Friday, December 18, 2015


ማስ
ተር
ህዝብ
ሀብት
መዝ
ረፍ
ነው
-
በቀለ
ገርባ
አለማየሁ
አንበሴ
የአዲስ
አበባና
የፊንፊኔ
ዙሪያ
ኦሮሚያ
ልዩ
ዞን
ማስተር
ፕላንን
በተመለከተ
የኦሮሞ
ፌደራሊስት
ኮንግረስ
ያለውን
ዝርዝር
አቋም
ግልጽ
አን
ደርግ
የፓርቲው
ተቀዳሚ
ምክትል
ሊቀመንበር
አቶ
በቀለ
ገርባን
አዲስ
አድማስ
ጋዜጠኛ
አለማየሁ
አንበሴ
በፅ
/
ቤታቸው
ተገኝቶ
አነጋግሯቸዋል፡፡
መንግሥት
ማስተርፕላኑ
ከተሞችን
በመሰረተ
ልማት
በማስተሳ
ሰር
እድገትን
ለማምጣት
ከፍተኛ
ጥቅም
አለው
ይላል፡፡
ፓርቲያችሁ
ደግሞ
ማስተር
ፕላኑን
አልቀበልም
ብሏል፡፡
በምን
ምክንያት
ነው
የማትቀበሉት
?
እኛ
ማስተር
ፕላኑን
የማንቀበለው
በትክክል
የህዝቡን
የልማት
ጥያቄ
ለመመለስ
የተዘጋጀ
ነው
የሚል
እምነት
ስለሌለን
ነው፡፡
መንግሥት
በዚህ
አሳቦ
ወደ
ኦሮሚያ
አጎራባች
ከተሞች
ዘልቆ
እየገባ
ለባለስልጣናትና
ለስርአቱ
አገልጋዮች
ተጨማሪ
ገቢ
ማስገኛ፣
የሀብት
መዝረፊ
ያ፣
በህዝብ
ላይ
ደግሞ
ሌላ
የጭቆና
ቀንበር
መጫኛ፤
ማንነቱን፣
ቋንቋውን፣
ባህሉን
የማጥፋት
ዘመቻ
ነው
ብለን
ነው
የምንወስደው
ይሄን
ለምን
አልን
?
ስርአቱ
ሲመሰረት
,
በህገ
መንግሥት
ተደንግጎ
እንደሚገኘው
ፌደራል
ስርአት
ነው፡፡
ማዕከላዊ
መንግሥት
ራሱን
ችሎ
የተሰጠው
የስራ
ድርሻ
አለ፡፡
ክልሎች
በዋነኝነት
ራሳቸውን
የማስተዳደር፣
ግብር
የመሰብሰብ፣
የሰበሰቡትን
ግብር
ደግሞ
እቅድ
አውጥቶ
በስራ
ላይ
የማ
ዋል፣
በአካባቢያቸው
የሚገኙ
ማናቸውንም
ነገር
የማስተዳደር
ስልጣኖች
አሏቸው፡፡
ስለዚህ
በአካባቢያቸው
ሊፈፅሙት
ያሰቡትን
ልማት
ለየትኛው
ቅድሚያ
እንደሚሰጡ
በትክክል
በገቢያቸው
ላይ
ተመስርተው
ማርቀቅ
ያለባቸው
ራሳቸው
ናቸው
እንጂ
ሌሎች
ክልሎች
ወይም
ማዕከላዊ
መንግሥት
ሊያቅዱላቸው
አይችሉም፡፡
አዲስ
አበባ
በኦሮሚያ
ክልል
ውስጥ
ላሉ
ከተሞች
እቅድ
የማውጣት
አቅሙም
ስልጣኑም
የላትም፡፡
በህገ
መንግሥቱ
በምንም
መንገድ
አዲስ
አበባ
ለነዚህ
ከተሞች
እቅድ
የማውጣት
ስልጣን
አልተሰጣትም፡፡
በአዲስ
አበባ
ከተማ
ቻርተርም፣
በኦሮሚያ
ክልል
ህገ
መንግሥትም፣
በሀገሪቱ
ህገ
መንግሥትም
ቢሆን
ይሄን
ስልጣን
አልሰጠም፡፡
የፌደራል
መንግሥትም
በከተሞች
ፕላን
ውስጥ
ጣልቃ
የመግባት
ስልጣን
አልተሰጠውም፡፡
እንደዚህ
ከሆነ
ከተሞች
ራሳቸውን
አስተዳደሩ
ማለት
እንዴት
ይቻላል
?
ህዝቡ
ምኑ
ላይ
ነው
ራሱን
አስተዳደረ
የሚባለው
?
እንደዚህ
ከሆነ
ትናንት
25
ዓመት
በፊት
ወደነበርንበት
ተመልሰን
እየገባን
ነው
ማለት
ነው፡፡
አሁን
ለተነሳው
አይነት
ጥያቄ
የፓርቲያችሁ
ፕሮግራም
ምን
አይነት
ምላሽ
ነው
የሚሰጠው
?
እኛ
አሁን
በአገሪቱ
ውስጥ
እየተተገበረ
ያለው
የፌደራል
ስርአት
ነው
አንልም፡፡
ምክንያቱም
በአንድ
ክልል
ውስጥ
የሚደረግን
ነገር
ሌላ
ክልል
ውስጥ
በተመሳሳይ
መልኩ
ይገኛል፡፡
ይሄ
ማለት
እቅዶች
ሁሉ
ከላይ
ወደታች
የሚፈ
ሱ፣
በትዕዛዝ
መልክ
የሚተላለፉ
ናቸው
ማለት
ነው፡፡
ለምሳሌ
በአንድ
የትግራይ
ወረዳ
ውስጥ
ያለ
የመንግሥት
አሰራር
በኦሮሚያ
ውስጥ
ወይም
በደቡብ
አቶ
በቀለ
ገርባ
ውስጥ
ይገኛል፡፡
ይሄ
የሆነው
ምንጩ
ማዕከላዊው
ስለሆነ
ነው፡፡
ፌደራሊዝም
ግን
ፅንሰ
ሀሳቡ
ይሄ
አይደለም፡፡
ለምሳሌ
አሜሪካን
ብንወስድ
በአንዱ
ስቴት
በህግ
የሚከለከል
ነገር
ሌላኛው
ይፈቀዳል፡፡
አንዱ
ስቴት
የሞት
ቅጣት
ተግባራዊ
ሊያደርግ
ይችላል፤
ሌላው
ጋር
ፈፅሞ
የተወገዘ
ይሆናል፡፡
ይሄ
የሆነው
እንግዲህ
ስቴቶች
ራሳቸውን
በራሳቸው
የማስተዳደር
መብታቸው
ሳይሸራረፍ
በመተግበሩ
ነው፡፡
በአንፃሩ
እኛ
ግን
ክልልና
ፌደራሉ
የሚለያዩበትን
ነጥብ
አናገኝም፡፡
አንድ
ክልል
የራሱ
እቅድ
ማውጣት
ቢችልም
አሁን
ባለው
አሰራር
ይሄ
የለም፡፡
አንድ
ክልል
ስንት
/
ቤቶች
ስንት
የጤና
ኬላ
እንደሚያስፈልጉት
አያውቅም።
ያንን
የሚያቅድለት
ማዕከላዊ
መንግሥት
ነው፡፡
ይሄ
ከፌ
ደራሊዝም
ፅንሠ
ሀሳብ
ጋር
ይቃረናል፡፡
የፓርቲያችን
የፌደራል
ስርአት
ግን
እነዚህን
በትክክል
አቃንቶ
የሚተገብር
ነው፡፡
በአንድ
በኩል
አዲስ
አበባ
የኦሮሚያ
ክልል
ዋና
ከተማም
ነች።
ከዚህ
ቀደምም
የኦሮሚያ
ነች
የሚል
ጥያቄ
ተነስቷል፡፡
በሌላ
በኩል
የኦሮሞ
ነች
የምትባለው
ይህቺ
ከተማ
ከሌሎች
የኦሮሚያ
ከተሞች
ጋር
እንድትተሳሰር
መንግስት
ያወጣውን
እቅድ
ትቃወማላችሁ፡፡
እነዚህን
ነገሮች
እንዴት
ነው
ምታስታርቁት
?
እኛ
ጥያቄያችን
ህገ
መንግሥቱን
መሰረት
ያደረገ
ነው፡፡
ህገ
መንግሥቱ
ላይ
ኦሮሚያ
ከፌደራል
መንግሥቱ
መቀመጫ
አዲስ
አበባ
ልዩ
ጥቅም
ታገኛለች፤
ዝርዝሩም
በሌላ
ህግ
ይገለፃል
የሚል
አለ፡፡
ዝርዝሩ
ግን
ሳይገለፅ
20
ዓመት
አለፈ፡፡
በኦሮሚኛ
ቋንቋ
የሚያስተምሩ
/
ቤቶችም
የሉም፡፡
አሁን
ያለው
አሰራር
ህጎች
የሚተረጎሙት
በባለስልጣናቱ
ምቾት
ላይ
ተመስርተው
ነው፡
ለራሳቸው
እስካልጠቀመ
ረስ
በህገ
መንግስቱ
እንደተጠቀሰው፤
ከከተማዋ
የኦሮሞ
ህዝብ
የተለየ
ጥቅም
እንዲያገኝ
አልፈለጉም፡፡
በተቃራኒው
ግን
የአዲስ
አበባን
ቆሻሻና
ሌሎች
ችግሮች
የመሸከሙ
ኃላፊነት
ያለው
ኦሮሚያ
ላይ
ነው፡፡
1997
ምርጫ
ጊዜ
ኢህአዴግ
አዲስ
አበባን
ሌላ
አካል
የሚረከብ
ስለመሰለው፣
የኦሮሚያ
መቀመጫ
አዲስ
አበባ
እንዲመስል
አደረገ።
በዚያ
ምክንያት
በፊት
የተከለከሉ
ጥቅሞችን
ክልሉ
እንዲያገኝ
አንድ
ፕሮፖ
ዛል
እንዲሰራ
አደረገ፡፡
አዲስ
አበባ
ከምታገኘው
ገቢ
ምን
ያህሉ
ወደ
ኦሮሚያ
መግባት
እንዳለበት፣
በኬላችን
ላይ
ቀረጥ
እንዲከፈልና
ኦሮሚያ
ገንዘብ
እንድታገኝ፣
በአዲስ
አበባ
ውስጥ
ካሉት
የምክር
ቤት
መቀመጫ
ውስጥ
ደግሞ
ኦሮሚያ
ያለ
ውድድር
የተወሰኑ
መቀመጫዎችን
እንድታገኝ
የመሳሰሉ
ፕሮፖዛሎች
ቀርበው
ነበር፡፡
የተባለው
ድርጅት
ከተማዋን
ሳይረከብ
ሲቀርና
መልሶ
ኢህአዴግ
ከተማዋን
ሲይዝ
የተዘጋጀውን
ፕሮፖዛል
መልሶ
ጣሉት
አላቸው፡፡
ስለዚህ
ኦሮሚያ
በፊትም
ማግኘት
የነበረበትን
ጥቅም
አላገኘም፤
ይባስ
ብሎም
አዲስ
አበባ
ውስጥ
ያለው
መሬት
በማለቁ
ሌላ
ጥቅም
ፍለጋ
ወደ
ኦሮሚያ
መሬት
እጃቸውን
መዘርጋት
ጀመሩ
ማለት
ነው፡፡
ፓርቲያችሁ
በአዲስ
አበባ
ጉዳይ
ያለው
አቋም
ምንድን
ነው
?
በቻርተሩ
ጊዜ
በተደረገው
ስምምነት
መሰረት፤
አዲስ
አበባ
ሙሉ
በሙሉ
የምትገኘው
በኦሮሚያ
ውስጥ
ነው
በሚል
ነው
የታለፈ
ው፡፡
የኦሮሚያ
ናት
የሚል
አልተቀመጠም፡፡
ነገር
ግን
በጣም
ወሳኝ
የሆነ
ቁጥር
በዚህች
ከተማ
እንዳለ
ይታወቃል፡፡
መጀመሪያም
ትንሽ
የኦሮሚያ
መንግስት
ከመሆን
ጀምራ
ነው
አሁን
ወዳለችበት
ደረጃ
ያደገችው፡፡
ይህ
እድገቷ
ዛሬም
እንዲቀጥል
እንፈልጋለን፡፡
እዚህ
ውስጥ
የኦሮሞ
ፍላጎትም
እንዲንፀባረቅ
እንፈልጋለን፡፡
የሌሎችን
ህዝቦች
ጥቅም
በማይጎዳ
መንገድ
አንዳንድ
የኦሮሞ
ተቋሞች
እንዲከፈቱ
እንፈልጋለን፡፡
ነገር
ግን
አሁን

Monday, December 7, 2015


ፊንፊኔ ከተማን ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለማስፋፋት የተነደፈውን ማስተር ፕላንን በማቃወም ከኦሮሞ ፖለቲካፓርቲዎች የተሠጠ መግለጫ

Flag_of_the_Oromo_Liberation_Front.svg
ፊንፊኔ ከተማን ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለማስፋፋት የተነደፈውን ማስተር ፕላንን በማቃወም ከኦሮሞ ፖለቲካፓርቲዎች የተሠጠ መግለጫ

እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተጠቀሰው አምስቱ የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም፡-
1. የኦሮሞ አቦ ነፃነት ግንባር
2. የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር
3. የገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ /ገዳ/
4. የመላ ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና
5. የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ


የሕዝባችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች እንዲመለስ በሰለማዊና መንገድ እያታገል እንገኛለን፡፡
“ከአጋም ጋር የበቀለ ቁልቋል ሁልጊዜ እያደማ ይኖሯል” እንደሚባለው የኦሮሞ ሕዝብ በምኒልክ ነፍጠኞች የሀገር ባለቤትነት ከተቀማ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የኦሮሞ ወጣቶች ደም በከንቱ እየፈሰሰ ይገኛል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት መስዋህትነት የሚከፍለው ከሌሎች ጋር አብሮ ተባብሮ ለመኖር ካለው ቅን ፍላጎት ነው እንጂ የራስህን ዕድል በራስ የመወሰን ዓለም አቀፍ መርህን ተጠቅሞ ከሰሜን ገዥዎች መለየት አቅቶት አይደለም፡፡


የሕወሃት መሪዎች የፌዴራል ሥርዓትና የአገሪቱ ሕገ መንግስት ከሚፈቅደው ውጪ የመከላከያን፣ የደህንነቱን፣ የውጭ ጉዳይና የኢኮኖሚ ሴክተሩን በመቆጣጠር በኦሮሞ ጉዳይ ውስጥ ቀጥታ ጣልቃ በማግባት ፊንፊኔ ከተማ ወደ ኦሮሚያ ልዩዞን ማስፋት አለባት በማለት በያዙት ግትር አቋም የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞታል፡፡ ተማሪዎች ተቃውሞያቸውን በሰለማዊ መንገድ ስለአሰሙ ደብተርና እስክሪፕቶ እንደያዙ በጭካኔ ተገድለዋል፡፡


የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በጥቅምት ወር 2008 ባደረግነው መደበኛ ስብሰባ በማስተር ፕላኑ ምክንያት አንድም የኦሮሞ ተማሪ እንዳይሞት በጋራ ተስማምተን እያለ የተማሪዎቻችን የጭካኔ ግድያ አሁንም መቀጠሉ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ የሕዝብ ጥያቄን በግድያ ማስቆም አይቻልም :: ስለሆነም:-

  1. እኛ እናውቅላቸዋለን በማለት የሕዝብ ጥያቄን ወደ ጎን በመተው ደብተርና እስክሪፕቶ የያዙ ተማሪዎቻችን ላይ እየተፈጸመ የሚኘው የጭካኔ ግድያ ካልቆመ በአገሪቱ ሰላምና አንድነት ላይ ስጋት ፈጥሮ ነገ ልጆቻችን አብሮ ለመኖር ስለማይችሉ ግድያው በአስቸኳይ እንዲቆምና ወንጀለኞቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ
  2. ከሕገ መንግስቱና ከፌዴራል ሥርዓት ወጪ የተነደፈው ማስተር ፕላን ለብዙ የኦሮሞ ወጣቶች ሕይወት ማጥፋትና ንብረት መውደም ምክንያት ስለሆነ በአስቸኳይ እንዲቆም እና ማስተር ፕላኑን ለማስተባበር የተቋቋመው ጽ/ቤትም እንዲዘጋ’ ኦሮሚያን እያስተዳደረ የሚገኘው ኦሕዴድም ኃላፊነቱን እንዲወጣ
  3. የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ብዛቱና እንደቆዳ ስፋቱ በአገሪቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሥልጣን ክፍፍል አላገኘም፡፡ በተላይ ለአንድ ፌዴራል መንግስት ቁልፍ መ/ቤት የሆኑት የመከላከያን’ የደህንነቱን፣ የውጭ ጉዳይና የኢኮኖሚ ሴክተሩን በአንድ ብሔር ቁጥጥር ስር መዋሉ አገሪቱን ወደ አለመረጋገትና መለያየት ስለሚወስድ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ39(3) መሠረት እነዚህን ቁልፍ የአገሪቱ ስልጣን ለኦሮሞ ሕዝብ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡
  4. የኦሮሞ ሕዝብ አንድነቱና የሀገሩ ባለቤትነት መብት አጥቶ በየጊዜው ለከፋ አደጋ ሊጋለጥ የቻለው ዋና ምክንያት ዴሞክራሲው የገዳ ሥርዓቱ ስለፈረሰበት ነው፡፡ ስለሆነም ያልተደረጀ ሕዝብ ለድል ስለማይበቃ ከሁሉም የኦሮሚያ ዞኖች ተውጣጥተን ሕብረት የፈጠረነው’ ከ40 ዓመት በላይ ለሕዝብ በመታገል ልምድ ያካበትነውና የገዳ ሥርዓትን ለመመለስ በጽናት እየታገል ያለነው የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስር ተደራጅታችሁበሕጋዊ መንገድ መብታችሁን እንዲታስከብሩ ለኦሮሞ ሕዝብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የሁሉም የአፍሪካ ብሔሮች መብት ከተከበረ አንድ የአፍሪካውያን ፌዴራላዊ መንግስት ማቋቋም ይቻላል!!
ፍትህ ለኦሮሞ ሕዝብ /Justice for Oromo Nation!!

ህዳር 25 ቀን 2008 ዓ.ም ‘ ፊንፊኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

2 Comments

  • Anonymous 2 hours ago
    menliken atekubene weyanan gen edefelegachu belachew
  • natati 3 hours ago
    Well said enough of killing feature qubee jeneration I aproved article 39 oromiyaa shall be free