Tuesday, February 26, 2013


EPCOU–IN GERMANY
NEWSLETTER/ 09.02.2013
ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በኑረንበርግ ከተማ
ተደረገ
ኦባንግ ሜቶ በጀርመን ኢትዮጵያውያን የ2012 ምርጥ ኢትዮጵያዊ ተባሉ
በጀርመን የኢትዮጵያ
የፖለቲካና የሲቪክ
ማህበር አባላት አንድነት
ድርጅት አዘጋጅነት
በጀርመን አገር
ኑረንበርግ ከተማ
ፌብሩዋሪ 9.2013
ዓ.ም ታላቅ ሕዝባዊ
ስብሰባ ተደረገ::
በዚህ ስብሰባ ላይ
የተለያዩ የፖለቲካ
ድርጅቶች፣ የነጻው
ቁጥራቸው ከ200 በላይ
የሆኑ በተለያዩ የጀርመን ከተማዎች ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል:: በዚህ ስብስባ
ላይ ወጣቱ ትውልድ በብዛት በመገኘት ሃገር ተረካቢነቱን ዳግም አስመስክሯል:: ሌላው
የሄንን ስብሰባ አድመቆት የታየው የሴቶች ተሳትፎ ሲሆን ስብሰባውን ያሰተዋወቁት እና ያስተናገዱት መቅደስ ፣ ሃኒም እና ፍቅርተ ወጣት ሴቶች
ስሆኑ ሴቶች በፖለቲካው መስክ የሚያደርጉት ተሳትፎ እንዲጎለብት እና ለወደፊቱ ድርጅታዊ አመራርና ተሳትፎ እንዲሁም ፍላጎትና ብቃት
እንዲኖራቸው ለማድረግ የስብሰባው አዘጋጅ ኮሚቴ ተኩረት የሰጠበት መሆኑን ተገንዝበናል::
በሌላ በኩል ይህ ስብሰባ እንዳይሳካ ከሚፈለጉ ወገኖች በተደረገው ከፍተኛ ጥረት እና ጫና በርካታ ኢትዮጵያውያኖች ስብሰባውን ለመካፈል
ፈልገው በተደረገባቸው ትጽእኖ እና ማሰፈራራት ሳይገኙ እንደቀሩ ለማወቅ ተችሏል:: ይህንን ከወያኔ የባሱ ለአገርም ለወገንም የማይጠቅሙ
ከፋፋይ የድርጅት አመራሮችና ግለስቦችን ህብረተሰቡ በንቃት እንዲከታተል እና እንዲያጋለጥ በዚህ አጋጣሚ ሳናሳስብ አናልፍም::
በዚህ ስብሰባ እንዲሳተፉ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች የተጋበዙ ሲሆን ጥሪውን አክብረው የተገኙት
1.የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)
2.የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት
3.የሞረሽ አማራ ወገኔ
4.የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር (በስልክ መስመር)
5.የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ሲሆኑከነጻው ፕሬስ ደግሞ ኢሳት፣ ጥላ መጽሄት፣ ሐገሬ መጽሄት እንዲሁም ቀንዲል መጽሄት ተወካዮች ተገኝተዋል
ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት በጀርመን የኢትዮጵያ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበር
አባላት አንድነት ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በላይነህ ወንዳፍራሽ ሲሆኑ
ይህንን ስብሰባ ያዘጋጀነው ከዚህ ቀደም ባደረግነው አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ
አባላቶቻችን የፖለቲካ ድርጅቶችን እንድንጋብዝ ባደርጉት ጥያቄ መሰረት መሆኑን
ገልጸው ይህ አይነቱ መድረክ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ህብረተሰቡን የበልጥ
ያቀራርባል ካሉ በኋላ ዛሬ በዚህ ስብሰባ ጥሪ ተደርጎላቸው ያልተገኙ ድርጅቶች ነገ
እንዴት የኢትዮጵያን ህዝብ ጥሪ ተቀብለው አገር ይመራሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ
አደባባይ የሚወጣ መሪ እንጂ ጓዳ የሚደበቅ ድርጅት አይፈልግም ብለው
በስብሰባው የተገኙትን ድርጅቶች አመስግነዋል::
ድርጅታቸው በጀርመን የኢትዮጵያ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበር አባላት አንድነት
ድርጅት አቶ ኦባንግ ሜቶን በሰብአዊ መብት ዙሪያ ባደረገው እንቅስቃሴ የአመቱ
ታላቅ ሰው አድርጎታል ለዚህም ማስታወሻ ይሆን ዝንድ ባመቱ ልዩ እትም
መጽሄታችን የፊት ገጽ የአቶ ኦባንግ ሜቶን ምስል ይዞ ወቷል ብለዋል::
ድርጅታቸው እስካሁን የሰራቸውን ስራዎች በዝርዝር አስረድተው ወደፊትም
ስራውን በተጠናከረ መንገድ እንደሚቀጥል ግልጽዋል ቀጥለውም በህዝብ ስር
ተሸጉጠው ስደትኞችን እያስፈራሩ እና እያሰለቀሱ ፖለቲካን ንግድ ያደረጉ ድርጅቶች ከወያኔ የማይለዩ በመሆናቸው እስኪጠፉ ድረስ
እንደሚታገሏቸው ለህዝቡ ቃል ገብተዋል::
ቀጥለው መድረኩን የተቀበሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ተወካይ የሆኑት አቶ ጥላሁን ጉደታ ሲሆኑ እሳቸውም አርበኛው በአገር
ቤት እየተዋጋ ነው የኛ ድርጅት አስመራ ከሚገኘው ጽ/ት ጋር ግንኙነት የለውም አስመራ የቁም እስረኞች እንጂ አርበኛ የለም ብለዋል:: ቀጥለውም
አርበኞች ግንባር 3 ቦታ ተከፍሏል ይባላል አርበኛ አንድ ነው አንዳንድ ሰው ለስደት ጉዳያቸው ሲሉ ድርጅት ሊፈጥሩ ይችላሉ ብለዋል::
በመቀጠል ንግግር ያረጉት የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ተወካይ አቶ
አገሬ አዲስ ሲሆኑ በጀርመን የኢትዮጵያ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበር አባላት
አንድነት ድርጅት የምያደርገውን እንቅስቃሴ አድንቀው የበለጠ እንዲጠናከር
ድርጅታቸው ሁልጊዜ እንደሚደግፈው ከገለጹ በኋላ ሸንጎ በየትኛውም ቦታ ጥሪ
ሲደረግለት በማንኛውም ቦታ እንደሚገኝ በጎ ከሚመኙ እና ከሚሰሩ ጋር
እንደሚተባበር ገልጸዋል:: ወያኔ ለሚፈጽመው ግፍና በደል ጉልበት የሆነው
የተቃዋሚ በአንድነት አለመቆም ነው ብለዋል:: በአንድነት መታገል ወሳኝ መሆኑን
በሰፊው ሲያበራሩ ዛሬ በተናጥል የሚደረግ ትግል ቢሳካ ነገ ከሌላው ጋር ተባብሮ
ለመስራት ፈላጎት አይኖረውም በማለት በተናጠል የሚደረግ ትግል ከጥቅሙ ጉዳቱ
እንደሚያመዝን ሰፊ ማብራሪያ ሰተው ድርጅቶች ለትብብር ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ
አስተላልፈዋል:: ወያኔ ራሱን በታለያየ መንገድ ማጠንከሩን ገልጸው ይህንን
ጥንካሬውን ለመቋቋም አንድነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል:: ሸንጎውም በውጪ አገር
ከሚገኙ 8 ድርጅቶች ጋር የጋራ እንቅስቃሴ አስተባባሪ አካል አቋቁሞ በመስራት
ላይ ሲሆን ወደ ጠንካራ ህብረት ሚለወጥበትን መንገድ በመሻት ላይ መሆኑን
አብራርተዋል:: በያላችሁበት አካባቢ ድጋፍ ኮሚቴዎችን በማቋቋም በድርጅትም ሆነ በግለሰብ ሸንጎውን መቀላቀል ትችላላችሁ በለው ጥሪያቸውን
አስተላልፈዋል::
 ሚዲያ አባላት ጥላ/ዳዊት/ -ሀገሬ/ዮናስ - ቀንዲል/ ሚሚና ሀና
ቃለ ጉባዒ ዘጋቢዎች ከግራ ቴዲ-ፍቅረሰብና ሰለሞንቀጥለው ንግግር ያደረጉት የሞረሽ አማራ ወገኔ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር አፈወርቅ ሲሆኑ ሞረሽ
የሚለውን ስያሜ አማራው በአደጋ ጊዜ የሚጠራራበት እንደሆነ ገልጸው ከዚህ ቀደም የመላው
አማራ ህዝብ ድርጅት ኪነት ቡድን መጠሪያ እንደነበረ ጠቅሰዋል:: በአምባ ገነኑ የወያኔ ቡድን
አማራው ላይ ላለፉት 22 አመታት የዘር ማጽዳት ዘመቻ እንደተከፈተበት በዝርዝር
አሰረድተዋል:: ወያኔ ስልጣን ከያዘበት 1983 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ የአገራችን ቦታዎች አማራው
እየታረደ ሲጣል በወቅቱ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ መአህድ የሚል ድርጅት አቋቁመው
አማራውን ከጥፋት ለመታደግ ታግለው በወያኔ እስር ቤት እንዲሞቱ መደረጋቸውን ገልጸው
ከሳቸው ሞት በኋላ ለአማራው የሚሟገት ምንም ድርጅት ባለመኖሩ አማራውን ለከፋ ስቃይ
እንደዳረገው ገልጽዋል:: ወያኔ ራሱ በፓርላማው 2.6 ሚሊዮን አማራ ህዝብ ሲስተማቲክ በሆነ
መንገድ እንዲጠፋ መደረጉን ያመነ መሆኑን አብራርተው ይህንን መንግስት ሆን በሎ በወባ፣
በኤችይቪ እንዲሁም በተለያየ መንገድ ህዝቡ እንዲጠፋ መደረጉን ገልጸዋል:: አሁንም በቅርቡ ከደቡብ ክልል ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ከ78 ሺህ
በላይ የሚሆኑ አማሮች ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየተፈጸመ መሆኑን በሰፊው አብራርተው ሞረሽ አማራ ይህንን ስቃይ ላይ ያለውን አማራውን
ከጥፋት ለመታደግ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል:: ለዚህም አማራ የሆነ እና ማንኛውም የአማራው ስቃይ የሚሰማው ኢትዮጵያዊ ከሞረሽ
ወገኔ ጋር አብሮ እንዲቆም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::
በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ኢንጅነር
ስለሺ ሲሆኑ እሳቸውም ስለድርጅታቸው እንቅስቃሴ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸው ላይ ኢትዮጵያዊያን በ4 ዜግነት ልንከፍላቸው እንችላለን 1ኛ
ደረጃ ዜጋ የሚባሉት የሕወአት አባላት ሲሆኑ 2ኛ ደረጃ ዜጎች ደግሞ የወያኔ
ተለጣፊ ድርጅቶች አባላት ሲሆኑ በ3ኛ ደረጃ ዜጎች ደግሞ በወያኔ 5ለ1
አደረጃጀት ለመኖር ለመስራትና ለመማር ሲሉ በኢሕአዲግ አባልነት የተመዘገቡ
ሲሆኑ 4ኛ ደረጃ ዜጎች ደግሞ ከነዚህ ውጪ ያለው አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል
ነው ብለው የወያኔን የስለላ መረብ በኢትዮጵያውያን መሃከል የፈጠረውን የኑሮ
ልዩነት አበራርተውታል:: በመቀጠልም ቢትዮጵያ 5 አይነት የሽግግር አማራጮች
አሉ ካሉ በኋላ
1ኛ ስራቱ ውስጥ በሚነሳ መሰነጣጠቅ በመዳከም ይወድቃል ብሎ በተስፋ
መጠበቅ ሲሆን ይህም የመሆን እድሉ በጣም ጠባብና የስንፍና ምልክት ነው
ብለዋል::
2ኛ የወያኔን ህገ መንግስት ተቀብሎ በምርጫ ማሸነፍ የሚል ሲሆን ይህም በምርጫ 97 ተሞከሮ እንደታየው ተግባራዊ ሊሆን አይችልም
ብለዋል::
3ኛ አንድ ጠንካራ ፓርቲ በሃይል ጠንክሮ ወጥቶ ወያኔን በመጣል ስልጣን መያዝ የሚለው ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ
አነጻር ለሃገራችን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮች ዘለቄታ ያለው መፍትሄ የማያመጣ ይልቁንም ልክ እንደ ወያኔ ለማሸነፍ ብዙ መስዋትነት
የከፈልኩት እኔ ነኝ ከሚል እሳቤ በመነሳት አምባገነናዊ ስራት የሚመጣበት እድል የሰፋ ይሆናል በማለት ይህን አማራጭ አጣጥለውታል::
4ኛ በሄራዊ እርቅ ማድረግና የሽግግር መንግስት ምምስረት የሚለው ሲሆን ብሄራዊ እርቅ የሚለው ሃሳብ የወያኔ መንግስት ለዘመናት ያለተቀበለው
ይልቁንም ወደ ጎን ሲገፋው የቆየ ሃሳብ በመሆኑ ይህንንም ሃሳብ በተጨባጭ ወደተግባር ለመተርጎም የማይቻል ሲሉት
5ኛ ሁሉን አቀፍ በሆነ ትግል የወያኔን ስራት ማስወገድ እና የሽግግር መንግስት ማቋቋም ሲሆን ይህን ሃሳብ ድርጅታቸው እንደሚያምንበት ገልጸው
የዚህን አማራጭ አዋጭነት ሲያስረዱ የወያኔ ስራት መወገድ አለበት የሚለው ያብዛኛው ህብረተሰብ ጥያቄ መሆኑ ትግሉም የጋራ ደሉም የጋራ
ከሚል መንፈስ መነሳት እንዲሁም በግብጽ የትከሰተው አይነት ሁኔታ እንዳይፈጠር ከለውጡ በኋላ የሚኖረውን ክፍተት ለመዝጋትና ሁሉም
ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ያልቅድመ ሁኔታ ለመስራት ስለሚረዳ ብለው ሃሳባቸውን ቋጭተዋል::
ቀጥለው ወደ መድረክ የመጡት የኢሳት ተወካይ ሲሆኑ ስለ ኢሳት እንቅስቃሴ በአጭሩ
ገልጽው የስብሰባውን ተሳታፊዎች ኢሳት በፌብሩዋሪ 16 ሙንሽን ከተማ
በሚያደርገው ፈንድ ሬይዚንግ ላይ ተገኝተው የህዝብ አይን እና ጆሮ የሆንውን ኢሳትን
መግቢያ ትኬት እንዲገዙ ጠይቀዋል
ከኢሳቱ ተናጋሪ ብኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ይውጭ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት
አርበኛ መንግስቱ ክግንባር በስልክ መስመር ገብተው ኢሕአግ በአሁኑ ውቅት ክፍትኛ
እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ግልጽው ነገር ግን በጀርመን አገር ወክለናቸው የነብሩት
ድርጅቶች ሃላፊነታቸውን ባገባቡ መወጣት ባለመቻላቸው ክድጋፍ ድርጅትነትየተወግዱ ቢሆንም እንሱ ግን በጀርመን አገር ስደተኛውን ሲዘርፉና ሲያሰቃዩት እንደቆዩ አሁንም እያጭበረበሩ እንደሆነ ገልጸው ባሁኑ ወቅት
ትክክለኛ ውክልና የተሰጠው የድጋፍ ድርጅት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ጀርመን መሆኑን ገልጸው ስደተኛው ከአጭበርባሪዎች
እንዲጠነቀቅ አስገንዝበዋል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ጀርመን
ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አንቀጻዊ በበኩላቸው የኛ አላማ ግንባር ያለውን አርበኛ
በተግባር መርዳት ነው ሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ከኛ ጋር ሆናችሁ ትክክለኛውን
አረበኛ እንድትደግፉ በማለት ጥሪያቸውን አስተላለፈዋል::
የጥላ መጽሄት ዋና አዘጋጅ የሆኑት አቶ ዳዊት ፋንታ በነጻው ፕሬስ ዙርያ ሰፋ ያለ
ንግግር አድርገዋል በንግግራቸውም ወያኔ ከጦር መሳሪያ ይልቅ ብእርን አብልጦ
እንደሚፈራ ገልጸው ስርአቱ በፈጠርው አፋኝ እና ዘረኛ አስተዳደር ምክንያት
ብእር የሚያነሱ እጆች አንድም ለስደት አልያም ለእስር ተዳርገዋል በማለት
በነጻው ፕሬስ ዙርያ ያልውን ችግር በሰፊው አብራርተዋል::
ከዛ ቀጥሎ የምሳ እረፍት ተደርጎ በአዳራሹ የተገኘው ተሰብሳቢ ምሳ ከበላ በኋላ
ቀጣዩ ዝግጅት የተጀመረው የተለያዩ ግጥሞችና ጽሁፎች ሲሆን የእስልምና
እምንት ተከታይ የሆኑት አቶ ሰሚር ኢትዮጵያ ውስጥ በስልምና እምነት ውስጥ
የሚደረገውን ጣልቃ ገበነትና ችግሮቹ ላይ ያትኮረ ጽሁፍ አቅርበዋል::
ፍቅርተ በዋልድባ አካባቢ የተከሰትውን ችግር እና የችግሩን መንስኤ በተመለከተ ሰፋ ያለ ጽሁፍ ስታቀርብ ፣ ዘውድነሽ አረብ አገር ሴቶች
እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል አስመልክታ ህይወት ባረብ አገር የሚል አጭር ግጥም አንብባለች፣በተጨማሪም አቶ ሰለሞን ንጋቱ ወቅታዊና
ቀስቃሽ ግጥም አስምተዋል፣
በመቀጠል ውይይቱን የመሩት አቶ የወንድወሰን አናጋው ሲሆኑ በህብረተሰቡም ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል
1.የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገርቤትም ባሉት ሆኑ በውጭ በሚገኙት መካከል የመሰነጣጠቅ ባህል ይታያል፤ምክንያቱ ምንድን ነው?የትኛውስ ፓርቲ
ነው የሚታመንና ሃቀኛው?በምንስ ይታወቃል?
2.የትኛው የአርበኞች ግንባር ነው በእውነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው?የሚንቀሳቀሰውስ የት ነው? ፍርድ ቤት አርበኞች ለ3 ተከፍሏል እናንት
የትኛው ጋር ናችሁ እየተባልን ነው ለምን አትስማሙም?
3. የሽግግር ምክር ቤቱ የፖለቲካ ድርጅት እንአልሆነ ተገልጿል፤ግን የለውጥ አቅጣጫዎችን ዘርግቷል፤እንዴት ነው በተግባር የሚገልጸው?
4.ሞረሽ ለአማራ ሕዝብ የቆመና የሚከራከር ድርጅት ነው፤ከዚህ ድርጅት የበለጠ ለአማራው ሕዝብ ደህንነትና መብት የሚከራከር የለም
ለአባልነትም ቅድሚያ የሚሰጠው ለአማራ ተወላጆች ነው
ተብሏል።ይህ ድርጅቱን ጠባብ አያደርገውም ወይ?የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት በምከንያት ለማፍረስ የሚደረገው ሂደት በአማራ ላይ ከተቀመረው
የጥፋት ዘመቻ አንዱነው ተብሏል፤አቡነ ጴጥሮስ
የአማራው ብቻ ናቸው ወይ?
5.ወጣቱ ወይም ስደተኛው ወደ አገሩ ጉዳይ እንዳይገባ የሚያግደው ነገር ምንድን ነው?እንዲገባስ ምን መደረግ አለበት?እስከዛሬስ ምን ያህል
ጥረት ተደርጓል?
6 የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ አስመራ ግንኙነት ከሌላችሁ ታድያ አስመራ ያለው ቢሮ ተዘግቷል ማለት ነው?እናነተ የት ቢሮ ነው
ግንኑነት ምታረጉት? ከ2 ወር በፊት መሪያችን መአዛ ጌጡ ነው ብላችሁ ነበር አሁን ምን ተገኝቶ ነው በ2 ወር ለውጥ ያመጣችሁት? የሚል ጥያቄ
ቀርበዋል
ከላይ ለተጠቀሱት ጥያቄዎች ድርጅቶቹ ማብራሪያ ሲሰጡ የትኛው የፖለቲካ
ድርጅት ትክክል ነው ሚለውን ማወቅ ሚቻለው ወስጥ ግብቶ ድርጅቶች
ጋር በመሳተፍ ስልሆነ ሁላችሁም በይደርጅቱ ገብታችሁ ተሳተፉ የናነት
ተሳተፎ ትክክለኛውን መለየት ያስችላችኋል ያሉ ሲሆን፣ የአርበኞቹን
ድርጅቶች በሚመለከት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ተወካይ
አቶ ጥላሁን በአንድ በኩል አስመራ ምንም ግንኙ ነት የለንም ሲሉ በሌላ
ብኩል ደሞ አሁንም መሪው መአዛ ጌጡ ነው በማለት የሚጋጭ መልስ
ከመስጠታቸውም ባሻገር አንዳንድ ቦታ ሚናገሩት ሲጠፋቸው ታይተዋል
ከህዝቡም ከፍተኛ ተቃውሞ ተስንዝሮባቸዋል::
የሞረሹ ተወካይ በበኩላቸው አሁን ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ተባበሩ
ማለት ሙታንን ተነሱና አንድ ሁኑ እንደማለት ነው ብለዋል፤ይህ ማለት
የፖለቲካ ትግል የሚያደርግ አንድም የፖለቲካ ድርጅት የለም ማለት ሲሆን
አያይዘውም ሞረሽ እና ኦነግ በጣም ይለያያሉ እኛ የመገንጠል ጥያቄ የለንምይልቁንም አማራው ድሮም የኢትዮጵያ አንድነት እንዲጠብቅ ታገሏል አሁንም ለኢትዮጵያ አንድነት እንታገላለን ብለዋል::
የሽግግር ምክር ቤቱም በበኩሉ አደረጃጀታችን ከታች ወደላይ በመሆኑ የህዝብን ፍላጎት ይዘን ነው የምንጓዘው ከሌሎቹ ድርጅቶች ሚለየንም
አደረጃጀታችን ነው ብለዋል እዚህ አዳራሽ ውስጥ ያላችሁ ኢትዮጵያውያኖች አንድ ድርጅት ውስጥ ግቡ ያመናችሁበትን ድርጅት ተቀላቀሉ ዝም
ብሎ መቀመጥ መፍትሄ አያመጣም የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል::
ከዚህ በላይ በቀረቡትና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ የተሰነዘሩት ጥያቄዎች ላይ የየድርጅቱ ተወካዮች መልስ፣ ማብራሪያና አስተያየት ሰጥተው
በመጨረሻውም ተሰብሳቢው የአርበኞች ግንባርን በሚመለከተው ጉዳይ የተለያዩት ወገኖች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በውይይት
አስወግደው በአንድነት እንዲሰለፉ ፣ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።
የዕለቱ ስብሰባ በጋራ መግለጫ እንዲጠናቀቅ በተወሰነው መሰረት
1 የተለያዩት የፖለቲካ ድርጅቶች፣መከፋፈልንና እርስ በርስ መጠላለፋቸውን አቁመው ትግላቸውን በአንድ ግንባር እንዲያቀዳጁ፣ የአንድነት ምሳሌ
ሆነው የተበታተነውን ደጋፊና ተስፋ ቆርጦ በየቤቱ የተቀመጠውን እንዲያነሳሱ፣ጥሪና ጥያቄ አቅርቧል።
2 በሙስሊምና በክርስቲያን እምነት ውስጥ የመንግሥትን ጣልቃ ገብነትና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በማውገዝ ተንኮሉን ተረድቶ ሕዝቡ እጅ ለእጅ
ተያይዞ የጋራ ጠላት የሆነውን እብሪተኛ፣ተንኮለኛና ዘረኛ የወያኔ/የኢሕአዴግ መንግሥት እንዲታገል ጥሪ አድርጓል አንድ ላይ ለመቆም ቃል
ገብቷል።
3 በየእስር ቤቱ የሚማቅቁትን የስነልቦና እስረኞች፣ጋዜጠኞች፣የሃይማኖት መሪና ተወካዮች፣የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ካለምንም ቅድመ ሁኔታ
በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እየጠየቁ የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ስርዓት እንዲሰፍን ያላቸውን ፍላጎት በመግለጽ በሚደረገው ትግል ያቅማቸውን
ለማበርከት ቃል ገብተዋል።
4 በቅርቡም በጋዜጠኛ አበበ ገላው ላይ የተደረገውን የመግደል ሴራ በማውገዝ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ እና የወያኔ ቡችሎች በየአገሩ
ከሚያደርጉት ተንኮልና ሴራ እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል።
5 ወያኔ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጣልቃ በመግባት በሃይል ፓርቲያልክ ምርጫ እንዲደረግ የሚያደርገውን ግፊት
አውግዘዋል::
በመጨረሻውም ታዳሚው፣ የስብሰባው አዘጋጅ የሆነው በጀርመን የኢትዮጵያ የፖለቲካና የሲቪክ ማህበር አባላት አንድነት ድርጅት አባላት
የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በማድነቅና በማመስገን ሁል ጊዜም ከጎናቸው እንደሚቆም ቃል በመግባት እንዲቀጥሉበት አሳስቦ ብስብሰባው ላይ
አስተዋጾ ላደረጉ አባላት የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቶ ስብሰባው ተበትኗል::

No comments:

Post a Comment