Tuesday, March 17, 2015

ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው የህወሃት ጀሌ ተጋለጠ (አዲስ ቮይስ) -- በጋዜጠኛ አበበ ገላው እና በቤተሰቡ ላይ ህገወጥ በሆነ መንገድ በተከታታይ ስልክ በመደወል ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር የሞከረው ግለሰብ ማንነት ተጋለጠ። ጋዜጠኛ አበበ ገላው የግለሰቡን ማንነት ለማጣራት ለበርካታ ሳምንታት ጥንቃቄ የተሞላበት ክትትልና ምርመራ መደረጉን እና ድምጹም ልምድ ባላቸው የፎረንሲክ ኤክስፐርቶች የተመረመረ መሆኑን ገልጾ በዚሁ መሰረት ይህን ህገወጥ የሆነ ድርጊት ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ ሙሉጌታ ካህሳይ የተባለ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ጀሌ መሆኑ እንደተደረሰበት ገልጿል። ግለሰቡ በተለይ በአለፈው ወር ላይ ወደ ኢሳት ሬድዮ የአድማጮች መልእክት መቀበያ በመደወል በተለይ ለጋዜጠኛው በተወው መልእክት ደምህን እንጠጣለን እንዲሁም ቤተሰቦችህን እንፈጃለን፣ በአዲስ አበባ ያለህን ቤት እናቃጥላለን የሚሉ ሁለት ተከታታይ መልእክቶችን አስቀምጦ እንደነበር ታውቋል። አበበ ገላው “ምንም እንኳን የሚቃጠል ቤት እና ንብርት ባይኖረኝም ከእኔ ስላማዊ የትግል እንቅስቃሴ እና የጋዜጠኝነት ስራ ጋር በተያያዘ ምንም በማይመለከታቸውን ደካማ ዜጎች ላይ ወንጀል ለመፈጸም መዛት የህወሃቶችን አስነዋሪ ድርጊት ብቻ ሳይሆን የሞራል ዝቅጠት የሚያሳይ ድርጊት ነው ፣” ሲል ድርጊቱን አጥብቆ አውግዟል። በትርፍ ሰአቱ በታክሲ መንዳት ስራ የሚተዳደረው እና ለበርካታ አመታት በለደን ቀንደኛ ከሚባሉት የወያኔ ተወካዮች አንዱ የሆነው ሙሉጌታ ካህሳይ አምስት የሚሆኑ የማስፈራሪያና የግድያ ዛቻ ያዘሉ መልእክቶችን ያስተላለፈ ሲሆን በተደጋጋሚ ጋዜጠኛው በቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ላይ ያሰማውን ተቃውሞ በመጥቀስ “የሞት ቅጣት ይገባሃል” ማለቱን ለማወቅ ተችሏል። በእንግሊዝ አገር ደቡባዊ የለንደን ክፍ ል የሚኖረው ሙሉጌታ ካህሳይን በህግ እፋረደዋለሁ እንዲህ አይነት ህገወጥ ሽብር ፈጠራ ፈጽሞ በቸልታ መታየት አይገባውም በማለት አበበ ገላው ተናገሯል። ግለሰቡ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባስተላለፈው አንድ መልእክት የሚከተለውን ተናግሯል፤ “ደምህን እነደምንጠጣው ልነግርህ ነው። በድጋሚ በአዲስ አበባ ቤት እንዳለህ ደረሰነበታል። እናቃጥለዋለን፣ ቤተሰቦችህን፣ አንተንም እነገድላችዃለን። ላደረከው ነገረ የሞት ቅጣት ይገባሃል፣ በርግጠኝንተ እነጨርሳሃለን። እመነኝ አንለቅህም። የፈለገ ያህል ግዜ ይውሰድ፣ አነተን ቤተሰብህን አንድ ባነድ እናድናችኻሃለን። ቤቶችህንም በቅርቡ እናጋያቸዋለን።” በሌላ መልእክት ደ ግሞ “እያንዳንዱን እርምጃህን እየተከታተልን ነው። አንተና ቤተሰብህን እናጠፋችሃልን።አንድ ቀን እነጨርስሃለን። የወሰደውን ግዜ ይወሰድ ደምህ በመንገድ ሲፈስ እናያለን። ወይ አንተ ወይ ቤተሰብህ መወገድ አለባችሁ።” በማለት ሽብርና ፍርሃት ለመፍጠር መሞከሩን ለማወቅ ተችሏል። አበበ ሙሉጌታ ካህሳይ ከብዙዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሶ ህወሃቶች በአገር ቤት የሚያደርሱትን ሽብር ፈጠራ በስደት በምንኖርበት የነጻነት ምድር ፈጽሞ ሊፈጽሙት አይገባም ለዚህም ህዝባችን በያለበት በህብረት መነሳት ይገባዋል በማለት ጥሪውን አቅርቦ የጉዳዩን ዝርዝር ከዚህ ዜና ጋር ከተለቀቀው ቪድዮ መረዳት ይቻላል በማለት አስረድቷል። ጋዜጠኛ አበበ ገላው ዛቻና ሽብር እኔንም ሆነ ለነጻነት የሚታገሉ ኢትዮጵያዊያንን ፈጽሞ እንደማያዘናጋ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች የሆኑት ህወሃቶች ሊረዱ ያስፈልጋል ብሏል። ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com February 3, 2012 ጋዜጠኛ አበበ ገላውንና ቤተሰቡን እንደሚገድል በተደጋጋሚ ሲዝት የነበረው በለንደን በታክሲ ነጂነት የሚተዳደረው የወያኔ ጀሌ ሙሉጊታ ካህሳይ
ቤተ-ክርስቲያን የማን ቤት ናት ? የማን ቤት ናት ? የማን ቤት ናት ? በላስ ቬጋስ ከተማ የምንኖር ህዝበ-ክርስቲያን ፤ በቅርቡ በቤተ-ክርስቲያናችን በደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካህናትና በሰበካ ጉባኤው ላይ በተደረገ ምርጫ ምክንያት ችግር ተፈጥሮ ነበር ። ችግሩን በመመካከር ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ለአመታት ካገለገሉበት ቤተ-ክርስቲያን የአሪዞና የዩህታና የኔቫዳ ሊቀ-ጳጳስን አቡነ ዮሴፍንና ካህናቱን ከስራ የሚያሰናብት ደብዳቤ ተልኮላቸው በቅርቡ ወደተገዛው ቤተ-ክርስቲያን ድርሽ እንዳይሉ ይነገራቸዋል ። ጉዳዩ እስከ ፖሊስ ድርሶ እስካሁን መፍትሄ ያላገኘ ጉዳይ ሆኗል ። እኔ ዛሬ ይህን መልእክት እንድፅፍ ያነሳሳኝ ማን በደለ ማን ተበደለ ለማለት አይደለም ። ምንንም ለመወንጀልም ሆነ ለመኮነን ፍላጎትም የለኝም ። ጳጳሱን አቡነ ዮሴፍን ጨምሮ ካህናቱ ወደቤተ ክርስቲያኒቱ እንዳይደርሱ ህጋዊ ደብዳቤ ከደረሳቸው በኋላ ፤ ለጊዜውም ቢሆን ምእመናኑን ለመሰብሰቢያ ተከራይተውት ከነበረው ቤተ- ክርስቲያን ድረስ ተሂዶ በሲኖዶስ የተወገዙ ናቸው አታከራዩአቸው በሚል ካህናቱ ቦታ አጥተው ምእመናኑን ባለፈው ሳምንት እሁድ በፓርክ ሰብስበውት ፀሎት ተደርጎ ተበትኖ ነበር ። በዚሁ እለት በፓርኩ የተገኘው ህዝበ- ክርስቲያን በሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የመምለኪያ ቦታ የሚያገኝበትን መንገድ ለመሻት ረቡዕ ፊብሩዋሪ 25 ቀን ቀጠሮ ይዞ ተለያዬ ። በቀጠሮው ቀን የተገናኙት ካህናትና ህዝቡ በዬራሳቸው ዝግጅት አድርገው ነበር የመጡት ። በእለቱ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ግብዣ የዲሲና ሜሪላንድና ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሳይታሰብ በቦታው መገኘት በህዝበ ክርስቲያኑ ላይ ተጨማሪ የደስታ ድባብ ዘረጋበት ። በመምህር ውብ አምላክ አስተናጋጅነት የተከፈተው የቀጠሮ ጉባኤ በብፁዕ አባታችን በአቡነ ሳሙኤል ፀሎት ከተከፈተ በኋላ የደብረ- ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ታቦት በሚቀጥለው ቀን እንደሚገባ ሲበሰር ወይዛዝርቱ በእልልታ ወንዱ በጭብጨባ መዘምራን በምስጋና መዝሙር አዳራሹን ሞሉት ። ይህን ብስራት የናኙልን ደግሞ የእለቱን ትምህርት “ቤተ-ክርስቲያን የማን ናት ?”†በሚል ርእስ የጀመሩት ድምፀ- ነጎድጓዱ ሊቀ-ህሩያን ቀሲስ መላኩ ባወቅ ነበሩ ። በትምህርታቸው ላይ የዚህች ቤተክርስቲያን አባልነታችሁ በአባልነት ፎርም ሳይሆን በጥምቀታችሁ ነው ሲሉ ህዝቡ በእኩልነትና በአንድነት መንፈስ የኢትዮጵያ ድርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን አባልነቱን አረጋገጡለት ። ክርስቲያኖች በተሰበሰቡበት ሁሉ የእግዚአብሂር መንፈስ ይኖራልና ፤ እዚህ ቤተ-ክርስቲያን እንዳትደርሱ የተባሉት ካህናት ህዝቡ በሰጣቸው ፍቅርና ሙቀት ፤ ባሳየቸው አንድነት ፊታቸው በደስታ ጸዳል ሲሞላና ስብራታቸው ሲጠገን እዚያው የነበርን ሁሉ ምስክሮች ሆንን ። ንብ ያለአውራው ባዶ እንደሆነ ሁሉ ፤ ህዝበ-ክርስቲያንም ያለ ካህናት ባዶ ነው ። ንብ በአውራው አማካይነት የመንጋውን ዘር ቋሚ የህይወት ቀጣይነት እንደሚያረጋግጥ ሁሉ ካህናትም የምእመናኑን መንፈሳዊ ህይወት ጠባቂዎች ናቸው ። በዚህ ወከባና ጩሀቱ በበዛበት አለም ካህናት የእግዚአብሄር እንደራሴዎች ናቸው ። እነዚህን የመንፈስ አባቶች ነው በሥጋዊው ህግ በብጥሽ ወረቀት ወደቤተ-ክርስቲያኒቱ እንዳይደርሱ የተወሰነባቸው ። የአምልኮት ተግባራችንን መፈፀም የሚያስችለን ካህናቱ ስርዓተ-ቅዳሴውን ሲመሩት ብቻ ነው ያለው ህዝበ-ክርስቲያን አውራዎቹን ይዞ በማምለኪያ ቦታ እጦት ለሳምንታት ተንከራተተ ። ብርድና ነፋሱ ሳያግዱት ምእመኑ ህጻናት ልጆቹን ይዞ በህዝባዊ ፓርክ ውስጥ የአንድ ሰንበት አምልኮ አደረገ ። ከላይ የጠቀስኳት የቀጠሮዋ ቀን ፌብሯሪ 25 በላስ ቬጋስ ኔቫዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ክርስትያናዊ ታሪክ ታላቅ ቀን ሆና የምትታሰብ ናት ። ምሽት ላይ በሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተ- ክርስቲያን አዳራሽ የተሰበሰበው ህዝብ ለላስ ቬጋስ አዲስ የሆነውን የደብረ-ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ታቦት በማግስቱ እንደሚገባ ብስራቱን ሲሰማ ፤ ታቦታችንማ በድህነት አይገባም ሲል ሁለት ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ $104 ሽህ 845 የአሜሪካን ዶላር በማዋጣት አከበረው ። ወንዱ የጣቱን የወርቅ ቀለበት ሴቷ የአንገቷን ሃብል እያወለቀች የታቦቱን ግባት ቀን በደስታ አከበርነው ። በማግስቱም ታቦቱ ሲገባ የዋዜማው በረከት ያልደረሳቸው ወንድሞችና እህቶች እኛስ ለምን ይቀርብናል በረከቱ ለኛም ለቤታችንም ይትረፍ በማለት ተጨማሪ $23 ሺህ በማዋጣት አዲሱን ታቦት ተቀበሉት ። ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ካደረጓቸው ንግግሮች ውስጥ አንድ የሩሲያ ሰው የትናገረው ነው በማለት እንዲህ ያሉት ይጠቀሳል ። “ሰው ገፍቶ ገፍቶ ከክርስቶስ እግር ስር ጣለኝ”†አዎ ይህን የተናገረው የሩሲያ ታዋቂ ደራሲ ደስተዮቭስኪ ነበር ። ደስቶዮቭስኪ በድርሰት ስራዎቹ ምክንያት ብዙ መከራ ደርሶበታል ። ከዚያም ፍርድ ቤት ቀርቦ የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል ። የፍርድ ቀኑ ደረሰችና የሞት ቅጣቱን ፈፃሚዎቹ የመስቀያውን ገመድ አንገቱ ውስጥ አስገቧት ። ሸምቀቆው እየጠበቀ እየጠበቀ ትንፋሹ እያጠረች ስትሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ የክርስቶስን ስም ጠርቶ እንዲያድነው ተማፀነ ። ወዲያው የመሰቀያው ክፍል በር ተከፈተና የሩሲያው ንጉስ መልክተኛ ፈጥኖ ገባ ። ከንጉሱ የተጻፈውንም መልእክት ከፍ አድርጎ አነበበው ። የሞት ቅጣቱ ተሽሮ በሩሲያው ንጉስ ምህረት ተደርጎልሃል የሚል ነበር ። ምሳሌው ለሁላችንም ግልፅ ነው ብዬ እገምታለሁ ። ህዝብ ያቀፈው ህዝብ የወደደው ዘለአለማዊ ነው ። በላስ ቬጋስ ላለፉት አስራ አራት አመታት የክህነት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ የነበሩት መልአከ-ብስራት ቆሞስ አባ ወልደየሱስም በተፈጠረው ሁኔታ ምክንያት ጨልሞ የነበረው ፈገግታቸው በምእመናኑ ፍቅርና ሙቀት እንደተመለሰላቸው ሊቀ-ሕሩያን ቀሲስ መላኩ ባወቅ ሲናገሩ ህዝቡ በእልልታ አዳራሹን ሞላው ። በመጨረሻም የብፁዕ ውቅዱስ አቡነ ዮሴፍን መልእክት እንዲህ ይላል ። የአገረ-ስብከቴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች ፤ ይህ ያከበራችሁት የደብረ ብስራት ቅዱስ ገብረኤል ታቦት የገባባት ቤተ-ክርስቲያን አባልነት በጥምቀታችሁ ብቻ ነው ። በተለያዩ ምክያቶች የአባልነት ክፍያ መክፈል ቢያቅታችሁ እንኳ በጥምቀት የክርስቶስ ልጆች ናችሁና አባልነት የሚከለክላችሁ የለም ። የአባልነት መታወቂያ ይኖራችኋል ። ዋናው በሃይማኖታችሁ መፅናት ነው ። ክርስቲያናዊ ፍቅራችሁና አንድነታችሁን እንዲሁም ፅናታችሁን ይህ ክፉ ቀን አሳይቶናልና አሁን እንዳላችሁት ሁሉ ሳትለያዩ ተፋቅራችሁ ተከባብራችሁ ኑሩ ። እኛ ለሚበድሉን ሁሉ እንፀልያለን ። ይህ ክርስትያናዊ የተሰጠን ግዴታችን ነው ። ከተለዩን ጋርም በአምላካችን ፈቃድ አንድ እንደምንሆን ተስፋየ ነው ብለዋል ። ከዚያም ይህች ቤተ-ክርስቲያን የምትተዳደረውም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ርዕሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ስር ባለው ሲኖዶስ መሆኑንም ገለፀዋል ። እንግዲህ ቤተ-ክርስቲያን የማናት ? የእግዚአብሄር ቤት ናት ። የናንተ ቤት ናት ፤ እናንተ በእምነታችሁ በተሰበሰባችሁበት ቤት ሁሉ የእግዚአብሄር መንፈስ አለ ፤ ካሉ በኋላ በዚህ በክፉ ቀን ሊያፅናኑን ከዋሽንግቶን ዲሲ ድረስ የመጡትን የዋሽንግተንና የሜሪላንድ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ፤ ከኔው ጋር መገፋቱ የደረሰባቸውን መላከ ብስራት ቆሞስ አባ ወልደየሱስን ፤ ከካሊፎርኒያ ድረስ ሊያበረታቱን የመጡትን ሊቀህሩያን ቀሲስ መላኩ ባወቅን ፤ ከኛ ቀድሞ የተገፋውን መምህር ውብ አምላክን ፤ ሁሌም ካጠገባችን ሳይለዩ አብረውን የቆሙትን ሊቀ- ጠበብት ዳኜ ፈረደን ፤ እኛማ ከአባቶቻችን አንለይም ሲሉ አብረውን የተንከራተቱትን ዲያቆናቱን በመጨረሻም ብርዱም ነፋሱም መንከራተቱም ሳያሸንፋችሁ አብራችሁኝ ለቆማችሁት ልጆቼ ፤ ከቅርብም ከሩቅም በስልክም ሆነ በኢሜል የማፅናኛ መልእክታችሁን ለላካችሁልን ሁሉ የእግዚአብሄር በረከት ቤተችሁን ይሙላ ፤ የኔም ምስጋና ይድረሳችሁ ፤ በፀሎቴም ሁሌ አስባችኋለሁ ፤ ብለዋል ። ከብስራተ-ገብርኤል ፡ ማርች 1 ቀን 2015 ። 

Friday, March 13, 2015

Ethiopia: Digital Attacks Intensify Spyware Firm Should Address Alleged Misuse
By Human Rights Watch
March 9, 2015


(New York, March 9, 2015) – The Ethiopian government has renewed efforts to silence independent voices abroad by using apparent foreign spyware, Human Rights Watch said today. The Ethiopian authorities should immediately cease digital attacks on journalists, while foreign surveillance technology sellers should investigate alleged abuses linked to their products. Independent researchers at the Toronto-based research center Citizen Lab on March 9, 2015, reported new attempts by Ethiopia to hack into computers and accounts of Ethiopian Satellite Television (ESAT) employees based in the United States. The attacks bear similarities to earlier attempts to target Ethiopian journalists outside Ethiopia dating back to December 2013. ESAT is an independent, diaspora-run television and radio station. “Ethiopia’s government has over the past year intensified its assault on media freedom by systematically trying to silence journalists,” said Cynthia Wong, senior Internet researcher at Human Rights Watch. “These digital attacks threaten journalists’ ability to protect the safety of their sources and to avoid retaliation.” The government has repressed independent media in Ethiopia ahead of the general elections scheduled for May, Human Rights Watch said. Many privately owned print publications heavily self-censor coverage of politically sensitive issues or have shut down. In the last year, at least 22 journalists, bloggers, and publishers have been criminally charged, at least six publications have closed amid a campaign of harassment, and many journalists have fled the country. Many Ethiopians turn to ESAT and other foreign stations to obtain news and analysis that is independent of the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front. However, intrusive surveillance of these news organizations undermines their ability to protect sources and further restricts the media environment ahead of the elections. Government authorities have repeatedly intimidated, harassed, and arbitrarily detained sources providing information to ESAT and other foreign stations. Citizen Lab’s analysis suggests the attacks were carried out with spyware called Remote Control System (RCS) sold by the Italian firm Hacking Team, which sells surveillance and hacking technology. This spyware was allegedly used in previous attempts to infect computers of ESAT employees in December 2013. If successfully installed on a target’s computer, the spyware would allow a government controlling the software access to activity on a computer or phone, including email, files, passwords typed into the device, contact lists, and audio and video from the device’s microphone and camera. Citizen Lab also found that the spyware used in the attacks against ESAT appeared to have been updated as recently as December 2014. On November 19, a security researcher, Claudio Guarnieri, along with several nongovernmental organizations, publicly released a tool called Detekt, which can be used to scan computers for Hacking Team RCS and other spyware. Citizen Lab’s testing determined that Detekt was able to successfully recognize the version of RCS used in a November attack, but not the version used in a December attack. Citizen Lab concluded that this may indicate that the software had been updated sometime between the two attempts. These new findings, if accurate, raise serious concerns that Hacking Team has not addressed evidence of abuse of its product by the Ethiopian government and may be continuing to facilitate that abuse through updates or other support, Human Rights Watch said. Hacking Team states that it sells exclusively to governments, particularly law enforcement and intelligence agencies. The firm told Human Rights Watch in 2014 that “we expect our clients to behave responsibly and within the law as it applies to them” and that the firm will suspend support for its technology if it believes the customer has used it “to facilitate gross human rights abuses” or “who refuse to agree to or comply with provisions in [the company’s] contracts that describe intended use of HT [Hacking Team] software.” Hacking Team has also stated that it has suspended support for their product in the past, in which case the “product soon becomes useless.” Media reports and research by independent human rights organizations in the past year have documented serious human rights violations by the Ethiopian government that at times have been facilitated by misuse of surveillance powers. Although spyware companies market their products as “lawful intercept” solutions used to fight serious crime or counterterrorism, the Ethiopian government has abused its counterterrorism laws to prosecute bloggers and journalists who merely report on public affairs or politically sensitive issues. Ethiopian laws that authorize surveillance do not adequately protect the right to privacy, due process, and other basic rights, and are inconsistent with international human rights requirements. Hacking Team previously told Human Rights Watch that “to maintain their confidentiality” the firm does not “confirm or deny the existence of any individual customer or their country location.” On February 25, 2015, Human Rights Watch wrote to the firm to ask whether it has investigated possible abuse of its products by the Ethiopian government to target independent media and hack into ESAT computers. In response, on March 6 a representative of the firm emailed Human Rights Watch that the company “take[s] precautions with every client to assure that they do not abuse our systems, and, we investigate when allegations of misuse arise” and that the firm is “attempting to understand the circumstances in this case.” The company also stated that “it can be quite difficult to get to actual facts particularly since we do not operate surveillance systems in the field for our clients.” Hacking Team raised unspecified questions about the evidence presented to identify the spyware used in these attacks. Human Rights Watch also asked the company whether contractual provisions to which governmental customers agree address governments’ obligations under international human rights law to protect the right to privacy, freedom of expression, and other human rights. In a separate March 7 response from the firm’s representative, Hacking Team told Human Rights Watch that the use of its technology is “governed by the laws of the countries of our clients,” and sales of its technology are regulated by the Italian Economics Ministry under the Wassenaar Arrangement, a multilateral export controls regime for dual-use technologies. The company stated that it relies “on the International community to enforce its standards for human rights protection.” The firm has not reported on what, if any, investigation was undertaken in response to the March 2014 Human Rights Watch report discussing how spyware that appeared to be Hacking Team’s RCS was used to target ESAT employees in 2013. In its March 7 response, the company told Human Rights Watch that it will “take appropriate action depending on what we can determine,” but they “do not report the results of our investigation to the press or other groups, because we consider this to be an internal business matter.” Without more disclosure of how Hacking Team has addressed potential abuses linked to its business, the strength of its human rights policy will be in question, Human Rights Watch said. Sellers of surveillance systems have a responsibility to respect human rights, which includes preventing, mitigating, and addressing abuses linked to its business operations, regardless of whether government customers adequately protect rights. “Hacking Team should publicly disclose what steps it has taken to avoid abuses of its product such as those alleged against the Ethiopian government,” Wong said. “The company protects the confidentiality of its customers, yet the Ethiopian government appears to use its spyware to compromise the privacy and security of journalists and their sources.”

Ethiomedia.com - An African-American news and views website. Copyright 2013 Ethiomedia.com. Email: editor@ethiomedia.com

Tedros Adhanom’s $20 million lie suffers fatal blow Scandal escalates as minister blames teenager
By Abebe Gellaw
March 9, 2015


Tedros Adhanom holding hands with the teen at the center of the $20 million fairy tale
Foreign Minister Tedros Adhanom’s scandalous bedtime fairy tale that he told to the people of Ethiopia on TV, radio and social media about an award-winning 14-year old schoolgirl that came all the way from Australia with 20 million dollars in her pocket to partner with the regime has suffered a final blow. Julie Mason, the principal of the Melbourne-based Baden Powell College, denied any involvement in the bizarre affair. It also emerged that the teenager, Beritu Jaleta Ahmed, was actually coached to lie on camera by the Minister, his PR team and advisers hours before her televised joint press conference with him, reliable ministry insiders told Addis Voice. The scandal-hit minister had declared on Facebook, radio and TV that Beritu won an “international prize” worth 20 million Australian dollars in school competitions for 8th grade students only to return home to partner with the regime to build a school in Gara Muleta, Eastern Ethiopia, a region well-known for its resistance against the oppressive rule of the TPLF. After the story was exposed as a blatant lie, the minister posted a Facebook message last Saturday that practically blamed the whole saga on the teenager despite the fact that there is ample evidence to show that she and her father were transported from Australia to Ethiopia at the expense of taxpayers to do the puzzling propaganda. The minister, his PR team led by Tewolde Mulugeta, the Ethiopian embassy in Australia as well as OPDO officials including the vice president of Oromia, Abdulaziz Mohammed, were involved in the ill-fated scheme, it emerged. School principal Ms. Mason told this reporter that she was as confused and mystified about the claims as everyone else. “We are quite mystified about it. So I have no more information. I have read what has been said in the media. I am just like everyone else. I am just grappling with it, just wondering,” she said. The principal confirmed that there was neither a competition of that nature nor such a prize to anyone. “I understand that is what she [the girl] said. But it has nothing to do with the school. They are on private family business. They are on family holiday in my understanding,” the principal said. “She [Beritu] said the Australian Government and Rotary gave her money. So I suggest you contact the Australian Government and Rotary Australia,” she added. Nonetheless, the Government of Australia and the Rotary Foundation have already denied knowing her or giving her any amount of money. Manager of Rotary International in Australia, Bruce Allen, pointed out that 1300 Rotary Clubs raised only $A 5.6 million dollars for the Rotary Foundation and its humanitarian projects last year let alone giving “an outrageous amount of money” to a 14-year old school girl. “It is totally out of question. There was no application or grant to this person,” he said.There is no way any Rotary Club in Australia could afford to pay that amount of money, according to the manager. The Government of Australia dismissed the claims on its part saying it does not even directly give funding for education to the Ethiopian government. “The Department of Foreign Affairs and Trade has not given 10 million Australian dollars to fund a school in Gara Muleta, Ethiopia. The Department of Foreign Affairs and Trade supports education in Ethiopia by providing core funding to the Global Partnership for Education. Ethiopia is a recipient of Global Partnership for Education funding,” said Jenna Hand, a media liaison officer at the department in a written statement sent to Addis Voice. The Embassy of Australia in Ethiopia also reiterated the same position and distanced Australia from the school project in Gara Muleta. Meanwhile, the Foreign Minister is taking hits on social media after he unabashedly blamed the teenager for the scandal and failed to take full responsibility for his questionable, wreckless and irresponsible behavior. “As you know, Beritu is a 14-year old teen. I think you would agree with me that kids have no malice. So I prefer believing what kids tell me. If trusting kids is a mistake, I prefer to err,” he wrote on Facebook and expressed hope that her dreams will come true despite the fact that there was already an agreement between TPLF and OPDO to build a school in the area. Some speculate that Bertu was brought in as a bait to divert the attention of Oromo youths and fleece the Ethiopian Diaspora. Numerous Facebookers criticized the Foreign Minister for failing to take full responsibility for dragging the teenager into disrepute for the sake of cheap and twisted propaganda. Some have said that his poor judgment, recklessness and lack of regret makes him unfit for his position as a foreign minister.” “I am 14 years old and I have been awarded $40 million. I want to donate it. I hope you believe me Dr. Can we have a picture with you and post it on FB?” a commenter mocked the minister. Many commenters vented their anger on the foreign minister and the TPLF-led regime, which they accused of being addicted to lies including jailing and torturing innocent citizens on trumped-up charges of terrorism. Many has pointed out that the teenager is a victim of the TPLF-led regime. Corruption the morals of a child is considered a criminal offense in Australia Baden Powell College, which was said to have organized the $20-million 8th grade student competition, is a government school with A$ 12 million annual budget. It has around 1800 students, 180 staff and 50 volunteers, it was learned.

Ethiomedia.com - An African-American news and views website. Copyright 2013 Ethiomedia.com. Email: editor@ethiomedia.com



1

ማስተርስ/ዶክተሬት እንደ መለዋወጫ እቃ!


ታሪኩ አባዳማ የካቲት 2007
ልጄ አስራ ሁለተኛ ክፍል ስለጨረሰ የደስታዬ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ… የሚል ግብዣ ደርሷችሁ አያውቅም? እናንተም ፋሽኮ ቪኖ ወይንም እናትና ልጅ አረቄ ይዛችሁ ድግሱን ለማድመቅ ሳትሄዱ አልቀራችሁም - የዚያን ዕለት ጎረምሶቹ የቀለጠ ፓርቲ ደግሰው እስኪነጋ ይጨፍራሉ አሉ… ይህስ ይሁን።

ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ላይ መሆኑን አንድም ቀን ሲናገር ሰምታችሁ የማታውቁት በቅርብ የምታውቁት ሰው ፣ እንዲያውም በመደበኛ ትምህርት ከስንተኛ ክፍል ነበር? አቋርጦ ወደ ሄደበት ሄዶ (ጫካ ወይንም ምርኮ) ግን የዛሬ ‘ሹም’ ‘የማስተርስ ፣ ዶክትሬት ዲግሬዬ በፖሰታ ስለደረሰኝ የደስታዬ ተካፋይ እንድትሆን ብሎ ቢጠራችሁስ? ይኼ ሰው ድሮ ትምህርት ቤት የተመዘገበበት ስም ሌላ ነበር… አሁን ደግሞ አዲስ ስም ብቻ ሳይሆን አዲስ ማዕረግ ፣ አዲስ ቤት ፣ አዲስ መኪና… ምኑ ቅጡ… ባናቱ ላይ ዲግሪ ሸምቶበታል።

ይድረስ ለተከበሩ… አስፈላጊውን ክፍያ ስላጠናቀቁ የ ማስተርስ ዲግሪዎን አያይዘን ልከናል – ለዶክተሬት ዲግሪዎ ተመልሰው እንደሚመጡ ተስፋ እናደርጋለን - የዋጋ ቅናሽም እናደርግሎታለን - ስለ ደንበኝነታችን ሲሉ አገልግሎታችንን ለስራ ባልደረቦችዎ እንዲያስተዋውቁልን ትብብሮን እንጠይቃለን – ለዚህም ተገቢውን ወሮታ እንከፍላለን - ያስታውሱ ‘ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ’ - ሴንቸሪ ዩንቨርሲቲ

ታዲያ እርሶም ለምርቃቱ ተጋብዘዋል - በተጠራው ድግስ ላይ ‘…ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትህን የት ነበር የጨረስከው ፣ ማትሪክ ውጤትህስ ስንት ነበር ፣ የመጀመሪያው ዲግሪህስ… ያጠናኸው ፣ የተመራመርከው እና መቸ ያዘጋጀኸው መመሪቂያ ቴሲስ ነው ለዚህ ያበቃህ?...’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ ወይስ ድግሱን ተቋድሳችሁ …እንኳን ለዚህ አበቃህ ብላችሁ መርቃችሁ ትመለሳላችሁ?

አነሳስቶ ላስጀመረን ፣ አስጀምሮ ላስጨረሰን ተብሎ ባደባባይ በግልፅ ሳይተያዩ ማስትሬት እና ፒኤችዲ እንደ መለዋወጫ እቃ ‘…ኦን ላይን ኦርደር…’ ማድረግ የወቅቱ የወያኔ ሹማምንት ልዩ መታወቂያ መሆኑን ስናይ ‘ኦ ዲግሪ ሆይ ከስምሽ ጀርባ ስንት ደደብ መሸገ’ እንድንል ያስገድደናል። ባንድ ጀምበር ሚሊየነር ፣ ባንድ ጀምበር ጄነራል እናም ባንድ ጀምበር ዶክተር እገሌ መባል ወያኔአዊ ተፈጥሮ ያመጣብን በሽታ ነው። እነኝህ ሰዎች በየመስኩ በሚፈጥሩት ስፍር ቁጥር የሌለው የተዛባና ህገ ወጥ አሰራር ጉዳቱ ውሎ አድሮ አገሪቱ ላይ በሁለንተናዊ መልኩ እየተንፀባረቀ መሆኑን ለመናገር የሚያስቸግር አይመሰለኝም። አዲሱ ሚሊየነር በሙስና እና ነጠቃ ላይ የተገነባ መሆኑ ፣ ጄነራሉ ችግር ሁሉ የሚፈታው በጠመንጃ ብቻ ነው ሲል የቁጩ ማስተርስ እና ዶክተርም የነሲብ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መፍትሔ ሲያረቅ ሲያማክር… እንዲያው ተያይዞ ገደል መግባት መሆኑ ቁልጭ ብሎ አይታያችሁም?

‘…ለኢህአዴግ ታማኝ እስከሆነ ድረስ ማይም እንኳ ሚኒስትር መሆን ይችላል…’ ያለው ማን ነበር? ሙት ወቃሽ እንዳልሆን ብዬ እንጂ ይኼ ድኩም ራዕይ የተሰነቀው ገና ከጠዋቱ እንደነበር አትዘንጉ ለማለት ነው። የአሳ ግማቱ ከወደ አናቱ!!

አንኳንስ ዶክተሬት ስምንተኛ ክፍል ሲጨርሱ ካባ ለብሶ ፎቶ መነሳት ፣ የምርቃት ቀን ደግሞ ሽክ ባለ ልብስ ፣ ባጌጠ አደራሽ ፣ ሞቅ ደመቅ ባለ ስነስርዓት ዘመኑን መቋጨት እዚህ በምእራቡ አለም ጭምር የተለመደ ነው። ከዩንቨርሲቲ ሲመረቁ ደግሞ ስርዓቱ ለየት ይላል - ይኼ ሁሉ የሚደረገው ግን አንድም ትምህርት በአግባቡ የተሰጠ ለመሆኑ ይፋዊ ማረጋገጫ ለመስጠት ሲሆን - ሽፍንፍን ፣ ድብቅብቅ ተመርቂያለሁ ማለት ባካዳሚው አለም ሆነ በህብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ መሆኑን ለማሳየት ጭምር ነው። ይህን ስል በወያኔ ተቋማት አደባባይ የተመረቀ ሁሉ ብቃቱ ተረጋግጧል ማለቴ አይደለም።

ወያኔ ሁሉንም ዘዴ እንደ አስፈላጊነቱ ይጠቀምበታል። ከገበያ መሸመት ያለባቸው ሹሞች በጀት ተይዞላቸዋል - በተጠረቡ ቤቶች ውለው አድረው ‘የሚመረቁ’ ደግሞ አሉ… ከሲቪል ኢንሲቲትዩት… ከዚህ ሰፈር ከዚያ ሰፈር ኮሌጅ… ከዚህ ከዚያ ህዝቦች ዩንቨርሲቲ… ኮብል ስቶን ጠራቢ ምሩቃን ከታማኝ የወያኔ ካድሬ ምሩቃን ጋር ተማክረው ስለጉዳዩ የበለጠ ሊነግሩን ይችላሉ።

በምዕራቡ የትምህርት አለም ግን ልጆቻችሁን አስተምረን እዚህ አድርሰናል ፣ አዘጋጅተናል ፤ ኑ ተረከቡን የሚል ጥሪ ለወላጆች ሲቀርብ - ወጣቶቹ ለመጪው የከፍተኛ ትምህርት ዘመን ወይንም ለላቀ ሀላፊነት መዘጋጀታቸውን ለማብሰር ብቻ ሳይሆን ጠንክረው በጥሩ ውጤት ያጠናቀቁትን በአርአያነት በአደባባይ በመሸለም ሌሎችም እንዲተጉ ለማበረታታት ጭምር ነው። ይህም የሚደረገው አለምክንያት አይደለም።

የትምህርት ደረጃ የማይዛነፍ ራሱን የቻለ እርከን ፣ አድማስ እና ጥልቀት አለው - በትምህርት ገበታ የተወሰነ አመታት ማሳለፍ በራሱ የተጠና ፣ የተወጠነ ግብአት ያለው መሆኑንም መረዳት አያዳግትም። እያንዳንዱ እርከን ከዕድሜና የአይምሮ መጎልመስ ጋር ተቀናጅቶ ፣ በጥንቃቄ ተመጥኖ እየተለካ ዕውቀት የመመገብ ዘዴ ተዘርግቷል - መደመር እና መቀነስ ብለው ሳይጀምሩ ፣ ረጅሙን የሂሳብ ጎዳና ሳይጓዙ ካልኩለስ ስሌት ውስጥ መግባት እንደማይቻል ሁሉ ወግ ያለው መደበኛ ትምህርት በተገቢው መንገድ ሳይታለፍ ባቋራጭ ማስተርስ እና ፒኤችዲ አገኘሁ ማለት ራስን ከማጃጃል አልፎ ጦሱ የት እየለሌ ነው።

የረባ ዕውቀት ሳይጨብጡ ድሀ አገርን ያህል ለመምራት መድፈር ፣ ‘ድህነትን ታሪክ እናደርጋለን’ ከሚል ባዶ መፈክር የዘለለ ፋይዳ የለውም - ውጤቱ ከባዶ ጣሳ ወደ ተቀደደ ጣሳ ውሀ አገላብጥኩ እንደ ማለት ያህል ነው። ይሄም ባዶ ያም ባዶ - ከባዶ ለባዶ!! Blank of blank ይሉታል ፈረንጆቹ።

በመጀመሪያ ዲግሪ ለመመረቅ አራት ዓመታት የሚፈጀው በሚሰጡት ኮርሶች የሚገኘው ዕውቀት ብቻውን ያን ያህል ዘመን ይፈጃል ተብሎ አይመስለኝም። ተማሪው አራት ዓመታት በዚያ የእውቀት ማዕከል ሲመላለስ ከመደበኛው ትምህርት ሌላ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣ አለም አቀፋዊ እና ቤተሰባዊ ልምድ እና እውቀት አጣምሮ በመቅሰም አይምሮውን ያጎለምሳል። ካንድ ደረጃ ወደሚቀጥለው ለመሻገር የትናንቱ ለዛሬው ፣ የዛሬው ለነገው የሚያወርሱት መሰረት እጅግ አስፈላጊ ናቸው። መደበኛ ትምህርት ወደ ስራ አለም ሲሰማሩ ሀላፊነትን በብቃት ለመወጣት የሚያስችል ስንቅ መደቆሻ አምባ ነው። በወጉ ሳይሰንቁ ሩቅ ለመጓዝ አይታሰብም ፣ በድፍረት የመጣው ይምጣ ብሎ መጓዝ ይቻል ይሆናል ውጤቱ ግን ባዶ መፈክር እያመረቱ ማደናገር ይሆናል - ከባዶ ጭንቅላት የሚመነጩ መፈክሮች መሬት ላይ ካለው ውነት ጋር የሚጣረሱ ለመሆናቸው ያለፉትን 23 ዓመታት ብቻ ማስተዋል ይበቃል - በቀን ሶስት ጊዜ ትበላለህ አይነት!!

ትምህርት እውቀት ነው ፣ እውቀት ደግሞ ሀይል ነው። የትምህርት ማዕረግ ሸምቶ ባልሰለጠኑበት ደረጃ እና ብቃት ሀላፊነት ላይ መቀመጥ ‘ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል’ እንዲሉ ፈታኙን የህብረተሰብ ሁለንተናዊ ችግሮች ለመጋፈጥ እና ለማቃለል ከቶውንም ማጠፊያው ይቸግራል። 2


ይህንነም በተጨባጭ እያየነው ነው - እቅድ ተነደፈ ተብሎ ወረቀት ላይ የሚለቀልቁት ቅዠት ከዕውቀት ማነስ የሚመነጭ መደናበር ነው። በየዘመኑ ማክተሚያ ‘እቅዳችን ያልተሳካው …’ 99 ሰበብ መደርደር።

በቅርቡ ይፋ ሆነው ባነበብናቸው የምርመራ ዘገባዎች እንደተገነዘብነው አገራችን ከቶውንም የዩንቨርሲቲ ደጃፍ መርገጥ ቀርቶ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወጉ ያላጠናቀቁ ባለስልጣናት የተሸከሙትን የሙያ ማረጋገጫ ምስክር ሰነድ እያየን ነው። ሳይማሩ የጠመጠሙ ዳውላ ሹማምንት እየበረከቱ መሆኑን በማስረጃ ተደግፎ የቀረበው ዘገባ አረጋግጧል። ይኼ ዜና አሳፋሪነቱ ድርጊቱን ለፈፀሙት ቱባ ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆን እነዚህን ታቅፎ ተመርኩዞ አገር እየገዛ ላለው የወያኔ ስርአት ጭምር ነው።

ወያኔ ግን ሀፍረት ያውቃል እንዴ?

ይችን አስተያየት ለመክተብ ያነሳሳኝ ዋና ምክንያት ድንቅ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ባቀረበው በዚህ ጥናታዊ ዘገባ ከተጋለጡት (ቅሌት ከተከናነቡት ብል ይሻላል) ግለሰቦች አንዱ አቶ ቆስጠንጢኖስን ባንድ አገጣሚ የማውቀው በመሆኑ ነው። ሰውዬውን ያገኘሁት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1971 - 72 አብረን ማዕከላዊ ብሎም ከርቸሌ በቆየንባቸው የእስር ዘመናት ነበር። ያንን የእስር ዘመን በሚመለከት በቃለ መጠይቅ የተናገረውንም ሰምቻለሁ… ቆስጤ ያው እንደ ጥንቱ ነው - ሲናገር ሳግ አያንቀውም - የሴንቸሪው ዶክተሬት በባህሪው ላይ ለውጥ አላመጣም።

በሰኔ ወር 1971 ዓም በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ደርግን የሚያሰጋ አንዳች ህቡዕ እንቅስቃሴ በደህንነት መስሪያ ቤት የተደረሰበት መሆኑ ይወራል። በዚህ እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል የተባሉ አስራ ዘጠኝ ያህል የጂጌሳ እና ሰንቀሌ እንጨት መሰንጠቂያ ወዛደሮች (በደን ልማት ባለስልጣን ስር የነበሩ ፋብሪካዎች ናቸው) የፋብሪካዎቹ ዋና ስራ አስኪያጅ አለማየሁ ዘውዴ እንዲሁም በሻሸመኔ እና አካባቢው በልዩ ልዩ መስክ የተሰማራን ግለሰቦች በአካባቢው የደርግ ተጠሪ ኮሎኔል አባተ መርሻ አዝማችነት ከያለንበት ታድነን ደቡብ ጦር ሰፈር በሚገኝ እስር ቤት ገባን። በማግስቱ በከፍተኛ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች አጀብ አዲስ አበባ ተጓጉዘን ማዕከላዊ እስር ቤት እንታጎራለን። የተከሰስንበት ጉዳይ መንግስትን በወታደራዊ ሀይል ለመገልበጥ ዝግጅት ማድረግ የሚል ነበር። ‘… ጦር መሳሪያ አከማችታችሁዋል ፣ ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዳችሁ ነው..’ ይላል የክሱ ቻርጅ። ከታሰርነው መካከል አንድም ወታደር የለም - እርግጥ ነው እሳት ከሌለ ጭስ የለም… እሳቱ ግን የነደደው ሌላ ሩቅ ሩቅ ሰፈር ነበር… ዝርዝሩ ወደ ሌላ ታሪክ ስለሚወስደን ለጊዜው እዘለዋለሁ።

ይህ በንዲህ እንዳለ አዲስ አበባ የደን ልማት ሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር ሀይሉ ዳኜ ተይዞ በኛ የክስ ሰነድ ተካተተ ፤ ብዙም ሳይቆይ ቀንደኛው ተጠርጣሪ ቆስጠንጢኖስ በረኼ ነው በሚል እሱም ተይዞ መጣ።

ቆስጤን በዝና እንጂ እስከዚያ ድረስ በአካል አላውቀውም ነበር… ደን ልማት ውስጥ ማለፊያ ስልጣን ያለው ሰው ሲሆን ተወዳጅ ተክለሰውነትም ነበረው… ረጋ ብሎ መናገር... ግን ሳያቋርጥ የመናገር ችሎታ አለው። ምንም ርዕስ ስጡት ቆስጤ እንደ ልዩ ባለሙያ ይተነትነዋል ፣ ያብራራዋል… ልዩ ተስጥኦ ነው። ታዲያ ከሚናገራቸው ነገሮች ውስጥ አብላጫው መጨበጫ መያዣ የሌለው ነገር ነበር… የቱ ውነት የቱ ውሸት መሆኑን እንኳ ለመለየት ይቸግራል። ያኔ እኔ ገና የ12ኛ ክፍል የህብረተሰብ ትምህርት ተማሪ ስለነበርኩ ቆስጤ የሚተነትነው የፊዚክስ ንድፈ ሀሳብ ሚስጥር ሆኖብኛል። በዚህ የተነሳ በጣም አደንቀዋለሁ - በብዙሀኑ እስረኛ ዘንድ በዚያን ዘመን ማዕከላዊ ከነበሩ ምሁራን እንደ አንዱ ይቆጠር ይከበርም ነበር።

አወይ ማዕከላዊ! እኛ በታሰርንበር ዘመን እስር ቤቱ ተጨናንቆ እና ገንፍሎ ከቤት ውጭ መተላለፊያው ላይ ሰሌን ዘርግተን መተኛት ነበረብን። ማዕከላዊ ስንገባ እነ ጋሼ አሰፋ ጫቦ በጨለማ ቤት እንደታሰሩ ነው ፣ እኔ የደረሰኝ ላይኛው ግቢ 8 ቁጥር ሲሆን ብዙ ሰዎችን የመተዋወቅ ዕድል አጋጥሞኛል። እዚህ አሜሪካ ባለፈው ዓመት ዋይት ሀውስ ተጋብዞ ከፕሬዘደንት ኦባማ ልዩ ክብር የተቸረው ሳይንቲስቱ ዶር ሰለሞን ቢልልኝ የ8 ቁጥር ባልደረባዬ እንደነበረም አስታውሳለሁ።

የቼዝ ጨዋታ ስልት አስተምሮ ለውድድር እንድሰለፍ ያበቃኝ ሙባረክ ሸሪፍ (የሸሪፍ ላውንደሪ ባለቤት ልጅ) ከዚያው ከ8 ቁጥር ነበር ሌሊት ሌላ ክፍል ታስረው ከነበሩ ጓዶቹ ጋር ተወስዶ የተረሸነው (ከብርሀነመስቀል ረዳ ጋር ከጫካ የተያዙ ወጣቶች ናቸው)። እስከዛሬ ድረስ በቤተሰብ ደረጃ ግነኙነታችን ተጠብቆ የሚገኝ የዚያን ጊዜ የ8 ቁጥር እስረኛ ባልደረባዬ በቀለ ተፈራ ዛሬ ከነቤተሰቡ ጀርመን አገር ይኖራል… አዲስ አበባ ታዋቂ ኮማሪቶች ፔጆ 504 ወርቅና ውድ ጌጣ ጌጥ እየሸመተ ሲያንቆጠቁጣቸው የነበረው የመንግስት እርሻ ልማት ሀላፊ የነበረውን በርሔ ተመልሶንስ ታስታውሱታላችሁ? እሱም 8 ቁጥር ነበር። ስንቱ ይነገራል።

አለም በቃኝ ሲወስዱን ደግሞ የልጅነት ጓደኛዬን የሽመልስ ኦላና ታናናሽ ወንድሞች ሀይለልዑል እና ዳኜ አገኘሁዋቸው። ሽመልስ ኦላና አምቦ አካባቢ በግፍ መገደሉ ሳይበቃ ደርግ መላ ቤተሰቡን ለረጅም ጊዜ በእስር አሰቃይቷል ፣ ቤት ንብረታቸውን ቀምቶ ባዶ አስቀርቷቸዋል። አባቱ አንጋፋው ኦቦ ኦላና ባቲ በወያኔ ዘምንም ቢሆን ከመንገላታታት አላመለጡም። አንዳንድ ቤተሰብ ላይ የወረደውን ግፍ ሲያስቡት ይዘገንናል።

ከርቸሌም ቢሆን በየቤቱ ከታጎረው እስረኛ ሌላ አለም በቃኝ ክልል ሜዳው ላይ የላስቲክ ጎጆ ቀይሶ የሚያድረው ቁጥሩ እጅግ ብዙ ነበር። የመጀመሪያ ቀን አዳሬን ያደረኩት የ8 ቁጥር ባልደረባዬ ከነበረው ከመሐመድ ኢዛም ጋር ሲሆን - (መቸም 8 ቁጥር ኖሮ መሀመድ ኢዛምን የሚዘነጋው ያለ አይመስለኝም)። ተናግሮ የሚያስቅ ፣ ፈገግታ ከፊቱ የማይለይ ፣ ጨርሶ እስር ቤት መሆኑን ለመዘንጋት እና ሌሎችም እንዲዘነጉ ለማድረግ የነበረው ተሰጥኦ የሚገርም ነው። የኮሜርስ ምሩቅ እና የባንክ ሰራተኛ ነበር - ታዲያ የዚያን ዕለት ሜዳ ላይ አነጣጥፈን ከመተኛታችን ዝናም መንጠባጠብ ይጀምራል - መጠለያ የሚሉት ነገር የለም ምክንያቱም ቤት ውስጥ የሚተኙት በሙሉ ተቆልፎባቸዋል - መሀል ላይ ያለው በረንዳ ለጠጠር መወርወሪያ የሚሆን ክፍተት አንኳን የለውም - እስረኛው እንደ ርስቱ የሚቆጥረው የመኝታ መደብ አጨናንቆታል። እናማ ከዝናም መሸሻ ቦታ የለም። መሐመድ ኢዛም ግን እንዲህ አለኝ ‘አይዞህ አትስጋ ዝናም በአስማት የማቆም ችሎታ አለኝ… ብቻ የሚሆነውን ጠብቅ’ ሲል በማይገባኝ ቋንቋ መለፍለፍ ጀመረ…. ውነትም አስገምግሞ የመጣው ዝናብ በመንጠባጠብ ቀስ በቀስ በረደ - እኛም አንቀላፋን። ሁዋላ ውጭ ከመተኛት የታደጉኝ የሸመልስ ወንድሞች ናቸው።

ብዙ ትዝታ ያተረፍንበት ዘመን። … ወደ ቆስጤ ልመልሳችሁ።

እንዳልኩት በዚህ ጉዳይ ላይ ለመፃፍ ያነሳሳኝ የቆስጤ ነገር ነው። ትምህርቱን ከአዲስ አበባ ዪንቨርሲቲ ያውም በአፄው ዘመን ያጠናቀቀ ማለፊያ ጭንቅላት የነበረው ቆስጤ ምን ሲያደርግ የዩንቨርሲቲ ደጃፍ ረግጠው ከማያውቁ እነ አባዱላ ገመዳ ተርታ የሚያስልፈው ድርጊት እንደ ፈፀመ ሳስበው ይገርመኛል? በውነቱ በፖለቲካ እምነቱ ከወያኔ ጎን ቢሰለፍ ፣ እሱም እንደነሱ የዘር ሐረግ መዝዞ ይህን እና ያንን ስልጣን ቢጨብጥ ለምን ይህን አደረክ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ላይሆን ይችላል - ሰልጣን በዘር መስፈርት እንደ ቆሎ በሚታደልበት ዘመን እሱም ከዚያ ሰልፍ ውስጥ መግባቱ ቢያስቆጭም ትምህርትን ያክል ታላቅ ነገር የዘረኞች ማላገጫ ሲደረግ ግን ለምን እሱ ራሱ ግንባር ቀደም አድራጊ ፈፃሚ ሆነ? ውሻ በቀደደው… 3


ቆስጤ ይበልጥ ትዝ የሚለኝ ከርቸሌ ወደኛ ክፍል ተዳብሎ መኖር ከጀመረ በሁዋላ የሆነው አጋጣሚ ነበር። ዘመኑ 1972 ወሩ ትዝ አይለኝም ለሆነ የእስልምና ብሔራዊ በአል ቀን ወህኒ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ጫት በይፋ እንዲገባ ይፈቀዳል - በዕለቱ ከውጭ በገባልን ጫት ምርቃና ሞቅ ደመቅ ያለ ውይይት ተከፍቶ ብዙም ሳይቆይ መድረኩ ለቆስጤ ይሰጠዋል። የንግግሩ ርዕስ ስለ ፊዚክስ የትምህርት መስክ ሲሆን በወቅቱ በመስኩ ስለተገኙ አዳዲስ ግኝቶች ምን ሊነግረን እንደሚችል ከቤቱ ጥያቄ ቀረበ። ቆስጤ ትንተናውን ጀመረ - ያኔ እኔ የ12ኛ ክፍል የሶሻል ሳይንስ ተማሪ ስለነበርኩ ስለፊዚክስ ብዙም ዝንባሌ አልነበረኝም። ይሁንና ቆስጤ ከሚሰጠው ትንታኔ በተለይ ስለ ህዋ ምርምር የተደረሰበትን ጭብጥ ሲያብራራ ሁላችንም ፈዘን በተመስጦ ‘በምርቃና’ መንፈስ እንከታተለው ነበር። አገላለፁ ቴክኒካል ተርም የሚበዛበት በመሆኑ ይመስለኛል አብዛኛው ነገር አልገባኝም - ሁላችንም ግን ባድናቆት ተከታትለነዋል። ያን ያህል ራሱን መግለፅ የሚችል ሰው ፣ የመጀመሪያ ዲግሪውን አንቱ ከተባለው የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ለፍቶ ደክሞ ያገኘ ሰው እንዴት መደበኛ ትምህርታቸውን በወጉ እንኳን ካላገባደዱት እነ አባዱላ ገመዳ ተራ ለመሰለፍ መረጠ? መልሱን በጨዋ ደንብ ሊሰጠን የሚችለው ቆስጤ ብቻ ነው።

ዛሬ አለም ያለበትን የቴክኖሎጂ ዕድገት ደረጃ ስናይ የሰውን ዘር ለዚህ ምጥቀት ያበቁ ሳይንቲስቶች በየዘመኑ ተጠበው በምርምር ባስገኙት ውጤት መሆኑ ግልፅ ነው። ከጥንት እስከ አሁን ደረጃ በደረጃ እየበለፀገ እየዳበረ ዕውቀት ይበልጥ እየረቀቅ ብሎም እያንዳንዱ መስክ ዳብሮ ልዩ የሙያ ዘርፍ መፍጠር አስፈላጊ የሆነበት ዘመን ላይ ነን። የስራ ክፍፍል ለብቃት መጎልበት አይነተኛ መሣሪያ እንደሆነ ሁሉ ካንድ የጠቅላላ ዕውቀት ዘርፍ ወደ ሰፔሸላይዜሽን ሽግግር የሚደረገው ያው ብቃትን ለማጎልበት ሲባል ነው። ይኼ ደግሞ በድህረ ምርቃ የትምህርት ዘርፍ ስልጠና እና ምርምር በማድረግ የሚጨበጥ ውጤት ነው። ታዲያ ከምድር ተነስቶ የድህረ ምረቃ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መሸመት ባጠቃላይ ባገሪቱ እና በተለይ በትምህርት ገበያ ዘንድ ያለውን ሚዛን ምን ያህል እንደሚያዛባው የሚጠፋው ማነው? ቆስጤ ኦን ላይን ኦርደር የተደረገ ዲግሪ መሸመት ትምህርትን በቁሙ ለመግደል ከተሰለፉ ማይማን ተርታ እንደሚያሰልፈው እንዴት ጠፋው?

አገርን ለመግደል የትምህርት ስርዓቱን መግደል ፣ የትምህርትን ብቃት ዋጋ ማሳጣት እና ስልጣንና ሀላፊነት ዘር መዝዞ ለተጠጋ ሆዳም ማስታቀፍ - ይኼ ነው ከወያኔ አንቀፅ 39 ያተረፍነው - ትምህርት እና በተግባር የተፈተነ የሙያ ብቃት ሳይሆን ከዚህ ከዚያ ዘር መምጣት… እናም ስለ ዲግሪው ሴንቸሪ ዩንቨርሲቲ ይጨነቅበት።

ዶክተሬት በፖሰታ ልኬልሀለሁ

የድሮ ስምህን ደልዠዋለሁ…. አጅሬ ዶክ…
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com



March 5, 2015

Thursday, March 12, 2015

1 ታሪክ መዛባቱ አያከራክር ንም! ለመሆኑ ማን ነው ያዛባው ? ዩሱፍ ያሲን (ኦስሎ) በቅርቡ ኤርትርያን የጎበኙት የኢሳት ጋዜጠኞች ከፕረዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ብዞዎቻችን እያነጋገረ ነው። እንደገና የሁለቱ ሃገራትና ሕዝቦች ዝምድናና የወደፊቱ እጣ ተጣማርነት በተለያዩ ሚዲያዎች መነጋገሪያ አጄንዳ እየሆነ እየመጣ ነው። ልክ እንደ በፊቱ እያወዛገበ ነው ማለቱ ሳይሻል አይቀረም። የኢሳት ጋዘጤኞቹ በኤርትራ ጉዞቸው ሌሎቹ ተጨማሪ ተልእኮዎች ነበሯቸው። እነሱንም አሳክተው ነው የተመለሱት።ዋናው ተልእኳቸው አድርገው የሄዱትን በኤርትራ በኩል የትጥቅ ትግል ላይ የተሰማሩትን ሃይሎችን ሁኔታ፣ ይዞታና እንቃስቃሴ በሰፊው ዳስሰው ለኢሳት ተመልካችና አድማጭ በተለየ፣ ለኢትዮጵያዊ በጥቅል በማሳወቅ ላይ ናቸው። የኤርትራ ሕዝብ አኗኗር ሁኔታም ተመልክተው በዲያስፖራ ለሚገኘው ሕዝባችን እያካፈሉ ናቸው። ከፕረዝዳንቱ በተጨማሪ ሌሎች የሃገሪቷ ባለሥልጣናትም ማነጋገራቸው ታውቆዋል።እነዚህን ርእሰ ጉዳዮች ሁሉ ይህ ጽሑፍ አይመለከታቸውም። ለጊዜው ትኩረቴ በፕረዝዳንቱ ቃለ ምልልስ ላይ ነው ። ከእሱም ውስጥ በተለይ ያነጣጠረው በታሪክ "መዛባቱ" ጉዳይ ላይ ነው። እንዲያውም ጠበብ አድርጎ ፕረዘዳንቱ የኤርትራና ኢትዮጵያ ሕዝቦች ትስስር አስመልክቶ የሰጡትን ረዥም ማብራሪያን ነው ቢባል ያስኬዳል። "ምዝንባዕ" የሚትለዋን የትግርኛ ቃል ብዙ ጊዜ ተደጋግማለች በፕረዘዳንቱ ኢንተርቪዩ ውስጥ።እንድያውም በእንግሊዘኛው የቃለ ምልልሱ ክፍልም "Distortion"አዝማችና ተዘውታሪ አባባላቸው ነበር።ትርጉሙ "መዛባት" ነው ወደ አማርኛ ሲመለስ። ማኛውም ተገንጥሎ አዲስና ነፃ ሃገር የመመሥረቱ ውጥን "የተለየ ማንነት ባለቤቶች ነን " ነው ሥርዎ መሠረቱና ውልደቱ። አዲስ ማንነት ለይታው ደግሞ አንዱን የማንነት መግለጫ መካድና ሌላውን ማንነት መገለጫ ወይም ዝምድና ማረጋገጥ ሂደት ነው ተብሏል።ተገንጠለው አዲስ ሃገር ለመመሥረት ከሚገነጠሉባት ሃገር የግድ ዝምድናም ሆነ ታሪካዊ ትስስር ፈፅሞ የለንም ማለት የተለመደ አካሄድ ነው። የኤርትራ ነፃነት ትግልም ከዚህ ያፈነገጠ ሂደት ከቶ ሊሆን አይችልም። በቅድሚያ የግድ ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ራሳቸውን "ነፃ ማውጣት" ነበረባቸው ማለት ይቀላል።ስለዚህ ለመዛባቱ ነበራዊ ምክንያቶች ነበሩ ለማለት ነው። "ብሔረተኛነት" በመሠረቱ የተለየ ማንነትን መገለጫዎችን ተንተርሶ የራስን መንግሥት የመቀለስ ኢድዮሎጂና እንቅስቃሴ ነው ቢባል እምብዛም ማጋነን የለበትም። የመገንጠል ጥያቄ አንግበው ለሚነሱ ወገኞች ይህ ሂደት ተፍጥሯዊ ነው።የተለመደ የነፃነት ፍለጋ ትግል አንዱ አካል ነው። ስለዚህ ታላቁ መዛባት ኤርትራ "በረዥም ታሪኳ ራሷን በቻለ ሕልውናዋ " ከጎሮቤት ኢትዮጵያ ጋር ምንም ዓይነት ትስስር ሳይኖራት የዘለቀች ሃገር ነበረበች ትረካ መሠረቱ ይህው ነው። ስለዚህ ትስስሩና ዝምድናው መካድ ነበረበትና ተካደ፣ ባጭሩ።ኢትዮጵያ የመጨረሻዪቱ የኤርትራ ቅኝ ገዢ ሃገር ነበረች ትረካ ቦታውን ተካ። በዚሁ ኤርትራ የቅኝ ገዢዎች ፍርርቆሽ ታሪክ መሠረ በቱርክ፣ በግብፅ፣በጣልያንና በእንግሊዝ ተራ በተራ ከተገዛች በኋላ የመጨረሻዪቱ የኤርትራ ቅኝ ገዢ ሃገር ኢትዮጵያ ነበረች ነው፡። የዛሬ አያድረገውና "ሓበሻነት" ሲያልፍ አይነካካንም ዓይነቱ ዓይኔን ግንባር ያድርገው ትረካውም ግልብ የዓረብ አሚሮችን ማሞኛ ማታልያ በዚህ ማዛባት ሥር ልጠቀስ የሚችል ታሳቢ ነው። ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊም ለሙዓመር አል -ጋዳፊ በትውልዱ የየመን ዓረብነት ዝምድናው ያረጋገጠው ይህንን ዱካ ተከትሎ ነው። የዛሬ አያደረገውና "ኮሌጅ ከመግባት ይልቅ ስምነት ሳዓት ከኢሳያስ ጋር ማሳለፉ ይበልጣል " ያለውም በዚያ ይፍ ይፍ በምያስብለው ፍቅራቸው ነበር። የኤርትራ ብሔረተኛው እንቅስቃሴ ኤርትራውያኑን ከኢትዮጵያዊ ማንነት ራሳቸው እንዲያገሉ ማድረግ ቀዳሚ ተግባሩ ነበር። "እኛ ኤርትራውያን እንጂ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ነው " የክርከሩ መነሻ።የራቢጣ እስላሚያው መሪው ሼክ ኢብራሂም ሡልጣን በ 1949 (እ.ኤ.አ) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መድረክ ላይ ከሰጡት ማብራሪያ አንስቶ የብሔረተኛው እንቅስቃሴ እንደርዳሪ ሃይሉ " እኛ ኤርትራዊያን፣ በረዥሙ ታሪካችን የኢትዮጵያ ታሪክ አካል ሆነን አናውቅም" ነው በየዓለም አቀፍ መድረክ ክርክሩና እሰጣ -አገባው ። በ 30 ዓመቱ የነፃነት ተጋድሎ ዘመን የተደረገው የርዮተዓለሙ ማጠንጠኛ ይህው ነበ። የብሔረተኛ እንቅስቃሴ ቀስ በቀስ ከዚያ በፊት ወደ እናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ጉያ እንመለሰ ብለው ለተ .መ.ድ.ጠያቂ ቡድን ከኢትዮጵያ መቀላቀል ፍላጎታቸውን ያረጋገጡትም ወገኖች ጭምር ለዚህ ዓላማ ከጎኑ ማሰለፍ ቻለ ማለት ነው።በመሠረቱ በዚህ ሂደት ብሔረተኛው እንስቃሴ ታሪክን ሁለት ጊዜ ነው ያዛባው።አንዴ በነፃነት ትግል ወቅት ሌላ ጊዜ ደግሞ ነፃነት እወጃ ማግሥት። በመጀመሪያው ጊዜ የነፃነት ትግሉን ሕጋዊነት ለማለባስ ተብሎ፣ ሌላው ጊዜ ደግሞ የአዲስቷ ሃገር ነፃ ሃገራዊ ሕልውናን ለማረጋገጥና የግድ አዲስ ሃገራዊ ማንነት ለማስረፅ ስሉ።ይህ በሃገሮች ግንጠላ ታሪክ ያልተለመደ አካሄድ አይደለምም፣ አልነበረምም። የታሪክ መዛባቶች መኖራቸው ከተቀበለን ዘንዳ ቀጣዩ ጥያቄ ለመሆኑ ማን ነው ? ታሪክን ያዛባው ነው የሚሆ ነው። እንዴት ? የትኛው ዓላማ ለማሳካት ? እንደ ወትሮው በርካታ ጥያቄዎች መግተልተላቸው አይቀሬ ነው።እውነት እነዚህ የታሪክ ማዛባቶች ናቸው በሁለቱ መንግሥታት ብሎም ሕዝቦች መሓል መልካም ጉርብትና ግንኙነት እንዳይኖር ዳንቃራ ሆነው አሁንም የሚያስቸግሩን? ላለመግባባቶቻቸን መሠረት የሆኑት ? እነሱን ከመንገዳችን አስወግደን ማለፊያ በይነ-መንግሥታት ትስስር እንዴትስ ነው የምንፈጥረው ?የኤርትራ ፕረዝዳንት ለምን በአማርኛ አልተናገሩም፣ ለምን ስለ አስተዳደጋቸው፣ ስለ ቤተ ሰብ ሁኔታቸው በሚገባ አልገለፁም ዓይነቱ ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ መዘፈቅ አይዳዳኝም።ግን ስለ ድርጅቶቹ ምስጢራዊነትና ስለ መሪዎቻችን ማንነት አደባባይ የማይወጡ መገለጫዎች እንደ አንድ የግርጌ ሕዳግ ጣል ማድረጉ አይከፋም።ወደ ጽሑፉ ማሳረጊያ ላይ እመለስበታለሁ። ባጭሩ ሲጠቃለል፣ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ትስስር ኖሯት አያውቅ ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ -ግዛት ነበረች ከትግራዊ ኢትዮጵያውን ጋርም ዝምድና የለንም ሓበሻም አይደለንም ፣ዓረብ እንጂ ብለው የሚያስተጋቡ መመሪያዎች በዚያን ጊዜ እንደ አንድ የትግል መሣሪያ የተወሰዱ ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያውያን ጋር የነበራቸው ትስስር የመካዱ ሥር የሚካተቱ ዋናዎቹ የብሔረተኛው ወገን ድርጊቶች ናቸው ለእኛ የታሪክ መዛቦች ሆነው የሚታዩት። ስለዚህ ክቡር ፕረዝዳንት! "ታሪክ መዛባቱ አያከራክረንም ! ነገር ግን አንድ ጥያቄ መልሱልን ለማለት ይሚንገደደው።ለመሆኑ ታሪክን ያዛባው ማን ነው ? እነዚህ በመሰሉ የሕዝቡን ማንነት "የሚያዛቡ መዛባቶችን" ሲገፋ የነበረው ማን ነው ?እነዚህ "ማንነት ያዛቡ " ታሪኮች ናቸው የሁለቱ ሕዝቦች ግንኙነትን "ያዛቡትም" አልፎ ተርፎ የመረዙት ከሚለው ግንዛቤ ነው አነሳሼ። እነዚህ አባባሎች ገባ ብለን እንመለከታቸው፣ እስቲ።ለዓረቦች ኢትዮጵያ እንደ ሃገር መጠሪያ ስሟ ሓበሻ ወይም አል -ሓበሻ ነው። ሌላ ትርጉም የለውም።ከታሪክ መዛግብት እንደምንረዳው፣ ከቅድመ እስልምና ጊዜ የነበራት ስያሜ ነው።አሁን በቅርቡ በወጣው ISIS የወደፊቱ ሙስሊማዊ ካሊፌት ካርታቸው ላይ ከሱዳን፣ ከሶማሊያና ኤርትራ ጋር ባንድ ላይ መድረ ሓብሻ (አርዳል- አልሓበሻ) በተሰኘው እንደ አንድ ትልቅ አድያም (ወላያ) ወይም ክፍፍል ነው የተከለለችው።በነፃነቱ ትግሉ ዘመን ዓረብ ሃገሮች "ሓበሾች ነን" ነገር ግን "ከሓበሻ ቅኝ ግዛትነት " ነፃ አውጡን ብለው እርዳታ መጠየቁ አስቸጋሪ እንደምሆንባቸው አያጠያይቅም።ግራአጋቢነቱም ያቺ በነፃነት አከባባር ዕለት ላይ ላቧ የተንጠፈጠፈ ከበሮ እየደለቅች ፃሓፊ ተስፋዬ ገብረአብ አገኝቷቸው ያን የመሰለ ፍንደቃቸው ምክንያት ሲጠይቋቸው "ከኢትዮጵያ" ነፃ የወጣንባት ዕለት በመሆኑ ነው" ያሉት የአሥመራ ወይዝሮ ታሪክ ያስታውሰኛል።ጋዘጤኛው "እናቴ! ስሞዎትን ማን ልበል" ብሎ ላከታተለው ጥያቄ ግን ምንም ሳያንገራግሩ ፈርጠም ብሎ "ኢትዮጵያ! ነዋ" በማለት የሰጡት መልሳቸው ፈገግ ከማድረጉ በላይ ነው "ቁጥርጥር" ያለው የአካባቢው የማንነት ግራአጋቢነት ገላጭ ነው።ይህ ዓይነቱ የማንነት ግብግብ ነው እንግዲህ ፕረዝዳንት ኢሳያስን ከሲዳማ ነፃ አውጪ መሪ ከነበሩት ከሟቹ ከወለደአማኔል ዱባሌ ጋር በኢትዮጵያ ታሪክና ዲሞክራሲ ጉዳይ በ 1986 በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ክፉኛ አፋጥጦ ግብግብ ያስገጠማቸው። ምስክርነቱን የሰጠው የኤርትራ ሕዝባዊ ሓርነት ግንባር (ኢ.ፒ.አል.አፍ) የቀድሞ ታጋይና የስለላ መረቡ የቀድሞ ተወካይ የነበረው የማነ ተክለጊዮርጊስ ነው። ባለታሪኩ በ 21 አውዲዮ-ካሴት በአሰና ራዲዩ በሰራጨው ረዥም የትግል ታሪኩና ስለ ፕረዝዳንት ኢሳያስ የሰጠው መግለጫ እምብዛም አውንታዊ ገፅታ የተላበሰ ባይሆንም ቅሉ "እኔ የምመለከተን የኢትዮጵያንና በሃገርቷ ዲሞክራሲ የማስፈን ጉዳያችን አይደለም ፣ የሲዳማ ነፃ ማውጣት እንጂ " የሚለውን የአቶ ወለደአማኔል ክርክር በብርቱ እንደመከቱ ይመሰክርላቸዋል። አቶ አኢሳያስ "ግንባራችን ኢትዮጵያን የማበታተን ዓላማ የለውም " በማለት ፈርጠም በማለት ነገሯቸው ይላል አቶ የማነ። እንዲያውም ቃል በቃል "ኢሳያስ ሊያብድ ነበር " ይላል (10 ኛው አውዲዮ ከደቂቃ 55፡16 ጀምሮ) የቀድሞ የስለላ ወኪልና የዚያን ጊዜ ግንባሩን ከኋላ የሚያሽከረክረው የሕቡዕ የኤርትራ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ አባል የምስክር ቃሉን ሲሰጥ። ስለዚህ ፕረዝዳንት ኢሳያስ "የትግራይ ነፃ ሪብፕሊክ ምሥረታን አልተቀበልንም " አባባላቸው፣ እኔም ለመቀበል አላንገራገርኩም። ፕረዝዳንት ኢሳያስ የሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ስብስቦች የራሳቸው መንግሥት ምሥረታ ውጥን የማይቀበሉበት ተጨማሪ ምክንያት እንደነበራቸው ልብ እንበል።ሁሉ ነፃ አውጪ ተብሎ ነፃ መንግሥታት ምሥረታ ትግል ካፋፋሙ የኤርትራ ጥያቄ ዋጋ ያሳጣዋል።ይራከሳል እንበል! ባልረቀቀ ቋንቋ። ያጉዳያቸው ልዩ ጥያቄና ከብሔራዊ ጥያቄዎች ጋር አለመመሳሳሉን አጠያያቂ ያደርግባቸው ነበር ፣በሌላ አባባል።ለወዲ አሥመራ የትግራዊ ሪብፓብሊክ ሆነ የሲዳማ መንግሥት ምሥረታ ፍላጎት " ከኤርትራውያኑ ጋር የመወዳደር ከማን አንሼ ማንጠራራት" ተደርጎ ቢወሰድ አይገርመኝም።ለመቀበል የሚያስቸግሩን የአቶ ኢሳያስም ሆነ የአቶ የማነ ትርክቶች ግን በርካታ ናቸው። ለምሳሌ የ 10 ዓመት የሽግግር ጊዜ ጠይቀን ነበር፤ ባንዱ ወይም በሌላው የመንግሥታዊ ቁርኚት እንጣምር ብለን ወያኔ እምቢ አለን ዓይነቱ አባባሎች ለማመን ያስቸግራሉ። የማንቀበለውና የማይዋጡን ለይተን በምክንያታዊነት እንጂ በጥላቻም ሆነ የሰሞነኛው ደርሶ የኤርትራ ትግልና የፕረዝዳንት ኢሳያስ አቱንኩብን ባይ ጥብቅናም ሆነ የፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝ አሥመራ ደርሶ -መልስ ተሞክሮ ምሬት ስሜታዊነት ቦታ ሊኖረው አይገባም። "አሰባሳቢ ማንነት ባንድ ሃገር ልጅነት " መጽሓፌ ውስጥም አልፎ አልፎ እነዚህ የማንነት አወሳሳቢ ታሳቢዎችን በመጠኑ ተዳስሰዋል።ለመጽሓፌ ማስታወቂያ እያደረግኩ አለመሆኔን ይታወቅልኝ ሓረግ መጨመር ልያስፈልግ ነው መሰለኝ !።ከዚህ በተጨማሪ ዓለምሰገድ ዓባይና የኖርዌይ ተወላጅ የሆነው ሸቲል ቱሮንቮል በኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ወቅት በሁለቱ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ማለት ትግራዊ ኢትዮጵያውና ትግርኛ ስብስብ ነኝ ባዩ ኤርትራዊ ብሔረሰብ መካከል በተለያዩ የትግሉ ወቅቶች የታዩትን የማንነት መለዋወጦች አጥንተው የምርምራቸው ውጤት አቅርበዋል ::የሁለቱም መጽሓፎቶች ርሶች በግርጌው መልክተዋል። ገና ገና ፕረዝዳንት ኢሳያስ ከዓረቦች ጋር ሳይገናኙ ፣ ዛሬ በሚያስገርም ሁኔታ የሚያቀላጥፉት ዓረብኛም ሳይማሩ ገና ገና ድሮ ለወታደራዊ ትምህርት ከታላኩበት ቻይና ሳይመለሱ እነ ዑስማን ሣሊሕ ሳቤ አይገቡ ገብተው በኤርትራ ዓራባዊ ማንነት የዓረብ አሚሮችና ርእሳነ መንግሥታት ድጋፍና እርዳታ ይሸምቱ ነበር። የሻዕቢያ ወታደራዊ ክንድ የፈረጠመውም በዚሁ ማቴሪያልና የገንዘብ እርዳታ አማካኝነት ነው ቢብላ እምብዛም ማጋነን የለበት።ይህ እንደ ተጠበቀ ሆኖ 25 ዓመታት ከነፃነት እወጃ በኋላም ኤርትራ እንደ ሃገር የዓረብ ሊጉ (ራቢጣው) ተመልካች አባል እንጂ ሙሉ አባል አልሆነችም።ሌለኛው የኤርትራ የማንነት ለይታ ያወሳሰበው ወገንተኛነት አሰላለፍ እንበለው! ቅኝ ተገዢዎች እንጂ ኢትዮጵያውያን አይደለንም፣ ጥያቄያችንም ቅኝ ግዛታዊ ነው ብቻ ሳይሆን ከእኛ ጋር አብሮ ለመታገል ይህንን የጥያቄያችን ባሕርይ መቀበል የግድ ነው ባዮች ነበሩ፣ የሻዕቢያ መሪዎች በዚያን ጊዜ። መለስ ዜናዊና የትግል ጓዶች ይህንን ተቀብለው ነው ድጋፍና ትብብር የተለገሳቸው። ይህንን መቀበል አሻፈረን ያሉትማ ድጋፍና ትብብር ተነፈጋቸው።ይባስ ተብሎ ወያኔና ሻዕቢያ ባንድ ላይ በመሆን ተዋጓቸውና ከትግል ሜዳ ውጭ አደረጓቸው። በዚህ ድግግፎች ሁለቱም ዓላማቸው ለማሳካት ስለበቁ ሁለቱም ተጠቃሚዎች ነበሩ። win-win situation ነው የሚትሉት! ይህ ብቻ አልነበረም።ከነፃነት በኋላም ባንድ ላይ የሚያጣምራቸው የጋራ አንገብጋቢ ግቦች ነበሯቸው። ሻዕቢያ በዓለም መድረክ ለአዲስቷ ሃገር ነፃነት የኢትዮጵያ መንግሥት እውቅና ማረጋገጥ ነበረበት።ሌላ ምክንያትም ነበረ።ከእነሱ ድርጅት ሌላ ማንም ኤርትራዊ ድርጅት እውቅና እንዳይሰጠው ፍላጎት ነበራቸው። 1991 ለአዲስ አበባው የሰኔ የሽግግር ኮንፊረንስ ኢሕአፓና የመኢሶን መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የኤ .አል፣ኤፍ አንጃዎች መሪዎችም ያልተጋበዙት እንበለ ምክንያት አልነበረም። ውያኔ / ኢሓዴአግ በሚግባ መሬት ሳይቆናጠጥ ከቀድሞ የትግል አጋሩ አለመግባባት መፍጠር አይፈልግም ነበር። እነዚህ ታሳቢዎች ብዙ የሚያነታርኩ ጉዳዮች አይመስሉኝም። እመለስበታለሁ ያልኩትን አደባባይ የማይወጡ የድርጅቶች መሪዎች ማንነት መገለጫዎች አልዘነጋሁም። ልከ እንደ ትናንቱ በአጼ ሃይለሥላሴ ዘመን የእናታቸው ስም (የሺእመቤት ዓሊ ጋንቾ ፈረዶ?) እንኳን በትክክል በይፋ ሊታወቅ ቀርቶ የሃገር ሕልውና -ነክ ምስጢር መስሎ ይታይ እንደ ነበረ የእናቱ ዘመዶች ሆኑ ፕረዝዳንት ኢሳያስ ራሳቸው ከትግራዊ ጋር የሚያቆራኛቸው የስጋ-ውልደት ዝምድና አሁንም የተጠቀሰ ነገር የለም።በተቃራኒው የሟቹ የመለስ ዜናዊ እናት ኤርትራዊነትና የሠራዬ አውርጃ ተወላጅነት ሃገር ያወቀው የአደባባይ ምስጢር ነው።አብራሃም ያየ የዛሬ ስንት ዓመት በፊት እሱ ከመረብ ሻገር ካለው ሠራዬ አውራጃ ብቻ ሳይሆን ከሦስቱ የኤርትራ ከበሳ ወይም ደጋ አውረጃዎች ከተለያዩ ግለሰቦች ጋር ያላቸው ጥልፍልፍ ያለ ማን ማን ቢወልድ የስጋና የደም ውህደት በግራፍ መሰል አገላለጽ በትግርኛ ከሽኖ አስነብቦናል።አባይ ስብሓትም ኤርትራዊ ቁርኚታቸውን አለደበቁም ወይም አላፈሩበትም ሊበል።በተቃራኒው የኤርትራ ቁንጮ ባለሥልጣናት መረብ -ሸገር ትውልድ ሓረግ እንደ መንግሥታዊ ብቻ ሳይሆነ እንደ አንድ የሃገር ሕልውና ምስጢር ዛሬም በአሥመራ በሽኩሽኩታ ነው የምወሳው።አይገርምም ! ይቺ ደግሞ ዓቢይ መነገገሪያ ጉዳይ ሆና ነው እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ።ግልፅነት የክፍት ሕብረተሰብ አንዱ መለያ መታወቂያ ነው። በዚህ አካባቢ የምንመለከተው የግራአጋቢው የማንነት ልውውጦች ማሳያም ጭምር ነው። በመጨረሻ ይህንን የሁለቱን ሕዝቦች ፣ እደግመዋለሁ ሁለቱን ሕዝቦች የወደፊት ትስስርና የሁለቱ መንግሥታት የወደፊቱ አዘቦታዊ በይነ -መንግሥታዊ ግንኙነት ያሰናከለው የታሪክ "መዛባት" ፕረዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ በቃለ ምልልሱ እንደሚያረጋግጡት እውነት የሚገባ የተሰነደ ታሪክ ከሆነ እዳው ገብስ ነው። "መዛባቱን" የማጥራቱ ቀዳሚው ተግባር ለተመራማሪ ፈታሽነት ለባለሙያዎቹ ማቀረብ ብቻ ነው ። መቼም እስካሁን የሰንዶቹ የምስጢራዊነት ይርጋ ዘመን ይገባደዳል በሚል ተስፋ በመሰነቅ ነው። እነዚህ ሰነዶች ለታሪክ ተመራማሪዎች ክፍት ማድረግ ነው።በዚህ ምርምር መንግሥት አወዳሽ ምሁራን ጎን ለጎን በሂስነታቸው የሚታወቁትን ፕሮፌሰር ተከሰተ ነጋሽ፣ ተስፋፅዮን መንግሥቱ የመሳሰሉ ምሁራን መጨመር ሊያስፈግ ይችላል። ውጤቱ ታማኣንነት እንዲላበሰ ከተፈለገ ማለቴ ነው። በሕዝቦች መካከል ዘላቂ ትስስር አለ። በሥልጣን በተደላደሉ መንግሥታት መካከል ግን ለትስስሩ መንስኤና መነሻ እስተረተጂካዊ ጥቅማጥሞች ናቸው ።በሁለት ድርጅቶች መካከል የነበረው በጋራ ጠላቶች ላይ የጋራ ክንዳቸውን በማሳረፍ ውለታ የመዋዋል ግንኙነት ተክቲካዊ ነበረ።ግንባሮቹም አይክዱም። ብዙ ውጣ ውረዶች ነበሩበት።ይህ ሓቅም አይክዱም።ከ 1975 ጀመሮ እስከ አሥመራና አዲስ አባባ በድል መግባቱ ድረስና ከዚያም በኋላም።የዚህ ፅሑፍ ዓላማ የሁለት ነፃ አውጪ ድርጅቶች ፀረ ደርግ ቃልኪዳና "እኔ ነኝ ውለታ የዋልኩልህ ፣ እኔ ነኝ እንጂ የዋልኩልህ" ገራንጃና እሰጣ-አገባ ለዚያኑ ጊዜው የጦር ኮማንዶሮቻቸው መተው ሳይሻል አይቀርም። እነሱ ይወዛገቡበት። በቅርቡ ሜጀር ጀነራል ፃድቃን የሰጠው እንተርቪዩን ይመለከታል።እኛ ጉዳያችን የወደፊቱ የሁለት ሕዝቦች ትስስር "ሊያዛባ የሚችለውን የታሪክ መዛባት" ነቅሶ ማውጠት ነው ብለናል። አሁንም የምናወሳው ስለ ሁለቱ ነፃ አውጪ ድርጅቶች ማለት ወያኔና ሻዕቢያ የጋራ ትግል ታሪክ፣ ትስስርና ውዝግብ እንጂ ሰማኒያ በላይ ስለ ሆኑት የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና ዘጠኙ የኤርትራ ማሕበረሰቦች ግንኙነትና ታሪክዊ ትስስር እንዳለሆነ መዘንጋት የለበትም።ገፋ ቢል ስለ ሁለ መረብ ዳርቻ ስላሉት ሁለቱ የትግርኛ ተናጋሪዎች ታሪክ መዛባት ነው።ተወደደም ተጠላም ወሳኝ ሚና ያላቸውም አሁንም በመረብ ወንዝ ዳርቻ ያሉት ትግራዊና ትግርኛ ስብስብ ትስስር ብቻ መሆኑን መሰመር ያለበት ሓቅ ነው።ይህም ሌሎቻችን መቀበል ያለብን መራራ ሓቅ ይመስለኛል።የታሪኩን መዛባት ለማስተካከል ብቻ ሳይሆን ዘላቂው ሰላምና መልካም ጉርብትናም ሆነ ማለፊያ የወደፊት ቁርኚት ወሳኙ የሁለቱ ማለፊያ ግንኙነት መሆኑ ላንድ አፍታም መዘንጋት ያለበት አይመስለኝም። እነዚያ ኤርትራን ተራ በተራ በቅኝ ግዛትነት ተፈራረቁባት የተባሉት ቱርኮች፣ ግብፆች፣ ጣልያኖችና እንግሊዞች ጓዛቸውን ሸክፈው በመጡበት እግር ወደ ሃገሮቻቸው ተመልሰዋል። እድሜ "አልዛባ" ላለው ጆዮግራፊ "የመጨረሻ ቅኝ ገዢዎቹ " ግን እንደ ጥንቱ በነበሩበት አሁንም እንደ ጎሮቤት አሉ።የትም አልሄዱም። የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች ትስስር መሠረቱ እዚያ ላይ ነው። ባንዱ ወይም በሌላው የመንግሥታት ተጣማሪነት ባይገናኙም ቢያንስ ጎን ለጎን በጉርብትና መኖሩ እጣ ፋንታቸው ሆኖዋል።ከሁሉ በላይ ያለፈውን ታሪክ ብቻ ሳይሆን መጪው እጣ ፋንታቸው የተቆራኘው።መንግሥታትም ድርጅቶችም ጠፊዎች ናቸውና።ሃገሮችና ሕዝቦች ይኖራሉ።በጉርብትና ይኖራሉ።ጎን ለጎን ባንድ ሃገር ጥላ ሥር ወይም በሁለት ራሳቸውን በቻሉ ሃገራት ዜግነት።ኤርትራ በትግል ነፃነት መቀጀት ቻለች።ወያኔ ኢትዮጵያን መቆጣጠር ቻለ።እንኳን በኢትዮጵያና በኤርትራ ሕዝቦች መሓል ሰላም ሊያሰፍኑ ቀርተው በድርጅቶቻቸው ውስጥ መረጋጋት መፍጠር አልቻሉም። ሁለቱ ድርጅቶች ቢታረቁም ቢጠፋፉም የሕዝቦቻችን እጣ-ፋንታ ተጣማርነት ከእይታችን መራቅ የለበትም።ከጊዜያዊ ድሎች ባሻገር አሻግረን እንመልከት! ጉዳዩን ጠለቅ ብላችሁ መመልከት ለምትሹት ተጨማሪ ንባብ፣ ዩሱፍ ያሲን ፣ የትግርኛ ተናጋሪዎቹ ቋሚና ተለዋዋጩ የማንነት መግለጫዎች - ሁለቱን ሕዝቦች በማቀራረቡ የሚኖራቸው ሚና፣ በሳን ሆዜ የኢትዮጵያና ኤርትራ ወዳጅነት ኮንፊረንስ ማርች 2010 ዩሱፍ ያሲን ፣ አሰባሳቢ ማንነት ፣ ባንድ ሃገር ልጅነት ኤሶፕ አሳታሚ 2014 ሓሰን ዑመር ዓብዳል፣ኢትዮጵያና ኤርትራ፣ ያልተጠናቀቀ ፍቺ፣ ያልተቻለ ጉርብትና፣ ታህሣስ 1991 ጦቢያ መጽሔት Hassan Umer Abdalla,Ethiopia & Eritrea: Let's get the facts clear 2009 (http://www.ethiomedia.com/adroit/2560.html) Abbay, Alemseged, Identity Jilted or Re-imagening Identity? The Different Paths of the Ertitrean and Tigrayan Nationalistic Struggles, Red Sea Press, 1998 Tronvoll, Kjetil, War & Politics of Identity in Ethiopia, Making of Enemies & Allies in the Horn of Africa, 2009 

Thursday, March 5, 2015

Top Ten Reasons Why Afan Oromo Should Be the Federal Working Language in Ethiopia

  • TopTenReasons2015_2


  • Here are the top ten reasons why:
    1. Demographic reasons: Afan Oromo, the language of the Oromo people, is the single most widely
     spoken language in Ethiopia and the fourth largest African language in terms of the number and size
     of speakers. It is spoken in at least three countries outside Ethiopia. Although statistical data may vary,
     about 50% of the Ethiopian population is estimated to speak Afan Oromo. In comparison, only about
    29.1% of the entire population of Ethiopia speaks Amharic, the legally imposed Official Language of
     the Federal Government, and the two largest cities of Dire Dawa and Addis Ababa. Given this
     demographic weight, it is unjust, undemocratic, and discriminatory, to say the least, not to use the
     language of the majority of the people as the Working Language of this multinational and multilingual
    country.
    2. Geographic reasons: All of the segregationist entities, including the Federal Government, the Addis
     Ababa City Administration and the Dire Dawa City Administration, are based in and hosted in the Afan
    Oromo-speaking State of Oromia. Yet, due to the discriminatory and exclusionary Amharic only
     language policy, the federal government institutions and these two large cities do not speak the
    language of the host people and the host state. These entities, which feel like occupying forces rather
     than governing forces, cannot continue as an Amharic-speaking island in the middle of the sea of
     Afan Oromo-speaking population while fully relying on the resources of the Oromo people for their
     existence, including food, water, electricity, ports, waste disposals and roads – at a very high human,
     financial and environmental costs to the Oromo people and the State of Oromia.
    3. Unity of the country as a reason: The exclusionary Amharic-only language policy is the antithesis
     of the multilingual and multicultural nature of Ethiopia. The Ethiopian Federal Government and the two
    segregationist cities under its administration have an urgent civic duty, if they care, to abolish this
     divisive and dangerous policy that undermines the equality, mutual respect and peaceful coexistence
     of the people. Ethiopia cannot continue as a united whole with its current segregationist policy – which
     benefits one segment of the population while fully excluding the other segment of the population.
    4. Economic and job opportunities. This segregationist and exclusionary Amharic-only language
    policy of the federal government and the two largest cities (Addis Ababa and Dire Dawa) have fully
    and completely excluded Afan Oromo speakers from all federal, municipal, corporate, and private jobs
     as well as all economic and business opportunities, including the right to do business and live in these
     jurisdictions unless one speaks Amharic. All employees of the Federal Government and these two
    largest cities are 100% Amharic speakers. Less than 10% of ethnic Oromos, who have been
     assimilated into Amharic-speakers, are presently employed both by the federal government
    institutions and by these two segregationist cities. Even worse, none of the federal government offices
    and offices of these two cities, including hospitals, businesses and all other service providers, provide
     translation services for Afan Oromo-speaking customers and users. Yet, Afan Oromo speakers and
    their State, Oromia, is the economic backbone and major sources of exports and tax-revenues for the
    Federal Government and the two segregationist cities.
    5. Representational reasons: The Ethiopian Federal Government institutions and its bureaucracies,
     and the two major cities of Addis Ababa and Dire Dawa, have legally excluded Afan Oromo speakers
     by adopting Amharic as their only Working Language. Under this condition, it is very hard to either say
    Afan Oromo speakers are represented in the Federal Government and these two cities, or to say that
     the Federal Government and these two cities represent the Afan Oromo speakers. The ruthless
    Amharic-speaking ethnic Oromo political appointees the government and these two cities flag as
    representatives of the Afan Oromo speakers are outlaws who don’t even represent themselves.
    Even the percentage of the assimilated, i.e. culturally and linguistically disconnected, ethnic
     Oromos employees in Ethiopian federal institutions, and the institutions of these two major cities,
    as a whole is less than 10%. This is in a country where the Oromo people constitute more than 40%
    of the total population.
    6. Legitimacy reasons: The government that does not speak the language of the people it claims to
     govern neither it does speak for that people nor it does legitimately represent the interests of that
    people. For the Ethiopian government to be considered a legitimate representative of the Afan Oromo-
    speaking population, it must speak Afan Oromo and be the representatives of the interests of the
    Afan Oromo speakers at all levels of its institutions, not just in nominal political appointee positions
    and portfolios.
    7. Justice, Equality, Equity and Fairness reasons: Justice, equality, equity and fairness demand
    equal opportunity and equal treatment of Afan Oromo speakers on the same basis as the Amharic-
    speaking segment of the population. The Amharic-only language policy of the federal government and
    the two segregationist cities have completely left the Afan Oromo-speaking population outside all
    economic, social, religious and educational institutional frameworks – creating a country where close
     to half of its population lives in subhuman situations, without any single institution of their own.
     The Ethiopian Federal Government and these two largest cities must not only immediately abolish
     this unjust, discriminatory and apartheid language policy, but also invest financial and human
    resources to create Afan Oromo economic, religious, cultural and educational institutions; and adopt
     economic empowerment policies that will remedy and address the historical injustice Afan Oromo
    speakers had passed through and are passing through right now.
    8. Multilingualism to create bond among various nations and nationalities: The Amharic-only policy
    – that was intended to assimilate over 80% of the Ethiopian population into the Amharic-speaking few
    or exclude them from the political, economic, religious, and social structure and institutional fabrics of
    the Ethiopian state – has created a very racist and hateful group which does not accept and respect
     the equality of various nations, nationalities, languages, and various ethnic identities. This dangerous
    policy has now lent legitimacy to the development of racist and hate groups which claim to struggle
    for the ‘unity of Ethiopia in the name of this Amharic-only language policy’ to openly discriminate,
    propagate hatred towards non-Amharic speakers, and even issue racist political manifestos in a
     way that will destroy the social bond among various nations and nationalities of Ethiopia. The main
     targets of these hate and racist groups – which have been incubated and developed through this
    Amharic-only racist and bigotry policy – are the Afan Oromo-speaking population of Ethiopia.
    9. One language and one ethnic hegemony policies will kill Ethiopia: Diverse and pluralistic
     Ethiopia can only stand on the acceptance of the policy of unity through diversity. The two most
     important challenges that work against this most important policy presumption to keep diverse and
    united Ethiopia are the effort to create one ethnic hegemonic country and the Amharic-only language
    policies. These are two equally cancerous and terminal policies that will kill Ethiopia. Ethiopia will only
     continue to exist on the multinational and multilingual federal structure – where mutual respect and
    peaceful coexistence of its multiple nations and nationalities are protected and respected by
    institutionalizing constitutional system of governance where fair economic power- and political
     power-sharing mechanism are legally established. Making Afan Oromo the Working Language
    of the federal government and the two largest cities will open the door to save this sick and disabled
     country that now operates with less than one third of its potentials.
    10. Language as a core factor in Human Development: The only means and avenue through
    which any human society could produce, develop, exchange and disseminate knowledge and
     information for self-actualization, economic and social development is language. The Ethiopian
    Federal Government and the two segregationist cities of Addis Ababa and Dire Dawa have denied
    the Afan Oromo-speaking population of Ethiopia this fundamental, inalienable and basic right through
     their Amharic-only policy. No wonder Ethiopia is the tail of the world and at the very bottom in the
     Human Development Index of the United Nations.
    As a conscientious member of the Afan Oromo- speaking society, and because of the above listed
     reasons and so many others, I call upon the Ethiopian government to immediately and unconditionally
    abolish the Amharic-only language policy and make Afan Oromo the Working Language of the
     Ethiopian Federal Government and the two largest cities of Addis Ababa and Dire Dawa.
    Birhanemeskel Abebe Segni is an Attorney & Counselor at Law, and a former Legal Affairs Advisor 
    in the Permanent Mission of Ethiopia to the United Nations.