶች እና የአነስተኛ እና ጥቃቅን የብድር ቡድኖች) እና የፓርቲ ሴሎችን (“እናቶች”፣ “አባቶች” እና “ወጣቶች”) ይመራል፡፡ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና፣ እና በኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ያሉት የፓርቲ ሴሎችም እንደዚሁ ተመሳሳይ ተግባራትን ያካሂዳሉ…“ ነበር ያሉት፡፡ የአሮሚያ ሕዝብ ነጻ በሆነ መልኩ እና በእራሳቸው ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት ብቻ ዘ-ህወሀትን ይደግፋሉን? ዘ-ህወሀት የመለስን የጨዋታ መጽሀፍ የሆነውን የምርጫ ዘረፋ መሪ ዕቅድ በመጠቀም ህዝቡ በግድ እንዲመርጠው ያስገድዳል ወይስ ደግሞ ሌላ መንገድ ይጠቀማል? እነዚህን እውነታዎች አጉልተው ሊያሳዩ የሚችሉ ሌሎች ሁለተኛ ደረጃ መረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጥቂቶች እንሚያቀርቡት የክርክር ጭብጥ ከሆነ አንዳንድ የትግራይ ሕዝቦች ከሌሎች የትግራይ ሕዝቦች በተለየ መልኩ ዘ-ህወሀት በመሰረተ ልማት ፕሮግራሞች፣ በመዋዕለ ንዋይ ፍሰቶች/ኢንቨስትመንቶ እና ከዓለም አቀፍ እርዳታ ከሚሰጠው ኢኮኖሚያዊ ልግስና ተመጣጣኝነት በሌለው ሁኔታ ከሌሎች በተለየ መልኩ ተጠቃሚዎች ናቸው የሚል የክርክር ጭብጥ ይቀርባል፡፡ ይህንን አባባል በመረጃ ለማስደገፍ ምን ተጨባጭነት ያለው ማስረጃ አለ? እ.ኤ.አ በ2016 በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ተከስተው ከነበሩት ድርቆች ሁሉ በበለጠ ደረጃ በአስከፊ ሁኔታ ከተጠቁት ክልሎች መካከል የትግራይ እና የአፋር ክልሎች ይገኙበታል፡፡ እ.ኤ.አ መጋቢት 2016 እንደቀረበው እንደ ውጭ ጉዳይ ዘገባ “በኢትዮጵያ የሰብል ምርት በሰሜን ትግራይ እና በአፋር ክልሎች ከ50 እከከ 90 በመቶ ባለው መካከል እንደቀነሰ ይፋ ተደርጓል፡፡“ ዘ-ህወሀት የትግራይን እና የአፋርን ክልሎች ለማገዝ ምን ያደረገው ጥረት አለ? የመለመኛ ሳፋዎቹን ይዞ ወደ ዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪ ለልመና ነው የተፈተለከው/ሸመጠጠው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ያለው ተጨባጭ እውነታ! በእርግጥ አምባገነኑ መለስ ስልጣንን ከተቆጣጠረ በኋላ እ.ኤ.አ በ1991 ለመጀመሪያ ጊዜ ለቀረበለት ቃለመጠይቅ እንዲህ የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር፣ “ኢትዮጵያውያን በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ ከቻሉ የእኔ መንግስት ስኬቱ የሚለካው በዚህ ነው“ነበር ያለው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አምባገነኑ መለስ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2015 የማንንም እርዳታ ሳትጠይቅ በምግብ እህል እራሷን ትችላለች ብሎ ነበር፡፡ የመለስ ቅጥፈት ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል ዘርፈብዙ ነው! እ.ኤ.አ በ2008 የትግራይ ዘላቂ የግብርና እና የአካባቢ ተሀድሶ በትግራይ/Sustainable Agriculture and Environmental Rehabilitation እን Tigray (SAERT) በሚል ስያሜ አነስተኛ ግድቦችን እና የመስኖ ስራዎች ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ ትግራይ በምግብ እህል እራሷን ትችላለች በማለት ዘ-ህወሀት እየተኮፈሰ ዲስኩሩን ሲያሰማለት የቆየው ባዶ ዕቅድ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን ሁኔታዎች በዚህ ደረጃ ላይ እንዳሉ ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ2016 ለትግራይ ሕዝብ የምግብ እህል እርዳታ ለማቅረብ የልመና ሳፋውን ይዞ ብቅ አላለምን? ከዚህ በላይ ውሸት እና ሕዝብን ማደናገር ከቶ ከየት ይገኛል? እ.ኤ.አ በ2014 በማዕካለዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም በቀረበው ዘገባ መሰረት ከፍተኛ የሆነ የምግብ ኃይል እጥረት ያላቸው አባወራዎች የሚገኙት በአዲስ አበባ (50%)፣ በአማራ (49%)፣ በድሬዳዋ (42%) እና በትግራይ (42%) ሆኖ እንደተመዘገበ ይፋ አድርገዋል፡፡ ከምግብ ድህነት አኳያ ደግሞ ከፍተኛ ተጠቂ ክልሎች ሆነው የተገኙት አማራ (35%) እና ትግራይ (30%) ናቸው፡፡ ዘ-ህወሀት ሕዝቡን በረሀብ አለንጋ፣ በኑሮ ውድነት እና በችጋር እያሰቃየ የሚኮፈስበት አንዳችም ነገር የለውም፣ ምንም! ይኸው ነው በቃ! እንደ ትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፕላን እና ገንዘብ ቢሮ ዘገባ ከሆነ በትግራይ ክልል ውስጥ 75 በመቶ የሆነው የገጠሩ ሕዝብ እና 61 በመቶ የሚሆነው የከተማ ኗሪው ሕዝብ ከድህነት ወለል በታች ኑሮውን በመግፋት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ዘ-ህወሀት የሚኮፈስበት አንዳችም ነገር የለውም፣ ምንም! ያለምንም ተጨባጭ ነገር ትግራይ በኢትዮጵያ ውስጥ የእንዱስትሪ ኃይል ማዕከል ትሆናለች እየተባለ ይደሰኮራል፡፡ እንደ አንድ ዘገባ ከሆነ “በኢትዮጵያ ውስጥ በትግራይ ጎሳ አባላት የሚንቀሳቀሱ እና 20 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው 66 ኩባንያዎችን በመምራት ላይ ይገኛሉ” ተብሏል፡፡ የ20 ሚሊዮን ብር ጉዳይ ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበው “ስንቶቹ ናቸው በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉት?” የሚለው ነው፡፡ እ.ኤ.አ ሕዳር 2015 የዩናይትድ ስቴትስ የግብርና ቢሮ መምሪያ የውጭ የግብርና አገልግሎት/United States Department of Agriculture Office Foreign Agricultural Service ዘገባ “ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የሸንኮራ አገዳ ከሚያመርቱ 10 ዋና ሀገሮች መካከል ለመሆን ታልማለች” የሚል ዘገባ አሰራጭቷል፡፡ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ በግንባታ ላይ ባሉት የስኳር ፋብሪካዎች እና ግምታዊ በሆነው የማምረት አቅማቸው ላይ ያለው መረጃ ዘ-ህወሀት ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት በማፍሰስ ትግራይን የእንዱስትሪ ኃይል ማዕከል አደርጋለሁ እያለ የሚያራመደውን ፕሮፓጋንዳ የሚደግፍ ሆኖ አልተገኘም፡፡ እንዲየውም በተጻራሪው ሆኖ ይገኛል! በትግራይ ውስጥ ያለው የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት መረጃ ምንድን ነው? እንደ ትግራይ የኢንቨስትመንት የስራ ሂደት ዋና ባለቤት እንደ ጎይቶም ገብረ ኪዳን መረጃ ከሆነ እ.ኤ.አ በ2015 የትግራይ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት እና የኮንስትራክሽን እንዱስትሪ ጽ/ቤት ከ800 በላይ ለሚሆኑ እና 10.5 ቢሊዮን ብር በጀት ለተያዘላቸው ፕሮጀክቶች ፈቃድ መስጠቱን ግልጽ አድርጓል፡፡ ገብረ ኪዳን እንዲህ ብሏል፣ “ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 829 እንዱስትሪዎች በግብርና፣ በአግልግሎት፣ በባህል እና ቱሪዝም ዘርፎች ላይ ኢንቬስት በማድረግ ተመዝግበው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡“ (ጉድ እኮ ነው 800ዎቹ ፕሮጀክቶች የአውሮፓው የገና ሺማግሌ ሳንታ ከሎስ የበረዶ ጋሪዉን በሰማይ አየጋለበ ሲሄድ ጂፒኤሱ (የመንገድ መምሪያ መሳርያ) ተሰብሮ በአስቸኳይ በገብረ ኪዳን ደጅ ላይ ያረፈ ጊዜ ነበር ፡፡) እ.ኤ.አ በ2009 የሚሊኒየም ከተሞች ተነሳሽነት እና የቬል ኮሎምቢያ ማዕከል/Millennium Cities Initiative and Vale Columbia Center “የኢንቨስትመንት ዕድሎች በመቀሌ በትግራይ መንግስት በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ ባቀረበው ባለ 80 ገጽ ዘገባ እ.ኤ.አ በ2016 የኢንቨስትመንቶች ሁኔታ ዲስኩር ምን ይመስላል? ምናልባትም ለዚህ ጥያቄ መልስ ከትግራይ ክልላዊ መንግስት እንዱስትሪ እና ንግድ ቢሮ ጽ/ቤት የሚገኝ ይሆናል፡፡ የእኔ ዓላማ ዘ-ህወሀት እያደረገው ስላለው ስለእያንዳንዱ ፕሮፓጋንዳ እና ስለትግራይ ሕዝብ ምን ተግባራትን እንደሰራ ለመቃወም አይደለም፡፡ ያ ውይይት ለሌላ ጊዜ የሚቆይ ይሆናል፡፡ የእኔ ዋናው ነጥብ ዘ-ህወሀት ለትግራይ ሕዝብ ሰራሁት እያለ የሚያሰራጨው ፕሮፓጋንዳ በጥንቃቄ መታየት ያለበት ጉዳይ መሆኑን ለማስገንዘብ ነው፡፡ ቀላል እውነታ ለመናገር ያህል የዘ-ህወሀት የኃይል መዋቅር ማንንም አይወክልም ሆኖም ግን እራሱን ፣ ደጋፊዎቹን፣ ግብረ አበሮቹን እና ጓደኞቹን ብቻ ነው ሊወክል የሚችለው፡፡ ዘ-ህወሀት በሰው ልጆች ላይ የሚፈጽማቸው ሰብአዊ ወንጀሎች እንደተራራ እየተቆለሉ በመጡ ቁጥር ከብቸኛ የወንጀል ተጠያቂነት እራሱን ለመደበቅ ሲል የትግራይን ሕዝብ በመጠለያነት እና በመደበቂያነት ይጠቀማል፡፡ ከዚህ ትምህርት አድርገን ልንወስደው የሚገባን ነገር ተራ የሆነውን የትግራይን ሕዝብ ከዘ-ህወሀት ጋር በመቀላቀል ለዘ-ህወሀት እርዳታ የሚያደርግ እና ደጋፊ ነው ብሎ መውሰድ የሞራል ስብዕና ዝቅጠት እና የእውነታነት ስህተት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ሲባል የብዙ ሚሊዮኖች ብሮች ካፒታል ያላቸው በርካታ የቢዝነስ ሰዎች እና የንግድ ድርጅቶች በጥቅም ከዘ-ህወሀት ጋር በጥብቅ የተሳሰሩ እና ህብረትን የፈጠሩ የትግራይ ጎሳ አባላት የሉም ማለት አይደለም፡፡ ይህም ማለት ዘ-ህወሀት በቤተሰባዊነት፣ በፖለቲካ ትስስር እና የሙስና ስርዓት በመዘርጋት ለትግራይ ጎሳ ደጋፊዎቹ እና ግብረአበሮቹ ልዩ የሆነ ጥቅም አልሰጠም ማለት በፍጹም አይደለም፡፡ የወንጀል ድርጊትን በመፈጸም የሚታወቀው እና ማህበረ ረድኤት ትግራይ (ማረት) እየተባለ የሚጠራው ድርጅት በተለይ የትግራይ ጎሳ የሆኑትን የዘ-ህወሀትን መሪዎች፣ ካድሬዎች፣ ግብረ አበሮች እና ደጋፊዎችን ለመጥቀም ሲባል የተቋቋመ ድርጅት አይደለም የሚል ሀሳብ ለመሰንዘርም አይደለም፡፡ ይህም ሲባል ዘ-ህወሀት የትግራይ ጎሳ ለሆኑት አባላቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር ለመንግስት የኮንትራት ስራዎች እና ከሀገሪቱ የህዝብ ባንኮች ሊከፈል የማይችል ብድር በልዩ ትዕዛዝ እየወጣ እንዲሰጣቸው አላደረገም የሚል ሀሳብ ለመሰንዘር አይደለም፡፡ ይህም ሲባል የትግራይ ጎሳ አባላት ከሌላው ጎሳ አባላት በተለየ መልኩ የመንግስት ስራ በመስጠት፣ በከፍተኛ ትምህርት ገብተው እንዲማሩ በማድረግ፣ ሕዝባዊ አገልግሎቶችን፣ ወዘተ እንዲያገኙ አላደረገም የሚል ሀሳብ ለመሰንዘር አይደለም፡፡ የትግራይ ጎሳ አባላት የሆኑ የዘ-ህወት አባላት፣ ካድሬዎች፣ ግብረ አበሮች እና ደጋፊዎች ግብር አይከፍሉም፣ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባ ዕቃ በጣም ዝቅተኛ የሆነ የቀረጥ ክፍያ ብቻ ወይም እንዲያውም አይከፍሉም የሚል ሀሳብ ለመስንዘር አይለደም፡፡ ዋናው ነጥብ ማንም ከማንኛውም የጎሳ ቡድን ቢሆን ህይወቱን እና ስብዕናውን ለዘ-ህወሀት ሰይጣን የሚሸጥ እስከሆነ ድረስ ተመሳሳይ ጥቅም ሊያገኝ ይችላል፡፡ ዘ-ህወሀት ከማንም ጋር፣ በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ቦታ የፋውስትን የአስመሳይነት የሸፍጥ ስምምነት ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነ፣ ችሎታ ያለው እና ዝግጁ የማፊያ ድርጅት ነው! የጎቴ ዶ/ር ፋውስት ለሀብት፣ ለስኬት፣ ለዓለም አስደሳች ነገሮች ሲል ከሰይጣን ጋር ስምምነትን ይፈጽማል፡፡ ዘ-ህወሀት እኩል የሆነ የሰይጣን ዕድል ሰጭ ነው፡፡ ዘ-ህወሀት ለእርሱ ነብሱን ለመሸጥ ለሚዘጋጅለት ለማንኛውም ሰው ሁሉ የጎሳ ማንነት፣ ብሄር፣ ኃይማኖት፣ ወዘተ ሳይል ሀብት፣ ስኬት ዓለም አቀፋዊ አስደሳች የሆኑ ነገሮች እና ስልጣንን ይሰጣል፡፡ ዘ-ህወሀት በመጨረሻው ሰዓት የአንተን ነብስ እስካገኘ ድረስ አንተ ማን እንደሆንክ እና በማንኛውም መልኩ ከማንኛውም ሰው ጋር ስምምነት ብትፈጽም ጉዳዩ አይደለም፡፡ አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ሁልጊዜ ማለት ይወደው እንደነበረው ለዘ-ህወሀት ታማኝነት መሆን ከጎሳ፣ ከኃማኖት፣ ከትምህርት፣ ከስራ ልምድ ወይም ደግሞ ከማንኛውም ነገር የበለጠ ጠቃሚ ነው፡፡ ለዘ-ህወሀት ታማኝነት ዋናዉና የመጨረሻው ፈተናን ማለፍ ማለት ነው፡፡ የእራሳቸውን ነብሶች በመሸጥ ለዘ-ህውሀት ታማኝ ሎሌዎች የሆኑ እና ህሊናቸወውን ለገንዘብ ያስገዙ በርካታ አማሮች፣ አሮሞዎች፣ ጉራጌዎች እና ሌሎች ሰዎች አሉ፡፡ ይህንን እውነታ የሚክድ ሊኖር ይችላልን? አጽንኦ በመስጠት ላቀርበው የምፈልገው ዋናው እውነታ በዘ-ህወሀት ሀጢያቶች እና ወንጀሎች ምክንያት የጎሳ ህብረትን በመፍጠር በተራው የትግራይ ሕዝብ ላይ ጥፋተኝነትን ለመፈለግ ባለመቻኮል ፍትሀዊ መሆን እና ከማንኛውም መጥፎ ድርጊት መቆጠብ እንዳለብን ላስገነዝብ እፈልጋለሁ፡፡ ተራው የትግራይ ሕዝብ እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ሁሉ እተሰቃየ እና መከራውን እያየ ያለ ምስኪን ሕዝብ ነው፡፡ እንደሚነዛው አሉባልታ ሳይሆን ሐቁ ይህ ነው፡፡ ህብረት በመፍጠር እና በመደራጀት የሚፈጸም ጥፋት ኢሞራላዊ እና አሳፋሪ ድርጊት ነው ምክንያቱም ስነአመክንዮያዊ ያልሆነ እና ውጤቱም የደጋፊዎቹ የጋራ የቅጣት መፈክር ነው፡፡ የዘ-ህወሀት ሰይጣኖች ሕግን እና የስነምግባር መርሆዎችን በመደፍጠጥ በሰሯቸው ሀጢያቶች እና ሰብአዊ ወንጀሎች ተራውን የትግይ ሕዝብ ማውገዝ ፍትሀዊ አይደለም፡፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች ሁልጊዜ በእነርሱ በእራሳቸው ላይ ስለሚደርሰው አደጋ እና ማስፈራራት ምንም ሳይጨነቁ በትግራይ ሕዝብ ህይወት እና ህልውና አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አድርገው ሌት ቀን የሀሰት ቅጥፈታቸውን ይሰብካሉ፡፡ ዘ-ህወሀት የእራሱን ዕጣ ፈንታ ከትግራይ ሕዝብ ዕጣ ፈንታ ጋር በማቆራኘት ወደ ፊት የሚመጣውን ማሰቃየት እና ከዚህም አልፎ የሚከሰተውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ሁሉ ከተራው ሕዝብ ጋር ለማያያዝ ይሞክራሉ፡፡ ተራውን የትግራይ ሕዝብ በሙስና እስከ አንገታቸው ድረስ ተዘፍቀው ከሚገኙት ከዘራፊ ወሮበላ የዘ-ህወሀት አባላት መለየት መቻል አለብን፡፡ ለኃጢያን የተባለው ለጻድቃን ይተርፋል ተረት ተግባራዊ እንዳይሆን አበርትቶ መስራትን ይጠይቃል፡፡ የዘ-ህወሀት መሪዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 25 ዓመታት የፈጸሟቸው ወንጀሎች የናዚ መሪ የነበረው ኸርማን ጎሪ በአንድ ወቅት በኑረምበርግ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የፍርድ ችሎት ላይ ቀርቦ ከሰጠው እና እንዲህ ከሚለው አባባል ጋር የቅርብ ትስስር አላቸው፡ በእርገጥ ሕዝቡ ጦርነትን አይፈልግም፡፡ ሆኖም ግን ከሁሉም በላይ የሀገሪቱ መሪዎች ናቸው ፖሊሲውን የሚወስኑት፡፡ እናም ሁልጊዜ ወደ ዴሞክራሲ፣ ፋሽስት አምባገናነዊነት ወይም ደግሞ ወደ ፓርላሜንታዊ አገዛዝ ወደ ኮሙኒስት አምባገነንነት ሕዝቡን የሚስቡት እነርሱ ናቸው፡፡ ሕዝቡ ድምጽ ኖረው አልኖረው ምንጊዜም ቢሆን ጉዳዩ የሚያልቀው በመሪዎቹ ነው፡፡ ያ ቀላል ነገር ነው፡፡ ሁሉም ልታደርጉ የምችሉት ነገር ቢኖር በሌላ ኃይል ሕዝቦች እንደሚወጉ ንገሯቸው፡፡ እናም በሰላማዊ መንገድ ግጭቶችን ለመፍታት የሚሞክሩትን ጀግንነት የሌላቸው እና በሀገሪቱ ላይ አደጋን ለማምጣት የሚፈልጉ ናቸው በማለት በማውገዝ አጋልጧቸው“ ነበር ያለው፡፡ ዘ-ህወሀት የጥላቻ እና የጥልቅ ጥላቻ ከበሮውን በመደለቅ የትግራይ ሕዝብ እየተወጋ ነው፣ እናም የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት ህብረት በመፍጠር ትግሬዎቹን ሊያጠቁ ነው በማለት መቀስቀስ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ይህ የሞኝ ብልጣብልጥነት ያለቀበት ያረጀ እና ያፈጀ ነው። በፍጹም አይሰራም፡፡ ዘ-ህወሀት በዚህ ጊዜ አይሰራም! የእኛ ጠላት ጥላቻ ነው፣ እ.ኤ.አ ሀምሌ 2008 “ከጠላቶቻችን ጋር ተገናኘን” በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ ሌላ ማንም ሳይሆን እኛው እራሳችን ነን፡፡ “ጠላት” በሚል ቃል የተደረገ ጥናት ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ2016 “ከጥላቻ አራጋቢዎች ጋር ተገናኘን፣ እናም እነርሱ እራሳችን ነን” በሚል ርዕስ ትችት አቀረብኩ፡፡ ነገሩ በቀላል መንገድ ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ጥላቻ የነብስ በሽታ ነው፡፡ ጥላቻ ሌላው የኃይለኝነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ነው፡፡ የፈላስፋውን እና የሰላም አባቱን የዳይሳቁ ኢቀዳን አባባል በመዋስ ስለጥላቻ የሚከተለውን እላለሁ፡ “ጥላቻ ከቆሰለ መንፈስ ይወለዳል፡ ጥላቻ በግትራዊነት እሳት ከተቃጠለ መንፈስ እና ካበጠ ቁስል፣ ኃይልየለሽ ከመሆን እና ከተስፋ ማጣት ከሚመነጭ ከተበጣጠሰ እና ከተቆጣ መንፈስ፣ ለህይወት ትርጉም ከማይሰጥ ደረቅ እና እርካታ ከማይሰጥ መንፈስ፣ በዝቅተኝነት ስሜት ከኮሰመነ እና ከተዳከመ መንፈስ ይመነጫል፡፡ ለራስ ክብር ከመስጠት ከሚመነጭ ቁጣ እና ከውርደት ኃይል ይወለዳል፡፡ ሌሎችን በመደምሰስ እና በመደብደብ የግፍ ሰለባ በማድረግ ደሰታን ለማግኘት ከሚደረግ ጥረት፣ በሕዝብ መገናኛ ዘዴዊች በህብረተሰቡ ውስጥ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት የጥላቻ እና የኃይል ባህል እውን ይሆናል…ከተፈወሰ፣ ከሰላማዊ ልብ ጨዋነት ይወለዳል፣ ከጨዋነት ደግሞ ሌሎችን የማዳመጥ ፈቃደኝነት ይወለዳል፣ ሌሎችን ከማዳመጥ ፈቃደኝነት ደግሞ የጋራ መግባባት ይወለዳል፣ ከጋራ መግባባት ደግሞ ሰላማዊ ማህበረሰብ ይወለዳል፡፡“ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በጥላቻ ከተሞሉት እና የጥላቻ ፖለቲካን ከሚያራምዱት ከጠላቶቿ ባሻገር ወደፊት በመመልከት በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች፡፡ እኛ በአሁኑ ጊዜ ለልጆቻችን፣ ለእራሳችን እና ለቀጣዩ ትውልድ ቅርጽ መስጠት፣ መልክ ማስያዝ፣ መፍጠር እና መገንባት ያለብን ለወደፊቱ ነው፡፡ የወደፊቱ ጊዜ ከፍርኃት፣ ከኃይል፣ ከጥላቻ፣ ከኃይማኖት እና ከጎሳ ያለመቻቻልነት ነጻ መሆን አለበት፡፡ የወደፊቱ ጊዜ በሕዝቦች መፈቃቀድ ላይ በጥብቅ የተመሰረተ አንድነት፣ የሕግ የበላይነት የሰፈነበት እና ጠንካራ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት የሚመሰረቱበት መሆን ይኖርበታል፡፡ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ኔልሰን ማንዴላ ለደቡብ አፍሪካ ሕዝብ ሲያልሙት እንደነበረው እና እንዲህ እንደሚለው መሆን ይኖርበታል፡ “በፍጹም፣ በፍጹም እናም በፍጹም ይህች ቆንጆ የተዋበች ምድር ሰዎች እንደገና አንዱ በአንዱ የሚጨቆኑባት እና ሕዝቦች የሚናቁባት እና የሚዋረዱባት ዓለም አትሆንም፡፡“ ወደፊት መንግስት የዜጎችን መብት የሚያከብርበት እና የእያንዳንዱን ዜጋ ነጻነት የሚጠብቅበት እንዲሁም መሪዎች ለሕዝቦቻቸው እና በሀገሪቱ ሕጎች ተጠያቂዎች የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡ የወደፊቱ ጊዜ ወጣቱ የመንግስቱን እና የሕዝቡን ስልጣን የሚይዙበት ነው፡፡ የጥላቻ አራጋቢዎች በኢትዮጵያ ቦታ የላቸውም፡፡ በእርግጥ የጥላቻ አራጋቢዎች ዘር የላቸውም፣ ሀገር የላቸውም፣ ብሄር የላቸውም፣ ጎሳ የላቸውም፣ ኃይማኖት እና ጾታ የላቸውም፡፡ የጥላቻ አራጋቢዎች የእራሳቸው የሆነ እና በአንድ አካባቢ የተቀነበበ የጥላቻ ፕላኔት ነው ያላቸው፡፡ “የጥላቻ አራጋቢዎች ወደ ጥላቻ ይሄዳሉ፡፡” የእኛ ስራ መሆን ያለበት እነዚህ የጥላቻ አራጋቢዎች በራሳቸው የብቸኝነት የግዛት ክልል ፕላኔት ውስጥ ብቻ ተወስነው እና ተቀፍድደው እንዲቆዩ ማድረግ ነው፡፡ የማንዴላን አባባል በመዋስ “ጥላቻን ማራገብ መርዝ በመጠጣት ሌላው ሰው ይሞትልኛል ብሎ እንደመጠበቅ ነው፡፡“ እዚህ ላይ መርዙን የጠጣው የጥላቻ አራጋቢ አስቀድሞ እንደሚሞት ልብ ይሏል፡፡ ወደ አንድነት ከሚያመጡን ነገሮች ይልቅ ከፍተኛ የሆነ ጊዜ በመውሰድ ስለሚለያዩን ነገሮች በከንቱ ጊዜ አናጠፋለን፡፡ የእኛ ችግር የፍትህ እጦት ነው፣ የእኛ ችግር የሰብአዊ መብት አለመከበር ችግር ነው፣ የእኛ ችግር የነጻነት እጦት ችግር ነው፣ የእኛ ችግር እራሳችንን በእራሳችን ማስተዳደር እንዳንችል የድምጻችን የመዘረፍ ችግር ነው፡፡ ስለእራሳችን መናገር አለብን፣ ስለእነርሱ መናገር አለብን፣ እኛ ሁላችንም የተባበረች ኢትዮጵያ በመባል እንታወቃለን፡፡ እኛው እራሳችን ማን እንደሆን እና ማን እንዳልሆን፣ ለማን እንደቆምን፣ በምን እንደምናምን፣ እርስ በእርሳችን እንዴት እንደምንረዳዳ እና እራሳችንን ከሚጎዱ ነገሮች መወገድ እንዳለብን፣ ሌሎችን የተሻለ ዕድል የሌላቸውን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ለመርዳት መተባበር እንዳለብን መነጋገር አለብን፡፡ ሁላችንም ኢትዮጵያውን ነን – የወሮበላ ዘራፊዎች ወንድማማቾች የግፍ ሰለባ የሆንን የአንዲት ሀገር ወንድማማቾች እና እህትማማቾች ነን ፡፡ ነጻነትን፣ ዴሞክራሲን እና የሰብአዊ መብትን ለማስከበር በምናደርገው ትግል በጠላትነት ሳይሆን በትብብር እና በመከባበር መንፈስ ነው ድልን መቀዳጀት የምንችለው፡፡ ለነጻነት፣ ለዴሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብት መከበር የምናደርገው ትግል ለድል የሚበቃው የጥላቻ ፖለቲካን ከላያችን ላይ አሽቀንጥረን ስንጥል እና የአንድነትን እና የብዝሀነትን ፖለቲካ እቅፍ አድርገን ስንይዝ ብቻ ነው፡፡ ስለወንድማማችነት እና እህትማማችነት ተቀራርበን መነጋገር አለብን እናም ረዥሙን ጉዞ እንዴት አድርገን እንደምናጠናቅቀው እና በመጨረሻ አረንጓዴ፣ ብጫ እና ቀይ ቀለም ወደያዘው ቀስተደመና እንዴት መድረስ እንዳለብን ደጋግመን መወያየት አለብን፡፡ ከዚያ ቀስተደመና በኋላ ስለሚገኘው እና ዋጋ ሊተመንለት ስለማይችለው ውድ እንቁ፡ የሰብአዊ መብት በሕግ ይጠበቃል፣ በሕዝቦች መፈቃቀድ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ለዘለቄታው ይጠናከራሉ፣ የመንግስት ተጠያቂነት በሀገሪቱ የሕግ የበላይነት እውን ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን እርስ በእርሳችን ጥላቻን በማራገብ የማይረቡ ፍሬከርስኪ ንግግሮችን እያደረግን በተመሳሳዩ እና በአሮጌው መንገድ እየተገዟን፣ እርስ በእርሳችን እየተካሰስን፣ ጥላሸት እየተቀባባን እና አየተዘላለፍን ወደ ጉዟችን መዳረሻ ልንደርስ ከቶውንም አንችልም፡፡ ወይም ደግሞ በጥላቻ ክንፍ እና በጠባባዊ የአእምሮ አስተሳሰብ ከቀስተደመናው ጫፍ ላይ በፍጹም ልንደርስ አንችልም፡፡ ብዙ ርቀት በማያስሄድ እና ቅርብ በሆነ መንገድ መጓዝ አለብን፡፡ የሮበርት ፍሮስት የግጥም ስንኞች በመዋስ አንዲህ በማለት ጉዳዩን ግልጽ አናርገው፡ … ድምጼን ከፍ አድርጌ መናገር አለብኝ፣ የትም የትም ቦታ እግሬ በወሰደኝ፣ ለሰው ልጆች ፍትህ የሰላሙ ዘብ ነኝ፣ የሕግ ልዕልና ዲሞክራት ታማኝ፡፡ ሁለት መንገዶች በእንጨት ተከልለው፣ አንዱ ቅርብ ሲሆን ሌላው ግን ሩቅ ነው፣ እኔ የመረጥኩት አጭር አቋራጭ ነው፣ ከጫፍ የሚያደርሰኝ ከቀስተደመናው፣ ከቀይ ቀለሙ ከብጫ አረንጓዴው፡፡ እናም አቋራጩ አጭሩ መንገድ፣ የለውጥ ራስ ሆነ ሰላም የሚወድ፣ ሕዝብን የሚያገኛኝ በብረት ገመድ። በአሁኑ ጊዜ ከጥላቻ አራጋቢዎች ጋር ተገናኝተናል፡፡ በወንድማማችነት እጅ ለእጅ እንያያዝ እና ለወደፊቱ ጉዟችን በጣም ርቀት የማያስኬደውን አቋራጭ መንገድ እንምረጥ፡፡ ይህ መንገድ እንደ ሰብአዊ ፍጡር የተለየ መልካም ዉጤት ያመጣል! ለእኛ እንደ ሕዝብ እና እንደ ሀገር የተለየ መልካም ዉጤት ያመጣል! ጆርጅ በርናንድ ሻው ብልህነትን በተላበሰ መልኩ እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “ያለለውጥ እድገት የማይቻል ነገር ነው፣ እናም አእምሯቸውን የማይለውጡ ሰዎች ምንም ዓይነት ነገር ሊለውጡ አይችሉም፡፡“ እራሳችንን ከፖለቲካ ጥላቻ በማጽዳት ወደ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት የፍቅር ፖለቲከ እንለውጥ፣ እናም “በዓለም ላይ እውን ሆኖ ለማየት ለምንመኘው እራሳችን ለውጥ እንሁን፡፡” ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል፡፡ ፍቅር ሁሉን ያሸንፋል! ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር! ነሐሴ 17 ቀን 2008 ዓ.ም
የማለዳ ወግ ... ዝም የማይባል የወገን ድረሱልን ጥሪ! * "የዛፍ ላይ እንቅልፍ!" ስደት * የኮንትራት ሰራተኞች “ድረሱልን” ድምጽ https://youtu.be/VZP-9yOvdg0 የመረጃ መረቡ ከሃገር ቤት በሚሰማው የህዝብ እንቢተኝነት አመጽ ተጨናንቆ እኛንም አጨናንቆን ከርሟል። በዚህ የመረጃ ቅብብሎሽ መካከል ወደ ምሥራቅ ሳውዲ ለስራ ጉዳይ አቅንቸ ነበር። ርያድ፤ ደማም፡ ጁቤል፤ ሃፍር አልበጠንን ለአንድ ሳምንት ሳካልል ከሃገር ቤት ከሚሰማው መረጃ እኩል በሳውዲ ዙሪያ ያሉ በርካታ ወገኖቸ የተለያዩ መረጃዎች በስልክ አድርሰውኛል። በተዘዋዎርኩባቸው ከተሞች ያገኘኋቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቸም የሚያመውን የስደት ህመም ሳይደምቁ አጫውተውኛል። ሁሉም አሳሳቢ ናቸው፣ ሁሉም ቢያንስ መፍትሔ ይሻሉና ዝም የማይባለውን የወገንን ድረሱልኝ ጥሪ አሳውቃችኋላሁ! ዛሬም በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተኑ ችግር የገጠማቸው ዜጎች መብት አስከባሪ አጥተው ሲንከራተቱ፣ ሲንገላቱና የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ ነው! በአንጻሩ አዲስ ኮንትራት ውል ከሳውዲ አረቢያ ጋር ለመስማማት ደጋግሞ ሞክሮ ያልተሳካለት የኢህአዴግ መንግስት ኮንትራት ውሉን ለማሳካት እየተሯሯጠ መሆኑን ከሪያድ ኢምባሲ ሁነኛ መረጃ ደርሶኛል። ይህ እየተሰራ ባለበት በሳውዲ በባህር መጥተው ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡትን መከራ መስማት ይከብዳል፣ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ኃይማኖት ከየመን በየመን በኩል በሚደረገው በሳውዲ መዳረሻ በመንገዱ ያለውን አሰቃቂ ሁኔታ እፍታ እፍታውን ደጋግሞ ገልጾታልና ደግሜ አላሰለቻችሁም! ብቻ መከረኞቸን መታደግ ሳይቻለን በመቀረቱ አልመች ብሏቸው እንጀራ ፈልገው በየመን የሚጎርፉት ዜጎች "መከራውን እያወቁት መርጠው የመጡት ነው! ይበላቸው!" የሚል ሰብዕና የጎደለው የጨካኝ ምክንያት እየሰጠን ለመርዳት ከመደገፍ መሸሽን መርጫችን አድርገናል! ... ያሳዝናል! የባህርተኞቹ ጉዳይ ይሁን ቢባል፣ ህጋዊ በተባለው በኮንትራት ስራ ሳይደራጁ "በተደራጁት" ኤጀንሲዎች መጥተው በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች የተበተኑት እህቶች ጉዳይ አሳሳቢ ከሆነ ከራርሟል። በኮንትራት በሚሰሩባቸው የአረብ ቤቶች በስራ ጫና፣ በሚደርስባቸው በደል፣ በሕመምና በጭንቀት፣ ብሎም "የተሻለ እናገኛለን" ብለው ከአሰሪዎች የጠፉና" የተሻለ ስራ እናስገባለን!" በሚሉ ሆድ አደር ደላሎች የተፈናቀሉ አብዛኛው እህቶች ቁጥር እጅግ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል! አንድ በኩባንያው ስራዬ በኩል በቅርብ የማውቀው ለፖስፖርት ጽ/ቤት መረጃ ቅርብ የሆነ ሳውዲ ከፍተኛ ኃላፊ በኮንትራት መጥተው ከአሰሪዎቻቸው የጠፉ “ሁሩብ" ተብለው የተመዘገቡ ኢትዮጵያን ቁጥር ወደ 60 እና 70 ሽህ እንደሚገመት አጫውቶኛል ። ለእኒህ ከአሰሪዎቻቸው የጠፉ ወገኖች መካከል በጠፉበት ሆነው ኑሮን በስደት ሲገፉ ጥቂት የማይባሉ "ህገወጥ" መሆናቸው ሳያስፈራቸው ቤት ይዘው፣ ትዳር መስርተው፣ ልጅ ወልደው የሚገኙት ቁጥር ቀላል አይደለም ። " የዛፍ ላይ እንቅልፍ !" ስደት ================== አደጋው የደላ ቤት ይዘው፡ ትዳር መስርተው፤ ቀን መዳር መኳሉ ልጅ መውለዱ አይደለም። የሞቀው ሲበርድ፤ አፍላው አልፎ፤ የእውነቱ ኑሮ ሲጀመር ኑሮን በሃላፊነነት የመግፋቱ ክብደት የመጣ ጊዜ ነው ፍተናው! ሞልቶ የማይሞላው "የዛፍ ላይ እንቅልፍ" የስደቱን ኑሮ እንዳሰቡት አልሰምር ሲል ደግሞ ከላጤዎች ይልቅ ቤተሰብ መስርተውና በስደቱ የልጅ ፍሬ በረከት ለታደሉት መከራው የከፋ ይሆናል። በስቃይ፣ መከራው፣ በእምነት ክህደት፣ ውስብሰቡ ህይወት ያመጧልቸው የስደት ፍሬ ልጆቻቸው ደግሞ የመከራው ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ! ነገሮች ይወሳቡባቸዋል! ...ታዲያ" የመጣ ይምጣ ወደ ሃገር እንግባ፣ የስደቱን ኑሮ ይብቃን!" ብለው ወደ ሐገር መግባት የፈለጉ ቀን ለከፋ ስቅየት ይዳረጋሉ …! በተለይም ከአስሪዎቻቸው ጠፍተው ከርመዋልና ጠፉ ወይም “ሁሩብ” ተብለው በፓስፖርት መ/ቤት የሚፈለጉት ወደ ሐገር ለመግባት ሲፈልጉ ጣጣው የከፋ ሆኗል ። በተለያዩ የሳውዲ ከተሞች ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው የሚይዛቸው እና የሚሸኛቸው አካል አጥተው ” ወደ እስር ቤት አስገብተን ወደ ሃገር እንልካለን በሚሉ የራሳችን ዜጎች ደላሎች ከፍተኛ ገንዘብ ከስክሰው እስር ቤት ከገቡ በኋላ ለወራት በእስር ቤት እየማቀቁ ያሉት ቁጥር ቀላል አይደለም ። ከዚ በታጓዳኝ ለደላላ የሚሰጥ ገንዘብ የሌላቸው ይዞ በእስር ቤት በኩል ወደ ሃገር ቤት የሚልካቸው ፖሊስ አጥተው የሚንክተቱ ቁጥር እጅግ ከፍ ያለ መሆኑን ተመለክቻለሁ ። በሌላ በኩል ከአሰሪዎቻቸው ሳይጠፉ “ኑሮው በቃኝ!” ያሉ ጊዘ ወደ ሃገር ለመግባት ፈልገው ፈቃድ ከአሰሪዎቻቸው የማይሰጣቸው፤ የመውጫ ቪዛ ለማስመታት ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቃቸው እጃቸው ለፖሊ ሰጥተው መያዙ የቀናቸው እስር ቤት ከገቡ በኋላ በወህኒ መጉላላት እንደሚደርስባቸው መረጃዎች ደርሰውኛል። ወደ ሃገር ቤት ለመግባት ፈልገው የተያዙት እና ሳይፈልጉ በቤት ለቤት ሰበራ ፍተሻ ተይዘው እስር ቤት የተወረዎሩት ከወራት በኋላ እንኳ ወደ ሀገረቸው ለመግባት የከፋ እንግልት እንደሚደርስባቸው በዝርዝር አጫውተውኛል! በከፋ አደጋ ላይ ስለመሆናቸው የገለጹልኝ ህጻናትን የያዙ እናቶች ወደ ሀገር ለመግባት ቢፈልጉም ከነገ ዛሬ እየተባሉ ለወራት በወህኒ ሲቆዩ በስቃይ ላይ መሆኑን አጫውተውኛል። ወደ ሃገር ቤት እንግባ ብለው እጃቸው የሰጡ በማናቸውም መንገድ ወደ እስር ቤት የገቡ የኮንትራት ሰራተኞች በተደጋጋሚ ባደረሱኝ መረጃ ህጻናት፤ ነፍሰ ጥሩዎችና አቅመ ደካማ የአእምሮ ህመምተኞች የሚቀይሩት የረባ ልብስ፤ ምግብና ንጹህ መጠጥ በበቂ ሁኔታ እንደማያገኙ ገልጸውልኛል። ነፍሰ ጥሩዎችና የአእምሮ መታዎክ የደረሰባቸው እህቶች መኖራቸውን ከእስር ቤት መረጃ ያቀበሉኝ እኒህ ወገኖች ሌላው ቀርቶ የጅዳ ቆንስልና የሪያድ ኢንባሲ ተወካዮች ልባቸው ለህጻናቱ ራርቶ ወተትና መጸዳጃ እንዲያገኙ እንደማያደርጉ ጠቁመው የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማ አደራ ብለውኛል። ሙሉና ዘርዘር ያለውን በድምጽና ምስል የተላከልኝን ጠልቆ የሚያመውን የድረሱልኝ መልዕክት መረጃ ዛሬ አላቀርበውም፤ ብቻ ድምጻቸው ይሰማ ዘንድ እነሆ ደረሰብን የሚሉትን መረጃው እንዲህ አቀብላቸኋለሁ! ቸር ያሰማን! ነቢዩ ሲራክ ነሐሴ 18 ቀን 2008 ዓም ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com August 25, 2016
የትግራይ ህዝብና ህወሓትን ለይቶ በመመልከት ጉዳይ ላይ በተቃዋሚዉ መሐል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ለማስወገድ የቀረበ ሃሳብ 1. ህወሓትንና የትግራይ ህዝብን በአግባቡ መለየት ዛሬ የአማራ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ መብታችን ተረገጠ ብለዉ በግንባር ቀደምትነት ትግል እያካሃዱ ይገኛሉ። ትላንት ደግም የትግራይ ህዝብ እንዲሁ አይነት ትግል አካሄዶ ነበር፣ መልሶ ሌላ ዓይነት ጭቆና ዉስጥ ሊወድቅ! የዛሬዉን ትግል አግባብንት አለዉ ብለን ስንቀበል የትግራይ ህዝብ ትላንት ላደረገዉ ተጋድሎ እዉቅና መስጠት የግድ ነዉ። ህወሓት/ኢሕአዴግ ጦርነቱን ይምራ እንጂ ድሉ የተገኘው የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ደርግን ተማሮ ይሁንታዉን በመስጠቱና ሲችልም አብሮ በመዋጋቱ ነበር፣ ያለሱም የሚገኝ ድል ስላልነበረ የ1983 ድል የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ነበር ማለት ትክክል ነዉ ብዬ አምናለሁ። በተመሳሳዩ የአድዋ ድል የአፄ ሚኒልክና ያስከተሉት መሳፍንትና መኳንንት ድል ብቻ አልነበረም፣ የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ድል እንጂ። አፄ ሚኒልክ ከአድዋ ድል በኋላ አረመኔ መሪ ቢሆኑ ኖሮ በአረመኔነታቸዉ እንኮንናቸዋለን እንጂ የአድዋ ድልን አናንቋሽሽም። ወደ 1983 የህዝብ ድል ልመለስና፣ ከ1983 ኢትዮጵያ ከዳር እስከዳር በኢሕአዴግ የሥልጣን ማእቀፍ ዉስጥ እንድትጠቃለል ያደረገዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነበር፣ ይሁንታዉን በመስጠትና ትግሬ ነዉ ብሎ እንደባዕድ ሃይል ባለማየቱ! ሆኖም ግን በተለይ የመንግስት ስልጣንን ኢሕአዴግ ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያን ሕዝብ መብት፣ የትግራይን ህዝብ ጨምሮ፣ በየደረጃዉ ገፈፈ። ለዚህ በቡድን የተደራጁ የጥቂት ሰዎች ክፉ ተግባር የትግራይ ህዝብ ፈጽሞ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም። ህወሓት የተከተለዉ የዘረኝነት ድብቅ ፖሊሲ የትግራይ ህዝብ ባለቤትም ተጠያቂም አይደለም። ትንሽ የታሪክ መጽሐፍትን ብናገላብጥ በ1983 ዓም ህወሓት ጋር ሲችል እየተዋጋ ያለበለዚያ ደግሞ በር እየክፈተ ህወሓት/ህወሓት/ 2ኛ ለአንድነት የቆመዉ የተቃዋሚ አጠቃላይ የትግል ስትራተጂ ሻዕቢያ ግብጽና ብዙ የአረብ አገሮች እንዲሁም አንዳንድ ጥቅማቸዉ ከሚነካ ኢትዮጵያ ብትፈርስ የሚመ ርጡ የህወሓትና የኢህአዴግ አባላትየኢትዮጵያን አንድነት የምንፈልግ ሰዎች ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ በሙሉ የሚያካትት የትግል ስትራተጂ ነድፈን፣ የሚያስፈልገዉን መስዋእትነት ከፍለን አገራችንን እንደ አንድ ሰላምንና መብትን አክባሪ፣ ህዝቦቿ ሰርተዉ፡ ተምረዉ፡ ያለሰቀቀን ወጥተዉ ገብተዉ፡ እምነታቸዉን አድርሰዉ፣ ከቤተሰብ ጋር ከዘመድ ወዳጅ ጋር እንደልብ ተገናኝተዉ፣የእለት ጉርሳቸውን አግኝተዉ የሚኖሩባት ተራ ሰላማዊ አገር ሁና ለማየት ከበቃን ጥሩ ጅምር ይሆናል። ይህ ትዉልድ በአንድንት ይሀን ማድረግ ከቻለ የሚቀጥለዉ ትዉልድ ደግሞ ለተራቀቀች ኢትዮጵያን መገንባት ይችላል። ይህን ሽግግር ለማድረግ ግን ሁሉን የሚያካትት የትግል ስትራተጂ የትግራይንም ህዝብ እንደሚጨምር ማስተዋል ይሻል። ከዚህም አኳያ የትግራይ ህዝብ ትግሉ ዉስጥ ዛሬ ተቀላቀለ፣አልተቀላቀለ፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የተቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለዉ ወንድማዊ ፍቅርና የዓላማ አንድነት አይቀየርም። ከሁሉ ባላነሰ እራሱን ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነዉ የትግራይ ህዝብ ዝምታዉንም፣ፍርሃቱንም፣ግራ መጋባቱንም በትእግስት ተረድተን ከትግሉ ሜዳ እንዲቀላቀል ያላቋረጠ ጥሪ ማድረግን ስትራተጂዉ ይጠይቃል። አንዳንድ ጠባብ ተቃዋሚዎች የትግራይ ህዝብ የገባበትን ይህን የታሪክ አጣብቂኝን አላግባብ በመበዝበር “የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ ነዉ! ስርዓቱን ቢደግፈዉ ነዉ ዝም ያለዉ” በማለት በባዕድ አነጋገር፣ በአጸያፊ ቃላትም ሲሳደቡ ይሰማል።በመጀመሪያ ትክክል አለመሆናቸዉን ቀጥሎ ደግሞ ከኢትዮጵያአገራዊ አንድነት የየትግል ስትራተጂ ጋር የማይሃድ መሆኑን ማሳየት ይኖርብኛል። “የትግራይ ህዝብ ስርዓቱን ቢደግፈዉ ነዉ ዝም ያለዉ” የሚለዉ አባባል ከታሪክ መጽሃፍት ስንመለከት በደርግ ጊዜ የትግራይ ህዝብ ላይ ያ ሁሉ ግፍ (ከመደበኛ ጦርነት ሰለባ ከመሆን ያለፈ፣በአገር አንድነት ስም ግፍ ሲፈጸም)የት ነበር የተቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ?ወይስ የተፈጸመዉ ተገቢ ነበር ብሎ ያምን ነበር ወይ?ወደ ኋላ ሄዶ ማንንም ለመኮነን አይደለም፣ ማንም ህዝብ በአምባገነኖች እጅ ዉስጥ እያለ ህሊናዉ የሚፈቅደዉን እንዳያደርግ ልጆቹንና ቤተሰቡን ሲል እንደሚፈራ፣ ከዛም አልፎ አንዳንዴ በጭንቀት ላይ ዘረኛ ፕሮፓጋንዳ ሲደገምበት በመደናገጥም ከጨቋኞች ጋር እንኳ ለአጭር ጊዜ ሊቆም እንደሚችል የኛም የዓለምም ታሪክ ይመሰክራል። በቅርብ ጊዜ እንኳ የኦሮሞ ህዝብ በመቶዎች በግፍ ሲገደል ድምጽ ማሰማት ያልቻለዉ የአማራ ህዝብ አንጀቱ ቢያርም በፍርሃትና ጥርጥር ቆይቶ የወልቃይት ሁኔታ ፍርሃቱን ቀደደለት። ይህም ሲሆን የወሎ፡የሽዋ አማራ እንዲሁም የተቀረዉ ብዙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና የፍርሃት መጋረጃቸዉን አልቀደዱም። የትግራይም ህዝብ እንዲሁ! ኦሮሞና አማራዉ ህዝብ ፍርሀቱን ቀዶ እንደጣለዉ የትግራይም ህዝብ ፍርሃቱን የሚቀድበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም። ከዛ በፊት የሚያሳስበኝ፣ የራሳችንን ታሪክ በደንብ ሳናስተዉል፣ የትግራይን ህዝብ አለመነሳሳት ከመንግስት ጋር እንደመተባበር ተርጉመነዉ፣ ይህም የድላችንን ዕድሜ እንዳያራዝም፣ የኢትዮጵያ አንድነትንም አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ነዉ።ወንድም የሆነዉን የትግራይን ህዝብ ወደትግሉ ሳንታክት መጋበዝ እንጅ መግፋትና ማንጓጠጥ በእሳት መጫወት ነዉ! የኢትዮጵያ አንድነትን ይጎዳል፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች እነሻዕቢያ፣ግብጽና የብዙ የአረብ አገር መሪዎች፣በአገር ዉስጥ ደግሞ ከሁሉም ዘውግ የተፈጠሩ ዘረኞችን ከማርካት ሌላ የሚፈይደዉ የለም። “ህወሓቶች ከአብራካችሁ የወጡ ልጆቻችሁ ስለሆኑ የትግራይ ህዝብ ልዩ ሃላፊነት አለበት” ብሎ ዛሬዉኑ ዉጤት መጠበቅ፣ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚበልጥ የስሜታዉያን ደካማ አካሄድ ነዉ። የትግራይ ህዝብ በነፃነት የሚኖር ህዝብ ቢሆን ኖሮ ዛሬዉኑ በወሰነ ነበር። የትግራይ ህዝብ ከተቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በበለጠ እንጂ ባላነሰ መብቱ እየተረገጠ፣ ከህወሓት ጥቂት ተጠቃሚዎች ጋር ስሙ ያላግባብ የሚጠፋዉ የሱ በመሆኑ፣ ሳናገለዉ ወገንተኝነትን በማሳየት ልናበረታታዉ የሚገባ ወገናችን ነዉ።、 ስለዚህም በተለይ ከትግራይ ህዝብ ጋር ለሚኖር የትግል አንድነት የሚከተሉትን ሃሳቦች አቀርባለሁ፡ 1ኛ የትግራይ ህዝብ ለ17 ዓመት አምባገነን ስርዓትን በመዋጋት ላደረገዉ ተጋድሎ እዉቅናን መስጠት፣ ህዝቡ የወየነበት ምክንያት ዘዉጋዊ ጭቆናን ማዕከል ያደረገ ብሶት በመሆኑ፣ የ1983 ድልም የአምባገነን ስርዓትን የገረሰሰ በመሆኑ የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ድል እንደነበረ ያልተቀበልን ካለን መቀበል 2ኝ በተቃራኒዉ ደግሞ ለ17 ዓመት ዘዉጋዊ ጭቆናን ማዕከል ያደረገዉ በህወሓት የሚመራዉ ትግል፣ የፌዴራል ስርዓታችን ይመለስ ከሚል ባሻገር ሃገራዊ ግንጠላና ኢትዮጵያን ለማፈራረሰ (”የመቶ ዓመት የቤት ስራ ለመስጠት“) ዕቅድ ከነበረዉ ሻእቢያ ጋር በመግጠሙና የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ በመጣሉ፣ ይህን ለመከላከል የኢትዮጵያ ሠራዊትና ህዝብ ለሃገሩ አንድነት ያደረገዉን ታላቅ መሰዋእትነትን ያልተቀበልን ካለን መቀበል 3ኛ የሌላዉን ዘዉግ፣ እምነት ወዘተ የተመለከተ ከመብት ጥያቌ ባሻገር፣ በጥላቻ ወይም ንቀት ማናቸዉንም ዛቻ፣ሰም ማጉደፍ በማንኛዉም ወገን ሲሰነዘር ያለቸልታ ፈጥኖ ማጋለጥ/ማስቆም 4ኛ የትግራይ ህዝብ አሁን በይፋ በተቃዉሞ ጎራ ባለመሰለፉ በአብዛኛዉ ተቃዋሚ ዘንድ የሚታየዉን አሉታዊ ትችት አግባብ እንዳልሆነና የሚያስከትለዉን ችግር ማስረዳት። በትግራይ አሁን በግለሰብ ደረጃ እየተደረጉ ያሉት ተቃዉሞዎችን በማበረታታት ወገናችን የሆነዉ የትግራይን ህዝብ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል የማያቋርጥ ጥሪ ማድረግ። “ትግራይ-ለኢትዮጵያ” (Tigray Lethiopia - Face book name) I can also be reached on tigrailethiopia@gmail.com ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com August 29, 2016
አገዛዙ በዐማራ ሕዝብ ላይ ይፋ ጦርነት አውጇል፤  በባሕር ዳር የሰባታሚት ማረሚያ ቤት ዐማሮች በጅምላ ተቀብረዋል (ሙሉቀን ተስፋው ከአማራ ታጋድሎ እንደዘገበው) • የአብራጂራ ሕዝብ የመከላከያ ታንክ ላይ ሰንደቅ ዓላማ ተከለ • የዐማራ ተጋድሎ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ ሒዷል፤ የጋይንት፣ የቋሪትና ግምጃ ቤት አካባቢዎች ከጠላት ቀጣና የጸዱ ናቸው . የወያኔ መከላከያ ሠራዊት በወገራ አውራጃ ሕጻናትና አቅመ ደካሞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል • የደባርቅ፣ የመተማ፣ ሸኽዲና ሽንፋ ከተሞች በቃጠሎ ታፍነው ውለዋል • በቡሬ ትንሳኤ ሆቴል ግቢ 2 አስከሬን ተደብቆ ተገኘ • በወንበርማ ሽንዲ ወረዳ የዐማራ ተጋድሎ ሁለተኛ ቀኑን አስቆጥሯል • በእጅባራ ሕዝብና መከላከያ ተፋጠዋል ባሕር ዳር፤ ከወደ ባሕር ዳር ያገኘነው መረጃ አስደንጋጭ ነው፡፡የትግራይ መንግሥት የጅምላ ጭፍጨፋ በዐማራው ሕዝብ ላይ በይፋ ማወጁን ተከትሎ ትናንት ብዙ ቁጥር ያላቸው ዐማሮች ተሰውተዋል። የባሕር ዳር፣ ጢስ ዓባይ፣ መሸንቲና መራዊ ከተሞች ከፍተኛ እልቂት ከደረሰባቸው ቀዳሚዎቹ ሆናዋል፡፡ ትናንት በነበረው የዐማራ ተጋድሎ የሰባታሚትና የጢስ ዓባይ ገበሬዎች በገፍ ታፍነው ታስረው የነበሩ ወጣቶችን ማስለቀቃቸው የታወቀ ቢሆንም ቁጥራቸው ያልታወቁ ወጣቶችን ግን ከማምለጣቸው በፊት በጥይት ተጨፍጭፈዋል፡፡ አንድም የተገደለ ዐማራ አስከሬን ወደ ሆስፒታል ያልተወሰደ ሲሆን የሟቾች ቁጥር አገዛዙን ያሳጣል በሚል የትግሬ መከላከያ ሠራዊትና ፖሊስ በጅምላ በማረሚያ ቤቱ ግቢ ውስጥ መቅበራቸውን ነው የዐይን ምስክሮች የገለጹት፡፡ ትናንት ከተሰውት ዐማሮች የሁለት የጢስ ዓባይና የሰባታሚት ገበሬዎች አስከሬን ብቻ ነው የወጣው ተብሏል፡፡ የሁለቱን አስከሬን ለማውጣት የገቡ የዓይን እማኞች እንደሚሉት በጣም ብዛት ያላቸው ዐማሮች አስከሬን መመልከታቸውን እና ሁሉም እዚያ ግቢ እንደተቀበሩም እንደሚያውቁ አክለው ተናግረዋል፡፡ የፈለገ ሕይወት ሆስፒታል የሚሠሩ ባለሙያዎችን የተባለውን ያክል አስከሬን በእነርሱ በኩል ማለፍ አለማለፉን የጠየቅን ሲሆን አሁን አሁን የተገደለውን ሰው ሁሉ ወደ እኛ ሳያመጡ ማፈን የተለመደ እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በመራዊ ከተማ የጦር ጀቶች ዝቅ ብለው ሲበሩ እንደዋሉም ለማወቅ ችለናል፡፡ አብራጂራ/ ሶሮቃ/ እርጎየ፤ የአብራ ጂራ ዐማራ ታሪክ ሰርቷል፡፡ የሆነው እንዲህ ነው፡፡ከሦስት ቀናት በፊት ወጣቶች በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል እስኪቆም የአርማጭሆን እና የጠገዴን ዐማሮች ቀሰቀሱ፡፡የአብራ ጂራና የእርጎየ ከተማ ሕዝብ በአንድነትተነሳ፡፡ የንግድ ተቋማትና የመንግሥት ሥራ እንዲቆም ወጣቶች ጠየቁ፡፡አንዳንድ ወያኔዎች አንዘጋም ብለው አንገራገሩ፡፡ እንርሱን ከቤት እያስወጡ የወያኔ ንብረት የሆነ ሁሉ በአንድነት በእሳት ወደመ፡፡ የወያኔ ጦር ሁለት ታንክ ይዞ መጣ፡፡ የአርማጭሆ አርበኛ ሕዝብ ግን ፊት ለፊት ገጠመው፡፡ የወያኔ ጦር ብሬኑንና ታንኩን እየተወ ፈረጠጠ፡፡የመከላከያ ሠራዊት ታንክ ላይ የአርማጭሆ ወጣቶች የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ አውለበለቧት፡፡እስካሁን ድረስ የአርማጭሆ አካባቢ በሕዝብ ሥር ነው፡፡ የእርጎየ ከተማም የአብራ ጂራን ሕዝብ ሞዴል ተከትላለች፡፡ ዛሬ የወያኔዎችን ንብረት አንድ ባንድ ለቅማ አቃጥላለች፡፡ ምሽቱን ከኹመራ 5 ኦራል የትግሬ ጦር ወደ አብደራፊ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የሰማን ሲሆን ሦረቃዎች ኬላውን ጥርቅም አድርገው ዘግተውታል፡፡ መተማ/ ገንዳውኃ/፤ የመተማ ወረዳ ዛሬ በቃጠሎ ታፍኖ ውሏል፡፡የመተማ ዮሃንስ፣ የገንዳውሃ (ሸኽዲ)ና የሽንፋ ከተማዎች የአገዛዙ የቅርብ አገልጋይ የሆኑ ግለሰቦች ቤትና ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡መተማ ዮሃንስ 2 ዐማሮች የተሰው ሲሆን ሕዝቡም የሞቱንሰዎች አስከሬን በመያዝ በቁጣ የበለጠ ገንፍሎ ወጥቷል፡፡ከመተማ ዮሃንስ አስተያየታቸውን የሰጡን ግለሰብ ‹‹መተማ ዮሃንስ ዛሬ በድርቡሽ ዘመን ስጥቃጠል የነበረውን ጊዜ ሳትመስል አልቀረም›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የወያኔ መከላከያ ሠራዊት በሕዝብ ላይ እየተኮሰ ሲሆን ዐማሮችም በመደራጀት ራሳቸውን እየተከላከሉ ነው፡፡ ወገራ/ደባርቅ፤ በወገራና ደባርቅ አካባቢዎች የትግሬ መንግሥት ይፋ ጦርነት አውጇል፡፡በአምባ ጊወርጊስና አካባቢው ሕጻናት እና ታዳጊ ወጣቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት አገዛዙ ፈጽሟል፡፡አንድ እማኝ እንደገለጹልን ከሆነ በጎንደር ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል ብቻ የስድስትሕጻናት አስከሬን ተከማችቷል፤ ከ20 የሚበልጡ ታዳጊዎች ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡ በደባርቅ ከተማ የአገዛዙ ቅጥረኞችና ወያኔዎች ቤትና ንብረት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሲወድም ውሏል፡፡የደባርቅ ከተማ ቃጠሎ ተከዜ ማዶ ድረስ ሊታይ እንደሚችልም አስተያየታቸውን የሰጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡በደባርቅና በጃናሞራ መካከል ያለው የሰሜንተራሮች አካባቢ ከወያኔዎች አገዛዝ እስካሁን እንደነጻ ነው፡፡ ነፋስ መውጫ/ጋይንት፤ የጋይንት ዐማሮች ከጨጭሆ በኩል የሚመጣውን መንገድ እንደዘጉ ነው፡፡ ዛሬ ላይ የጎብጎብ ወጣቶች ነፋስ መውጫ በመሄድ የመንገድ መዝጋቱን ሥራ አግዘዋል፡፡ ወታደሮች ወደ ጋይንት መጥተዋል የተባለ ቢሆንም ከተማዋን ግን አልፈውእንዳልሄዱ በቦታው ያናገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡የጋይንት ከተማ አንድም ካቢኔ የለባትም፡፡ የአገር ሽማግሌዎችና የጎበዝ አለቆች የጸጥታ ሥራውንና ሰላማቸውን በራሳቸው እያስከበሩ ነው፡፡ በስማዳ ወረዳ ከ4 የሚበልጡ ቅጥረኛ ባንዳዎች መገደላቸውን የሰማን ቢሆንም የመገናኛ መስመሮች በመዘጋታቸው ማረጋገጥ አልቻልንምምዕራብ በለሳ ምንም ዓይነት መገናኛ ዘዴ ባለመኖሩ በምን ሁኔታ ላይ ሕዝቡ እንደሰነበተ የታወቀ ነገር የለም፡፡ ደብረ ታቦር/ ጋሳይ፤ የጋሳይ ከተማ የጎበዝ አለቆች ከተማዋንና አካባቢውን ማስተዳደር ከጀመሩ ቀናትን አስቆጥረዋል፡፡ማንም በሞክሸዎች ሰፍር የሚያልፍ የለም፡፡ የደብረ ታቦር ከተማ ሕዝብ ደግሞ ከቤት ከተደበቀ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡በቤት ውስጥ አድማውሊጎዱ የሚችሉ ሰዎችን ሕብረተሰቡ እየተንከባከበ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ የቤት ውስጥ አድማው ሰው እርስ በእርሱ እንዲተጋገዝና እንዲቀራረብ በር ከፍቶለታል ብለውናል፡፡ ቻግኒ/ እንጅባራ፤ የእንጅባራ አገው ዐማራ ሕዝብ ከትግሬ መከላከያና ፖሊስ ጋር ተፋጦ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል፡፡የጅባራን ከተማና የአዊ ዞንን የሚያስተዳድሩ ካቢኔዎች ሙሉ በሙሉ ከከተማ ወጥተው የገቡበት አይታወቅም፡፡ወጣቶችን ለማሳር የሚሞክሩ የወያኔ መከላከያዎችም ተባረዋል፡፡ሕዝቡ ተነቃንቆ ከወጣ ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን የግምጃ ቤትን ሞዴል በመከተል የጎበዝ አለቃ ለመምረጥ ማቀዳቸውን ገልጸዋል፡፡የእንጅባራ ሕዝብ የደጀን፣ ሉማሜ፣ አወበል፣ ማርቆስ ሕዝብ መንገድ በመዝጋት የሚመጣውንመከላከያ እንዲያስቆም ጠይቀዋል፡፡ በሌላ በኩል የቻግኒን ሕዝብና የትግሬ መከላከያና ፖሊስ ኃይል ባለመመጣጠኑ ብዙ አገው ዐማሮች መታሰራቸውን ሰምተናል፡፡ይህ ዜና በሚጠናቀርበት ሰአት ከ40 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን የሰማን ሲሆን በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪወች ከተማዋንለቀው ወጥተዋል፡፡ የቻግኒ ሕዝብም የአገዛዙ ንብረት የሆኑ ቤቶችንና የንግድ ተቋማትን አቃጥለዋል፡፡ አንክሻ ጓጉሳ/ግምጃ ቤት፤ በአንክሻ ጓጉሳ ወረዳ የግምጃቤት፣ የአዘናና የእሁዲት ከተሞች በጎበዝ አለቆች መተዳደር ከጀመሩ ቀናትን አስቆጥረዋል፡፡ ማንም ወደ እነርሱ መግባት አይችልም፤ ሕብረተሰቡም የራሱን ሰላም በራሱ እያስጠበቀ ነው፡፡የወያኔ መንፈስ ከተባረረሰንብቷል፡፡ ፈረስ ቤት፤ የደጋ ዳሞት ዐማራ ለተጋድሎ ከወጣ ቀናትን አስቆጥሯል፡፡ ትናንት ነሃሴ 24 ቀን 2008 ዓ/ም ቅዳሜ ገበያ 4፡00 አካባቢ እንደገና የተነሳው የዐማራ ተጋድሎ የወያኔ ባንዲራዎችን በማቃጠል ሰንደቅ ዓላማችን በሁሉም ሴክተር መሥሪያ ቤቶች እየሄደቀይሯል፡፡ በዚሁ ሁሉ መካከል 2 ዐማሮች ተሰውተውብናል፡፡3 ሰዎች ደግሞ በፈረስ ቤት ጤና ጣቢያ ሕክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ሁለት ደግሞ ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል ሕክምና ላይ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ የፈረስ ቤት ካቢኔ አንድም በከተማዋ እንደማይታይለማወቅ ችለናል፡፡ ደንበጫ፤ የደንበጫና የጨረቃ ሕዝብ ተጋድሎ ከጀመረ አምስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል፡፡እስካሁን ድረስ ምንም ሥራ የሌለ ሲሆን ከፍተኛ የወያኔ ጦር መሥፈሩን ከቦታው አረጋግጠናል፡፡ ቡሬ፤ በቡሬ ከተማ ባለቤትነቱ የሕወሓቱ ቀንደኛ አባልና ሰላይ የሆነ ትንሳኤ የሚባለው ሆቴል ግቢ ውስጥ ሁለት ዐማሮች ተገድለውና ሸንኮራ አገዳ ቅጠል በላያቸው ላይ ተደርጎ ተገኘ፡፡ይህ አስደንጋጭ ሁኔታ የሕወሓት ሰዎች ንብረት በሆኑ በዐማራው አካባቢበተመሳሳይ መልኩ ሊፈጸም እንደሚችል ይጠበቃል፡፡የቡሬ ከተማ ሕዝብ እካሁን ተጋድሎ ላይ ነው፡፡ ሽንዲ/ ወንበርማ፤ በወንበርማ ወረዳ ወያኔዎች ከዐማራው ላይ ይፋ ጦርነት እያካሄዱ ነው፡፡ እስካሁን ሦስት ወንድሞቻችን ተሰውተዋል፡፡የወንበርማ (ሽንዲ) ሕዝብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አደባባይ በመውጣት ከአገዛዙ ጋር እየተጋደለ ነው፡፡ወደ ወለጋ የሚወስዱናየሚያመጡ መንገዶች ሁሉ ዝግ ናቸው፡፡ ማሳሰቢያ፤ በሁሉም አካባቢ ያላችሁ ዐማሮች መረጃ በማቅረብ ትተባበሩን ዘንድ ልናሳስብ እንወዳለን፡፡ ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው፡፡ ምንጭ - Muluken Tesfaw #AmharaResistance; ዐማራ ዛሬ (ነሃሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም) ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com August 31, 2016
 እጅግ በጣም አስቸኳይ መልእክት ብሥራት ደረሰ በአሁኒቷ ቅጽበት በዐማራው አካባቢ ሕዝቡ ከወያኔ ታጣቂዎች ጋር በባዶ እጁ እየተፋለመ ይገኛል፡፡ ይህ ለዓመታት ታፍኖ የነበረ የነፃነት ጥያቄ ወቅቱን ጠብቆ አሁን በቅርብ ከሞላ ጎደል በሁሉም የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች ፈንድቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው ጭቆናና ምሬት በኃይል ታፍኖ ሊቀር የማይችል መሆኑን ነው፡፡ ይሁንና ነፃነት የጠማው የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሣና በሃይማኖት ተወስኖ የአንዱ ንቅናቄ ለሌላኛው ባይተዋር ሊሆን እንደማይገባ ሁላችንም ማሰብ ይኖርብናል፡፡ እርግጥ ነው እስካሁን ስህተቶች አልነበሩም አንልም፡፡ ንስሃ ልንገባባቸውና ይቅርታ ልንባባልባቸው የሚገቡ ስህተቶችን ሁላችንም ስንሠራ ለመቆየታችን ትልቁ ማስረጃ የወያኔ ሥልጣን ላይ ለ25 ዓመታት ተገሽሮ ሁላችንንም ሲቀጠቅጥ መቆየቱ ነው፡፡ ብንተባበር ኖሮ 25 ዓመታትን ቀርቶ 25 ቀናትንም አራት ኪሎ ምንሊክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ወያኔ አይቆይም ነበር - ታሪካዊ ፀፀት፡፡ ስህተት አንድ - ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የመብት ጥያቄ አንስቶ ብቻውን ሲታገል ሌላው በአብዛኛው በታዛቢ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ያ ትልቅ ስህተት ነበር፡፡ እርግጥ ነው የሙስሊሙን ጥያቄ ከሃይማኖት አውጥቶ ወደ አጠቃላይና ሁሉንም ሊያቅፍ ወደሚችል የመታገያ መስመር ማስገባት ይቻል እንደነበር ብንጠቁም አግባብ ነው፡፡ ጥያቄዎችን ከማጥበብ ይልቅ ማስፋትና ሁሉንም አሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል፤ ይቻላልም፡፡ ጠባብ ጥያቄዎችን መጠየቅ ለወያኔዎች የተናጠል ብትር ይዳርጋል፤ ማንም ደግሞ በተናጠል ጥያቄዎች ድልን ሊቀዳጅ አይችልም፡፡ በትልቅ ጥያቄ ፍቺ ውስጥ ብዙ ትንንሽ ጥያቄዎች ሊፈቱ እንደሚችሉ ባለመረዳት ወይም ለመረዳት ባለመፈለግ ብዙ ዘመን ተሞኝተናል - በዚህም ሰበብ ለወያኔ ምቹ ፈረስና መጋጃ ሆነን ለብዙ ዘመን ባጅተናል፡፡ ይህን ሞኝነታችንን ተረድተን ባፋጣኝ ካልተስተካከልን የሰሞኑ እንቅስቃሴም ከጊዜያዊ ጫጫታነት አያልፍም፡፡ ስህተት ሁለት - ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን በተለይ ከዚህ ዓመት(2008) መባቻ ጀምሮ በየአካባቢያቸው ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያደርጉና በወያኔ ቅልብ የአጋዚ ጦር እንደዐይጥ ሲጨፈጨፉ ሌላው ዳር ቆሞ ይታዘብ ነበር - የወንድሞቹ ቁስል አልተሰማውም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ሥልት ተንበርክከን ራሳችንን በየግል ቋጠሮ በማስቀመጣችን ግን አልተባበርንም፤ በዚያም ምክንያት ወያኔ ተመቸውና በተናጠል መደቆሱን ቀጠለ፡፡ አሁንም እርግጥ ነው - የኦሮሞዎችን ጥያቄ ከኦሮሞ ግዛት መጥበብና መስፋት ጋር ብቻ ከማያያዝ ይልቅ እሱን በእርሾነት ይዞ ለትልቁ ሀገራዊ ነፃነት ሁሉም በአንድነት እንዲነሣ ቢደረግ ኖሮ ይሄኔ ይሄ በየአካባቢው የሚደረግ የቁጥ ቁጥ ትግል ባላስፈለገ ነበር፡፡ ይህችን ሒሣባዊ ቀመር እንዴት ማወቅ እንዳልቻልን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ ጥቂት ወያኔዎች በአእምሮ ማለትም በተንኮል በተካነ አእምሮ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ይህን ያህል እንዴት ሊበልጡ እንደቻሉ ሳስበውም እንደዚሁ ይደንቀኛል፡፡ በምን አፈዘዙን? ስህተት ሦስት - ሰሞኑን የዐማራው ሕዝብ ፀረ ወያኔ እንቅስቀሴውን ጀምሯል፡፡ የዘገዬ ቢሆንም ጅምሩ መልካም ነው፡፡ ሆኖም በተለይ በመነሻው አካባቢ ጥያቄው ልክ እንደላይኞቹ ሁሉ ጠበበና ወይም የሚጠበቀውን ያህል ሌሎችን አሳታፊ ሆኖ የተገኘ አልሆነምና ከክልሉ ውጪ ያሉትን ለመሳብ አቅም ያነሰው መሰለ፡፡ ጎንደር ላይ “የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የኛም ደም ነው” በሚል ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነት የኦሮሞ ወንድምና እህቶቹን ሰማዕትነት ማስታወሱ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ ሁለቱን የወያኔ መጫወቻ ታላላቅ ብሔሮች (በእስካሁኑ ሁኔታ ማለቴ ነው) ቢያቀራርብም አሁንም ብዙ የሚቀረው ነገር እንዳለ መገንዘብ ይገባል፡፡ ወያኔዎችና ተባባሪዎቻቸው ለዘመናት የሠሩት ዕኩይ ተግባር በአንድና በሁለት የተቃውሞ ሰልፎች የሚናድ እንዳልሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ሁለትም ይሁኑ ከዚያ በላይ ትልልቅ ግንዶችን የሚያሸንፍ ቅርንጫፍ - ቅርንጫፉ ምንም ያህል ቀጭንና ላንቁሶም ይሁን - የግንዶቹን ሥሮች እንደምሥጥ እምሽክ አድርጎ በመብላት ግንዶቹን ከናካቴው ሊያጠፋቸው እንደሚችል እስካሁን ማንም አልተረዳም፡፡ ታላላቆችን ለማጥፋት ደግሞ አካላዊ ግዝፈት የግድ አይደለም - ብልጠትና መሠሪነት ብቻቸውን ብዙ ሚና ይጫወታሉ - በዚያ ላይ መካሪና ሁለገብ ረድኤት የሚሰጥ አጋዥ ኃይል ካለ አናሳዎች የጥፋት መንገዳቸው ቀኝ በቀኝ ነው የሚሆንላቸው፡፡ በዓለም 14.2 ሚሊዮን አካባቢ የሕዝብ ቁጥር ያላት እስራኤል የዓለምን ፖለቲካና ኢኮኖሚ በተቆጣጠሩ ምርጥ የኅቡኣን ድርጅቶች አባላት ልጆቿ አማካይነት የሰባት ቢሊዮኑን የዓለም ሕዝብ የዕለት ተለት ሕይወትና እስትንፋስ እንደምትቆጣጠርና እንደምትወስንም ለሚረዳ ዜጋ ከስድስት ሚሊዮን የፈለቁ ጥቂት አሰለጦች ከውጪ ረዳቶቻቸው ጋር ተዓምር አይሠሩም ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ብዛት ብቻውን አይጠቅምም - በራሱ ዋጋቢስ ነው፤ እንዲያውም ብዛት ያጃጅላል ይመስለኛል፡፡ የሌለህን እንዳለህ፣ ያልሆንከውን እንደሆንክ በሥነ ልቦና ጥጋብ እያሰከረ ተጠቂ ያደርግሃል - ብዛት፡፡ ስታንስ ግን ጠርጣራና ፈሪ ያደርግህና ከቢጤዎችህ ጋር እያቆራኘ - እንደሙጫ እያጣበቀ - ብዙ ትንግርት እንድትሠራ ያደርግሃል - ጥቂትነት፡፡ ዕድሜ ደጉ… ማንበብም ደጉ… ከብዙው ጥቂቱን አየን፡፡ ከቅርብ ቀናት ወዲህ የዐማራው ጥያቄ ለአጠቃላዩ ሀገራዊ ነፃነት የጥሪ ደወል ማሰማት ቢጀምርም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በመነሻው አካባቢ በወልቃይት ዙሪያ ያጠነጥን ስለነበር ያ ጥያቄ ለጋሙጎፋውና ለአፋሩ ሩቅ መስሎ ሊታይ ቢችል አያስወቅስም ባይ ነኝ፤ ጥያቄው ሁሉን ቆንጣጭ ነበር ለማለት አያስደፍርም፡፡ አሁን መስተካከሉና ብሔራዊ አጀንዳ መያዙ ግን ደግ ነው፡፡ መስተካከሉን አምነን ታዲያ እንቀላቀለው፡፡ ምክንያቱም የዋናው ድል መቋጫ በዋናነት አዲስ አበባን ጨምሮ የሁሉም ሕዝብ ንቁ ተሣትፎ ነውና፡፡ ስህተት አራት - የዐማራው ጥያቄ ከጎጥና ከሸጥ አልፎ ሀገራዊ ቅርጽ ከያዘም በኋላ የመላዋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለጋራ ሀገራዊና ብሔራዊ ነፃነቱ በአንድነት “ሆ!” ብሎ እንዳይነሣ ያደረገው ነገር አለ፡፡ ይህን ነገር ሁነኛ የፖለቲካ ቡድች በአፋጣኝ አጥንተው መፍትሔ ካልተፈለገለት ይሄ አንዴ ወለጋ ሌላ ጊዜ ጎንደር የሚደረግ ሕዝባዊ የእምቢተኝነት ዐመፅና የነፃነት ትግል የትም አይደርስም፡፡ አዎ፣ የትም! ለሕወሓት ግን ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ ለዚህ ጎጠኛ የአናሳዎች ቡድን መሠሪ ተንኮል መሸነፍ ይብቃን፡፡ ነፃነት ቆራጥነትንና እልህን ትፈልጋለች፡፡ ነፃነት ሸረኝነትና ተንኮልን ያዘለ ፉክክርን አትሻም - የነፃነት ፍልሚያ ውጤታማ እንዲሆን በቀናነትና በእኔ እብስ አንተ ትብስ የጋራ መግባባትና መተሳሰብ መቃኘት አለበት፡፡ ሁሉም እንደየአቅሙ በስሜትና በከፍተኛ ወኔ ከተሳተፈ የነፃነት ቀን ቅርብ ናት፡፡ ነገር ግን “ቆይ እነእንትና ይለይላቸው፣ እነሱ ሲያዳክሟቸው እኛ እንቀጥልና የመጨረሻ ግብኣተ መሬታቸውን እናሳያቸዋለን…” በሚል የማይረባ ሥልት በተናጠል መጓዝ ካለ መቼም ቢሆን ነፃነት አትገኝም፡፡ ነፃነት በእልህ አስጨራሽ የጋራ ትግል እንጂ በብልጣብልጥነትና ከጋራ ትግል በመሸሽ ልትገኝ አትችልም፡፡ በአንዱ ሞት ሌላው ነፃ እንዲወጣ ተደብቆ ወይ አሸምቆ ቢጠባበቅ ደግሞ ከኅሊናም ከሃይማኖትም አንጻር ወንጀልና ኃጢኣትም ነው፡፡ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ፡፡ “ማን ይጠይቀኛል? ማንስ ያየኛል?” የሚሉት ጥያቄዎችም የጅል ፈሊጦች ናቸው፤ በመጀመሪያ ዋናው ጠያቂ ኅሊናችንና የሚሰውት ወገኖቻችን ነፍሳት ናቸው፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ ሁሉም ዐይን ነውና እንዳንታለል፡፡ ስህተትን ለማስወገድ እንዲህ ቢደረግ ጥሩ ይመስለኛል፡- ኦሮሞው፣ ዐማራውና ሌላው ጎሣ ሁሉ በተጀመረው መንገድ ለአንድ ዓላማ ይተባበር፡፡ የተናጠል ትግል የትም እንደማያደርስም ከልምድ ይረዳ፡፡ ጠላት አንድ ነው፡፡ የጥቃቱ ሰለባዎችም አንድ ናቸው ወይም ቢያንስ አንድ መሆናቸውን ሊረዱ ይገባቸዋል፡፡ ራሳቸውን እየለያዩ በተለያዬ ጊዜ ከሚጠቁ በአንድነት ተባብረው ከዘላለም ባርነት በአንዲት ጀምበር የዘላለም ነፃነታቸውን መጎናጸፍ ይችላሉ፡፡ እንደእስከዛሬው በመለያየትና የመቃብር ጉድጓድ እየቆፈሩ በዐፅምና ባለፉ ሰዎች የታሪክ ጠባሳ የሚጃጃሉ ከሆነ ግን ልክ እንደስካሁኑ ለጠላታቸው ምቹ እንደሆኑ አንዱ ምዕተ ዓመት አልፎ ሌላው ይተካል፡፡ በሰው ሠራሽና በጠላት-ጠመድ የልዩነት ቦምቦች ፍንዳታ ጊዜያቸውን በከንቱ ማባከን የለባቸውም፡፡ ከዚህ ሞኝነታቸው ተምረው ብልኅነትን ገንዘባቸው ያድርጉ፡፡ ለምሣሌ የቋንቋና የሰንደቅ ዓላማ ልዩነቶች ወደ ውስጥ ገብተው ካጤኗቸው መሠረታዊ ችግሮች አይደሉም፡፡ ያገሬ ባላገርና ሕጻናት ልጆቹ በሕወሓት አልሞ ተኳሾች ጭንቅላታቸው እየተበተነ በቀያቸው ሥጋቸውን አሞራና ውሻ እየጎተተው ሳለ፣ ሕወሓት ኑሯችንን አመሰቃቅሎና ሰብኣዊ ተፈጥሯችንንም ከእንስሳነትም በታች አውርዶ በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ የሰቀቀን ኑሮ እየገፋን ሳለ፣ እትብቴ በተቀበረባት የገዛ ምድሬ እኔን ለመንግሥት ሥራ መቅጠሩ እንደቅንጦትና ብርቅ ይቆጠርና እንደህንድ የካስት ሲስተም ሊጨብጡኝ እንኳን እየተፀየፉኝ በምገኝበት ሁኔታ … ፖለቲከኞች ሚዛን በማይደፉ የአዛኝ ቅቤ አንጓች ዓይነት ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ቢጠመዱ ሕዝብና ታሪክ ይቅር የማይሉት ሌላ ስህተት ነው - “ቀድሞ የመቀመጫየን” ብላለች ዝንጀሮ፡፡ ከሌላው እንቶፈንቶ ይልቅ የተበላሸን በማቃናት፣ የተሳሳተን በማረም፣ የተዛነፈን በማስተካከል … ወደ ደገኛው መንገድ እንግባና እንደቀድሟችን በቶሎ አንድ ብንሆን ሁላችን እንጠቀማለን፤ ሌላው ቀስ ብሎ ይደረስበታል፡፡ ሞኝነትንና ብልጣብልጥነትን አርቆ መቅበር ይገባል፡፡ ይህን በሕዝብ ደምና አጥንት ላይ የቆመ ከፋፋይ የወያኔ ብልሹ ሥርዓት ከሥሩ መንግሎ ከነሰንኮፉ ለመጣል ሁሉም “ሆ!” ብሎ በአንድ ወቅት መነሣት አማራጭ የሌለው የጊዜው አንብጋቢ ጉዳይ ነው - ከዳር እዳር ተነጋግሮና በጥሞና ተመካክሮ በአንድ ወቅት መነሣት!! ጎጃም የሚፈሰው ደም የአርሲው ነው፤ ወለጋ የሚፈሰው ደም የጎንደሬው ነው፡፡ የወያኔን ሤራ በጣጥሰው ካልጣሉና ሰሞኑን በተጀመረው የአንድነት መንፈስ ካልታገሉ ማንም ነፃ ሣይወጣ የወያኔ አሽከርና ደንገጡር ሆኖ የመከራ ኑሮን መግፋት ነው - እስከወዲያኛው፡፡ መጥፎ ህልም ስታልም መፍትሔው ከእንቅልፍህ መንቃት ነው - ከወያኔ ሰቆቃ ለመዳንም መፍትሔው በከፋፋይ ሤራው ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ኅብረትን ማጽናት ነው፡፡ ያለፈ አልፏል፡፡ “ላለፈ ክረምት ቤት አይሠራም”፡፡ በእጃችን ያለችዋ ጊዜ ናት ወርቃማ ጊዜያችን፡፡ ወንድሞቻችን በጎጃምና በጎንደር እየተዋደቁ በወሎና በሸዋ እንዲሁም በአዋሣና በጋሙጎፋ የሚገኝ ሕዝብ ተኝቶ እንቅልፉን የሚደቃ ከሆነ የምትጠበቀዋ ነፃነት ቅዠት ናት - አትገኝም፡፡ ጎንደርና ባህር ዳር እየታመሱ አዲስ አበባና ናዝሬት በአሥረሽ ምቺው “ዓለማቸውን የሚቀጩ” ከሆነ የነበረችን አነስተኛ በሕይወት የመቆየት ነፃነት ራሷ ወደለዬለት ባርነት ትለወጥና ትልቁ እሥር ቤታችን - ዞን ዘጠኝ - ወደማዕከላዊ የወያኔ የ”ወንጀል ምርመራ” ዘብጥያነት ይለወጣል፡፡ ለዚህም ነው “የነብርን ጅራት አይዙም…” የሚባለው፡፡ ወያኔና የቆሰለ ነብር አንድ ናቸው፡፡ የወያኔን ተፈጥሯዊ የበቀለኛነት ስሜት አዲስ አበቤዎች በተለይ ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡ ከ97 ምርጫ በኋላ ምን እንደደረሰብን እንኳንስ እኛ ሌላው ዓለምም ያውቃል፡፡ ወያኔ በየጊዜው በደም ካልዋኘ ያስተበተበው ድግምት አይሠራለትም - ትልቁ የሰይጣን ምስ ወይም ግብር ደግሞ ደም ነው፡፡ ለዚህም ነው በበቀል የሰከሩት ወያኔዎች በተለይ ዐማራውንም ሆነ ሌላውን - ዓላማቸውን የማይደግፍና የሚቃወማቸውን ትግሬም ሳይቀር - አዛዣቸው ዲያብሎስ በሉ ባላቸው ቁጥር ባልተወለደ አንጀታቸው ጭንቅል ጭንቅሉን እያሉ ለአባታቸው የሚገብሩት፡፡ እነሱ ካልጠፉ ሞታችንና አሟሟታችን እየከፋ እንጂ እየቀነሰ አይሄድም፡፡ በሰይጣን የቆረበ ሰው የተጎጂዎች አበቅቴ እስኪብት ድረስ ዘመኑ ከሚፈቅድለት የወንጀል ድርጊት ውጪ ሌላ ደግ ነገር ይሠራል ተብሎ አይጠበቅም - የባሕርዩ መገለጫ ክፋት ብቻ ነውና፡፡ ምርጫው የኛ ነው እንግዲህ፡፡ በሕዝብ መተባበር ወያኔዎች ሰሞኑን ደንግጠዋል፡፡ የድንጋጤያቸው ደረጃም ሱሪያቸው ከፊትም ከኋላም እስኪረጥብ ድረስ መሆኑን ምሥጢሩን የሚያዉቁ እየተናገሩ ነው፡፡ ይህን በጥርጣሬ ደረጃ ያለ የወያኔ መረጣጠብ ማፋጠንና የዚህን ሰው-በላ የአፓርታይድ ሥርዓት ዕድሜ በደቂቃዎች እንዲገመት ማድረግ ይቻላል፡፡ እንደዚያ የሚሆነው ግን የተጨቋኞች ዓላማና ፍላጎት አንድ ሆኖ ሁሉም በያለበት ወያኔን ሲያርበደብድ እንጂ አንዱ ከነሱ ጋር ማኪያቶ እየጠጣና ውስኪ እየጨለጠ፣ ሌላው ደግሞ በአልሞ ተኳሾች ልዩ ጥይት ጭንቅቱ እየፈረሰ አይደለም፡፡ አሁንም እርግጥ ነው - ኢትዮጵያ ኢያሪኮ እንዳልሆነች ልብ ይሏል፡፡ የኢትዮጵያ ነፃነት ካለደም እንደማትገኝ የጎንደርና የጎጃም ዐማሮች እያስመሰከሩ ነው፤ ከወያኔ ተፈጥሮ የምንረዳውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ያልቃታል እንጂ ወያኔዎች ፈረንጆቹ ዴሞክራሲ በሚሉት ቀልድ ወይም በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ቤተ መንግሥት እንደማይለቁ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም የነሱን ፈለግ በመከተል ሁሉም በተቻለው መፋለም ይገባዋል እንጂ በጩኸት ብቻ ወያኔ አራት ኪሎን ይለቃል ማለት ዘበት ነው፡፡ የዓለም ገዢ ኃይልም ከነርሱ ጋር ስለሆነ ሰሞነኛው ጩኸታችን ቀርቶ የገፍ ዕልቂታችን እንኳን ተገቢውን ዓለም አቀፍ ትኩረት አላገኘም - ማን እንደሰው ቆጥሮን! ይሄኔ የሮበርት ሙጋቤ የክብር ዘብ የአንድ ነጭ ዚምባብዌያዊ የሣሎን ውሻን በባረቀ ጥይት አቁስሎ ቢሆን ኖሮ የነቢቢሲና ሲኤንኤን እንዲሁም የነስካይኒውስና አልጀዚራ ቲቪዎች የአንድ ሣምንት የመክፈቻ ዜና በሆነ ነበር፤ ዘርንና ምጣኔ ሀብትን መሠረት ባደረገ መልክ ዓለም ይህን ያህል አሽቃባጭ ናትና ወደ አምላካችን ብቻ እንጩህ ይልቁንስ፡፡ ከሰው ምንም አንጠብቅ፡፡ ከራሳችን ውስጥ ብዙ ሥጋዊና መንፈሣዊ ኃይል አለ፡፡ ያን እናውጣውና እንጠቀምበት፡፡ ሕዝባችንንም እናንቃው፡፡ የምንችል እናስተምረው፡፡ ከተኛበትም እንቀስቅሰውና የጥንት የጧት አያት ቅድመ አያቶቹ የሠሩትን የመሰለ ታሪክ እንዲሠራ ለዳግም ልደት እናብቃው፡፡… ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ሕዝቡ ማናቸውንም ዓይነት ፖለቲከኛ በልጦ ሄዷል - ወያኔንም ተቃዋሚንም፡፡ ወያኔ ተጎልቶ ያለው ከ41 ዓመታት በፊት በነበረበት ደደቢት ላይ ነው - ሰውነታቸው በዐማራና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጥላቻ እንደተሞላና ገድሎ በማይረካ የበቀል ስሜት እንደተምቦገቦገ፡፡ ተቃዋሚዎች ያሉት የዛሬ 160 ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያ የነበረችበት የዘመነ መሣፍንት ወቅት ላይ ነው - በማይጨበጥ ህልማዊ ሥልጣን እርስ በርስ ሲራኮቱ፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም አእምሮውን የነሣው ነገር አለ፤ ሆድ ይሁን የዝናና የታዋቂነት ልክፍት በውል ለይቼ አላውቅም፡፡ ግን ግን አሁን እኔ እምለው ሁሉም ምናልባትም አብዛኛው ራሱን መፈተሸና ከሕዝብ የነፃነት ፍላጎትና የአርነት ትግል ጎን መሰለፍ የሚችልበትን ብልሃት ባፋጣኝ መቀየስ ይገባዋል ነው - በሕዝብ መበለጡን አውቆ ራሱን “ሳያስፎግር” በቶሎ ይስተካከል - በተቃዋሚነት እያምቧተሩና በሕዝብ ስም እየቀለዱ(እየነገዱም) መኖር ከእንግዲህ የሚታሰብ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዱ ተቃዋሚ ይህን ዓይነት ሕዝብ የሚቀድምበትን የአጣብቂኝ ወቅት የጠበቀ አይመስልም - ለዚህም ነው ተደናግጦና ፈዝዞ ጥግ ጥጉን ይዞ እንደማንኛውም ተራ ዜጋ የነገሮችን አነሳስና ጡዘት እየታዘበ የሚገኘው፡፡ በየተወሰነ ወቅት ይሰጥ የነበረው መግለጫና ፉከራ(ፉገራም ቢባል ያስኬዳል) እንግዲህ ለላንቲካው ነበር ማለት ነው፡፡ አዎ፣ ትዝብትንና ምን ይሉኝን ዕንወቅ፡፡ እንደካሮት ወደታች ሣይሆን እንደሸምበቆ ወደላይ እንደግ፡፡ የአእምሮ መካንነትን እንዋጋና ጤናማ ሰው እንሁን፡፡ ያኔ ሀገራችን ትነሣለች፡፡ … ብዙ ማሰብ፣ ብዙ መሥራት፣ መጥፎ ነገሮችን መርሳት፣ ደጋግ ነገሮች ማስታወስ፣ ፍቅርንና አንድነትን መዘከር፣ ቂምንና በቀልን እርግፍ አድርጎ መተው፣ ወንድማማችነትን መስበክ፣ ጎሠኝነትን መጠየፍ፣ ሰውኛነትን ማጉላት፣ ከሕዝብ መማር፣ በሌሎች ወንጀል ንጹሕን ሰው ከመጠየቅና በሌሎች ደግ ሥራና ምሥጉን ትውፊት ምንም ያልሠሩ ሰነፎችን ማወደስን መተው፣ … በቃ … ባጭሩ ጤናማ ኅሊና ያለው ሰው መሆን …. የሁሉንም ችግር እንደራስ ችግር መቁጠር፣ የሁሉንም የነፃነት ትግል እንደራስ ትግል አምኖ በጋራ መታገል፣ ያንደኛው መክሸፍ የሌላኛውም መክሸፍ መሆኑን ከልብ መገንዘብና የጋራ ኃላፊነትን መውሰድ … ከሌሎች ብዙ አለመጠበቅ፣ የራስንም ድርሻ መወጣት … በገንዘብም በጉልበትም በዕውቀትም በጊዜም … አቅም በቻለ ሁሉ ለዚህች የጋራ ሀገራችን መስዋዕትነትን መክፈል፣ ካለመስዋዕትነት ነፃነት እንደማይገኝ መረዳት…ነፃነት እንደቡና ቁርስ ከሙዳይ ተቆንጥራ የምትሰጥ የዳቦ ፍርፋሪ ወይም ጭብጥ ቆሎ ሣትሆን የደምና የአጥንት ግብር የምትጠይቅ መሆኗን አምኖ ለሚፈለገው ግዳጅ ሁሉ ራስን ማዘጋጀት …ገና ለገና ሥልጣን አገኝ ይሆናል በሚል ከመጠን በላይና ለትዝብት በሚዳርግ ሁኔታ በሥልጣን ሱስ/አራራ አለመስገብገብ … ከሁሉም በላይ በሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ማመን … ፡፡ ወቅቱ የክተት ነው፡፡ ዐጤ ምንሊክ ወደ ዐድዋ ሲዘምቱ በዘርና በጎሣ የተከፋፈለ የውጊያ ጥሪ አላደረጉም - ይህን ዓይነት ሸንካላ ወያኔያዊ አካሄድ አያውቁትምም ነበር፡፡ ባጠፋሁ ይቅርታ … በስሜት ስትናገሪ የምታስቀይሚው ሰው ይኖራል መቼም፡፡ … ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ ለአሁኑ በቃኝ፡፡ ኢትዮሚድያ Ethiomedia.com August 30, 2016
በብዙ የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች መንግሥት ፈርሷል፤ የጎበዝ አለቆች ክፍተቱን እየሞሉ ነው ክፍል አንድ፤ #AmharaResistance; • ባሕር ዳር፣ መራዊና ዳንግላ ከተሞች በጪስ ታፍነው ተኩስ ሲናጡ ውለዋል • ‹‹በአዴት ከተወለዱ በጤና እያለ አንድስ እንኳ እቤት የዋለ የለም›› የአዴት ሪፖርታዥ • ከወረታ ከተማ አቅራቢያ ጉማራ ላይ በገበሬውና በወያኔ መከላከያ መካከል ከባድ ጦርነት ሲደር ግ አድሯል • ቋሪት፣ አገው ምድር፣ ጋይንት፣ በለሳ፣ አብዛኛው የደባርቅና የጃናሞራ አካባቢዎች ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ናቸው • በአንዳቤትና በፋርጣ የጎበዝ አለቆች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ባሕር ዳር፤ በባሕር ዳር ከተማ በሕዝብ የተጠረውን የቤት ውስጥ አድማ ለማደናቀፍ በሞከሩ የወ ያኔ አባላትና ቅጥረኛ ባንዳዎች ንብረት ላይ ዐማራው እርምጃ እየወሰደ ነው። የዐማራው ሕዝብ ቆራጥነቱን በተግባር ያሳየበት ከዛሬ የበለጠ ቀን አልነበረም። ጠዋትአካባቢ አድማውን ችላ በማለት ሥራ የጀመረ አንድ የከተማ አውቶቡስ ሾፌር መኪናውን ሰ ባብረው ልጁን እንዲማር መጠነኛ አካላዊ ጉዳት ደርሶበት አሰናበቱት፡፡ ሥራ የጀመረው የንግድ ባንክም ሕንጻ መስኮቶች ተሰባብረዋል፡፡ በሕዝብ አስቀድመው የተለዩየሕወሓት አባላት እና የዐማራ ቅጥረኛ ባንዳ ሰዎች ስም ዝርዝር አስ ቀድሞ የተሰራ ሲሆን ተራ በተራ ሲቃጠል ውሏል፡፡ ባሕር ዳር አሁን ከዝናቡ ጋር በጭስ ታፍናለች። ከቦታው አስተያየቱን እንዲሰጠን የጠየቅነው የከተማዋ ነዋሪ ‹‹የጥይት ሩምታው ይሰማሃል?የቤት ጣራ ላይ ሆኜ ነው የማወራህ አንድ ሁለት… ወደ ዘጠኝ ቤት ሲቃጠል ይታየኛል እኛ ሰፈር እንኳ የአምቡላንስና የጥይት ድምጽ እየረበሸኝ ነው›› ሲል የነበረበትን ሁኔታ ገልጦልናል፡፡ ቀበሌ 08 የሚባለው ሰፈር በርካታ ቤቶች የተቃጠሉበት ነው ተብሏል፡፡ በባሕር ዳር በዛሬው የዐማራ ተጋድሎ ቀበሌ 06 ሦስት ዐማሮች ተሰውተዋል፡፡ ቀበሌ 14 ኤፍራታ እሚባለው አካባቢ ደግሞ ለታጋይ ዐማሮች ውሃና ምግብ ለማቅረብ ሲሄዱ የነበ ሩ እናት ወድቀው መሰዋታቸውን ሰምተናል፡፡ በርካታ ተሸከርካሪዎች የተቃጠሉ ሲሆን ዐማራው በየሰፈሩ የጎበዝ አለቃዎችን እየመረጠ በመታገል ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ያልተዘጋ መንገድ የለም፡፡ የዐማራ ፖሊስ ሕዝብን በመጠበቅ ያደረገው ተጋድሎ የሚደነቅ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በባሕር ዳር ዛሬ የተደረገው ተጋድሎ እጅግ የሚያኮራናከተማዋን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሕ ዝቡ የተቆጣጠረበት ሁኔታ እንዳለ ሰምተናል፡፡ የባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢ የዐማራን ተጋድሎ ሲያንጸባርቁ ውለዋል፡፡ ከባሕር ዳር ከተማ 17 ኪሎ ሜትር አካባቢ ያለችው የመሸንቲ ከተማና የይባብ ኢየሱስ ቀበሌም የ ዐማራ ተጋድሎ ከዋለባቸው ቦታዎች ውስጥ ናቸው፡፡ መሸንቲ ያለው የሕወሓት አባል የድንጋይ ጠጠር ማምረቻ ፕላንትም ተቃጥሏል ተብለናል፡፡ መራዊ፤ በመራዊ ከተማ የዐማራ ሕዝብ ለተጋድሎ የወጣው በጠዋት ነበር፡፡ የሜጫዋ መራዊ ከተማ እንደ ባሕር ዳር ሁሉ በጢስ ታፍና ውላለች፡፡ ለተጋድሎ የወጣው የዐማራ ሕዝብ ከጉያው ተሸጉጠው ሲያንገላቱት የነበሩትን የሕወሓት አባላትና ቅጥረኛ ባንዳዎችሀብትና ንብረት ተለቅሞ ተቃጥሏል፡፡ የገብረ ሥላሴ ኃይለማርያም ክሊኒክና ፋርማሲ፣ የገ/ድህን ክሊኒክ፣ ፒታ ዳቦ ቤት፣ ኃይሌ ፎቅ፣ የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት፣ ብአዴን ጽ/ቤትና በርካታ የሰላዮች መኖሪያ ቤትና ንብረት ወ ድሟል፡፡ የዐማራ ሕዝብከተማዋን ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ጊዜ ድረስ ተቆጣጥሯት ይገኝ እንደነበር ለማ ወቅ ችለናል፡፡ አዴት፤ የይልማና ዴንሳዋ አዴት ከተማ በዐማራ ተጋድሎ ስትናጥ ውላለች፡፡ ከአዴት ከተማ የሚገኘው ሪፖርተራችን የላከልን መረጃ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ የአዴት ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ወያኔን ሲቃወም ዋለ፡፡ በአዴት ከተወለዱ በጤና እያለ አንድስ እንኳእቤት የዋለ የለም፡፡ ከወጣት እስከ ሽማግሌ፣ ሴትና ወንድ፣ እስላምና ክርስቲያን ሁሉ በቁጣ ገንፍሎ ወጥቷል፡፡ ሰልፉን የሰሙ የይልማና ዴንሳ አርሶ አደሮችም ከወንዳጣ ድረስ እየመጡ በወኔ ተጋድሎውን ተቀ ላቅለው ውለዋል፡፡ ‹‹ወያኔ ሕወሓት ሌባ ነው፤ ቅጥረኛው ብአዴን አይወክለንም፤ ድንበራችን ተከዜ ነው፤ ወልቃይት ዐማራ ነው፤ በዐማራ ላይ የሚደርሰው ጭቆና ይቁም፤ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ይቁም፤ …›› እ ና ሌሎችም መፈክሮች ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የዐማራው ሕዝብ ወደባሕር ዳር በኩል 2 ኪሎ ሜትር መንገድ በመጓዝ አቦላ ተራራ አካባቢ ያለ ውን መንገድ መዝጋት ቅድሚያ የሠጠው መርሃ ግብር ነበር፤ ይህም የወያኔን አልሞ ተኳሾች እን ዳይመጡ መንገዱን ማበላሸት ሲሆን ይህን የሰሙት የባሕር ዳር አናብስት ወጣቶች ሰባታሚትአካባ ቢ መንገዱን ጠርቅመው በመዝጋት የአዴት ዐማሮችን ተባብረዋል፡፡ ሰልፈኞች ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ወጣቶችን ሰብረው በመግባት አስፈትተዋል፤ የአስተዳደር ቢሮው ተሰባብሯል፡፡የገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ኮምፕዩተሮች በእሳት ጋይተዋል፡፡ አካለመንግሥቱ የሚባለው የወያኔ ቅጠረኛ ዐማሮችን ሲሰልልና ሲያሰቃይ የሰነበተ ሲሆን የሕንጻ መሣሪያ መደብሩ ወድሞበታል፡፡ ክሊኒክና ፋርማሲ በመክፈት የአዴት ዐማራን ጊዜው ባለፈበት መድኃኒት ሲበዘብዙና ሲሰልሉ የነ በሩት የገ/እግዚአብሔር ቤተሰቦች ከሳምንታት ቀደም ብለው ከአዴት ቢወጡም ንብረታቸውና መ ኖሪያ ቤታቸው በእሳት ከመጋየት አልዳነም፡፡ የገ/እግዚአብሔር ልጅየሆነው አቶ አማኑኤል ዐማሮችን በሽጉጥ ሲያስፈራራ የሰነበተ ሲሆን ዛሬ ተ ፈልጎ የገባበት ሳይታወቅ ቀርቷል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የወያኔ ቀኝ እጅ የሆኑት የሃይማኖት አባቶች ሰልፉን ለመገላገል ቢገቡም እናን ተን አንሰማም ብሎ አሳፍሮ መልሷቸዋል፡፡ ይልማና ዴንሳበህዝብ ቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ለዘጋቢያችን ምስጋና ይድረሰው፡፡ ዳንግላ፤ የአገው ምድሯ ዳንግላ ከተማ የዐማራን ተጋድሎ የተቀላቀለችው ትናንት ነበር፡፡ ትናንት ነሃሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1ጀምሮ የዳንግላ አገው ዐማራ ሕዝብ ለተጋድሎ ወጣ፡ የዐማራውን ጥያቄዎች አንግቦ ወደ ወኅኒ ቤቱ አቅጣጫ ሲሄድመዘጋጃ ቤት አካባቢ ሲደርስ የወያ ኔ አባል የሆነው የመዘጋጃ ቤት ሠራተኛ አቶ ሀብተወልድ ወደ ሕዝብ በመተኮስ ሁለት ሰዎችን አቆሰለ፡፡ሕዝብ ተቆጣና የአቶ ሀብተወልድን ቤት ሙሉ በሙሉ አቃጠለው፡፡ ወደ መሃል ከተማ ሲመጣ አንድ ቅጥረኛ የሆነ ያረጋል የሚባል ፖሊስ የዳሸን ቢራ ማስታወቂያን ከሚቀዱት የአገው ዐማራ ወጣቶች ላይ ጥይት አርከፈከፈ፡፡ ፖሊሱ የቤቱን አጥር ጉድብ ይዞ ሁለት ሰዎችን ገደለ፡፡ ከሕዝብ ጋር በሚያደርገው ትንቅንቅ ጥይትጨረሰ፡፡ ሕዝቡ ሊይዘው ሲል ጎረቤቱ አንድ ካዝና ጥይት ሲሰጠው አናብስቶቹ አዩት፡፡ ባንዳው ጎረቤቱ ተጨፍጭፎ ተገደለ፡፡ፖሊሱ ቢያመልጥም ቤቱ ከመቃጠል አላመለጠም፡፡ ይህ ሙሰኛ ፖሊስ መኖሪያ ቤት ውስጥ 50 ኩንታል ስኳርና 20 ጀሪካ ዘይትተደብቆ ተገኘ፡፡ ሁሉም ንብረት አብሮ እንዲወድም ተደረገ፡፡ መኪናም ነበረችው፤ ወደመች፡፡ ዳንግላዎች ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡ ነሃሴ 23 ቀን ጠባ፡፡ ዳግም ለተጋድሎ ተሰለፉ፡፡ ከዚያም ዳንግላ ከተማ ከክረምት ጉም እኩል የእሳት ጭስ አፈናት፡፡ የህወሓት አባላትና የቅጥረኛ ባለሥልጣናት ቤት ሙሉ በሙሉ ወደመ፡፡ ከተማዋም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆነች፡፡ የከንቲቫው (አቶ ሙላት እሸቴ) በሙስና የተከማቹ ሦስት ቤቶች፣ የጥቃቅን ኃላፊው አቶ ያለው ዘ ለቀ፣ የብአዴን ኃላፊው አቶ ዳዊት ብርሃኑ፣ የማዘጋጃ ኃላፊው አቶ መንግሥቴ ቢተው፣ የትራፊ ክ ፖሊሱ አቶ አይተነው፣ የደኅንነቱ አቶ ይመኑ፣ እና ሌሎችም ዛሬ ወደአመድነት ከተለወጡ በ ቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የአጋዚና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ቢወሯትም ሕዝብን ግን እስካሁን ማሸነፍ አልተቻለ ም፡፡ ክፍል ሁለት፤ #AmharaResistance; ዱርቤቴ፤ የዱርቤቴ እና የሰሜን አቸፈር ወረዳዋ ይስማላ ከተማዎች በዐማራ ተጋድሎ ሲናጡ ው ለዋል፡፡ የአቸፈር ገበሬዎች የይስማላ ከተማን መቆጣጠራቸው የታወቀ ሲሆን በዱርቤቴ ደግሞ የጎበዝ አለ ቃዎች ምርጫ ተካሒዷል፡ዝርዝር መረጃዎችን በኔትወርክምክንያት ማቅረብ አልቻልንም፡፡ እንጅባራ፤ በእንጅራባራ ከተማ ትናንት ነሃሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ ከመቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ወጥቷል፡፡ የሕዝቡን ብዛት ሲገልጹ በባሕር ዳር፣ በጃግኒና በአዲስ አበባ መውጫ መንገዶች እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር ድረስ የሚረዝምየሰው ጎርፍ ነበር ብለዋል መረጃዎቻችን፡፡ ወልቃት ዐማራ ነው፤ የታሠሩ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፤ ዐማራነት ወንጀል አይደለም፤ የሚሉና ሌ ሎችም መፈክሮች ተሰምተል፡፡ በእንጅባራ በዞኑ ጸጥታ ዘርፍ የሚሠራ አንድ ታፈረ የሚባል አገው ዐማሮችን በማሰቃየት የታወ ቀ ቅጥረኛ በሕግ አምላክ እየተባለ አንድ ሰው ገደለ፡፡ ከዚያ የትግሬ አጋዚ ሠራዊት ደርሶ ሌሎች 5 አገው ዐማሮችን የገደለ ሲሆን 19 ሰዎችን ደግሞ አ ቁስሏል፡፡ ሕዝቡበንዴት እና በደም ፍላት አቶ ታፈረ የተባለውን ባንዳ ሊገድል ቢሞክርም በማምለጡ ልጁ ተገድሏል፡፡ሕዝብ በንዴት ወደ ቤት ሳይገባ በውጭ አድሯል፡፡ የእንጅባራ የዐማራ ተጋድሎ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በርካታ የሕወሓት አባላትና የቅጥር ባንዳ ዎች መኖሪያ ቤቶችና ንብረቶች ተቃጥለዋል፡፡ እንጅባራም በጭስ ታፍነው ከዋሉ ከተሞች አንደኛ ሆናለች፡፡ የአገዚ ጦር ዛሬ ሌሎች 6 ወንድሞቻችን በሞት ነጥቆናል፡፡ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ ዛሬም እየተውለበለበ ሲሆን የእንጅባራ ከተማ አሁንም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ነው፡፡በርካታ መኪናዎች እየተቃጠሉ ነው፡፡ የተጋድሎው መቀጠል አለመቀጠል በተመከተ ለአንድ የእንጅባራ ነዋሪ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹ገ ና ገና ገና ይቀጥላል!›› ሲሉ በሙሉ ልብና በእርግጠኛነት ተናግረዋል፡፡ እኚሁ አስተያየት ሰጪ እንደሚሉት ‹‹የዐማራ ጥያቄ ሳይመልስ መቼም ቢሆን እኛ አናቆምም፤ መንግሥቱን አፍርሰነዋል፤ ቀጣይ ሥራችንም የጎበዝ አለቆችን መምረጥ ነው፤ ወቅቱ የአዝመራ ጊዜ ቢሆንም ገበሬው ከነጻነት በኃላ ይደርሳል እያለ እየተቀላቀለን ነው›› ሲሉ አክለው ገልጸዋል፡፡ ስማዳ፤ የስማዳዋ ወገዳ ከተማ ዐማሮች ዛሬ በጠዋት ነበር ተጋድሏቸውን የጀመሩት፡፡ ዛሬ ሦስት አካበቢ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ የዐማራውን ሕዝብ ጥያቄ ሲያስተጋባ ከዋለ በኋላ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ተውለብልባለች፡፡ በወረዳው የወያኔ ቅጥረኛየሆነ አንድ ፖሊስ ሦስት ያክል ሰዎችን ገድሎ ከዐሥር በላይ ደግሞ ማቁ ሰሉን ከቦታው አረጋግጠናል፡፡ ዛሬ በስማዳ የተሰው ዐማሮች ጠቅላላ አምስት ደርሷል፡፡ የአስተዳደር ቢሮ ተሰብሮ ቅጥረኛው ኃላፊ ከከተማዋ ተሰውሯል፡፡ ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴየቆመ ሲሆን በአቅራቢያ ባሉ የሙጃና የሦስቻም የገጠር ቀበሌዎችም ላይ ተጋድሎ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡ ጃግኒ/ መተከል፤ ዛሬ በጃግኒና በመተከል ባሉ ከተማዎች የዐማራ ተጋድሎ ቀጥሎ የዋለ ቢሆንም በስልክ ችግር የተሟላ መረጃ ማቅረብ አልቻልንም፡፡ አንዳቤት/ጃራ ገዶ፤ የአንዳቤት ዐማሮች ዛሬ ሳይነጋ ሌሊት ዘጠኝ ሰአት ነበር የዐማራውን ተጋድ ሎ የጀመሩት፡፡ የጃራ ገዶ ከተማ ከወልሽ ከተማ 10 ኪሎ ሜትር የምትርቅ ሲሆን በሌሊት የወጣው ዐማራ አንዳ ቤት ወረዳን ድብልቅልቅ አድርጓት ውሏል፡፡ የወልሽከተማ ነዋሪዎች ወደ ጃራ ገዶ በመሄድ የጃራ ገዶ ደግሞ ወደ ወለሽ በመምጣት አዳማ የ ሚባለው አካባቢ ተገናኝተዋል፡፡ የአንዳቤት ዐማሮች የጎበዝ አለቆችን እየመረጡ ሲሆን ቀጣይ ቀናት ወረዳው ሙሉ በሙሉ በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአንዳቤት 5 ዐማሮች በቅጥረኛ ታጣቂዎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቢሆንም የሰው ሕይወት አለመጥፋቱን ሰምተናል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የእስቴዋ መካነየሱስ ከተማ በቤት ውስጥ አድማ መመታቷን ሰምተናል፡፡ የእስቴ መካነየሱስ መንገዶች በሰውና በመኪና ድርቀት ተመተው ውለዋል፡፡ የእስቴን ጤፍ ዘርገቶ የሚይዘው የመካነየሱስ ገበያ አእዋፋት ብቻ ወረውት ውለዋል፡፡ የመካነየሱስ የቤት ውስጥ አድማ ነገም ይቀጥላል፡፡ ጋይንት/ ነፋስ መውጫ፤ ትናንት ነሃሴ 22 ቀን የተጀመረው የቤት ውስጥ አድማ በጽጥታ አካላት ጣልቃ ገብነት ደፈረሰ፡፡የጋይንት አናብስት ተቆጡ፡፡ ተኩስ ተጀመረ፡፡ አንድ ቅጥረኛ ፖሊስ ሦስት ዐማሮችን በጥይት አቆሰለ፡፡ሕዝቡ ሊገድለው ሲል አመለጠ፡፡ ቤቱ ሔዱ፡፡ ተከራይ ሆኖ አገኙት፡፡የቤቱን ሙሉ እቃ አውጥተው አስፓልት ላይ አቃጠሉት፡፡ ዐማሮች ከተማዋን ተቆጣጠሩ፡፡ የጋይንት ዐማሮች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ዋለ፡፡ በጨጭሆ በኩልና በደብረ ታቦር መምጫ መንገዶች በሚገባ ተዘግተዋል፡፡ የነፋስ መውጫ ከተማ ሙሉ በሙሉ በዐማሮች እጅ ከሆነች ሁለተኛ ቀኗን አስቆጥራለች፡፡ የጋይንት ወጣቶች በአድማው የሚበሉትን ላጡሰዎች የምግብ እና የመጠጥ እርዳታ አድርገዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የታች ጋይንት ዐማሮችም ለተጋድሎ መውጣታቸውን ብንሰማም ከቦታው ያገኘነ ው መረጃ ባለመኖሩ ማካተት አልቻልንም፡፡ ደብረ ታቦር፤ የደ/ታቦር ዐማሮች የቤት ውስጥ አድማ ከመቱ ሁለተኛ ቀናቸው ነው፡፡ አንዳንድ ቅጥረኞች ሥራ ለመጀመር ትናንት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ያን የተቃወሙት የታቦር ል ጆች በቅጥረኛ ወታደሮች ሁለት ወንድሞቻችን ተነጥቀዋል፡፡ በደብረ ታቦር 94 ቅጥረኛ ሰላዮች የተለዩ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት ዐማራው ሕዝብ እርምጃ እንደ ሚወስድ ይጠበቃል ሲሉአስተያየት የሠጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡ የታቦር ዐማሮች የፌደራል ፖሊሶችን መሣሪያም መንጠቃቸውን ሰምተናል፡፡ በጎበዝ አለቆችምመደራጀት ተጀምሯል፡፡ ደብረ ታቦር ግማሽ ነጻነት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የጋሳይና የክምር ድንጋይ ዐማሮች የካቢኔ አመራሮችን በሙሉ ማስወገዳቸውም ተገልጧል፡፡ጋሳይና ክምር ድንጋይ መንገዶች ዝግ ናቸው፡፡ ወረታ/ ጉማራ፤ የወረታ ከተማም ትናንት ጀምሮ የቤት ውስጥ አድማ ላይ ናት፡፡ ትናንት ቅጥረኛ የሆኑ ሥጋ ቤታቸውን የከፈቱ 2 ግለሰቦች የወረታ ዐማሮች አዘግተዋል፡፡ መከላከያ ሠራዊት አስለቃሽ ጪስ በመጠቀም ወጣቱን የበተነ ቢሆንም መንገዶችን ሙሉበሙሉ በ መዝጋት የገባውን መከላከያ እንዳይወጣ አስጨንቀውት ሰንብተዋል፡፡ ትናንት ለዛሬ ሌሊት ጉማራ ላይ በገበሬውና በወያኔ መከላከያ መካከል ከፍተኛ ተኩስ አድሯል፡፡ በተኩስ ልውውጡ ሦስት የፎገራ ዐማሮች የተሰው ሲሆን ከሦስት በላይ የመከላከያሠራዊት አባላት ተገድለዋል፡፡ጉማራ ድልድይ መንገድ ተዘግቷል፡፡ ደባርቅ/ ጃናሞራ፤ ከደባርቅ ከተማ እስከ ጃናሞራና ደረስጌ ያለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ከመንግሥ ት ቁጥጥር ውጭ መሆኑን ዛሬ ሰምተናል፡፡ የፖርክ ጠበቂ የነበሩ ሚሊሻዎችን በማባረር ዐማራው ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ነው፡፡ በለሳ/ አርባያ፤ የአርባያ በለሳ ሕዝብ መንግሥትን ካባረረ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ነው፤ ሆኖም በስልክ ችግር ምክንያት የተሟላ መረጃ ማቅረብ አልቻልንም፡፡ በየቦታው መረጃ በማቅረብ ለምትተባበሩን ቁርጥ የዐማራ ልጆች ሁሉ በዐማራ ሕዝብ ስም ምስጋ ናችን ከፍ ያለ ነው፡

Thursday, June 16, 2016

ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ “ህወሃት ሲፈጠርም ጀምሮ ዓለምአቀፋዊ ወሮበላ ነው” (ጎልጉል) ህወሃት በቦንድ ስም ህግ ጥሶ ሲሰበስብ የነበረውን ገንዘብ ክስ ተመስርቶበት ጉሮሮው ሳይታነቅ ወዶ ለመትፋት መስማማቱ ታወቀ። ድርጊቱ ኢትዮጵያን መሳቂያ፣ የምትተዳደረው በህገ አራዊት መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑንና የህወሃትን የወሮበላነት ባህሪ እርቃን ያወጣ ነው ተባለ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከውጭ ምንዛሬ ገበያ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራ ሊካሄድ የሚችልባቸው በርካታ አግባቦች እንደሚኖሩ ነው። ራሱን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ” የሚለው አገዛዝ ከቦንድ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሰሞኑንን ይፋ የሆነበት ዜና “ነጻ አውጪው ሃይል” አሁንም ከጫካ አስተሳሰብ አለመላቀቁን የሚያመለክት እንደሆነ ተጠቆመ። በፍርድቤት ተከስሶ እና ጉሮሮውን ታንቆ ከውርደት ጋር በርካታ የገንዘብ ክፍያ ውስጥ ከመግባቱ በፊት “ጥፋተኛ ነኝ፤ ፍርድቤት አትውሰዱኝ፤ ያላችሁኝን አደርጋለሁ” በማለት ተስማምቶ ራሱን ለክፍያ አዘጋጅቷል፡፡ በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል (SEC) Securities and Exchange Commission (የዋስትናዎችና ልውውጥ ኮሚሲዮን) ተብሎ የሚጠራው የአሜሪካ ፌዴራል መንግሥት መሥሪያቤት ከተቋቋም 80ዓመታት ያለፉት ሲሆን ሶስቱ መሠረታዊ ተልዕኮዎቹ ባለሃብቶችን መከላከል፤ የፋይናንስ ገበያው በሥርዓት፣ በብቃትና በእኩልነት እንዲካሄድ ማድረግና የካፒታል ምስረታን ማበረታታት ናቸው፡፡ ኮሚሽኑ ሰኔ 1፤2008ዓም (June 8, 2016) ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በማለት የጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (በቀድሞ ስሙ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን) በአሜሪካ ውስጥ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በመሸጥ ለፈጸመው ወንጀል 6.5 ሚሊዮን ዶላር (በግምት 150ሚሊዮን ብር) ለመክፈል መስማማቱን ገልጾዋል፡፡ በተለምዶ “የአባይ ቦንድ” ተብሎ የሚጠራውን አሜሪካ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለ አሜሪካ መንግሥትና ያለ ኮሚሽኑ ፍቃድ መሸጡ በማስረጃ ሲረጋገጥ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከማምራቱ በፊት ህወሃት 6.5 ሚሊዮን ዶላር ለኮሚሽኑ ለመክፈል መስማማቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አንዳንድ ወገኖች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ቢመራ ኖሮ ከሚያስከትለው ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሣራ በተጨማሪ የቅጣቱ መጠን ከዚህ በእጅጉ እንደሚልቅ ያስረዳሉ፡፡ ሁኔታው ያላማረው ህወሃት ከጠበቆች በተሰጠው ሙያዊ አስተያየት በመነሳት ጥፋቱን አምኖ ክሱን በስምምነት ለመዝጋት መወሰኑን ስለ ጉዳዩ በቅርበት የሚያውቁ ለጎልጉል በሰጡት አስተያየት ጠቁመዋል፡፡ ጉዳዩ በሕግ የሚታይ በመሆኑ ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው የክስ ማመልከቻ ላይ በግልጽ እንዳመለከተው ኮርፖሬሽኑ እኤአ ከ2011 እስከ 2014 ድረስ ያለ አንዳች ፈቃድ በአሜሪካ በተለያዩ ዋና ዋና ከተሞች ሕገወጥ ቦንድ ሲሸጥ ቆይቷል፡፡ ይህንንም ለማድረግ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው “ኤምባሲ” (የኢህአዴግ ጽ/ቤት) ድረገጽ፤ እንዲሁም የተለያዩ የሬዲዮና የቲቪ ማስታወቂያዎችን መጠቀሙን ገልጾዋል፡፡ (ኮሚሽኑ ያወጣው ባለሰባት ገጽ የክስ መረጃ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡) ከሚያዚያ 2011 ጀምሮ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በተሸጠው የአባይ ቦንድ አማካኝነት የተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ለምሳሌ ያህል ከዚህ የሚከተለው እንደነበር የክሱ ማመልከቻ በግልጽ ያስረዳል፡፡ (የገንዘብ መጠኑ በአሜሪካ ዶላር ነው) ሃይለማርያም ደሳለኝ በዋሽንግተን ዲሲ ለአባይ ግድብ ቦንድ ተሸጦ የተሰበሰበውንና በመጪዎቹ 30 ቀናት ውስጥ የሚመለሰውን ሰኔ 2012 በተቀበሉበት ወቅት፤ (ፎቶ ምንጭ፡ tigraionline.com) ነሐሴ 2011፤ በዴንቨር ኮሎራዶ፤ $130,000.00 ሰኔ 2012፤ በዋሽንግተን ዲሲ፤ $1,500,000.00 ሰኔ 2012፤ በሺካጎ ኤሌኖይ፤ $110,000 ሚያዚያ 2013፤ ሳን ዲያጎ ካሊፎርኒያ፤ $43,000 ሚያዚያ 2013፤ ሒውስተን ቴክሳስ፤ $50,000 ግንቦት 2013፤ ኒው ዮርክ ከተማ ኒው ዮርክ፤ $100,000 ይህ እንደ አመላካች ሆኖ የተሠራ መዘርዝር የቦንዱ ሽያጭ በኤምባሲው ስፖንሰር አድራጊነት በሕዝባዊ አዳራሾች የተሰበሰበውን ለማሳየት የቀረበ ነው፡፡ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ያደረገው ሽያጭ በሬዲዮና በቲቪ እንዲሁም በኤምባሲውና በሌሎች መንገዶች መቅረቡን የክሱ ማስረጃ ያመለክታል፡፡ ቦንዱ የሚወልድበት ዓመት ከደረሰ በኋላ በየስድስት ወሩ ወለድ የሚከፈል መሆኑን ገዢዎች ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያስገቡት የማስታወቂያ መመሪያ ላይ የተመለከተ ሲሆን ክፍያው በቀጥታ ወደ ባንክ ሒሳባቸው ወይም ባንክ ቤቱ ድረስ በመቅረብ መቀበል ከሚለው አንዱን በመምረጥ ከ3,100 (ሶስት ሺህ አንድ መቶ) በላይ የሚሆኑ በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ$5 እስከ $10,000 (ከአምስት እስከ አስር ሺህ ዶላር) ዋጋ ያለውን ቦንድ መግዛታቸውን የኮሚሽኑ የክስ መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዞ እነዚሁ ገዢዎች ያወጡት አጠቃላይ ገንዘብ $5,800,000.00 (አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ዶላር) እንደሆነና ከገዢዎቹ መካከል 64 በመቶው የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ያስረዳል። አገር በዘፈቀደ የሚመራው ህወሃት/ኢህአዴግ ይህንን ሕገወጥ ቦንድ ሉዓላዊነቷ በተከበረ አገር ላይ ሲሸጥ በአገር ውስጥ እንደሚያደርገው በአሜሪካም ማንአለብኝነቱን ለማሳየት መሞከሩ ድንበር ዘለል ሕገወጥነቱን እና ወራዳነቱን ያመለክታል የሚሉ ወገኖች ይህ እንደ አገር “አሳፋሪ” ነው ይላሉ፡፡ ቢያንስ “የተማሩ” የሚላቸው “ሚኒስትሮቹና ዴኤታዎቹ” እንዲሁም ከአምባሳደሩ ጀምሮ በተዋረድ ያሉ የኤምባሲው ሹማምንት ይህንን አስቀድመው ለማስቆም ወይም ህጋዊ እንዲሆን ለማድረግ አለመቻላቸው “የዲግሪ ወፍጮቤት ምሩቃን” መሆናቸውን በገሃድ የሚመሰክር፤ ህወሃት/ኢህአዴግም እስካሁን በሕገ አራዊት የሚመራ ዋልጌ መሆኑን ያለተጨማሪ ማስረጃ ገሃድ ያወጣ ተግባር ነው በማለት እነዚሁ ወገኖች ምሬታቸውን ይናገራሉ፡፡ ኮሚሽኑ ባቀረበው ማመልከቻና ህወሃት በፍርድ ቤት ከመከሰሱ በፊት በተስማማው መሠረት የክሱ ትዕዛዝ ከወጣበት ሰኔ 1፤2008ዓም (June 8, 2016) ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ “የበላውኸውን ትፋ” ተብሏል፡፡ በዚህም መሠረት ህወሃት/ኢህአዴግ $6,448,854.87 (በዶላር ስድስት ሚሊዮን አራት መቶ አርባ አራት ሺህ ስምንት መቶ አምሳ አራት ከሰማኒያ ሰባት ሳንቲም) አንዳች ሳይቀንስ በኮሚሽኑ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ገቢ እንዲያደርግ ታዝዟል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ህወሃት ከቀነ ገደቡ ቢያልፍ በኮሚሽኑ ሕገ ደንብ መሠረት ከነወለዱ እንዲከፍል የሚገደድ መሆኑን የክሱ ማስረጃ ጨምሮ ያብራራል፡፡ ይህ ከተጠናቀቀ በኋላ በሚቀርበው ማስረጃ መሠረት ቦንዱን የገዙ ግለሰቦች ገንዘባቸው (ተገቢም ከሆነ ከነወለዱ) እንዲመለስ የሚደረግበት ሂደት እንደሚቀጥል መረጃው ጨምሮ ያስረዳል፡፡ የሁኔታውን ግዝፈትና የሚያደርሰውን ኪሣራ ጫና የተመለከቱ ወገኖች “ህወሃት ሰኔና ሰኞ ሳያስበው ገጥመውበታል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ውሳኔውን ያስቆጨው አይጋፎረም “ጽንፈኛው ዳያስፖራ (በዚህ ክስ) ያሸነፈ ሊመስለው ይችል ይሆናል፤ ነገርግን ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ነች” በማለት ድንቁርና በለገሰው ድፍረት የህወሃትን መንበርከክ እንደ ሽንፈትን አልቀበልም ብሏል፡፡ ከዚህም አልፎ በዚሁ ድንቁርና በመነዳት “አሁን በሕጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ትሰበስባለች” በማለት ፍቅረ ህወሃት ህልሙን በኢትዮጵያ ስም በማስታወቅ ሰዎችን እንደገና ወደገደል የሚመራ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡ አገሪቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ቀውስ ውስጥ ባለችበትና የዱቤ ደብዳቤ (ኤል.ሲ.) ለመፍቀድ እጅግ በርካታ ወራትን ማስቆጠሩ ነጋዴውን ፍጹም እያስመረረና እያከሰረ ባለበት ሁኔታ ህወሃት ሰብስቦ የበላውን እንዲተፋ መገደዱ የሚያስከትለው የፋይናንስና የገንዘብ ኪሣራ አፍቃሪ ህወሃቶችን እምብዛም ያስጨነቀ አይመስልም፡፡ የጉዳቱን መጠን የሚያውቁት ግን የጠገገ ቁስሉን እንደገና ሲያደሙበት የጣዕር ሲቃ እንደሚያሰማ ስስ ብልታቸው ላይ መመታታቸውን የተረዱ ጩኸታቸው ከሩቅ ይሰማል፡፡ የዛሬ አምስት ዓመት የቦንዱ ሽያጭ ይፋ በሆነ ጊዜ በወቅቱ የንግድ ባንክ ማመልከቻዎችንና የቦንድ ግዢ መመሪያዎችን አባሪ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ባለሙያ ለሆነ ጠበቃ የማስተላለፍ ሥራቸውን የሰሩ ይህ ዓይነቱ ጉዳይ ተጠናክሮ መቀጠል ቢችል ህወሃትን ያለብዙ ችግር ማንበርከክ የሚቻል እንደሆነ አስረግጠው ይናገራሉ፡፡ ቀላሉ መንገድ የዶላሩን መስመር መከተል ብቻ ነው፤ እዚያ መስመር ላይ ህወሃትን ማግኘት ብዙም አይከብድም በማለት ሰሚ ባያገኙም አሁንም ይመክራሉ፡፡ ክቡር ከሆነው የሰው ህይወት ይልቅ ገንዘብ አምላኩ የሆነው ህወሃት የአገርን ክብር ያዋረደውና ዜጎችን በእብሪት እየረገጠ ያለው በገንዘብ ኃይል ነው፡፡ በገንዘብ መከታ ዜጎችን ድሃ ያደርጋል፤ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ያፈርሳል፤ ታማኝ ተቃዋሚ ይመሠርታል፤ ያደኸየውን “ያጠግብና” ተገዢ ያደርጋል፤ ሕገወጥ ዳኞችን ይሾማል፤ ሕግ ያወጣል፤ ሕግን በፍትህ ስም ያረክሳል፤ ፍትህንም በሕግ አንቀጽ ያዋርዳል፤ እስከ ዓለምአቀፍ ቦታዎች ድረስ በገንዘብ ኃይል አሽቃባጮቹንና ተላላኪዎቹን ያስሾማል፤ …፡፡ ህወሃት ለጌቶቹ በገንዘብ የተገዛና አንዳች ክብር የሌለው ወራዳ ስለሆነ የገንዘብን ጥቅም ከማንም በላይ ያውቀዋል፡፡ ይህንን በውል የሚረዱ ወገኖች ደግሞ የህወሃትን የገንዘብ ምንጭ በተቻለው ሁሉ ለማድረቅ ሙከራው ቢቀጥል በገንዘብ ከገዛቸው ተራ ካድሬዎች ጀምሮ እርስበርስ መበላላት መጀመራቸው አይቀሬ ይሆናል ይላሉ፡፡ ከዝግጅት ክፍሉ፤ አገራችን እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ዓይነት በወንበዴ አስተሳሰብ የሚመራ ቡድን የምትገዛ ባትሆን ኖሮ ይህ ዜና ለፍጆታ መቅረብ የሚያስፈልገው አልነበረም፡፡ ይልቁንም እንደ አገርና እንደ ዜጋ ይህ የሁላችንም ገመና በመሆኑ ሁላችንንም የሚያሳፍር መሆን ይገባው ነበር፡፡ ከታላቅ አገራዊ ቁጭትና ጥልቅ ሃዘን ጋር ይህንን ዜና ለፍጆታ ማቅረባችንን አንባቢዎቻችን እንዲረዱልን እንፈልጋልን፡፡ (ምንጭ - ጎልጉል) ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com – June 15, 2016
Ethiopia is behind UN Crimes Report, accuses Eritrea 
By Tom Miles, Reuters
June 15, 2016

GENEVA (Reuters) - Eritrea accused Ethiopia on Tuesday of having orchestrated evidence in a landmark U.N. report last week that accused Eritrean leaders of committing crimes against humanity including torture, murder and enslavement.
The report by independent experts called for the case to be referred to the International Criminal Court.
The U.N. Human Rights Council, which is holding a three-week session in Geneva, is expected to consider a resolution to recommend future action on Eritrea.
"The gathering of information from 'witnesses' organised by Ethiopia allows the latter to advance its propaganda against a country that it aims to destabilise," Eritrean Foreign Minister Osman Saleh told the 47-member state forum.
The two Horn of Africa nations were involved in a war in 1998-2000 that killed 70,000 people. They routinely accuse each other trying to destabilise and topple the other's government.
The minister called Ethiopia "an African face for other countries with a regime change agenda" and said it had initiated an unprovoked military attack against Eritrea on Sunday.
"The armed attack two days ago is timed with the release of the report, supposedly for maximum impact on the territorial integrity and sovereignty of Eritrea."
Echoing comments earlier by an Ethiopian government spokesman, Ethiopian Ambassador Negash Kebret Botora told the Geneva forum Eritrea had launched the unprovoked attack, shelling the population around the border area.
"The regime always chooses when to divert the attention of the international community from its repugnant human rights record," he said.
Osman said Eritrea was focussing on human rights, including cooperating with the U.N. human rights office to strengthen its justice system, seeking U.N. help on its penitentiary system, and freeing Djiboutian prisoners of war.
(Reporting by Tom Miles; Editing by Alison Williams)



Ethiomedia.com - An African-American news and views website.
Copyright 2016 Ethiomedia.com. 
Email: editor@ethiomedia.com

Sunday, June 5, 2016




TPLF Leaders will be Responsible for the Bleeding of the Oromo Nationals

Home » News » Press Release » TPLF Leaders will be Responsible for the Bleeding of the Oromo Nationals
By admin on January 8, 2016.
Statement of the Oromo Liberation Front
asxaa_oromoThe bitter struggle the Oromo people are waging to protect their rights and to maintain their very existence as a nation and the sacrifices they are paying to defend the declaration war and an act of terrorism currently perpetrated on them by the TPLF-led Ethiopian regime is extremely heavy.
As the regime displays its utmost contempt to the Oromo people and intensifies the war of aggression to exterminate the Oromo race, the determination of the Oromo people is getting more and more strengthened and they are intensifying their peaceful protest by the day.
The TPLF/EPRDF (aka Woyane) minority regime in Ethiopia, instead of giving the appropriate response to the legitimate questions of the Oromo people presented through peaceful means, is attempting to put down the ongoing protests through force of arms by deploying the regular army which is supposed to be used to defend the country from an external aggression and is shamelessly engaged in terrorizing the unarmed civilian population.
It is vividly seen that the oppressed people are not fearful of the force of arms and are not flinching from protesting. They have continued their opposition through various means of non-violent struggle.
In unexpected turn of events, the over-flooded non-violent protest in Oromia has shocked the repressive Woyane regime forcing it to decide to stop the movement by committing heinous atrocities and merciless killings, massive imprisonments, severe beatings and torture as usual.
In doing so, the regime has proved itself to be the category of states committing state-terrorism by spilling the blood of peaceful and innocent civilian population.
The open declaration of war of December 15, 2015 in which it labelled the protesting Oromo school children as “terrorists” and ordered its forces to take “merciless action” against them and its immediate action to put the declaration into practice has proved that the regime is no different from the well-known terrorist groups of the globe.
Just like terrorist groups that terrorize peaceful citizens to support them and to fulfill their wishes and interests and behead those who refuse their demand, the TPLF-Woyane regime is forcing innocent and peaceful Oromo citizens to fulfill its interest by killing them with military force for no reason other than asking their legitimate rights.
Just as terrorist groups divide the population through religious lines, prevent people from freely practicing their own religion and mercilessly behead those who are not willing to follow their religion, the Woyane regime is also openly engaged into discriminating and targeting the Oromo people from the rest of the citizens of the country and killing, arresting, and harassing only because of their nationality. Just as terrorists mercilessly massacre unarmed civilians, the TPLF-Woyane regime is killing school children in front of their parents and parents in front of their children.
The current killing of a mother for attempting to save her son and also wounded her son after killing the mother on the spot in Chanka, Kelem Wollega zone is a case in point. Just as terrorists do not have any respect for the dignity of human being and impose their wishes through brutal killings, the minority TPLF-Woyane regime is showing its savage character by killing and hiding the bodies of those that are killed, deny burial in several cases.
At this point, it is confirmed that the TPLF-Woyane regime has killed at least 85 Oromo nationals. Thousands have been injured and disabled by bullets and beating. Tens of thousands are rounded up and undergoing severe torture. The killings, arrests, beatings, and severe torture are continuing with intensity as we write.
Unsatisfied by all these atrocities, the TPLF Woyane minority regime has intensified its act of terrorism by eliminating the most conscious and educated elites of the Oromo society and has continued arresting leaders of the opposition Oromo Federalist Congress (OFC) political party, the university lecturer Mr. Bekele Gerba, the lawyer Mr. Dejene Tafa, and several leaders of various levels of the party.
The Oromo Liberation Front (OLF) strongly condemns the unlawful beatings, mass arrests, torture and killings perpetrated on the Oromo people by this terrorist TPLF-Woyane regime.
We demand that an independent investigative body identify those who are killed, those who participated on the killings and those who gave the orders of the killings and other atrocities.
The OLF once again appeals to the international community and human rights organizations to bring to justice the perpetrators of the gross human rights of violations on the Oromo nationals in particular and other citizens of the country in general.
Victory to the Oromo People!
Oromo Liberation Front
December 26, 2015