Monday, August 24, 2015



1

የፕሬዝደንት ኦባማ "ታሪካዊ ጉብኝት"


አምባገነን አወዳሽ ወይንስ ዲሞክራሲ አጎልማሽ?

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

የዚህ ሃተታ ዓላማ የፕሬዝደንት ኦባማን ጉብኝት አግባብና ሚዛናዊ ባለው መንገድ ተንትኖ አሉታዊና አወንታዊ ገጽታወቹን ለአማርኛ ተናጋሪዎች ለማቅረብ፤ የወደፊቱ የኢትዮጱያ ህልውና አስተማማኝ ሆኖ፤ የሰብአዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት መከበር አለባቸውና የዲሞክራሳዊ አገዛዝ ምስረታ ሂደቶች ሕዝብን ማእከል ማድረግ አለባቸው የሚለው ብሂል ያገባናል የሚሉ ክፍሎች፤ ፈቃደኛነት ካላቸው፤ በጋራና በተናጠል ሊሰሯቸው የሚችሉትን የተወሰኑ መንደርደሪያ ሃሳቦች ለማቅረብ ነው። ባለፈው ሳምንት በድህረ ገጾች ላይ የተሰራጨው ተመሳሳይ ትችት ሆነ ተብሎ ለእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች፤ በተለይ ለአሜሪካ ሕዝብ ቀርቧል፤ ብዙ ጠቃሚና የተለመደው "ለምን ይኼ ተባለ፤ ለምን ይኼ አልተባለም" የሚሉ ትችቶች ተሰራጭተዋል። ሁለቱንም አስተናግዳለሁ።

ፕሬዝደንት ኦባማ የጋበዛቸውን ተባባሪ መንግሥት ላለማስቀየም ሲሉ ዲፕሎማሲ በሚጠይቀው መሰረት የኢትዮጵያ መንግሥት "ዲሞክራሳዊ በሆነ ሂደት የተመረጠ ነው" ያሉት የተሳሳተና ከሃቁ የራቀ መሆኑ አያከራክርም። ይኼ ብዙ ትችት የቀረበበት፤ የሳቸውን ዝናና ታሪክ የበከለ አነጋገር እንዳለ ሆኖ፤ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ህወሓት) በበላይነትና በብቸኛነት የሚያሽከረክረው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ፤ ዲሞክራሳዊ ግንባር (ኢህአዴግ) አፋኝ፤ ጨቋኝ፤ ጎሰኛና ሙሰኛ አገዛዝ በማያሻማ ደረጃ ተጋልጧል። የፖለቲካ ተቃዋሚዎች፤ ጋዤጠኞች፤ ምሁራን፤ የሰብአዊ መብቶች ደጋፊ ድርጅቶችና ሌሎች በተደጋጋሚ ያቀረቡትን የመጥፎ አገዛዝ ትችት እሳቸው በማንዴላ አዳራሽ በዝርዝር አቅርበውታል። ለመሰረተ ልማት ትኩረት የሰጠው፤ በውጭ እርዳታ ግብዓቶች ድጋፍ እንቅስቃሴ ያሳየው እድገት ዘላቂነትና ፍትሃዊነት እንዲኖረው ከተፈለገ አምባገነኑ አገዛዝ በዲሞክራሳዊ አገዛዝ መለወጥ እንዳለበት ተናግረዋል።

በዓለም ታዋቂ የሆኑ የልማት ልሂቃን--ጆሴፍ ስቲግሊትዝ፤ አማሪታ ሴን፤ ዊሊያም ኢስተርሊ፤ ሞሃመድ ዩኑስ ወዘተ-- የሚጋሩትና እኔም ሙሉ በሙሉ የማምንበት አንድ መሪ ፅንሰ ሃሳብ አለ። ይኼውም ጥሩ፤ አሳታፊ፤ የሕዝብ ተወካይነት ያለው ወይንም ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ለዘላቂና ፍትሃዊ እድገት ወሳኝ መሆኑን ነው። የዚህ አይነት አገዛዝ የተራውን ሕዝብ ኑሮ ከማሻሻሉ በላይ ለሽብርተኞችና ሌሎች አመፀኞች በር አይከፍትም፤ መሸሸጊያ አይፈጥርም። በተጻራሪው፤ ተመሳሳይ ባይሆኑም፤ በግብፅ፤ በሊቢያ፤ በሶሪያ፤ በኢራክ፤ በየመን፤ በአፍጋኒስታን፤ በሶማሊያ፤ በደቡብና ሰሜን ሱዳን፤ በኢትዮጵያ ወዘተ እንደሚታየው በጭካኔ፤ በአፈና፤ በጎሰኛንትና በሙሰኛነት የተበከለ አገዛዝ የእርስ በእርስ ግጭቶች፤ የሃገር መፈራረስ፤ የዘር ወይንም የኃይማኖት ማጥፋት፤ የጥላቻ፤ የቂመኛነት፤ የአመፀኛነት፤ የሽብርተኛነትና የፀረ-እርጋታነት ወዘተ በሮች ከፋች ነው። ሶሪያን ያየ ይፍረድ። እነዚህ ክስተቶች እየተባባሱ ሲሄዱ ምንም አይነት ክትትል፤ ስለላና ኃይል ሊገታቸው እንደማይችል በግብጽና ሌሎች ሃገሮች አይተናል።
በዓለም ብቸኛውና ታላቅ የሆነው የአሜሪካ መንግሥት ጨቋኝና ሙሰኛ መንግሥታት እድሚያቸው አጭር መሆኑን ያውቃል። ሆኖም፤ አምባገነኖችና ሙሰኞች የአሜሪካን ወቅታዊ ጥቅም እስካገለገሉ ወይንም እስካለተጻረሩ ድረስ የአሜሪካ መንግሥት የሚሰጣቸውን ድጋፍ የነፈገበት ወይንም የከለከለበት ሁኔታ የተወሰነ ነው። አሜሪካ "ለአሜሪካ ጥቅም እንጅ ለራሷም እሴቶች ደንታ የላትም" የሚሉ ብዙ የውጭ ሃገር ምሁራንና ተቋሞች አሉ። ለምሳሌ እስቲግሊትዝ። ይኼ እውነት ቢሆንም፤ ሌሎች ሃገሮችም በመጀመሪያ የሚያስተናግዱት የራሳቸውን ጥቅም መሆኑን መዘንጋት አንችልም። ቻይና ምሳሌ ናት፤ ሕንድ ምሳሌ ናት፤ ሳውዲ አረቢያ ምሳሌ ናት፤ ግብጽ ምሳሌ ናት ወዘተ። ቁም 2


ነገሩ፤ አሜሪካን የሚያሰጋት አፋኝ፤ አምባገነን፤ አግላይ፤ ጎሰኛና ሙሰኛ የሆኑ መንግሥታትን መርዳት አስተማማኝ አለመሆኑ ነው። የሙባረክ መንግሥት አምባገነና ሙሰኛ ስለነበረ በሕዝብ አመጽ ወደቀ። የቱኒዢያም እንደዚሁ። ብዙ ምሳሌዎች ለመጥቀስ ይቻላል። ስለሆነም፤ ለአሜሪካ ዘላቂ ጥቅም አስተማማኝ የሚሆነው፤ አምባገነኑን አገዛዝ ማወደስ ሳይሆን፤ የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም፤ ብሄራዊ ክብር፤ አንድነት፤ ሉዓላዊነት፤ የሕዝብ እኩልነት የሚያስከብር፤ ተወዳዳሪ የሆነ አገር በቀል የግል ኢኮኖሚ የሚፈጥር፤ በሕግ የበላይነት የሚያምንና የሚገዛ፤ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያገናኝና የሚያስማማ፤ ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብርና የሚያስከብር፤ እውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲመሰረት የፖለቲካውንና የማህበረሰቡን ምህዳር ሙሉ በሙሉ የሚከፍት መንግሥትና ተቋማት ሲኖሩ ነው። በማንኛውም መስፈርት ሲታይ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ የጎሳ ልሂቃን ስብስቦች የተመሰረተ አምባገነናዊ እንጅ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ አይደለም። እነዚህን መስፈርቶች አያሟላም።

ይህ አምባገነን ቡድን፤ ሕዝብን ከሕዝብ፤ ኃይማኖትን ከኃይማኖት፤ ቋንቋን ከቋንቋ፤ ክልልን ከክልል ለያይቶ አደገኛ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። ወጣቱ ትውልድ የሚነጋገርበት የጋራ የሆነ ቋንቋ እንዳይኖረው ተደርጓል። የኢትዮጵያን የብዙ ሽህ አመታት ታሪክ የመቶ ዓመታት ታሪክ ነው ብሎ ፈርጆ ነበር። ይኼ የተሳሳተ አዲስ ታሪክ ፈጠራ አደገኛ ነው። ለማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ትሥስር በቀላሉ የማይፈታ ማነቆ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ብዙ ብሄር፤ ብሄረሰብ የሚኖርባቸው ሃገሮች---ሕንድ፤ አሜሪካ፤ ጋና፤ ናይጀሪያ፤ ኬንያ-- ወዘተ የዚህ አይነት ማነቆ አልተከሰተባቸውም። ጋና በጎሳ የመደራጀት ፖለቲካን በሕገ መንግሥቷ የከለከለችበት ዋና ምክንያት አደጋውን አይታ ነው። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ዝቅ ብለው ጠባብ ጎሰኛነት መሪ ርእዮት ሲሆን ሊከተል የሚችለውን አደጋ በዩጎስላቪያ፤ በሩዋንዳ ወዘተ አይተናል። አንዳንድ ታዛቢዎች ይኼን ተመልክተው "ኢትዮጵያ የመፈራረስ እድል አላት" እና "የእርስ በእርስ ግጭት የማይቀር ነው" ይላሉ። እኔ ይኼን ባልቀበልም አደጋው መኖሩን አልክድም። ብልህ የሆነና እውቀት ያለው፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ ተቆርቋሪ የሆነ ግለሰብ፤ ቡድን፤ ፓርቲ ወዘተ ሁለቱም አደጋዎች እንዳይከሰቱ በአስቸኳይ ተፈላልጎና ተከባብሮ ለመነጋገር፤ ለመወያየት፤ ለመደራደርና መፍትሄዎችን ለመቀየስ ይችላል። ሆኖም፤ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ ፍላጎትና ፈቃደኛነት አይታይም። ልክ ችግሮች እንደሌሉ ተደርጎ፤ ሁሉም በሃይል ታፍኖ፤ በፍርሃት ተወጥሮ፤ "ዓላማቸውን ስኬታማ ለማድረግ እድል የሚጠብቁ ኃይሎች" በመሳሪያ ተዘጋጅተው ሲታዩ "እኛ ኢትዮጵያዊያን ምን ሆነን" ብሎ ራስን መጠየቅ አግባብ አለው። ጥያቄውን የማቅረብና መልሱን የመፈለግ ሃላፊነት የገዢው ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ነው።
የማይካደው፤ የኢትዮጵያ ህልውና በፈተና ላይ መሆኑ ነው። ባጭሩ ለማስቀመጥ፤ ይህች ታላቅና የሚኮራ ታሪክ ያላትና በአጭር ጊዜ ሃብታምና ዘመናዊ ለመሆን የምትችል አገር፤ በአንድ ላይ ተሰብስበው ለመስራት የሚችሉ የበሰሉ ሰዎች፤ ተደማጭነት ያላቸው መሪዎች፤ ምሁራን፤ አባቶች፤ ወጣቶች፤ የኃይማኖት መሪዎች ወዘተ እንደሌሏት ሆኖ ሲታይ ለውጭ ታዛቢዎች ብቻ ሳይሆን ለተራው ኢትዮጵያዊ ግር ይላል፤ ያስጨንቃል፤ ያሳስባል። ለማጠናከር፤ ይህችን የሚያኮራ ታሪክና ለመላው ሕዝቧ የሚበቃ መሬትና እምቅ ጥሪት ያላት አገር ለማዳንና ዲሞክራሳዊ ስርዓት እንዲመሰረት ለማድረግ የሚችለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ነው። የውጭ መንግሥታት ወይንም የሰብአዊ መብት ተቋሞች፤ ወይንም አበዳሪዎች ኢትዮጵያን ከአደጋ ሊያድኑ አይችሉም፤ ድህነትን ፈጽሞ ለመቅረፍ አይችሉም፤ ዲሞክራሳዊ ስርዓትን ሊመሰርቱልን አይችሉም። የሚያበረታታው ሁኔታ ግን ለኢትዮጵያ ዘላቂነት፤ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፤ ለፍትህ፤ ለሕግ የበላይነትና ለዲሞክራሲ የሚታገሉ፤ በእስር ቤት የሚሰቃዩ፤ የሞቱና የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን መኖራቸው ነው። ውጭም ሆነ አገር ቤት በዓል ሲከበር፤ ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ወዘተ የሚታየው ክስተት ኢትዮጵያዊነት እያደገና እየተስፋፋ መሄዱን ያሳያል። አፈናው፤ ስለላው፤ ፍርሃቱ አላቆመውም፤ እንዲያውም እያጠናከረው ነው። ይኼ የሚያበረታታ የማህበረሰብ ሂደት ወደ ድርጅትና ወደ ጥሩ አመራር መለወጥ አለበት። 3


ፕሬዝደንት ኦባማ የጎበኟት ኢትዮጵያ፤ በመሰረት ልማት እድገት እያሳየች ነው ቢባልም፤ ዘርፈ ብዙ የሆኑ የማህበረሰብ፤ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፤ የኃይማኖትና የባህል ቀውሶች ተከስተውባታል። ወጣቱ ትውልድ ወደ ውጭ ይጎርፋል። የኑሮ ውድነት አብዛኛውን ሕዝብ አድክሞታል። የገቢና የኃብት ልዩነት አደገኛ ከሆነ ደረጃ ላይ ደርሷል። አብዛኛው ሕዝብ የሚፈልገውና የሚመኘው የፖለቲካ ነጻነት ብቻ አይደለም። ከአሰቃቂና መዋቅራዊ ከሆነ የኑሮ ውድነት፤ ከተዛባ የገቢና የኃብት ስርጭት ሰቆቃ፤ ከጉቦና ሙስና፤ ከጎሳዊ አድልዎ፤ ከውጭ እርዳታ ወዘተ አሮንቃ ነጻ ለመሆን ይፈልጋል። የጥቂቶች ኢኮኖሚ ይኼን መዋቅራዊ ችግር ሊወጣው እንደማይችል UNCTAD ያወጣው ዘገባ ያሳያል። ሌላው ቀርቶ የገዢው ፓርቲ አሞጋሽ የሆነው ዓለም ባንክ አንድ ሶስተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ "ምስኪን" እንደሆነ መዝግቦታል። መዋቅራዊ አሮንቃ ስርዓት ወለድ ነው። ስርዓቱ ካልተለወጠ እድገቱ የሚያገለለው ጥቂቶችን መሆኑንና የጥቂቶች መገልገያ የሆነ እድገት አደጋ እንደሚያስከትል ፕሬዝደንት ኦባማም በንግግራቸው አቅርበውታል።

ፕሬዝደንት ኦባማ ኢትዮጵያን ለምን ጎበኙ?

ፕሬዝደንት ኦባማ በስልጣን ላይ ካሉ የአሜሪካ መሪዎች የመጀመሪያው ሆነው ወደ ኢትዮጲያ የሄዱበት ምክንያት "ዱብ እዳ" አይመስለኝም። የኢትዮጱያና የአሜሪካ ግንኙነት የተመሰረተው በብልሁና ዘመናዊው መሪ በአፄ ምኒልክና በአሜሪካው ፕሬዝደንት ቲዎዶር ሮዝቤልት አማካይነት ነው። ኢትዮጵያ በአድዋ የተጎናጸፈችው ድል በዓለም እውቅና እንደሰጣት ታሪክ መዝግቦታል። አሜሪካኖችና ሌሎች መንግሥታት "ምን አይነት የጥቁር መሪ ነው የአውሮፓን ኃያል ለማጥቃት የቻለው" ብለው እንደተነጋገሩ ይታወቃል። በዚያ ወቅት የአረብ ምሁራን ኢትዮጵያ "ልክ እንደ ጀርመኒ፤ በፍጥነት ለማደግ ትችላልች" እንዳሉ አውቃለሁ። ሆኖም ሰላም አላገኘችም ነበር። ቁም ነገሩ፤ የዛሬ ሁለት መቶ አስራ ሁለት ዓመት የተመሰረተው የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት በፋሽስቱ ወረራና በደርግ ፀረ-አሜሪካነት ፕሮፓጋንዳ ቢበከልም፤ ተከታታይነት አለው። ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት የራሳቸውን አገር ጥቅም ለማስከበር ሙከራ እንዳደረጉ ሁሉ፤ የአሜሪካም መንግሥት የራሱን ጥቅም ለማስከበር ሞክሯል፤ አሁንም ይኼን መርህ ተከትሏል። ፕሬዝደንት ኦባማ የታሪክ፤ የውጭ ግንኙነትና የፖለቲካ ምሁር እንደመሆናቸው መጠን በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የቆየውን ግንኙነት በጽሞና ያውቃሉ። አንድ መንግሥት በሌላ ቢለወጥ ግንኙነቱ የሚቀጥል መሆኑን ይገነዘባሉ ብል ከሃቁ የራቅሁ አይመስለኝም።
ለመሆኑ በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መርሆዎች የቶቹ ናቸው? የትኛው ይቀድማል፤ ለምን? ሽብርተኞች በአሜሪካ ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ሲያደርሱ፤ የቡሽ መንግሥት በዓለም ዙሪያ ወዳጆች ፈልጎ በአሜሪካ ጥቅም የተመሰረተና ስትራተጂክ የሆነ የቅርብ ወዳጆች ፈጥሯል። ኢትዮጵያ ለዚህ አመችና አስተማማኝ የሆነ አገዛዝ አላት ከሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሶ በህወሓት ከሚመራው የኢህአዴግ መንግሥት ጋር ሽብርተኞችን ለማዳከም፤ ቢቻል ለማጥቃት "ቃል ኪዳን" ተገባ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መርሆዎች ከሆኑት---አንድ፤ ሽብርተኞችንና አመፀኞችን መታገልና ማጥቃት፤ ሁለት፤ ንግድንና ኢንቬስትሜንትን ማስፋፋት፤ ሶስት፤ ከቻይና ጋር አቻ ለአቻ መወዳደር፤ አራት፤ ድህነትን ለመቅረፍ እርዳታ መስጠት፤ አምስት፤ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ስር እንዲሰድ ድምጽ ማሰማትና የተቻለውን ድጋፍ ማድረግ---ከሚሉት መካከል አሜሪካ ቅድሚያ የምትሰጠው ለመጀመሪያው ነው። ከዚያ ለንግድ፤ ኢንቬስትመንትና ከቻይና ጋር ለሚካሄደው ውድድር፤ ቀጥሎ ለእርዳታ፤ በመጨረሻ ለሰብአዊ መብቶች መከበር። እርዳታን ጠለቅ ብለን ብንመረምር፤ ማንም አገር የሚሰጠው እርዳታ ከራስ ጥቅም ጋር የተያያዘ ነው። ሽብርተኛነትን ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ከተፈለገ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ገዢ ቡድን የገንዘብ፤ የስለላ፤ የጦር መሳሪያ፤ የዲፕሎማሲ ወዘተ ድጋፍ መስጠት አለባት፤ ራሷ ብቻ ሳትሆን የምትቆጣጠራቸውም፤ እንደ ዓለም ባንክ ያሉ ድርጅቶች እርዳታ የሚሰጡበት ዋና ምክንያት ይኼው ነው። ለኩባ፤ ለሰሜን ኮሪያ፤ ለኢራን አይስጡም። እኔ የምከራከረው፤ አሜሪካ፤ ሽብርተኛነትን ለማጥቃት ብቻ ( ለአጭር ጊዜ ጥቅም) 4


አፋኝና ጨቋኝ ለሆነው ለህወሓት/ኢህአዴግ "አገልጋይ መሰል" አገዛዝ ድጋፍ እየሰጠች የረዢም ጊዜ ችግርና አደጋ በመፍጠር ላይ ናት። አፋኝና አሸባሪ አገዛዝ ሽብርተኛነትን ያጠናክራል። በሳይናይ፤ ግብፅ በእየቀኑ የሚሆነውን ማጤን ለዚህ ይረዳል።

የአሜሪካንና የኢትዮጵያን መንግሥታት የሚያዋጣቸው የፀረ-ሽብርተኛውን ዘመቻ ከሰብአዊ መብቶች መከበር ጋር፤ ከመልካም አገዛዝ አስፈላጊነት ጋር አጣምረው ቢያዩት ነው። ሕዝቡ መብቱ በሚጠይቀው መሰረት ተከብሮ፤ በልቶ ካደረ፤ የተሻለ ኑሮ ከኖረ ሽብረተኞች መግቢያ አይኖራቸውም። የኢትዮጵያ ገዢዎች ሊያደርጉት የሚገደዱት የመጀመሪያው እርምጃ የታሰሩትን ጋዜጠኞች፤ ብሎገሮች፤ የሰብአዊ መብት ታጋዮች፤ የእስልምና ኃይማኖትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችንና አባላትን መፍታት ነው። በተጨማሪ፤ የአገሪቱን ግዙፍ ችግሮ ለመፍታት ከተፈለገ፤ ከመንግሥት ቁጥጥር ነጻ የሆነ መገናኛ ብዙሃን ሕጋዊ እውቅና እንዲኖረው ማድረግ፤ ከሃገር የተሰደዱ ጋዤጠኞችና ሌሎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማድረግና ለደህንነታቸው ዋስትና መስጠት፤ የፖለቲካ ምህዳሩን በማያሻማ ደረጃ መክፈት ይገኙበታል።

ፕሬዝደንት ኦባማ እነዚህን ችግሮች አያውቁም ለማለት አንችልም፤ ያውቃሉ። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤታቸው፤ የስለላና የደህንነት ተቋሞቻቸው ስለ ኢትዮጵያ የማያውቁት አበይት ጉዳይ የለም። የጋበዛቸውንና ተባባሪ የሆነውን ፓርቲ ላለማስቀየም ይሁን ሌላ "የኢትዮጵያ መንግሥት ዲሞክራሳዊ የሆነ የምርጫ ውጤት ነው" ያሉት አግባብ የሌለው፤ ከእውነቱ የራቀና ራስን አገልጋይ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፤ የዓለም ሕዝብ አልተቀበለውም። እንዲያውም ትዝብትን አትርፎላቸዋል። የራሳቸው የደህንነት ባለ ሥልጣን የሆነችው የህወሓት መሪ የነበረው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ወዳጅ ስለ ምርጫው ሂደትና ገዢው ፓርቲ "መቶ በመቶ አሸንፊያለሁ" ያለውን ተጠይቃ፤ እያሾፈች ከትከት ብላ ስቃለች። ቲያትር ስለሆነባት፤ መልስ አያስፈልገው ማለቷ ነው። "ዲሞክራሳዊ በሆነ የምርጫ ሂደት የተመረጠ መንግሥት" ያሉትን ብዙ የአሜሪካ ተመልካቾችና ታዛቢዎች ተችተውታል። ምክንያቱም፤ ምርጫው አንዱንም ዓለም የተቀበለውን መስፈርት አያሟላም። ሳሙኤል ሃንቲንግተን የተባለው የታወቀ ምሁርና ደራሲ፤ "Dead Souls: the denationalization of the American elite, the National Interest, 2002 በተባለው ጽሁፉ እንዲህ ብሏል። "Elections, open, free and fair, are the essence of democracy, the inescapable sine qua no (የዲሞክራሲ መሰረት አንድ ብቻ ነው። ያልተዛባ፤ ክፍት፤ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ይባላል፤" ከዚህ ውጭ ምርጫ ለይስሙላ ብቻ ነው። የፎርብስ ጋዜጠኛ ማይክ ጎንዛሌዝ ፕሬዝደንቱ የተናገሩት አስገርሞትና አስቆጥቶት እንዲህ ብሏላ። "For Obama to make excuses for Hailemariam Dessalegn government’s horrendous human rights record by calling the country’s past hardships and the relative infancy of its Constitution" is inexcusable. የህወሓት/ኢህአዴግን "ጨካኝና ኢ-ሰብአዊ" የሆነ የመብቶች ረገጣና አፈና ካለፈው መንግሥትና ሁኔታ ጋር ማመዛዘን አግባብ የለውም። ለዚህ ለሚዘገንን አገዛዝ" ድጋፍ እንደ መስጠት ነው ብሏል። የአሁኑ አገዛዝ መነጻጸር ያለበት ከቦትስዋና፤ ከሞሪሸስ፤ ከጋናና ከሌሎች በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ዲሞክራሳዊ ሃገሮች ጋር ነው። በተጨማሪ፤ ራሳቸው ከተናገሩት ጋር ሲነጻጸር ምንም ግንኙነት የለውም። አንዳንድ ታዛብዎች፤ ምርጫው ሲካሄድ፤ "እንደ ሌሎች ሃገሮች ብጥብጥ አልነበረም፤ ሰው አልሞተም፤ መራጮቹ ጨዋነት አሳይተዋል" ወዘተ የሚለውን መሰረት አድርገው ይሆናል ይላሉ። ይኼ አያስኬድም። የኢትዮጵያ ሕዝብ መከራም ተሸክሞ ጨዋነቱን አይረሳም። የረጋ አእምሮና ባህል ያለው መንፈሳዊ ሕዝብ ነው። ብጥብጥ አለመኖሩና ሰው አለመሞቱ ምርጫውን ዲሞክራሳዊ አያደርገውም።
ወደ አወንታዊው አቀራረባቸው ከመዞሬ በፊት፤ እንደ ተመልካች ሆኘ ያየሁት ያቀባበል ትዝብት አለ። ኢትዮጵያዊያን ከሚታወቁባቸው እሴቶች መካከል የእንግዳ አቀባበል አንዱ ነው። ዓለም ባንክ ስሰራ ማርቲን ሬቫሊየን የተባለ የጥናትና ምርምር ዲሬክተር የነገረኝ ትዝ ይለኛል። የድህነትን አስከፊነት 5


ለማጥናት ገጠር ይሄዳል። አንዲት ምስኪን እናት ያነጋግራል። "አይ፤ ከመነጋገራችን በፊት ምሳ መብላት አለብወት ብላ፤ ያላትን አንዲት ዶሮ አርዳለሁ" ትላለች። ፈረንጁ "እንዴት ይሆናል፤ የተገላቢጦሽ" ብሎ ያስቸግራል። "አይ፤ እኔ ደሃ ብሆንም ክብር አለኝ፤ እርሰዎ እንግዳየ ነውት፤ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ባህሌን አከብራለሁ" ብላ ዶሮዋን አርዳ ምሳ ጋበዘችው። እጅግ በጣም ተደንቆ ጎጆዋን አክብሮና አመስግኖ የዶሮዎች መግዣ የሚሆን ገንዘብ ለአስተርጓሚው ሌላ ጊዜ እንዲሰጥለት ትቶ ተሰናበተ። በመንግሥት መሪ ጉብኝት፤ የኢትዮጱያ መንግሥታት ያለ የሌላቸውን ወጭ እንደሚያፈሱ አስታውሳለሁ። የአገር ክብር ከዋጋ በላይ ስለሆነ። አፄ ኃይለ ሥላሴ የአፍሪካ አንድነት ማህበርን ሲያስመሰርቱ መሪዎችን በሚያስደንቅ አቀባበል እንዳስተናገዱ አስታውሳለሁ። ቲቶ፤ ናስርና ሌሎች እንግዶች ሲጎበኙ አቀባበሉ ሃገሪቱ ካላት አቅም በላይ መሆኑን አስታውሳለሁ። የመጀመሪያው የአሜሬካ መሪ በኦፊሴል ደረጃ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ከፍተኛ ዝግጅት ይደረጋል፤ ሕዝብ እንግዳውን በሚያይበት ሰዓት ይመጣሉ፤ ለሕዝብ ንግግር ያደርጋሉ ወዘተ የሚል ግምት ነበረኝ። ሕዝብ አበባ ይዞ እንደማይቀበላቸው አውቃለሁ። እንዲያውም ሰልፉን ተጠቅሞ "ሌባ፤ ሌባ፤ አፋኝ፤ አፋኝ፤ ጎሰኛ" ወዘተ እንደሚል እገምታለሁ። አቀባበሉ ለታላቋ የአሜሪካ መሪ አግባብ አለው ወይንስ የለውም የሚለውን ጡሮታ ሲወጡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲገልፁ ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ። ከሄዱ በኋላ ይሁን ከመሄዳቸው በፊት የአሜሪካ ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት የትግርኛ ሙዚቃ እየሰሙ እንዲደንሱ የተደረገው ትይንት የኣቀባበሉን ግድፈት አያሻሽለውም፤ ያባብሰዋል። ቪዲወውን ሳይ፤ እራሴን "ምን መልእክት ለመስጠት ነው" ብየ ጠየቅኩ፤ ገዢዎቹ እኛ ነን ለማለት ነው? እንኳን ወደ "አዲሲቷ በጎሰኛነት የተከፋፈለች ኢትዮጵያ" መጣችሁ ለማለት ነው? ወይንስ፤ እመኑን፤ ከእናነት ጋር መደነሳችን እንቀጥላለን?" ለማለት ነው? ኢትዮጵያን የሚጎበኝ ፈረንጅ ወይንም ሌላ ስጦታ ሳይሰጠው፤ ሳይሰጣት የተመለሰ፤ የተመለሰች ፈልጎ ለማግኘት አይቻልም።

በማንዴላ አዳራሽ ያደረጉት ንግግር ምን መልእክት አቀረበ?

ስለ ሰብአዊ መብቶች መከበር አስፈላጊነት

"የተናገርኩት ሁሉ-- ሁሉን አቀፍና ዘላቂንነት ያለው እድገት፤ ልማት፤ ደህንነት-- ስኬታማ ሊሆን የሚችለው መልካም አገዛዝ ሲኖር ብቻ ነው። ይኼን ከኢትዮጵያ ባለ ሥልጣናት ጋር በግልጽ ተነጋግረናል። በተያያዘና የጦፈ ውድድር ባለበት የዓለም ኢኮኖሚ ዘመናዊ መገናኛ፤ የማህበረሰብ ቴክኖሎጅና ነጻ የዜና/የእውቀት ስርጭት ወሳኝ ነው። እኔ የማምነው የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድምጽ ሲሰማና ሲከበር፤ ሁሉም ዜጎች በሃገራቸው የፖለቲካ ጉዳይ ለመሳተፍ ሲችሉ አገር ጠንካራና የበለፀገች ትሆናለች የሚል ነው። ይኼን በሚመለከት የኢትዮጵያ መንግሥት ሊወስዳቸው በሚገባው ፖሊሲዎች ላይ፤ ለምሳሌ፤ የመልካም አስተዳደር፤ የመሰረታዊ ነጻነትና የሰብ አዊ መብቶች መከበር አስፈላጊነት፤ የዲሞክራሲ ሂደት መጠናከር ጥልቀት እንዲኖረው" አሳስቤአለሁ። ይኼን በቃለ መጠይቅ የተናገሩትን አስኳል ጉዳይ ለአፊሪካ አንድነት ባቀረቡት ንግግድ አጠናክረውታል።
"ለጠቅላይ ሚንትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንዳልኩት፤ ባለፈው ምርጫ ብጥብጥ አለመኖሩ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ናት ለማለት አያስችልም፤ ጉዞው መጀመሩን ያሳያል። በእኔ እምነት፤ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ካሰረችና እንዳይንቀሳቀሱ ከከለከለች፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያለ ምንም እገባና አፈና እንደ ልባቸው በፖለቲካው ለመሳተፍ ካልቻሉ፤ እምቅ የሆነው የማደግ ኃይሏን ለራሷ እድገትና ልማት ለመጠቀም አትችልም... ዲሞክራሲ ለይስሙላ ምርጫ ማካሄድ መሆን የለበትም... ጋዜጠኞች ስራቸውን ሲሰሩ ማሰር፤ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪዎችን በወንጀለኛነት እንዲከሰሱ ማድረግና ማሳደድ፤ የማህበረሰብ ድርጅቶችን ማፍረስ ወዘተ የኢምንት ያህል ዲሞራሳዊ ስርዓት መኖሩን አያሳይም።" ከዚህ ጋር ጨምረው ያስተላለፉት መልእክት የአምባገነኖች መሪነት ጎጅ መሆኑንና ግለሰብ መሪዎችና ፓርቲዎች በተከታታይ ራሳቸውን መተካት መቆም እንዳለበት ነው። "አፍሪካ ጠንካራ ተቋሞች እንጅ ግለሰቦች አያስፈልጓትም። "ግልጽ ላድርገው። መሪዎች (ፓርቲዎች) ስልጣን አንልቀም ሲሉ የሚፈጥሩት ችግር ቀላል አይደለም። አንለቅም የሚለው ፈጽሞ አይገባኝም። እኔ፤ ፍላጎትም ቢኖረኝ፤ 6


በአሜሪካ ሕገ መንግሥት እገዛለሁ፤ ሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር አልችልም።" ስልጣን የጊዜ ገደብ ያስፈልገዋል ማለታቸው ነው። ይኼም በተከታታይ አምስት ምርጫዎችን "አሸንፊያለሁ" የሚለውን ህወሓት/ኢህአዴግን በቀጥታ ይመለከታል።

ስለ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ አስፈላጊነት

ፕሬዝደንት ኦባማ ለአፍሪካ መሪዎች የማያሻማ መልእክት አቅርበዋል። "በእኔ እምነት የአፍሪካ እድገት አስተማማኝ የሚሆነው ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ሲመሰረት ብቻ ነው። እንደ ሌላው የዓለም ሕዝብ አፍሪካዊያን የራሳቸውን ህይወት ለመቆጣጠርና ለመምራት መቻል አለባቸው። የእያንዳንዱ ዜጋ ክብር በሕግ እውቅና ማግኘት አለበት። ዲሞክራሲ መስፈርቶች አሉት---ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ፤ የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመንቀሳቀስ፤ የመደራጀት፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ--መብቶች መከበር አለባቸው። እነዚህ መብቶች በተባበሩት መንግሥታትና በአፍሪካ አንድነት ድርጅት እውቅና አግኝተዋል። ለምሳሌ፤ የአፍሪካ የሰብ አዊ መብቶች ቻርተር "እያንዳንዱ ግለሰብ ሰብእነቱና ሰብአዊ መብቱ መከበር አለበት። ሴራ ሊኦን፤ ናምቢያ፤ ቤኒን፤ ቦትስዋና፤ ጋና፤ ደቡብ አፍሪካ የዲሞክራሲ መሰረት ጥለዋል። በናይጀሪያ፤ ሃያ ስምንት ሚሊየን ሕዝብ ድምጽን ሰጥቷል...ባጭሩ፤ የአፊርካ መንግሥታት የሕዝባቸውን መብት ካላስከበሩና ካላከበሩ ከቅኝ ገዢዎች ነጻ ሁነናል ለማለት አይችሉም።" ፕሬዝደንቱ ዲሞክራሳዊ መንግስታት ሁሉን ችግር ይፈታሉ አላሉም። "ማንም ሃገር፤ አሜሪካን ጭምሮ፤ ሁሉን ነገር አስተካክሏል ለማለት አቻልም...የማይካደው፤ የዜጎች መብት ከተጣሰ ሁላችንም የመናገር ሃላፊነት አለብን... አንዳንዴ፤ የእኛ ወዳጆች በሆኑ መንግሥታት ላይ የምናደረገው ትችት ለዚህ ነው።"

ስለ ጠባብና የተዛባ እድገት አስጊነት

"ዛሬ አፍሪካን የገጠማት ፈተና ለአሁኑና ለወደፊቱ ትውልድ የስራ እድል ለመፍጠር አለመቻሏ ነው...ይኼ ጊዜ የማይሰጥ የማህበረሰብ ችግር ሁኗል...እያንዳንዱ ሃገር ብዙ ሚሊየን የስራ እድል መፍጠር አለበት....ኢኮኖሚስቶች እንደሚነግሩን፤ ወጣት ትውልድ ያለበት ሃገር በፍጥነት ያድጋል..ለማደግ ትምህርትና ጉልመሳ ያስፈልጋል፤ የስራ እድል መፈጠር አለበት" ብለው እድገት ለጥቂቶች ገቢ፤ ኃብትና ኑሮ መሻሻል ብቻ ከዋለ አደጋ እንዳለው አስምረውበታል። "እድገት ማህበራዊ ጥቅምና ዘላቂነት የሚኖረው ውጤቱ በጥቂቶች፤ ለጥቂቶች ሲሆን አይደለም። የመስራትና የራስን ስራ የመፍጠር እድል መስፋፋት አለበት....ወጣቱ ትውልድ እድልና ድጋፍ ካገኘ፤ አስደናቂ ውጤት ያስገኛል።" ካላገኘ ይሰደዳል፤ ለሃገርና ለቤተሰብ ሸክም ይሆናል።

የሙስናና ከሕግ ውጭ የሚሸሽ ኃብት ጎጅነት
በአህጉር ደረጃ ሲነጻጸር እንደ አፍሪካ ለስርቆት፤ ለጉቦ፤ ለሙስናና ከሕግ ውጭ ከድሃው ሕዝብ እየተዘረፈ ወደ ውጭ ለሚሸሽ ግዙፍ ኃብት የተመቸ የዓለም ክፍል የለም። ጥናት ያደረጉ ተቋሞችና ምሁራን አፍሪካ በየዓመቱ ከ$300 እስከ $400 ቢሊየን እንደምትዘረፍ ማስረጃዎች አቅርበዋል። ሁኔታው ያሳሰባቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅትና የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ያቀረቡት ዘገባ አፍሪካ እየደማች መሆኑን ያሳያል። የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ኢምቤኪ የመሩት ጥናት ግዙፍ ሃብት ከሚሸሽባቸው አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገልፀዋል። ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ $10 ቢሊየን ተዘርፋለች። ይኼ ኃብት ስንት ፋብሪካዎች፤ ስንት የመስኖ ግድቦችና ሌላ እንደሚሰራና ለስንት ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን የስራ እድል እንደሚፈጥር ለመገመት አያዳግትም። ፕሬዝደንት ኦባማ "አፍሪካ ያላትን እምቅ የእድገት ጥሪት ለመጠቀም ከፈለገች የሙስናን ካንሰር ማቆም አለባት" ብለዋል። እስማማለሁ፤ መጽሃፍት ጽፌበታለሁ። ችግሩ፤ የውጭ ንግድ፤ ኢንቬስትመንት፤ እርዳታ፤ ከስደተኛው የሚላክ የውጭ ምንዛሬ ለሙስናና ከሕግ ውጭ ለሚሸሽ ኃብት ግብአት መሆኑ ጭምር ነው። ከሕግ ውጭ የሚሸሸው ኃብት መደበቂያ ያስፈልገዋል። የምእራብ፤ የመካከለኛው ምስራቅ፤ የኤዝያና የላቲን አሜሪካ/ካሪብያን ባንኮች መደበቂያ ናቸው። ስለሆነም፤ የአሜሪካና ሌሎች መንግሥታት 7


የሚሰረቀውና የሚሸሸው ገንዘብ መግቢያ እንዳያገኝ ለማድረግ የበለጠ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ሙስናና ከሕግ ውጭ የሚሸሸው ኃብት ስርዓት ወለድ ነው። ባለ ስልጣናት ተጠቃሚዎች ናቸው። የአፍሪካ መንግሥታት መሪዎችና ደጋፊዎቻቸው ራሳቸው ሙሰኛ ከሆኑ ሙስና ሊገታ አይችልም። ስለዚህ፤ አገዛዙ መለወጥ ይኖርበታል።

ከህወሓት/ኢህአዴግ የተለየ የፖሊሲ መርህ ጉዳይ

ፕሬዝደንት ኦባማ ከህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ጋር ልዩነት እንዳላቸው አልደበቁም። "እኛ ከልዩ ልዩ ታላላቅ ሃገሮች ጋር ግንኙነት አለን...ለምሳሌ፤ ቻይና፤ በምንጋራቸው ጉዳዮች ላይ አብረን የመስራት መብት አለን፤ ልዩነቶቻችንም እንገልጻለን... ሽብርተኛነትን በሚመለከት፤ አንዳንድ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የመንግሥት ተቃዋሚ የሆኑ ወይንም ለውጥ እንዲመጣ" የሚታገሉ ክፍሎች እንዳሉ" እናውቃለን። እነዚህ ለኢትዮጵያ መንግሥት አስጊ መሆናቸው ይገባናል። ሆኖም የእኛ የመረጃና የስለላ ድርጅቶች እነዚህ እንቅስቃሴዎች "ሽብርተኛ" ወደሚያስብል ደረጃ መድረሳቸውን አይቀበሉም...ስለ አበይት ጉዳዮች መናገራቸው፤ መንግሥትን መቃወማቸውና እንደ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መንቀሳቀሳቸው መብታቸው ነው። እኛ እነዚህን ለዲሞክራሲ የቆሙ እንቅስቃሴዎች እንከባከባለን" የሚል ግልጽ አቋም አቅርበዋል። ወሳኙ ይኼ አባባል ተግባራዊ ሲሆን ነው።

በአጠቃላይ ፕሬዝደንቱ በማያሻማ ደረጃ ለዲሞክራሳዊ ለውጥ ያላቸውን ድጋፍ፤ ተስፋና ምኞት ገልፀዋል። ሆኖም፤ ይኼን ስኬታማ ሊያደርግ የሚችለው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ነው።

የአሜሪካ መንግሥት ሊያደርገው የሚችለው እርምጃ

አንድ፤ የአሜሪካን የዲፕሎማቲክ፤ የእርዳታ፤ የመሳሪያ፤ የስለላና ሌላ አቅማና ድጋፍ መሰረት አድርጎ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብር፤ ጎሳዊ አድልዎንና ሙስናን እንዲያቆም፤ ጋዜጠኞችንና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈታ ያልተቆጠበ ጫና ማድረግ፤

ሁለት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሽብርተኛነት ወንፊት የሆኑ ድርጊቶችን እንዲያቆም ማድረግ፤ ለምሳሌ፤ ዜጎችን ከቀያቸው ማባረር፤ የዘር ማጥፋትና ማሳደድ፤ ተቃዋሚዎች ድምጽ ስላሰሙ ከማሳደድ እንዲቆጠብ ጫና ማድረግ፤

ሶስት፤ በአገር ቤትና ከአገር ውጭ ለሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ መብት ታጋዮችና የዲሞክራሲ ጠበቃዎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ መስጠት፤ በገንዘብ መርዳት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ በሚኖሩ የአሜሪካ ዜጎችን ላይ የሚያደርገው ክትትል ከሕግ ውጭ መሆኑን በይፋ መናገር፤

አራት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ለእርቅና ሰላም ውይይት፤ ከዚያም ለስልጣን መጋራት ፈቃደኛ እንዲሆን ማመቻቸት።

የአሜሪካ ምክር ቤት ሊወስድ የሚችለው እርምጃ

ከዚህ በፊት በሰብ አዊ መብቶች መከበር፤ በሕግ የበላይነት፤ በኢኮኖሚ ነጻነት፤ በደህንነትና በዲሞክራሲ አስፈላጊነት ተጀሞር የነበረው ሕግ እንዲያንሰራራ ጥረት ማድረግ

ለዲሞራሳ ግንባታ ሂደት ያልተቆጠበ የባጀት ድጋፍ መስጠት

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያደርገው የሚገባው እርምጃ
አንድ፤ ኢትዮጵያዊያን በሰላም እስከ ተንቀሳቀሱ ድረስ፤ ያለ ምንም ገደብ የመናገር፤ የመንቀሳቀስ፤ የመጻፍና የማሳተም፤ የመሰብሰብ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፤ የድጋፍ ገንዘብ የመሰብሰብ፤ የፈለጉትን ኃይማኖት የመከተል መብታቸው ሙሉ በሙሉ እንዲከበር የማድረግ ኃላፊነት አለበት፤ 8


ሁለት፤ የፖለቲካ ምህዳሩ መዘጋት ለኢትዮጵያ አደገኛ መሆኑን ተረድቶ የፖለቲካው ምህዳር ሙሉ በሙሉ እንዲከፈት ማድረግ፤

ሶስት፤ ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በሕግ ፊት እኩል መሆኑን ተቀብሎና አምኖ ፍትሃዊ በሆነ መልክ ማስተዳደር፤ ማንም ግለሰብ ከሕግ በላይ ሆኖ የሚያደርገውን ወንጀል በሕግ ፊት ማጋለጥ፤

አራት፤ ከመንግሥትና ከፓርቲ ቁጥጥር ነጻ የሆነ የመገናኛ ብዙሃን ባህልና ልምድ መሰረት እንዲይዝና ጋዜጠኞች፤ ብሎገሮች ያለምንም ገደብ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድ፤ የተሰደዱ ጋዜጠኞች ፍላጎት ካላቸው እንዲመለሱ መጋበዝ፤

አምስት፤ የጸረ-ሽብርተኛውና የማህበረሰብ ሕጎች እንዲሻሻሉ፤ የማፈኛ መሳሪያ እንዳይሆኑ ማድረግ፤ ከመንግሥትና ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ የሆኑ የማህበረሰብና ሌሎች ተቋሞች መሰረት እንዲይዙና ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መፍቀድ፤

ስድስት፤ የጸረ-ሙስናው ኮሚሽን በሞያቸው በታወቁ ግለሰቦች ከመንግሥትና ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሆኖ እንዲሰራ ማድረግ፤ ማንም ሙሰኛና ከሕግ ውጭ ኃብት ያሸሸ ግለሰብ ወይንም ቡድን በሕግ እንዲጠየቅ ማድረግ፤

ሰባት፤ በቂም በቀል፤ በጥላቻ፤ በዛቻና በማስፈራራት የሚደረገው የፖለቲካ ባህል ለኢትዮጵያ ህልውናና ለሕዝቧ አብሮ መኖር አደገኛ ስለሆነ ይኼን ጎታችና ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህል በአስቸኳ ማቆም፤

ስምንት፤ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅምና ጥሪት ሙሉ በሙሉ ተጠቅማ ከድህነትና ከጥገኝነት ነጻ እንድትሆን፤ አገር በቀል የሆነ የግል ክፍል እንዲያብብ፤ ሁሉን አሳታፊ የሆነ የእርቅና የሰላም ድርድር በአስቸኳይ እንዲካሄድ ፈቃደኛ መሆን፤ ተቃዋሚ ክፍሎች አጋር እንዲሆኑና ብሄራዊ ችግሮችን አብረው እንዲፈቱና ወደ እውነተኛ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ለመሸጋገር እንዲቻል አግባብ ያላቸውን የፖለቲካና ሌሎች ክፍሎች ያካተተ ብሄራዊ የአንድነት መንግሥት ለማቋቋም ፈቃደኛ መሆን፤

ዘጠኝ፤ ተቃዋሚውን ሁሉ ከማውገዝ ተቆጥቦ እነዚህ ኃይሎችና ድምፆች የሚያቀርቧቸውን አማራጮች ማስተናገድ፤

አስር፤ በውጭ ለሰብአዊ መብቶች መከበርና ለዲሞክራሲ በሚታገሉ ግለስቦችና ቡድኖች ላይ የሚደረገውን ክትትል በአስቸኳይ ማቆም።

የተቃዋሚው ክፍል ሊያደርገው የሚገባው

አንድ፤ የእርስ በርሱን የፖሮፓጋንዳ ጦርነት በአስቸኳይ ማቆም፤ የመከባበርና የመደማመጥ ፖለቲካ ባህል ልምድ ማድረግ፤

ሁለት፤ በተናጠል የሚደረገው ትግል የትም እንደማያደርስ ተገንዝቦ አበይት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተባብሮና ተቻችሎ መስራት፤

ሶስት፤ በዲፕሎማሲ የሚደረገው ጥረት ተደማጭነት የሚኖረው በመተባበር ስለሆነ ተወያይቶ ዘላቂነት ያለው ተቋም መፍጠር፤

አራት፤ ኢትዮጵያን ከመፈራረስና ሕዝቧን ከእርስ በእርስ ግጭት ለማዳን ተባብሮ መነሳት።

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)
Ssemegn@yahoo.com 9
Ethiopian Bloggers in Kangaroo (Monkey) Kourt
By Alemayehu G Mariam
August 24, 2015


Kangaroo/monkey kourt (in)justice T-TPLF style
Last week, young Ethiopian bloggers collectively known as “Zone 9 Bloggers” (named after a cell block  holding political prisoners at  the infamous  Meles Zenawi Kality Prison, a few kilometers outside of the capital) returned to  the kangaroo/monkey  kourt system of the Thugtatorship of the Tigrean People’s Liberation Front (T-TPLF) for  the 33rd time  since April 2014.
(Ethiopia is the ONLY country in the world where the police arrest and detain a criminal suspect and then go out looking for evidence of wrongdoing for months and even years!)
“Justice delayed is justice denied.”  Justice delayed 33 times is justice denied 33 times.
Justice delayed 33 times while the young bloggers are held in prolonged pretrial detention, denied bail, effective assistance of counsel, speedy trials and an impartial fact finder is a travesty of justice.
In anticipation of Barack Obama’s visit in July, the T-TPLF released two bloggers and 3 journalists.
Since 2006, I have been writing about the T-TPLF kangaroo (monkey) kourt system.
I wrote my first commentary in December 2006 entitled, “Keystone Cops, Prosecutors and Judges in a Police State.” That commentary examined the “trials” of the “Kality defendants” (opposition leaders) jailed by the late Meles Zenawi following the 2005 election.
In December 2007, I wrote “Monkey Trial in Kangaroo Kourt” examining the “trial” of Daniel Bekele (manager of ActionAid International in Ethiopia at the time), presently Executive Director of the Africa Division of Human Rights Watch, and Netsanet Demessie who founded and directed the Organization for Social Justice in Ethiopia. I compared their “trial” to the grim and chilling fictional story of Joseph K., in Franz Kafka’s The Trial.
I have written numerous commentaries on the T-TPLF’s Banana Republic and its monkey kourts for years.
In June 2014, I wrote a commentary entitled, “Who is afraid of the Ethiopian bloggers?, on the legal plight of the Zone 9 bloggers.
I use the metaphor of “kangaroo” and “monkey” kourt to describe the T-TPLF’s (in)justice system, not out of malice, but out of necessity for descriptive precision.
The phrase “kangaroo court” has nothing to do with the marsupial kangaroos of Australia.
The phrase is said to have originated in the American West in the 19th century to describe bogus, sham and phony judicial proceedings run by self-proclaimed judges.
The phrase has often been defined as 1) “a mock court in which the principles of law and justice are disregarded or perverted”, 2) “a court which blatantly and intentionally disregards recognized standards of law or justice”, 3) a “court held by a legitimate judicial authority who intentionally disregards the court’s legal or ethical obligations”,  and 4) a court projecting the “appearance of a fair and just trial, even though the verdict has in reality already been decided before the trial has begun.”
The T-TPLF judicial system fits all of the foregoing definitions to a T.
The phrase has found its way into one of the most important landmark criminal constitutional cases in the U.S. legal history. In In Re Gault, the U.S. Supreme Court condemned a judicial process “where police take matters in their own hands, seize victims, beat and pound them until they confess. It is the right of the accused to be tried by a legally constituted court, not by a kangaroo court”.
That is the essence of the T-TPLF’s kangaroo courts. T-TPLF police thugs arrest suspects in political crimes on instruction of the T-TPLF political bosses, place them  in detention, beat the hell out of them and extract confessions, delay filing charges, deny them counsel and shuttle them to and fro before judicial hacks appointed by the T-TPLF, deny them speedy trials and force them to languish in vermin-ridden jails for months or years as hack judges grant endless continuances to “prosecutors” to gather (fabricate) evidence on the suspects.
Kangaroo courts on Planet T-TPLF become monkey kourts.
To read the full commentary, click here.

Ethiomedia.com - An African-American news and views website. Copyright 2013 Ethiomedia.com. Email: editor@ethiomedia.com