Wednesday, March 5, 2014

የገዢዎቻችን መጨረሻና የተከተላቸው ሀቅ
አንዱ ዓለም ተፈራ
የእስከመቼ አዘጋጅ
የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓመተ ምህረት
የመጨረሻውን በማያውቁት ያዘቀዘቀ ጨለማ መንገድ እየተውዘረዘጉ መሪዉን በማስተካከል ከመጨረሻው ለመድረስ የሚጣድፉ መሪዎች፤ የድንቁርና
ኒሻን ይገባቸዋል። በፈጠሩት የራሳቸው የመኖሪያ የገዢነት መኮፈሻ “ሀቅ” ተጀንነው በመቀመጥ፤ ፈንጠር ብሎ ርቆ ሌላውን ማየት ባለመቻላቸው፤
የተከተላቸውውን ሳይውቁት እጃቸውን ሠጥተዋል። የተለዬ የመሰለ የራስ “ሀቅ” የብዥታ ጭጋግ፤ ሩቅ ማየትን ነፈጋቸው። ማስተዋልን ከአእምሮ
መዝገባቸ ሰወረው። መደናበርን አነገሠባቸው። ካይናቸው ፈት በተገተረው የእብሪታቸው መነፅር ዓለምን ግቢ ውጪ እያሉ በማስገደድ፤ ያለው የሌለ
ሆኖ፣ ከተጨባጩ ይልቅ በምኞታቸው ዓለም ሲዳክሩ፤ የቆሙበት መሬት ከዳቸው። ከሕዝቡ መሆናቸው ቀርቶ ሕዝቡ የነሱ አገልጋይ ሎሌ ሆነና፤ የነሱ
መኖሪያና የሕዝቡ መኖሪያ በአጥር ተለያዬ። መኖሪያቸው ዓለማቸው ሆነና ከሕዝቡ ዓለም ወጡ። ረጋ ብለው ያሉበትን ለመመርመር ጊዜ አጠራቸው።
ያጠራቸው ጊዜ ጥሏቸው ሄደ። እናም ባሉበት ቆመው ቀሩ።

መንግሥትን ለመምራት፤ ከፍተኛ ብስለትና ጥንቃቄ ታላቅ መሣሪያ ናቸው። “ጠላት” እና “ወዳጅ” ብሎ በመፈረጅ፤ ወዳጅን መጥቀምና ጠላትን
መጉዳት በሚሉት ጋቢ ከተሸፈኑና በዛሬ ወንበር ከረጉ፤ ነገ የራሷን ወዳጅና ጠላት አበጅታ ከጎን ብቅ ስትል፤ የሚይዙትን ታሳጣለች። ለሁሉ ጥሩ ነገሮች
ባለቤት ወዳጅ ብሎ የፈረጀውን ወገን ያቀሰሰና ለሁሉ ነገር መጥፎ ባለንብረት፤ ጠላት ብለው የፈረጀውን ሠፈር የወነጀለ ገዢ፤ መጨረሻው አያምርም።
የኛ ገዢዎች እንዲያ ነበሩ፤ አሁንም እንዲያ ባይ በጀርባችን ተሸክመናል። ፍርሃትን በሕዝብ በመዝራት ለመግዛት የተነሱት ገዥዎቻችን፤ ራሳቸው
በፍርሃት ተውጠው ከሕዝቡ ራቁ። ሕዝቡን ጠላት አድርገው ፈረጁት። መውደቃቸው የጊዜ ጉዳይ ሆነ።

ገዢዎች ከአመጣጣቸው ማንነታቸውን መገንዘብ ይቻላል። አንድ የተለዬ ወገን ቦድነው የመጡ ክፍሎች፤ ያንኑ ምርኩዝ ይዘው እስከመጨረሻው ሲሄዱ
አየናቸው። ያ አመጣጣቸው ለተከተሉት ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያቸው መነፅራችን ነው። እናም እምነታቸውና ተግባራቸው ይኼንኑ
አንፀባረቀልን። እብሪት የጉልበተኞች መመኪያ ሆነች። እብሪተኞች ዘለዓለማዊ ነን አሉ። በሥልጣን ላይ ሲሆኑ የረጋ አእምሮን መንገድ መጥረግ
አቆሙ። በስሜትና በፍላጎት መብራት ጨለማውን ለማለፍ ተደናበሩ። የተፈጥሮ ሕግን ጠምዝዘው ሊዘውሩ ሞከሩ፤ ራቁታቸውን ተጋልጠው ቆማ።
ንጉሡ ባሉበት ደነዘዙ፣ ደርጋማው መንግሥቱ ጭራውን ቆልፎ ሐራሬ ምሽግ ውስጥ ተደበቀ። ያሁኖቹ ደግሞ በተራቸው የት ይገቡ ይሆን?
እኔ ራሴ ባየኋቸው ሶስት የተከታተሉ ገዢዎቻችን፤ ይህ ሀቅ በጣም ጎልቶ ታይቷል።

በመጀመሪያ ንጉሠ ነገሥቱ፣ ራሳቸው በፈጠሩትና ባመኑበት “ከአምላክ የተቀባሁ ነኝ!” ባይ እብሪት፤ ሕዝቡን ለሳቸው የተሠጠ አገልጋይ በማድረግ፤ ጊዜ
ሲለውጥና የዓለም ፖለቲካ መልኩን ሲቀያይር፣ ከኋላችን የነበሩትና አዲስ ነፃ የወጡ የአፍሪቃ ሀገሮች ቀድመውን ሲሄዱ፣ በሀገራችን በሚሠጠው
ትምህርት የዓለምን ግስጋሴ የተገነዘበው የተማረው ክፍል የስልጣኔ ናፍቆቱ ሲያድግ፣ የዓለም ህዝብ የኑሮ ደረጃ ከፍ እያለ ሲወጣና የኛ ኑሮ ባለበት
ከመዘፍዘፉ የተነሳ የኋሊት ጉዞ ሲጀምር፤ ያመኑበት መለኮታዊ ገዢነታቸው ዓይናቸውን አውሮ ማየት ተሳናቸው። እናም የግል ጠባቂ ብለው ያደራጁት
የጦር ኃይል ያለበት የኑሮ ሁኔታ አላስጨነቃቸውም። ሁሉም በተዓምርና በሳቸው ምኞት ብቻ የሚመራ አድርገው ሲያዩት፤ ታሪክ ያልተገናኙ አድርጎ
ከሥራቸው መሬት ካዳቸው። እናም ሲነቁ በጨለማ ተውጠው የሚጨብጡትን አጡ። ተነድተው የታሪካቸው የመጨረሻ ምሽት፤ ባልታወቀበት ቦታ
ሆነ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በየካቲት ፲ ፱ ፻ ፷ ፮ ዓመተ ምህረት ባንድነት ተነስቶ የራሱን መንግሥት ለመመሥረት ሲዘጋጅ፤ ባቋራጭ የገባው የወታደሮች ቡድን
አብዮቱን አኮላሸው። በሂደቱም አንድ አምበገነን ወጥቶ፤ የፈራቸውን፣ የጠላቸውን፣ በሕልሙ የሚያስበረግጉትን፣ ለሱ ሠጥ ለጥ ብለው፣ አሜን ጌታዬ
ብለው ያልተገዙለትን በማሰር፣ በመግደልና በተለያዬ መንገድ በማጥፋት ሊገዛ ተነሣ። ሰዎችን እንደ ጠጠር በፈለገበት ማስቀመጥና ማዞር፣ ማሽከርከርና
መጣል የዕለት ተዕለት ተግባሩ ሆነ። ራሱን ኢትዮጵያ፣ የሱን ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ፣ እሱን ያልተቀበለ ኢትዮጵያን ያልተቀበለ በማድረግ ሊገዛን
ፈለገ። በመሐል ቤት ራሱ በሚያልመው መነፅር ሀገሪቱንና የሀገሪቱን የፖለቲካ ሀቅ እየተመለከተ ከህዝቡ ተለዬ። ሕዝቡ ለማያባራ ጦርነት ልጆቹን
መገበር እምቢ አለ። ሕዝቡም መጥፎ ነገር እንደነካ እንጨት ራቀው። እናም ብቻውን ቀረ። ዙሪያውን ሲከበበ፤ ጅራቱን ቆልፎ እንደሚሮጥ ፈሪ ውሻ፤
እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ሐራሬ ፈረጠጠ።

በቦታው የተተካው ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ደግሞ፤ ራሱን ልዩና ብቸኛ ሆኖ የተፈጠረ አዳኝ በማድረግ፤ ለሁሉም ነገር እሱ ብቻ
መፍትሔ አዋቂና ራሱ ብቻ ትክክለኛ ሆኖ በመቅረብ፤ እሱም እንደቀደሙት ሁሉ፤ ሕዝቡ ገዢው የሚለውን የሚሰማ፤ ገዢው የሚያዘውን የሚፈፅም
አድርጎ እየገዛ ነው። በዚህ ተግባሩ ከሕዝቡ ተነጥሎ ተንሣፏል። ቀደም ያሉ ገዢዎቻችንን ያስቆጧቸው ወገኖች በሥራቸው እንዳቆጠቆጡት ሁሉ፤
በአዲሱ ገዥዎቻችን ላይም የሕዝብ ወገን የሆኑ ተቃዋሚዎች በየቦታው ተኮልኩለዋል። አሁንም ያለበትን ሀቅ ሳይሆን፤ የሚያልመውን እየተቀበለ
እውነቱን ማየት አቃተው። ጊዜያዊ የመሰለያ አምስት ለአንድ ጥፋሮውንና ወታደራዊ ጥንካሬውን የማይበገር ምሽግ አድርጎ ወስዶታል። የሚታየውን
በሀገሪቱ የሠፈነ የኅብረተሰብ ችግርና የኑሮ ሁኔታ እንዳያይ የራሱ ቅንጦትና ምቾት አውሮታል። እንደቀድሞዎቹ ራሱን ዘለዓለማዊ አድርጎ ወስዷል።
እንደቀደሙትም ተራውን እየጠበቀ ነው።

ለኔ፤ የወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ ቡድን ነገ፤ ጉዳዬ አይደለም። ጉዳዬ፤ የኛ የኢትዮጵያዊያንና የሀገራችን የኢትዮጵያ ነገ ነው። እንደትናንቶቹና ዛሬ
በዙፋኑ ላይ ቁጢጥ እንዳለው፤ ሌላ አምባገነን ገዢ እንዲተካ አልፈልግም። የእስከዛሬው አንገፍግፎኛል። ይህ ምን ጊዜም መረሳት የለበትም። ግፉ
እንዲቀጥል በምንም ሁኔታ መንገድ አሠልጢዎች መሆን የለብንም። ታዲያ እኛ ምን ማድረግ አለብን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። መልሱን ደግሞ
ነገ ሳይሆን ዛሬ መሥጠት አለብን። እጆቻችን አጣጥፈን መጪውን መጠበቁ፤ በተዓምር ኢትዮጵያዊያን የምንፈልገውን ሀቅ እንዲከተል አያደርግልንም።
እናም እኔ ኃላፊነቴን መወጣት አለብኝ። ብቻዬን የምጥረው የትም እንደማያደርስኝ አውቃለሁ። ችግሩ የሁላችን የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው።
መፍትሔውም በሁላችን በኢትዮጵያዊያን ጥረት የሚገኝ ነው። እናም ለርስዎና ለመሰሎችዎ ጥያቄ አለኝ።

ያሁኑ ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ሲወገድ ምን እንዲተካ ነው የሚፈልጉት? ይህ እንዴት ሊመጣ ይችላል?
የኔና የርስዎ፤ የያንዳንዳችን አስተዋፅዖ ምንድን ነው ይላሉ?

የኔን ላጋራዎ፤

አሁን በሀገራችን ያለው ወራሪ ዓይነት ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት ነው። ሀገራችንን ወደ ከፍተኛ አደጋ እየመራት ነው። የነገው የሀገራችን
ዕጣ አደገኛ ሁኔታ ላይ ወድቋል። እኛ የዚህን ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መከታተላችን፤ ኢትዮጵያዊያን
የምንፈልገውን ሕዝባዊ አስተዳደር አያመጣልንም። የራሳችንን ተግባር ነው መወሰን ያለብን። ሀገር አቀፍ የሆነ ሁሉን ኢትዮጵያዊያንን ያጠቃለለ
የሽግግር መንግሥት ተቋቁሞ፤ የዴሞክራሲያዊ አሠራር መሠረቱ ሲጣል ብቻ ነው አስተማማኝ የሆነ የወደፊት የሚኖረን። ለዚህ ደግሞ ሁላችንን
የሚካትት ራዕይና ተልዕኮ ሊኖረን ይገባል። ይህ መንግሥት በሕዝቡ ግፊም ሆነ ራሱ በውስጡ በመንቀዙ መውደቁ አሌ አይባልም። ጥያቄው መቼ? ብቻ
ነው።

በኔ እምነት፤ ኢትዮያዊነታችንን የተቀበልንና የሕዝቡን ትግል የምንደግፍ ሁሉ፤ በመጀመሪያ ማመን ያለብን፤ የምንፈልገው ተከታይ ሥርዓት፤
ለምናደርገው ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ነው። ምን እንፈልጋለን? በአንድነት ሆነን ተሰባስበን በምናደርገው የአደረጃጀት ተሳትፎ፤ በግል ወንም በቡድን
ሥልጣን መያዝ ወይንም አንድን ርዕዩተ ዓለም የማራመድ ጉዳይ ቦታ የለውም። ቦታ ያለው፤ በአንድነት ሁላችን፤ ሀገራችን ከዚህ ወራሪ ከመሰለ
አስተዳደር ነፃ ወጥታ፤ ሕዝቡ የወደደውን መንግሥት ለማቋቋም መሸጋገሪያ መንገድ ማዘጋጀቱ ነው። ሕዝቡ የወደደውን ከመምረጡ በፊት የመሸጋገሪያ
ወቅት አለ። እናም የኛ የትግሉ ተሳታፊነት በትግል ዕሲውቶቻችን ይመራል። እናም የትግል ዕሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፤

ሀ) ሕዝቡ ሉዓላዊነቱ ተከብሮለት፣
ለ) የሀገራችን አንድነት ተጠብቆ፣
ሐ) የሕግ የበላይነት ሠፍኖና፤
መ) የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው፤

የሚኖሩባት ሀገር እንድትሆን የሚያመቻች የሽግግር መንግሥት መቋቋሙ ነው። እኒህ አራት የትግል ዕሴቶች ሁላችንም በታጋይ ክፍል የተሠማራነው
የምንጋራው ስለሆነ፤ በነዚህ ዙርያ መሰባሰቡ ወደ አንድ ያመጣናል። እናም እነኚህን አራት የትግል ዕሴቶች የተቀበልን ኢትዮጵያዊያን፤
በኢትዮጵያዊነታችን መሰባሰባችን ግዴታ ነው።

ታሪክ ጥሏቸው ሲጓዝ ባሉበት ቆመው የተያዙትን ገዢዎቻችንን እናጢን። ኃላፊነቱ የኛ ነው ብለን እስካልጨበጥንና ግዴታችንን እስካልተወጣን ድረስ፤
ሌሎች በሚያመጡት ለውጥ የኛን ፍላጎት እንዲሟላ እጃችንን አጣጥፈን መቀመጡ፤ በቀላሉ ጅልነት ነው። ከአፄው የከፋና የከረፋ ደርግ ተከተለ።
ከደርግ የገማና የተግማማ ወገንተኛ አምባገነን ሕገወጥ ተከተለ። የከፋ አይመጣም እያልን የተሻለ ባጠገባችን አላልፍም አለ። የሚቀጥለውስ የመዓት
ነው። እኛ ካላወቅንበት! ምን ይላሉ?






ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
March 3, 2014 
Free all politcal prisoners in ETHIOPIA

Tuesday, March 4, 2014

In Ethiopia, truth is stranger than fiction 
By Abebe Gellaw
March 4, 2014



Hailemedhin Abera Gezehegn
Hailemedhin Abera
The life of the young Ethiopian co-pilot who sought political asylum while flying in the airspace of Switzerland two weeks ago will never be the same again. If the amount of money people make is a measure of success, the 30-year old co-pilot Hailemedhin Abera Tegegn had a relatively “privileged” life in Ethiopia, where per capita income is around $400.In contrast to the paltry income of the majority of Ethiopians, the average pilot working for the state-controlled Ethiopian Airlines is said to make well over $2000. That is a fortune in Ethiopia, a country where crony capitalism has widened the disparity between the fortunate haves and the unfortunate majority that barely affords to eat a decent meal. It could indeed be puzzling how the young pilot chose to risk it all with what appears to be a deliberate and dramatic “hijacking” incident that he executed calmly despite the inevitable consequences awaiting him upon landing. But man does not live by bread alone. Man also needs guarantees for dignity, rights and freedom.
Hailemedhin is now a prisoner under the custody of the Swiss police facing air piracy and hijacking charges that carry a penalty of up to 20 years in jail. The incident is actually another testimony to the fact that people living under tyranny tend to resort to extreme measures riking their comfort and lives to call for attention and win their freedom. According to media reports, Hailemedhin took control of the plane when the pilot left the cockpit to take a toilet break over the airspace of Sudan. He locked out the pilot and commandeered the Ethiopian Airlines Boeing 767-300, Flight ET702, with 202 passengers and crew en route to Rome and diverted it to Geneva, where he sought political asylum in midair, a daring action that attracted global attention.
The measure is definitely extreme as the young man could have quietly slipped out of the country to seek political asylum in the United States or Europe. Tens of thousands of professionals leave the country every year. So many pilots and crew members from the Ethiopian Airlines have fled the country without attracting glaring attention at a global scale. The reaction of the Ethiopian government, which is dominated by the Tigray People’s Liberation Front (TPLF), was not unexpected. It is a minority government that routinely makes every effort to hide its appalling human rights record from the attention of the international community. The Minister of Government Communication, Redwan Hussein, told reporters in Addis Ababa that the incident "beggars belief".
While is it an open secret that the Ethiopian constitution is not worth the paper it is written on, Mr. Hussein said the action of the co-pilot was in violation of article 32 of the Ethiopian Constitution, which guaranteed the freedom of citizens to travel out of the country.” He also claimed that basic liberties such as freedom of expression are fully respected in Ethiopia and claimed that citizens have no reason to flee from their own country. But the citizens enjoying such privileges might be TPLF members. What beggars belief is actually the depressing reality on the ground and the cruel way that ordinary citizens are oppressed and stifled in Ethiopia. Thousands of journalists, human rights activists and dissidents are languishing in harsh jails where torture and other forms of inhuman treatment are rampant. The Draconian anti-terrorism law is routinely invoked to jail anyone who dares to speak out against the gross human rights violations and corruption which characterizes a regime that ironically enjoys cozy relationships with Western powers as well as China.
The United States, which considers the Ethiopian government a credible ally in the “war on terror”, doles out about a billion dollars annually in the form of foreign aid to prop up the brutal TPLF-led regime. It is a crucial support for a government that significantly depends on foreign aid to survive and maintain its tight grip on power. To please its Western funders, the ruling party periodically holds inconsequential elections and regularly pays lip service about “flourishing” democracy.
Press freedom is a far cry in Ethiopia. Three award-winning journalists that have been convicted of terrorism offenses because of their critical writing are serving long-term sentences. Eskinder Nega is winner of the 2012 PEN America’s Barbara Goldsmith Freedom to Write Award. Earlier this year Eskinder was also awarded the 2014 Golden Pen of Freedom by the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA). But the award given to him by the Ethiopian government for his courageous work as a journalist is 18 years behind bars after he was convicted of “terrorism” offenses. His most serious crime was writing a few critical articles that predicted that Ethiopia would face a popular uprising in the style of the Arab Spring. In fact, all tyrants don’t want to believe that reality but the doom is inevitable.
Reeyot Alemu is another courageous journalist who celebrated her 33rd birthday in a harsh jail last month. She is suffering from breast cancer but has been denied proper medical care. While in jail, Alemu has bagged three coveted international awards for her extraordinary commitment to press freedom and courage in journalism. She was awarded the 2012 Courage in Journalism Award by the International Women's Media Foundation, Human Rights Watch’s press freedom prize, Hellman/Hammett award, and the 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize. Woubishet Taye also received the Hellman/Hammet and CNN Free Press Africa Journalist Awards.
Journalists are by no means the only victims. While journalists are mostly the primary targets due to the nature of their jobs, individuals like Hailemedhin, no matter what their profession and education, sometimes tend to take inexplicable actions such as choosing to live in jails rather than living in fear and silence. The most extreme measure was taken by Yenesew Gebre, a 29 year-old Ethiopian school teacher. Frustrated by the lack of basic freedom, he set himself ablaze in November 2011 and died a horrific death shortly after the incident.
In a New York Times piece, “Letter From Ethiopia’s Gulag”, which journalist Eskinder Nega penned from jail, he noted: “I’ve never conspired to overthrow the government; all I did was report on the Arab Spring and suggest that something similar might happen in Ethiopia if the authoritarian regime didn’t reform.”
Authoritarian and totalitarian regimes live under the illusion that they can sustain repression forever through intimidation and killings. As history shows time and again, those who fail to reform create their own demise by forcing people to rise up in anger to claim their own destiny. The case of a defiant young pilot is not unprecedented. Defiance is a familiar alarm bell in nations like Ethiopia where the truth is stranger than fiction.
Hailemedihin seems to be more interested in calling for global attention to the plight of the people of Ethiopia than just seeking asylum. While he could have sought asylum quietly, he chose to do it in full view of the world over Geneva. For most Ethiopians, he is a hero and a protester against the injustice they are facing under the boots of their cruel rulers that have no regard for the rights, dignity and freedom of their subjects.
As the former US Attorney General Ramsey Clark once said: "One man's terrorist is another man's freedom fighter." Switzerland and the rest of the world should definitely take note of this reality.




Ethiomedia.com - An African-American news and views website.
Copyright 2013 Ethiomedia.com. 
Email: editor@ethiomedia.com

የዎያኔ አገዛዝ የወንጀል አፈጻጸም ዘዴ (ሞደስኦፐራንዴ)
ወያኔ መንግስት መሰል ታቋማት እና መዋቅር የዘረጋ እጅግ ኣደገኛ የሆነ ኢትዮጵያን ኣፈራርሰው የነርሱ
ሊያደርጓት በሚመኙ ሃይሎች የተቀጠረ ቡድን ነዉ፣፣ወያኔ ባለሙያወችን ከሙያቸዉ ኢትዮጵያዊያንን
ካገራቸዉ በመግፋት ኣገራችንን ለባዳን ኣሳልፎ የሰጠ ቡድን ነዉ፣፣ በመሆኑም ወያኔ ከባእዳን በሚሰጠዉ
ኢትዮጵያን የማፍረስ ተልኮ የሚመራ በኢትዮጵያ ላይ የዘመተ ሃይል ነው፣፣ በዚህ መሰረት ወያኔ ህግን
ወረቀት ላይ ኣስፍሮ በተግባር ወንጀል ይፈጽማል፣፣ ወያኔ ስለህግ ሲባል ከመስማት ዉጭ ጣእሙን
ኣያዉቀዉም፣፣ የህግ የበላይነት እና የወያኔ ኣገዛዝ ኣጥፊና ጠፊ ናቸዉ፣፣
የህግ የበላይነት ማለትም ፥ በዚህ የሰለጠነ ዘመን እና የብዙሃን ፓርቲ ስርዓት በሚከተሉ ዘመናዊ ኣገሮች፥
ባገሩቱ ዉስጥ ፖለቲካዊ፥ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን ለማስተዳደር ብቃት ያለዉ፣ሁሉም ሰዉ
በህግ ፊት እኩል የሆነበት፣ የህግ ስርዓት ያለበት ማለት ነው፣፣ ”በህግ ፊት ሁሉም ሰዉ እኩል ነዉ”
የሚለዉ የህግ መርህ ለወያኔ ባእድ ነዉ፣፣ ባ17 ዓመት የትግራይን ህዝብ ሲጨፈጭፍ፣ሲዘርፍና ባለቆቹ
መመሪያ መሰረት ኢትዮጵያዊ የትግራይ ጀግኖችን ሲገል እና ትጥቅ ሲስፈታ ያካበተዉን ልምድ ወደ መሃል
እና መላዉ ኢትዮጵያ ይዞ በመግባት ከጸረ ኣገር ቅጥረኛ ሽፍታ ወደ ቅጥረኛ መንግስትነት፣ሲለወጥ
ለማስመሰል የሚጠቀምበት ባዶ ቃል ነዉ፣፣የህግ የበላይነት እዉን የሚሆነዉ የፖለቲካ መሪዎች በነጻነት
የህግ ከለላ ተሰጧቸዉ እርይ ኣቸውን ሲያራምዱ፣ ነጋዴዎች በነጻ ገብያ ዉድድር ነግደዉ ጤናማ ትርፍ
የሚያግኙበት : ማህበራዊ ፍትህ ተገቢውን የህግ ጥበቃ አጊንቶ ዜጎች በእኩልነት የሚታዩበት ስርዓ-
መንግስት ሲኖር ነው:: ይህ ሲኖር ግልጽነት ና ተያቂነት ያለው የህግ አውጪ ተርጉአሚና አስፈጻሚ አካላት
ይኖርራልኡ ማለት ነው:: ወረቀት ላይ የሰፈረውን ህግ ባግባቡ የሚያስፈጽሙ የመንግስት ተቁአማት
ክከሌሉ ህግ ብወረቀት ላይ የሰፈረ ተረት ተረት ነው::
ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች ዘመናዊ መንግስታት የህግ የበላይነት መርሆች ይቅበላሉ: ተቀብለውም
ተቁአማትን ይገነባሉ መዋቅርም ይዝርጋሉ:: በዚህም ህጋዊነትን ሽፋን ኣድርጎ የወያኔን ተቁአማዊ
አደረጃጀት ና መዋቅራዊ የወንጀል አፈጻጸም ዘዴውን ከዚህ ቀጥልን ዕናያለን::
ማንኛውም ዘመናዊ መንግስት አገርን ከውጭ ጥቃትና ከውስጥ ከሚነሳ የወንንጀል ድርጊት ለመከላከል
የጸጥታ ተቁአማት የመጀመሪወቹ ናቸው:: እነዚህ ተቁአማት በየትኛውም የህግ መመዘኛ : የየትኛውም
የፖለቲካ :የእምነት ወይም የሃይማኖት: የጎሳ ቡድን ወገንተኛ መሆን የለባቸውም:: ወገንተኝነታቸውም
ለህግ ና ለህግ ብቻ ነው:: ይህን አጠቃላይ ግንዛቤ ከያዝን በሁአላ ወያኔ ወንጀል ለመስራት እንዲያመቸው
ተቅኡአማቶቹን ና አወቃቅራችውን እንዴት እንዳዋቀረ እናያለን::1. ደህንነት : መከላከያ: እና ፖሊስ:- እነዚህ ተቁአማት መዋቅራቸው የተሞላው ለ 17 ዓመት
የትግራይን ወጣቶች በጅምላ በመረሸን : የትግራይ አዛውንቶችን ኢትትዮጵያዊ ክብራቸውን
በመግፈፍፍ: የትግራይ ጅግግኖችን ትጥቅ በማስፈታት: የኢትይኦጵያን የግዛት አንድነት ለመፈ
ታተን ለተከፈተው ሰፊ ዘመቻ ታማኝነታቸውን ባስመሰከሩ ና ለ 23 ዓመታት በመንግስትትነት
ስም ኢትዮጵያንን እያዋረዱ ባሉ ግለሰቦች ነው::እነ ዮሃነስ ኣንገታቸዉን የሰጡበትን፣ እነ ኣሉላ
ክንዳቸዉን ያሳዩበትን የኢዮጳያ ኣካል ያስደፈረ የሃገር መከላከያ ሳይሆን የቅጥረኛዉ ወያኔ የግል
ዘበኛ ሆኖኣል፣፣
2. የፍትህ ተቁአማት:- የሚባሉ ፍርድ ቤት ና አቃቢ ህግ ሲሆኑ በወያኔ አገዛዝ የፍትህ
ተቁአማት:- የሚባሉ ፍርድ ቤት ና አቃቢ ህግ ሲሆኑ በወያኔ አገዛዝ ጀግኖችን ለመወንጀል
ፈሪወችን ለማስፈራራት: ህዝብን መሪ ለማሳጣት ወንጀለኞችን የህግ ሽፋን ለመስጠት: ተግተው
የሚሰሩ ናቸው: በሃገራችን ከቤተክርስቲያን ና ከቤተ-መስጊድ ቀጥሎ ክብር የነብረው ፍርድ ቤት
ዛሬ ረክክሶ የወያኔ ወንጀለኞች : የተውኔት መተወኛ አዳራሽ ሆኑአል::
3. የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ተቁአማዊ ና መዋቅራዊ : ወያንያዊ ወንጀል መሳሪያወች ናችዉ::
ወያኔወች የኢትይይኦጵያን ህዝብ በቡድን መብት ስም አቡአድነውና አስረው ለያንዳንዱድም ስም
በመስጠት እነሱ ከፈቅዱላቸው ውጪ እንዳያስቡ በማድረግ ኢሃዴግ ና አጋር ፓርቲ
በሚሉአቸው ተግተው በመስራት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ የማለያየት ስራ ይሰራሉ::
በዚህም መሰረት ከውስጣችቸውም ሆን ከውጪ የፖለቲካ ፈተና ሲያጋጥማቸው አማራውንን
ትምክተኛ : ኦሮሞውን ጠባብ: ትግራዩን ተንበርካኪ: ደቡቡን ጥቅመኛ: አጋር ፓርትወችን ጥገኛ
በማለት በማሸማቀቅ እና የስነ ልቦና ጦርነት በተከታታይ ይፈጽማሉ፣፣ ከላይ በተጠቀስት ተቋማት
በመጠቀም እያንዳዱ ኢትዮጵያዊ በነሱ ውስጥ ያለውም ሆነ ከነሱ ውጭ ስለ ኢትዮጵያዊ
አመለካከት ና ብሄራዊ ራይ እንዳይኖረው ተግግተው እየሰሩ ነዉ::
4. ዲፕሎማቲች ተቁአማት፣ ላለፉት 23 አመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒሥቴርን በመውረር ኢትዮጵያ
በታሪኳ ገጥሟት የማያዉቅ የዲፕሎማቲክ ኪሳራ ባለማቀፍ መድረኮች ተከናንባለች: ሉአላዊነቷ
ተድፍሩአል: ዳሩ ቀርቶ መሃሉ ዳር ሆኑአል:: ኢትዮጵያችን መቀነቷን ፈትታ ገላዋን ለርኩሳን ገብያ
ኣቅርባለች፣፣የወያኔ ተላላክኪወች ለኢትዮጵያ ጥቅምና ክብር ሳይሆን ለኢትዮጵያ ጠላቶች ጥቅም
ሽንጣቸውን ገትረው ትከራክረዋል:: ይህን በማድረግም ኢትዮጵያን የማፍረስና የማዋረድ
ተልኩአቸውን በተቋማትና በመዋቅሮቻቸው ፖሊሲ ነድፈው ስትራተእጂ ቀይስው እየተወጡት
ናቸው:: አደረጃጀታቸውን ስንመለከተው የሚነግረን አንድ አደገንኛ የሆነ ጉዳይ አለ: እርሱም በኢትዮጵያ
ውስጥ ተራ የግለሰቦች ዘረኝነት ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ ና መዋቅራዊ ዘርረኝነት ውስጥ መግባታችንን
ነው:: የትናንቱን የደቡብ አፍሪካው አፓርታይድ የዛሬው የኢትዮጵያው ወያኔ መተካቱ ነዉ::ልዩነቱ
ኣፓርታይዶች ላገራቸዉ ብልጽግና ሲሆን ወያኔወች ለቀጠሯቸዉ ባእድ ኣገሮች መሆኑ ነዉ፣
ዘርኝነትን በ ሶስት ደረጃ ከፍለው የሚከራከሩ የህብረተሰብ ሳይንስ ምሁራን አሉ :: አንደኛው በግለሰብ
ደረጃ ያለ ዘረኝነት ሲሆን ይህም ሌላውን ዝቅ አድርጎ የማየት: ማዋረድ: ማራከስ: የመሳሰልሉትን
የሚያካትት ሲሆን: ሁለኛው ዘርረኝነት ይህንን ውርደት ና የበታችነት ተቀብሎ ከዚህ ጋር አብሮ የሚኖር
ተስፋ ቢስ እና የተሸነፈ ህብረተሰብን የመፍጠር አዝማሚያ ያለው ነው:: ሶስተኛው ተቋማዊ ዘረኝነት
የሚባለው ሲሆን ይህ ፖሊሲ ተነድፎለት በፖለቲካ ኢኮኖሚና በአግገልግሎት ሰጪ ተቁአማት ፣መዋቅር
ተዘርግቶለት አንድን ዘር ጠቅሞ ሌላውን ዘር የሚያቀጭጭ እና የሚያገል አደገኛ የሆነ የዘረኝኝንነት
የመጨረሻ አስከፊ ገጽታው ነው:: በዚህ መሰረት የወኔን ተቋማት መዋቅራዊ ይዘትት ስንመለክት እጅግ
በጣም አሳፋሪ በሆነ ደረጃ በአንድ ቡድን የተሞሉ ሆነው እናገኛቸዋለን:: ለምሳሌ:- መከላከያ ሚኒስቴር :
የደህንነት መስሪያ ቤት: ኢሚግሬሽን ባለስልጣን : የፌደራል ፖሊስ: የኢትዮጵያ አየር መንገድ: የትዮጵያ
ቴሌ-ኮሙኒኬሽን: የመከላከያ ኢንዱስትሪ: ጉምሩክ: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትቲያን: ባንኮች እና
ከሃገሪቱ ከ 50% በላይ የ ንግድ ተቁአማት መዋቅራቸው በተቋማዊ ዘረኝነት የተሞሉ ናቸው::
እነዚህ መስሪያ ቤቶች ለአንድ አገር ብኄራዊ ህልውና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና: እና ማህበራዊ ዋስትና ምን
ማለት እንደሆኑ ለማንም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግልጽ ነው::
ይህን ካልኩ በሁአላ አገራችንን ለማዳን የትግልሉ አቅታጫ መሆን ያለበት ከላይ የተጠቀሱትን ተቋማዊ
ዘረኝነትና አድሎ ለማስወገድ ትግሉ የህግ የበላይነትን ለማስከበር መሆን አለበት:: የህግ የበላይነትን
ለማስከበር ደግም ተቋማትና መዋቅሮቻቸው ሙያው በሚጠይቀው ብሄራዊ ሃላፊነትን ሊሸክከሙ
በሚችሉ ዜጎች መያዝ አለብበት:: ይህንም ለማየት ህግ አልባ የሆነውን ወያኔን በህጋዊና ኢትዮጵያዊ ሃይል
መተካት ያስፈልግጋል:: ለዚህም ትግሉ ከብዙ ፓርርቲወች ጋጋታ : ከይሥሙላ ምርጫ : ከውሸት የነጻ
ገባያ ማጭበርበሪያ፣ በፊት በዘረኝነት የጠመደና የተሳከረ የፖለቲካ ቅዥትን መስመር ማስያዝ
የመጀመሪኢያው ስራ መሆን ኣለበት:: የህግ የበላይይነትን የሚያስፍፈጽሙ ተቋማት ከተቋማዊ ዘረኝነት
መዋቅር መጽዳት አለባቸው:: ይህ በሌለበት እኩልነት የለም:: እኩልነት በሌለበት ዲሞክራሲ የለም:: አለም
ከተባለ ፌዝ ነው: እያፌዙ ደግሞ አገር መምራት አይቻልም:: የሚፌዝበት የኢትትዮጵያ ህዝብ
በየአቅጣጫው ትግሉን ኣጠንክሮ መግፋት አለበት::
አበረ አዳሙ፣ ወርሃ ህዳር 2006 ዓ፣ም፣፣